Thursday, November 8, 2012

አማረ አረጋዊ ተዘለፉ። (ደረጀ ሃብተወልድ)

አማረ አረጋዊ ተዘለፉ።

(ደረጀ)

የኢትዮጵያ ፈርስት ድረ-ገጽ አዘጋጁ ቢኒያም(ቤን)፤ወይዘሮ አዜብ ከቤተ-መንግስቱ ለመልቀቅ እምቢተኛ የመሆናቸውን ወሬ <<አሰራጭተዋል>> ያሏቸውን የሪፖርተሩን አቶ አማረ አረጋዊን፦- <<መሰሪና ተንኮለኛ>> በማለት በአደባባይ (በሚዲያ)ዘለፋቸው።

<<ለመረጃ ቅርበት አለኝ የሚሉት አቶ አማረ አረጋዊ ሆነ ብለው ሀላፊነት የጎደለው መሰሪ መረጃ ለሰንደቅ ጋዜጣ አዘጋጅ በማቀበል ጋዜጣውን ጭምር አሣስተዋል>> ብሏል-ቤን እየተብሰከሰከ።

ቤን በዚህ አላቆመም፦<<አቶ አማረ መረጃውን ለሰንደቅ ካቀበሉ በሁዋላ በጎን ደግሞ ፦”ለሰንደቅ መረጃውን ያቀበላቸው እገሌ ነው” በማለት የሌላ ሰው ስም ሲያጠፉ ተደምጠዋል>> ብሏል።

ይሁንና በአቶ አማረ አማካይነት- መረጃውን ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳቀበሉ ተደርገው ስማቸው ጠፍቷል የተባሉት ግለሰብ ማን እንደሆኑ ቤን አልገለጻቸውም።

ቤን በዚሁ አማረን በዘለፈበት ፕሮግራሙ፦<<ብረት ይዛ ስትታገል የነበች ጀግና ታጋይ፤ይህኛው መኝታ ቤት ጠበበኝ ያኛው ጎረበጠኝ ልትል እንደማትችል ማንም ያውቀዋል>> በማለት ነበር ወይዘሮ አዜብ ከቤተ-መንግስት ለመልቀቅ እምቢተኛ ሊሆኑ እንደማይችሉ ማረጋገጫ ለመስጠት የሞከረው።

(በትግል ጊዜ ጸሀይና ውርጭ እየተፈራረቀባቸው ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ስለፍትህና ዲሞክራሲ ሲወያዩ የነበሩ ታጋዮች ከስልጣን በሁዋላ እንዴት እንደበሰበሱና እንዳረጡ ለቤን ለማስረዳት ምን ያህል ርቀት መሄድ ይኖርብን ይሆን?)

በስልጣን ማግስት ጆሯችንን ማመን እስኪያቅተን ድረስ ስለሚሊዮን ብሮች ቢዝነስ ሲያወሩ የሰማናቸውኮ -እነዚያን በጥይት ላይ ለመራመድ ይሽቀዳደሙ ነበር እየተባለ የተወራላቸውን ታጋዮችን ነው-ቤን። ለምን በድሮ በሬ ለማረስ ትሞክራለህ?

No comments:

Post a Comment