Saturday, November 23, 2013

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ


obang-o-metho-hearingበሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
“አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ችግሩ አስቀድሞ እንደሚከሰት ቢታወቅም ምላሽ የሚሰጥ ብቃት ያለው አካል ባለመኖሩ አንገት የሚያስደፋና ኃፍረት የሚላብስ፤ “አገር አለኝ ወይ?” የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ኃፍረት ሊደርስብን ችሏል፡፡ “ይሁን እንጂ” አሉ ኦባንግ “ይህ መራር ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የጋራ ንቅናቄው የበኩሉን” ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡
“ከተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊ አካላትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረናል” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ ለዓብነት ያህልም የሳዑዲ ም/ጠ/ሚ/ር እና የመከላከያ ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መ/ቤቶችን ጨምሮ በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን የሳዑዲ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR)፣ ወዘተ ማነጋገራቸውንና በየደረጃውም ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡
በመላው የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕረፍት የሚሰጥ እንዳልሆነ የጠቆሙት “ጥቁሩ ሰው” ሳዑዲ ካላትና ከምትከተለው “የበርህን ዝጋ ፖሊሲ” አንጻር በአካል በቦታው ላይ ከመገኘት ይልቅ አቅም ካላቸው ዓለምአቀፋዊ አካላት ጋር በአፋጣኝና በቅርበት መሥራቱ ድርጅታቸው የወሰደው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሎጂስቲክሱ ጉዳይ መስመር ሲይዝም የጋራ ንቅናቄው ከዚህ በፊት በየአገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ሲያስፈጽምበት የነበረውንና በውጤታማነቱ የሚታወቀውን አማራጭ እንደሚተገብር ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኢህአዴግ አገርን እንደሚያስተዳድር ድርጅት በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ አለመመከቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ወገኖቻችንን ድንበር በማሻገርና ኤጀንሲ ከፍተው ወደ አረብ አገራት ሲልኩ የነበሩት ሁሉ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የተለያዩ ተግባራት” እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
alamudi-ሼክ መሐመድ አላሙዲ የሠራተኛ ኃይል ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ከኢህአዴግ ጋር በይፋ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ከሚፈልጉበት ክልል መሬት ለመውሰድ፣ ከሚፈልጉበት ባንክ ኮሪደር ገንዘብ ለመበደር ገደብ የሌላቸውና በሞቀበት ሁሉ ባለመጥፋት በጀት መድበው በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች እንዲሁም አንደበታቸውን በሙስና ላሰሯቸው ባለሥልጣናት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ በተገኙበት ቦታ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚደሰኩሩትና ግጥም የሚያስደረድሩት ሼክ መሐመድ አላሙዲ፣ “ወገኔ” የሚሉት ሕዝብ በአባታቸው አገር ወሮበሎች ሲያልቅና ሲጨፈጨፍ ዝም ማለታቸው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ አሰቃቂ ድርጊት መስመር ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት የሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ከርስ እንዲሞላ በኢትዮጵያ የተቋቋመው ሳዑዲ ስታር ኩባንያ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደሚችል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ ስታር በኪሣራ ወደ መዘጋት መድረሱ የኩባንያው “ባለቤት የሆኑትን ሼክ ሙሐመድ አል አሙዲንና የሳዑዲ ዓረቢያን ስም የሚያጎድፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪታክት የተወራለት ይህ ፕሮጀክት መና መቅረቱ ሁለቱን አካላት በሕዝቡ ዘንድ ለከፍተኛ ትችትና ወቀሳ እንደሚያጋልጣቸውም” ጠቁሞ ነበር፡፡
mohammed bin nayef
ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ
በአሁኑ ጊዜ “ሕገወጥ ናችሁ” በሚል ሰብዓዊነት የጎደው እርምጃ እየተወሰደባቸው ያለው የበርካታ አገራት ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር ሕገወጦችን የማባረር “ዘመቻ” በማለት ያቃለሉት የሳዑዲው አገር ውስጥ ሚ/ር ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ወንጀለኛ ሬንጀር ለባሾችን፣ ፖሊሶችንና ወሮበሎቹን ሸባቦች አደፋፍረዋል፡፡ “ዘመቻው ይቀጥላል … በተወሰነ ጊዜ የተገደበ አይደለም” በማለት “እስክንጨርስ እንጨርሳችኋለን” የሚመስል የማፊያ መሪ መሰል መልዕክት ለአንጋቾቻቸው አስተላልፈዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊነት የሚኖሩትም ጭምር በሳዑዲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢነት ወደፊት ችግር ውስጥ ሊከትታቸው እንደሚችል በመገመት ወደ አገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ሰቆቃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን “ቤት አለን ቤታችን መልሱ” እያሉ የሰቆቃና የድረሱልን ጥሪ በሚያስተላልፉበት ወቅት ሰብዓዊነት የጎደላቸው የኢህአዴግ መሪዎች ይህ ነው የሚባል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸው “በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብሎ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በርካታዎች የሚጋሩት ነው፡፡
አቶ ኦባንግ በበኩላቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንድ ሳምንት ሥራውን አቋርጦ እንኳን ቢሆን ስደተኞቹን ባፋጣኝ የማመላለስ ተግባር መፈጸም ይገባው ነበር በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ህይወታቸው እየተቀጠፈ “3ሺህ ዛሬ ገቡ … ድምሩ 10ሺህ ሆኗል …” የሚል የሞላ ጎደለ ቁማር ዓይነት ጨዋታ በትዊተር መጫወት የቴድሮስ አድሃኖምን ዘመነኛነት ሳይሆን ለሰውልጅ ህይወት ያላቸውን ደንታቢስነት የሚያሳይ መሆኑን ሁኔታው ያስቆጣቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ኦባንግም “ቤቴ መልሱኝ” ብሎ ለሚለምን አንድ ዜጋ የተከፈለው ተከፍሎ ትራንፖርት በማቅረብ ክቡር ህይወትን በአስቸኳይ ለመታደግ አለመቻል ለትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Monday, November 11, 2013

በሳኡዲ አረቢያ የሚፈጸመው ግድያ እና የኢትዮጵያ መንግስት ሴራ



999410_10201428110199302_1866404023_n
ባሳለፍነው ወር ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት በሳኡዲ አረቢያ የሚጓዙ ስደተኞችን አግደናል ሲል ለመገናኛ ብዙሃኖች መጠቆሙ የሚታውስ ሲሆን ያንን ተከትሎም ሆነ ከዚህ ቀደም ይደረጉ የነበሩ አንዳንድ ሁኔታዎችን ተመልክቶ አንዳንድ ምልከታዎችን ለመጠቆም ወደድን ።
የኢትዮጵያ መንግስት በሃገር ውስጥ የሚገኙትን ለኡምራ ጉዞ በሚል ፈቃድ በማግኘት እስከ አረብ አገራት ድረስ በመደለል ስራ እናስገባቿለን በማለት ሴት እህቶቻችንን እና ወንድሞቻችንን ጉዞአቸውን ወደዚያው እንዲያመሩ አቅጣጫቸውን እየቀየሩ ህብረተሰቦችን ወደ አልተፈለገ ጉዳት ውስጥ ሲጥሉአቸው እንደነበር በተለያዩ ጊዜያቶች ይነገሩ የነበሩ የረጂም ጊዜ ታሪኮች ናቸው ።ይባስ ብሎ እነዚህ ደላላዎች በሃገር ውስጥ ተቀምጠው ከአሰሪዎቻቸው ጋር በመነጋገር ገንዘብ ወደ ደላላዎቻቸው ብቻ እንዲላክ እንጂ ለሰራተኞቹ በእጃቸው እንዳይደርሳቸው በማድረግ የብዙሃኑን የድሃ ቤተሰብ ልጆች ደም ሲነጥቁ መክረማቸውም ሌላኛው ግልጽ ዘረፋ የተካኑት ግለሰቦች መሆናቸውን ማንም ሰው የሚረዳው ጉዳይ ነበር ።ሆኖም እንዲህ አይነቱ ክስተት ተፈጠረ ሲባል እኛ አናውቅም አሰሪዎቻቸውንም ሆነ በአረብ አገራት የሚገኙትን ደላላዎች አናውቅም በማለት የብዙዎችን ደም ደመ ከልብ ያደረጉት እነዚሁ የግል አስጎብኝ ድርጅት ኖሮአቸው ዜጎቻቸውን በህገወጥ እና በቀላሉ ልጥቅም ብለው በአረብ አገራት ላሉት ባለሃብቶች የሸጡአቸው ዜጎች መሆናቸውን ሳልገልጽ አላልፍም ።ለዚህም ሁሉ ጥፋት ተጠያቂ እነዚህም ወገኖች በህገ ወጥ ስራቸው ብቻ ሊጠየቁበት የሚገባው ዋነኛው ጉዳይ ሆኖ ሊታይ ይገባዋል ።
ከዚህም ባሻገር ለዘመናት እንዲህ ዜጎቻችንን ለርካሽ ባርነት የላኳቸውን ወገኖች ዘወር ብለው ያላዩአቸውን እንዚህን ደላላ ተብዬዎች ከባለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ መንግስት እና እንዲሁም ጥቂት የመንግስት ደጋፊ የሆኑ ባለስልጣናት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ይህንን ስራ በህጋዊ መልኩ አድርገን እንሰራለን በማለት በወር ወደ 45.000 የሚጠጉ የቤት ሰራተኞችን እንልካለን በማለት ከባለሃብቱ ሼክ መሃመድ አላህሙዲ ጋር የሚሰራ አንድ ትልቅ የጉዞ አስጎብኝ ወኪል በመፍጠር ለሳኡዲ መንግስት ሴትም ሆነ ወንድ ሰራተኞችን ሊያቀርቡ እንደሚችሉ መፈራረማቸውን በይፋ መግለጻቸውን እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህገ ወጥ የሚሰሩትን ድርጅቶች ቀስ በቀስ እያመነመኑ እንዲዘጉ ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን ..ለህዝባችን በተወሰነ መልኩ እፎይታን ቢሰጥም በእጅ አዙር እራሳቸው ስራውን ሊሰሩት ማሰባቸውን እና ሃሳቡን መቀልበሳቸው በሰፊው የተጋለጠባቸው ግን አሁን መሆኑን ሁሉም ሰው  ተረድቶታል ።መንግስት በህጋዊ መንገድ አቀርባቸዋለሁ ያላቸውን ሰራተኞች እራሱ ጉዳዩን ፈጽሞ እራሱ ልኮ ጠበቃ ነኝ ብሎ በሳኡዲ አረቢያ የሚገኘው ቆንጽላ በጥቃታቸው ጊዜ ጉዳታቸውን እንዲሰማላቸው አደርጋለሁ ሲልም መናገሩ አይዘነጋም ።
ዛሬ ደግሞ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ  በቃል አቀባይነታቸው መሰረት
በሳዑዲ በመከራና ስቃይ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን አስመልክቶ የመንግስት ቃል አቀባይ  የተባሉት የቁጭ በሉ ሰው ዲና ሙፍቲ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፦”እየተባረሩ ያሉት ህጋዊ ያልሆኑት ናቸው” ብለዋል ተናግረዋል ።ዲና  በሌላም በኩል  ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ፖሊሶች ስለመገደላቸው የተረጋገጠ ማስረጃ እንደሌላቸው አስረግጠው ገልጸዋል  ሆኖም የሃገሪቱ መንግስት በመገናኛ ብዙሃኑ የተገደሉትን ዜጎች እያሳየ መዋሉን ሲ ኤን ሲ የተባለው የቻይና ቴሌቪዥን ሲያሳይ ቆይቶአል ። ሆኖም የ ዲና ሙፍቲ አነጋገር የሁሉንም ቀልብ ስቦአል ምክንያቱም የሃገሪቱ ተወካይ ሳይሆኑ የሳኡዲ ቃል አቀባይ መስለው መታየታቸው ነው ።
የዲና ሙፍቲ ጉዳይ ወደ ኋላ ተወት እናድርገው እና አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም በሰሞኑ በተጠመዱበት ቲዊተር ስለ ህዝቦቻቸው ሲናግሩ ከአረብ መንግስታቶች ጋር በመምከር ላይ እንዳሉ እና መፍትሄ ሊያመጡ እንደሚችሉ ገልጸዋል ።በትላንትናው እለትም በመንግስት ሃይሎች የሚመራው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም እንደዚሁ ጅብ ከሄደ ጩኸቱን አስምቶአል ።
ከ16500 በላይ ኢትዮያውያኖች በመካ አቅራቢያ ፣በየመን ዳር ድንበር እና እንዲሁም በሳኡዲ አረቢያ ከተማ በሚገኙ እስርቤት ውስጥ ተጉዘው በእስር ስቃይ ላይ እየማቀቁ ይገኛል ።እንደ ሃገሪቱ ናሽናል ቴሌቪዥን ዘገባ ከሆነ እያንዳንዱ እስረኛ ከ500 እስከ 1000 የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቀዋል ይህንን የማይፈጽም ከሆነ ደግሞ እስሩን ጨርሶ ሊፈታ እንደሚችል እና ዳግመኛ ወደዚያች ምድር እንዳይመጣ በሚያደርግ የአሻራ ፊርማ አስወጥተው ሊያባርሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል ። ታዲያ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ከኢትዮጵያ መንግስት በተሰጠን  ትእዛዝ ነው ብለው ተናግረዋል የሚሉ መረጃዎች ከወደ ሳኡዲ እየተሰማ ይገኛል ፣ሆኖም ግን ይህ ምን ያህል እውነታ እንደሆነ ማረጋገጫው ባይኖረኝም ይህንን የጻፈውን ብሎግ ግን ማቅረብ መቻሌን ውሸታም አያሰኘኝም ስለዚህ ሙሉውን እንዲህ ይነበባል
ከዚህ ቀጥሎ ከክሊክ ሃበሻ የተዘገበውን ዜና አንዲህ ተቀናብሮ የተቀመጠ ሲሆን እኔም በዚህ መልኩ  ጽሁፉን አስቀምጠው እና ከዚያም ሊንኩን አያይዤ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ ። “ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥ ኢትዮጵያውያን እንዲያዙ የተስማማበት ሰነድ አለን”የሳኡዲ ባለስልጣናት
 | 10 בNovember 2013 | 0 Comments
በሪያድ የዛረው ሰልፍየሚመጣውን አደጋ በመፍራትተበትኗል::
“ቴዎድሮስ አድሃኖም ህገወጥኢትዮጵያውያን እንዲያዙየተስማማበት ሰነድአለን”የሳኡዲ ባለስልጣናት
አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሳኡዲጸረ ኢትዮጵያውያን ዘመቻእንደቀጠለ ሲሆን ሁኔታዎችንለመፍታት የተደረጉ ጥረቶችከዚህ
ቀደም የኢትዮጵያመንግስት እና የቆንስላውዲፕሎማቶች በሰርኡት ስህተትመስመር ሊይዝ አልፈለገም::
እንደ ሳኡዲ ባለስልጣናትአነጋገው የውጪ ጉዳይሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ባደረጉት ጉብኝት ሃገራቸው ህገወጥ ኢትዮጵያውያንን እንዲያስወጣ እና በምትኩ40,000 ህጋዊ ስደተኞችን እንደሚልኩ የፈረሙበትን ማስረጃ ይዘዋል::
በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስትየወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ሰልፍ መውጣታቸው ተሰማ። እንደ አረብ ኒውስ ዘገባ መሰረት በሰልፈኞችበተወረወሩ ድንጋዮች አንድ የሳውዲ ዜጋ መሞቱንም ዘግቧል።
እነዚሁ በነዋሪዎች ድብደባና በደል የደረሰባቸው ኢትዮጲያውያን ወደ ሪያድ ኢምባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤትበእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ግጭት አንድ የፖሊስ መኪናእንደተሰበረ የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።http://www.clickhabesh.com/?p=103630
ታዲያ እንዲህ ከሆነማ ሴራውን የጠነሰሱት የራሳችን ወገኖች ከሆኑ ለዚህም ተጠያቂው እራሳቸው ስለሆኑ ፣በወጥመድ ውስጥ እራሳቸውን አሾልከው ላለማስገባት ባደረጉት ጥረት ሸፋፍነው ማለፍን ስለፈለጉ የህዝባቸውን ሰቆቃ እያዩ ዝም ማለትን መርጠዋል ፡፤ይህንንም ሰቆቃ እና ግፍ ግድያ እንዲሁም የሴቶችንም ሆነ የወንዶችን አስገድዶ መደፈር እንዲመጣ ያደረጉት እንዚሁ ጨካኝ የሆኑ ገዢ መደቦቻችን ናቸው ማለት ነው። በነገራችን ላይ በመካ መዲና አካባቢ የተወሰዱት እስረኞች በሙሉ ፣የታሰሩት ወገኖች በግብረ ሰዶማውያን በታሰሩበት እስርቤት እንደሆነ ለመጠቆም እወዳለሁ ።
ይህ ቦታ ከፍተኛ ሙቀት ያለው አካባቢ ከመሆኑ የተነሳ የሰው ልጆችን ለመቅጣት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ እና ማኛውም ሰው በተፋፈነ ክፍል ውስጥ አይደለም ለቀናት ለሰአታት መቀመጥ የማይችልበት እስርቤት ሲሆን ከዚህም ባሻገር የሚጠጣው ዉሃ ከፍተና ጨዋማ የሆነ ከመሆኑም በላይ ስውነትን ለመላላጥ እና ለተለያዩ ጉዳቶች ሊያደርስ የሚችል መሆኑን ያገኘኋቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ ።ይኅንን ስቃይ እና መከራ ለምን ዜጎቻቸው እንዲጋፈጡት ፈለጉ ፣መንግስት እንዲህ አይነቱን የክፋት ወንጀል ለምን በህዝቦቹ ላይ መፈጸም አስፈለገው ፣ለምንስ በስደት ያሉት ወገኖች ላይ አነጣጠረ የሚለው ምላሽ ።
ዋነኛው ምክንያት በህገወጥ ገቡ የተባሉት ወገኖች በሳኡዲ አረቢያ የሚገኘውን ክፍት የስራ ቦታ ስለሚሸፍኑት መንግስት በህጋዊ መንገድ አቅርባቸዋለሁ ያላቸው ሌሎች ዜጎቹን ስራ አጥተው እንዳይሰቃዩበት ስጋት ስለያዘው እና ፣አዲስ የሚጀምረው የጉዞ ሂደት እንዳይደናቀፍበት ቅድመ ጥንቃቄ ለመውሰድ ያስችለው ዘንድ ህጋዊ አልሆኑም ያላቸውን ህዝቦቹን በግዳጅ ከሳኡዲ መንግስት ጋር በመተባበር እንዲያስወጡ መምከሩ ግድ ሆኖ ስለታየው ያንን ሃላፊነት እራሱ ላይ መሸከምን ችሎአል ።ለዚህ ሲባል የሳኡዲ መንግስት በንጹሃን ህዝቦች ላይ ጥቃትን ፈጽሞአል መንግስትም ይህንን አላየሁም ሲል ድፍን አድርጎ የገለጸ ሲሆን በትላንትናው እለት በቴሌቪዝን የአየር ሰአት ላይ ለማረጋገጥ እንጥራለን ሲል ቃሉን ሲያጥፍ ተሰምቶአል ።
እንደ ማጠቃለያ ...መፍትሄው በሃገር ውስጥም ሆነ ተለያዩ አገራት የምንገኝ ዜጎች የህዝቦቻችንን መብት ለማስከበር በምናደርገው ጥረት ማናችንም በአለን ሃይል ተጠናክረን በመምጣት የህዝቦቻችንን መብት ማስከበሩን ግፊት በማድረግ በአረቡ አለም ላይ ጫና እንዲደረግ መጠየቅ እና መምከር ያስፈልገናል ከዚያም ባሻገር በሳኡዲ አረቢያ ኢምባሲ ቅርንጫፍ ቢሮዎችም ሆነ ቆንጽል ስህፈት ቤቶች በመገኘት ድምጻችንን እናሰማለን ከዚያም ቀጥሎ የዚህን አድሃሪ የሆነ መንግስት ሴራ ማጋለጡም ቢሆን ለጉዳት የሚዳርገን አይመስለኝም እና ሁላችንም ለህዝቦቻችን ቅድሚያ በመስጠት የንጹሃኖችን ህይወት እናትርፍ እያልኩኝ እለያችኋለሁ ።ስለያችሁ በአሜሪካ የሚገኙትን ሴናተሮች እና አገረ ገዢዎችን ኢሜል አድራሻ አያይዤ ሳቅርብላችሁ ሁላችሁም ጩኸታችሁን በኢሜሎቻቸው ላይ ያድርሱአቸው የሚለው የመጨረሻው የልመና ቃሌ ነው ሰላም ያገናኘን ።ዘላለም ገብሬ ከማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ።
maleda times | November 10, 2013 at 9:11 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-2sc
Comment    See all comments