Sunday, November 25, 2012

"መፈረካከሱ ቀጥሏል፤ ፍርሃት፣ ጭንቀትና መደነባበሩም በወያኔ መንደር ተባብሷል”

 

ከይኸነው አንተሁነኝ (ህዳር 21 2012)
የሐምሌና ነሐሴ ከባድ ዝናባማ ወራት ጠቅልለው ከሄዱ ቆይተዋል። ለወጥሮው የኢትዮጵያን ሰማይ ሸፍኖ የነበረው ከባድ ጥቁር ዳመና ከረር ከረር እያለች በመጣችው የፀሐይ ሙቀት ምክንያት እየተሸነፈ እንደ ባለሙያ ሴት የጥጥ ንድፍ እዚህም እዚያም በተን በተን ያለ እጅግ በጣም ስስ ጉም መሆን ከጀመረ ውሎ አድሯል። ሜዳ፣ ጋራና ሸንተረሩ ውሃ ጠግቦ በቃኝ ብሎ በሙሉ ደረቱ የሚያፈስባቸውና በተለምዶ የአበባ ወራት ተብለው የሚጠሩት ወራቶችም ምድሪቱን ካስወቡበት ምትሃታማ አስደማሚና ህሊናን ያዥ ህብር ቀለማቸው እየሸሹ የምድሪቱን አላባ እንካችሁ የሚሉበት ወርሃ ጥጋብ ወርሃ ምርት ጊዜ እየደረሰ ነው። ጓዳ ጎድጋዳው፣ ሸጥና ወንዙ፣ ኩሬ ሸለቆው፣ ወጣ ገባ ተራራው ባጠቃላይ ምድሪቱ በሚላስ በሚቀመስ ሲሳይ የምትጎበኝበትና የምትሞላበት መልካም የደስታና የጥጋብ ወራት፤ ወርሃ ምርት ኢትዮጵያ።

No comments:

Post a Comment