Friday, November 30, 2012

የኃይለማርያም ደሳለኝ የካቢኔ አባላት ሹመት

     
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ።
የካቢኔ ጉዳዮች በማህበራዊ፣ በመልካም አስተዳደር እና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ ተከፋፍሎ ሹመቱ መካሄዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ፥ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር።
ዶክተር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ፥ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ተጠባባቂ የንግድ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ከበደ ጫኔ ደግሞ የንግድ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ደግሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ሹመቱ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ያስመዘገቡ እና ፓርላሜንታዊ ስርዓት ያላቸውን ሀገራት ተሞክሮ ፣ ከሽግግር መንግስቱ እስካሁን ያለውን የካቢኔ አደረጃጀትና አሰራርን ክፍተቶችና ያሉትን ጥንካሬዎች ፥ እንዲሁም ዋና ዋና ክልሎች በካቢኔያቸው ውስጥ የተከተሏቸውን አሰራሮች መሰረት በማድረግ የቀረበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አብራርተዋል።
አዲሶቹ ተሿሚዎች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

No comments:

Post a Comment