Saturday, November 3, 2012

ከ72 በላይ ኢትዮጵያዊያንን የያዘ ጀልባ የመን ድንበር አቅራቢያ ሰመጠ ግሩም ተ/ሀይማት

በአመት ከሁለት ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሞቱ IOM የገለፀበት ገልፍ ኦፍ አደን ባህረ ሰላጤ ላይ ከሶስት ቀን በፊት 72 ኢትዮጵያዊያን እንደሞቱ ተረጋገጠ፡፡ 

ከሶማሊያዋ ቦሳሶ ወደብ የተነሱ ሁለት ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች ከነጫኑት ሰው ሰመጡ፡፡ በዚህ የመስመጥ አደጋ የሞተው ሰው ቁጥር በትክክል የማይታውቅ ሲሆን ለጊዜው ባህሩ ላይ ሬሳቸው የተለቀመ እና ባህሩ ዳር ተፍቶት የተገኘ ሲሆን ከዛ ውስጥ 72 ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ታውቋል፡፡

 ሸቡዋ የተባለው የየመን ጠረፍ ላይ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው እንደሰመጠ የተነገረው ይህ ጀልባ ምን ህል ሰው እንደጫነ አልታወቀም፡፡ እኛ ስንጓዝ በምናውቀው ምን ጊዜም የሚጭኑት ከአንድ መቶ ላይ ሰው ነው፡፡ ሁለተኛው ጀልባ ይስመጥ አይስመጥ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ መግባታቸውም አልተረጋገጠም፡፡
 
 የየመን መንግስት ባለስልጣናት ከዚህ በኋላ በህገ-ወጥ መንገድ የሚገቡት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ይህንን አባባላቸውን 2011 መግቢያ ላይ ከጅቡቲ በጀልባ ሲገቡ በ3 ቀናት ልዩነት ሶስት ጀልባዎች ሲሰምጡ ተናግረውት እንደነበር ይታወሳል፡፡ 

መሳሳይ ነገር ቢናገሩም ስደተኞችን ክፍት በተተወ ድንበር ህገ-ወጥ አጓጓዦች እንደልብ እያስገቡበት በመሆኑ በአመት እስከ 75 ሺህ ስደተኞች ወደ የመን እንደሚገቡ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መግለጹ ይታወሳል፡፡ 

ይህ ችላ ባይነት በየመን መንግስትም ሆን በኢትዮጵያ መንግስት በመታየቱ ከባህር መስመጥ አልፈው የሚገቡት ኢትዮጵያዊያን ላይ በተደራጀ ሁኔታ የማፈን እና 5000 የኢትዮጵያ ብር ከቤተሰብ ማስላክ አለበለዚያ ታጋቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረስ የተለመደ ሆኗል፡፡
ይህ ከሶማሊያዋ ቦሳሶ አነስተኛ ወደብ የሚነሳው የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጀልባ አደጋው የደረሰበት በአየር መዛባት የተነሳ ሀይለኛ ንፋስ /ማዕበል/ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የዛሬ ሳምንት ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ በተከፈተ ተኩስ ሰዒድ የሚባል ኢትዮጵያዊ ህገ-ወጥ አጓጓዥ ጨምሮ ሶስት ኢትዮጵያዊያኖች መሞታቸው ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment