Sunday, January 20, 2013

የቴዲ አፍሮ የደቡብ አፍሪካው ሙዚቃ ዝግጅት በብሄራዊ ቡድኑ መለያ የታጀበ ነበር በደማቅ ሁኔታ አለፈ


 

በሳውዝ አፍሪካ የተዘጋጀው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ በደመቅ ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ ከስፍራው ለማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ሪፖርት ለማድረግ የሄደው ባለደረባችን ገልጾአል ። እንደ ባልደረባችን አገላለጽ ከሆነ የቴዲ አፍሮ ፕሮግራም በከፍተኛ ድምቀት ከመጀመሩ በፊት ሙሉ ባንዱ የብሄራዊ ቡድኑን መለያ ለብሶ እንዲጫወት መደረጉን ገልጾአል ይህ ደግሞ ደጋፊውን ህብረተሰብ እና የሙዚቃ ወዳጆቹን ይበልጥ ሊያስደስት እንደሚችል እና የብሄራዊ ቡድኑን ይበልጥ ድጋፋቸው ሊያጠናክረው እንደሚችል አክሎ ተቁሞአል ። ከቴዲ አፍሮ ጀምሮ አጃቢ ሩት ገብረመስቀል ኪቦርድ ቴዲ አሃዱ አሁንም፣ ኪቦርድ ያሬድ አብርሃም፣ ጊታር  ኤርሚያስ ከበደ ፣ ቤዝ ጊታር አበራ አለሙ ፣እና ሩፋኤል ወልደማርያም ድራም በመጫወት ከነ ሙሉ መለያቸው ደምቀው መታየታቸውን እና በስፍራው ከተጠበቀው ህዝብ በላይ መታደማቸውን ረዳት ሪፖርተራችን ተወልደ ከስፍራው ዘግቦአል ።
staff reporter | January 19, 2013 at 9:59 pm | Categories: AMHARIC NEWS, ENTERTAINMENT | URL: http://wp.me/p2gxmh-1le

Comment   

No comments:

Post a Comment