Gudu Kassa |
- ሥልጣነ ፕትርክና ሲፈልጉ ተረከቡኝ፣ ሲፈልጉ መልሱኝ እየተባለ የሚከራከሩበት ሥልጣን ባለመኾኑ ዐራተኛውን ፓትርያሪክ ወደ መንበረ መመለስ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውስጥ ሥርዐተ አልበኝነት እንዲሰፍን መፍቀድ ነው፡፡ ከዚህም ጋራ አምስተኛው ፓትርያሪክ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው የተሠራው የኻያ ዓመታት ሥራ ደምስሶና ሠርዞ ወደኋላ በመመለስ ዐራተኛው ፓትርያሪክ ብሎ መቀበል ፍጹም የማይቻል በመኾኑ፣ የቀድሞው ዐራተኛ ፓትርያሪክ በፓትርያሪክነት የሥልጣን ደረጃ እንደማይቀበል ቅዱስ ሲኖዶስ በማያሻማ ኹኔታ በድጋሚ ወስኖአል፡፡
- ቤተ ክርስቲያን በአሁን ጊዜ ከዚህ በላይ ያለመሪ ለብዙ ጊዜ እንድትቆይ ማድረግ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥራዋ እንዲስተጓጎል፣ መልካም አስተዳደሯም እንዲዳከም የሚያደርግ ስለኾነ ቀደም ሲል በተወሰነው መሠረት የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ቤተ ክርስቲያንነና ቀኖናው ተጠብቆ የምርጫው ሂደት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡
- ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም የሰላምና የአንድነት መሪ እንደመኾኗ መጠን የተጠቀሱት አባቶች የተሰጠውን የሰላም ዕድል ተጠቅመው ወደ ሰላሙና አንድነቱ ለመምጣት ፈቃደኞች ኾነው እስከተገኙ ድረስ ኹኔታዎች ሲመቻቹ ቀደም ሲል የተጀመረውን የሰላምና ዕርቅ ሂደት እስከመጨረሻው ድረስ ለማስቀጠል አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን ዝግጁ መኾኗን ቅዱስ ሲኖዶስ በማረጋገጥ ጉባኤውን አጠናቋል፡፡
Comment | See all comments |
No comments:
Post a Comment