Friday, December 28, 2012

የኦርቶዶክ ቤ/ክርስቲያን አመራር ለሃይማኖቱም ሆነ ለአጠቃላይ ሥርዓቱ አደጋ ወደመሆን ተቃርቧል” – ስብሃት ነጋ (ቃለምልልስ)


(በፋኑኤል ክንፉ)
አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይ ስብሃት) ህወሓትን ከ1971 እስከ 1981 ዓ.ም በሊቀመንበርነት የመሩ ግንባር ቀደም ታጋይ ናቸው። በአሁኑ ወቅት
ከፓርቲው አመራር አባልነት የለቀቁ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሠላምና የልማት ኢንስቲትዩትን በዋና ዳይሬክተርነት ይመራሉ።
በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ አነጋግረናቸዋል።
ሰንደቅ፡- ከቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ ያለው የአመራር ለውጥ ሒደት እንዴት ተመለከቱት?
አቶ ስብሃት፡- በአሁን ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕገ መንግስታዊ ስርዓት አላቸው። ይህ የሆነው ግን ዕድለኞች በመሆናቸው ሳይሆን በረጅምና መራራ ትግላቸው የስርዓቱ ባለቤት መሆን በመቻላቸው ነው። ሕገ መንግስቱ መሰረታዊ ማንነታቸውን የመዋዕሉ ሁኔታዎችን በትክክል ያንፀባርቃል። በዚህ ሂደት፣ ማለትም ኢትዮጵያ ራስዋን በማወቅ ሂደት፣ ወሳኝ ሚና ያካሄደውና በሕገ መንግስቱ መሰረት በሕዝብ የተመረጠ ኢህአዴግ አለ።
ስለዚህ ኢህአዴግ ዕጩ አመራሮችን ይዞ ፓርላማ አቀረበና አፀደቀ። ሌላው አካሄድ ለዘለዓለም ዝግ ስለሆነ ሂደቱ የግድ መሆን ያለበት ሕገ መንግስታዊና ኢህአዴጋዊ በመሆኑ ባልገረምም፤ የሂደቱ ውጤት ግን አስደስቶኛል። ከዚህም በተጨማሪ እንደሌሎቹ የኢህአዴግ የአመራር አባላት ትምህርታቸው መሬት ነክቶ ከሕዝብ እንደገና ተምረው ሃቀኛ ኢትዮጵያዊነታቸውን እያረጋገጡና እየተረጋገጠ የመጡ አመራሮች ናቸውና ያስደስታል።
ሰንደቅ፡- ከአመራር ለውጡ ሽግግር በኋላ አራቱ ድርጅቶች (ሕወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን) ስልጣኑን በጋራ የተከፋፈሉት ይመስላል። በምክንያት የሚነሳው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ሁለት ተጨማሪ ሹመቶች መሰጠታቸው ነው። ይህ ሒደት የኢህአዴግን ጥንካሬ አያሳይም እንዲሁም ሕገመንግሥቱን ይጥሳል የሚል አስተያየት እየቀረበ ነው ያለው። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድነው?
አቶ ስብሃት፡- የአመራር ለውጥ ሽግግር የተባለው ትክክል አይመስለኝም። ክፍት የአመራር ቦታ ስለነበር መደረግ የነበረበት የተለመደ የጠ/ሚኒስትር እና የምክትል ጠ/ሚኒስትር ሹመት ነው። ከዚህ በኋላ ከህወሃትና ከኦህዴድ በም/ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሾሙ።
ከኢህአዴግ ውጭ ሌላ ቢያደርጉ ድርጅቱም፣ ፓርላማም ሕዝቡም አይቀበልም። የኢሕአዴግ ሕዝባዊ አመለካከትና ይህ ሕዝባዊ
አመለካከት የነደፈው ፕሮግራም ስለሆነ የሚያራምዱት የሚሾሙት ከአንድ ድርጅት ብቻ ቢሾሙ ኑሮ ኢሕአዴግች እስከሆኑ ድረስ ብዙ የተለየ ትርጉም አይሰጡትም። ስለዚህም ሁለቱ ሹመኞች ከአንድ ድርጅት ብቻ ለማግኘት ስላልቻለ ወይም እኔ እንደሚመስለኝ የሕዝቡን ንቃተ ሕሊና ከግምት ውስጥ ያስገባ አመዳደብ ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ ጉዳዩ የድርጅት እንጂ የሃገር መሰረታዊ ፖለቲካዊ ጉዳይ ስላልሆነ እዚህ ጋር እንተወው።
ሌላው የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አደረጃጀት ድሮም የነበረ ነው። አደረጃጀቱ ከጠቀሜታ አንፃር መመልከቱ ተገቢ ነው
የሚሆነው። ምክንያቱም፣ በመሰረተ ሃሳብ የጋራ አመራር ያጠናክራል። የጋራ አደረጃጀትና አመራር ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው። ቀደም ባሉት ጊዜም በድርጅቱ ውስጥ የጋራ አመራር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደነበረው ይታወቃል። አሁን በተዘረጋው የጋራ አመራር ጊዜ ሳይወስዱ ወቅታዊ ችግሮችን መፍታት ጀምረዋል። ለምሳሌ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ እየታየ ያለው እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ተስፋ የሚሰጥ ነው።
ስለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ወደዚህ አደረጃጀት መግባታቸው ምን ያህል ለጋራ አመራር መነሳሳታቸው ነው
የሚያሳየው። ይህም በመሆኑ ጥራት ያለው ፈፅሞ ወደኋላ የማይመለስ እርማት ከገመትነው ጊዜ ባጠረ ይመጣል።
ይህ አደረጃጀት ህገ መንግስቱ ይጥሳል፣ አይጥስም እኔ ልመልሰው አልችልም። ህገ መንግስቱን ጥሶ ከተገኘ በህገ መንግስቱ መሰረት ህገ መንግስቱን ማሻሻል ወይም ሌላ መንገድ መፈለግ ነው እንጂ፤ የአሁኑ ሰፋ ያለ የጋራ አመራር የሚያረጋግጥ አደረጃጀትና አሰራር መቀጠል አለበት የሚል እምነት አለኝ። በጣም የሚገርመኝ ነገር ግን ሕገመንግስቱ ተጣሰ ብለው ከሚጮሁና ከሚያለቅሱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ሕገመንግስቱ ይቀደድ ብለው ሲፅፉና ሲናገሩ የነበሩ ናቸው። ሆኖም ግን ከጠያቂዎቹ ሰዎች መካከል በቀናነት ጥያቄውን የሚያነሱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም እገምታለሁ። ያም ሆነ ይህ ሕገመንግስቱ ተጥሶ ከሆነ በባለሙያዎች ቢታይ ጥሩ ይመስለኛል።
ሰንደቅ፡- በአመራር ለውጡ (ሽግግር) ላይ የእርስዎ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል? በዚህስ ነጥብ ላይ የእርስዎ ምላሽ ምንድንነው?
አቶ ስብሃት፡- በዚህ ሂደት ውስጥ የእኔ ሚና ምን እንደነበረ ለምን ጠየቅከኝ? የአመራር አባል አይደለሁም። ተራ አባል ነኝ። በየት በኩል ወደ ሂደቱ እገባለሁ። በምንም አጋጣሚ ቀዳዳ አግኝቼ ገብቼ የራሴ ያልሆነ የሰው ስራ ብሰራ፤ ማለትም ስርዓት አልባ ብሆን ሰውም ባያየኝ ሕሊናዬ ምን ይለኛል? ተቋማዊ ስርዓቱ በመራራ ትግል የተገነባ የህዝብ የፀጋዎች ፀጋ ነው።
click on the following link and read the complete interview:http://www.maledatimes.com/2012/12/26/%e1%8b%a8%e1%8a%a6%e1%88%ad%e1%89%b6%e1%8b%b6%e1%8a%ad-%e1%89%a4%e1%8a%ad%e1%88%ad%e1%88%b5%e1%89%b2%e1%8b%ab%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%88%ab%e1%88%ad-%e1%88%88%e1%88%83%e1%8b%ad/


staff reporter | December 26, 2012 at 5:58 pm | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-1fl
CommentSee all comments

         

No comments:

Post a Comment