Saturday, December 29, 2012

Breaking News (ሰበር ዜና)፡ 6ኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ ለተሾሙት ሰዎች ከሲኖዶስ የተጻፈላቸው ምስጢራዊ ደብዳቤ እጃችን ገባ

 

(ዘ-ሐበሻ) የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ታኅሣሥ 6 ቀን በዋለው ጉባኤው ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ ዕጩ ሊቃነ ጳጳሳት ለውድድር እንዲቀርቡ ወስኗል፤ አስመራጭ ኮሚቴም ተመርጧል ስትል ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል። ሆኖም ግን አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ እንዲህ ያለ ውሳኔ አለመወሰኑን አስተባብሎ ነበር።አሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ከሲኖዶስ የወጣና ለፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴዎች የተጻፈው ደብዳቤ ግን ማን ውሸታም እንደሆነ የሚያጋልጥ ነው ተብሏል። ግን እንዴት ይህ ሁሉ የኦርቶዶክስ ምዕመንን መዋሸት አስፈለገ? ምስጢራዊው ደብዳቤን አይታችሁ ፍረዱ።Holy-sinodHoly-sinod-1

1 comment:

  1. ወገኖቼ፥ ይህች ቤተክርስቲያን እስከ መቼ በልዩነት ትቀጥል? ዛሬ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በማረፋቸው ምክንያት ሌላ ፓትሪያርክ ከሾምን፥ ነገ ደግሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ቀናቸው ደርሶ ሲያርፉ ሌላ ፓትሪያርክ ሊሾም ነው ማለት ነው። እንዲህ እያለ ሊቀጥል ነው? “ለአንድ እረኛ አንድ መንጋ ይሆናሉ፤” የሚለውን የጌታ ቃል የት እናድርሰው? ዮሐ ፲፥ ፲፮ ። ስለዚህ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አባቶቻችን አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን። የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖራችሁ እንደ ተለያያችሁ አትቅሩ። የተወጋገዛችሁትን ውግዘት አንሡ። ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል። እኛን በተለይም በውጭው ዓለም ለምናገለግል ካህናትና ለሚገለገሉ ምእመናን ከባድ ቀንበር ሆኖብናል። ይህንን ቀንበር ስበሩልን። የልዩነቱ ምክንያት የታወቀ ስለሆነ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱን አስቡ። ዓለምን ከናቁ መናኞች የሚጠበቀው ይኽ ብቻ ነው። በሀገር ቤት ያላችሁ አባቶች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዎስ ከሃያ ዓመታት ስደት በኋላ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የተከፈለው ተመልሶ አንድ እንደሚሆን፥ ልዩነቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደ ሚፈታ ይጠፋችኋል ብዬ አላስብም። ማን ያውቃል? ዕርቅ ይውረድ ሰላሙ ይምጣ እንጂ እርሳቸውም “እኔ ሥልጣኑን አልፈልገውም፥ በእንደራሴ ይመራ፤” ሊሉ ይችላሉ። አንድነቱ ይምጣ እንጂ መሪው መንፈስ ቅዱስ ነው። በመሆኑም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ “እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ይህን ወስነናል፤” እንድትሉን እስከ መጨረሻው ተስፋ እናደርጋለን። በመሆኑም አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅን መሪ ለቤተክ ርስቲያን ይሰጣታል። ቤተክርስቲያኒቱም የጸጥታ ወደብ ፥ የሰላም ማማ ትሆናለች። አባቶቻችንም በጥቅምትና በግንቦት ሲኖዶስ ይታይ የነበረው የእርስ በርስ ሙግት ይቀርላችኋል ። እኛም አባቶቻችን ተሰባስበው ተጨቃጨቁ ከሚለው ሰቀቀን እንድናለን። ሃይማኖት አጽንተው ሥርዓት ወስነው አስተዳደሩን አስተካክለው በፍቅር ተለያዩ ብለን በአራቱም መዓዝን እንሰ ብካለን። እናንተም በሚቀጥለው ስብሰባ እስክትገናኙ ትነፋፈቃላችሁ። እንዲህ ሲሆን በመካከላችሁ ነፋስ አይገባም። ማንም ተነሥቶ ቀን ከፈለኝ ብሎ “ጳጳሳቱ አይረቡም” አይላችሁም። ዓለም ይፈራችኋል እንጂ አትፈሩትም። “እምነ መንግሥት የዓቢ ክህነት” ትሉታላችሁ። እንደ አባቶቻችሁ አራዊቱ እንኳን ይታዘዙላችኋል። ልዑላን ትሆናላችሁ። ስለሆነም፥ ለራሳ ችሁም፥ ለቤተክርስቲያናችሁም፥ ታሪክ ሠርታችሁ እለፉ፥ እኛንም የአባቶቻችንን ገድል ለመጻፍ የበቃን እንሆን ዘንድ አድርጉን። ይህ ካልሆነ ግን አድሮብን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ያዝንብናል። ኤፌ ፬፥፴።

    ReplyDelete