Saturday, May 23, 2015

ኢትዮጵያና ዐባይ - ግብፅና እስልምና!! አንተነህ ሽፈራው (ኢ/ር)


መጋቢት 19 ቀን 2007 ዓ.ም (March 28, 2015)
. . . ይኩኑ አምላክ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ሥልጣን ከዛጉኤ ሥረዎ-መንግሥት (ከላስታ) እ.ኤ.አ
1270 ዓ.ም ነጥቀው ወደ ሸዋ ሲወስዱ የመጀመሪያው እቅዳቸው በሁሉም የኢትዮጵያ የግዛት
ማዕከሎች ያሉ ክርስቲያኖችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሃይማኖታዊ ግልጋሎት የሚሰጥ
አባት/አቡን/ ይፈልጉ ስለነበር ትኩረታቸውን ወደ ግብጽ አደረጉና የዛን-ግዜውን የግብፅን
ፈርሆን/ንጉሥ/ ሱልጣን ባይባርስን እ.ኤ.አ በ1272 በይፋ ቢማጸኑም ሱልጣን ባይባርስ ግን
የክርስትና ሃይማኖት መኖርን አለመፈለጉ ብቻ ሳይሆን የክርስቲያን ኑባ ሥረ-ወመንግሥትን
ጭራሽኑ ለማውደም በከፍተኛ ዘመቻ ላይ ነበርና የይኩኑ አምላክን ተማጽኖ ሊያስተናግድ
ፈቃደኛ ባለመሆኑ ይኩኑ አምላክም (ከብዙ ቆይታ በኋላ) ፊቱን ወደ ሶሪያ በማዞር አባትነቱን
ለሶሪያው ጃአኮቢት ሰጡ. “Baybars, was engaged in the conquest of the
Crusaders' last strongholds in the Holy Land. But he also directed a
campaign aimed at destroying the Christian Kingdom of Nubia] …
appointed Syrian Jacobite Priests as head of the national church.”
[Ethiopia and the Red See, 1980 M. Abir, p. 21] ያም ሆኖ ግን ከሶሪያ የመጡት
አቡንም ቢሆን የነበረውን ችግር ይበልጥ አባባሱ እንጅ መፍትሄ ሊሆኑ አልቻሉም::
ይኩኑ አምላክ ከግብፅ ጋር የጀመሩት የፖለቲካ ግንኙነት በሂደት ይበልጥ ከሉአላዊነትና
የሃይማኖት ነጻነትና እኩልነት ጋር በቀጥታ እየተቆራኘ ቢሄድም የግብፅ ፈርሆኖች ግን ከአቻነቱና
ከሁለቱ አገሮች ትብብሩ ይልቅ በአገራቸው የነበረውን ጥንታዊ የክርስትና ሃይማኖት ጨፍልቆ
እስላማዊ ሃይማኖትን በዜጎች ላይ መጫንን ይበልጥ መሠረት እያደረጉ በመሄዳቸው በሂደት
የኢትዮጵያው ንጉሥ ዘረ-ያዕቆብን (r. 1434 - 1468)ና የግብጹን ሱልጣን ጃቅማቅ ወደ ለየለት
የሃይማኖት መፋጠጥ እንደወሰዳቸው ታሪክ በሚገባ ያስረዳል:: ለአብነት ያህል "Jaqmaq
(1438 - 1458) had reversed the tolerant policy of his predecessor towards
the Copts and demolished one of their holiest shrines." [Ibir p.31]
ምንም እንኳን ዘረ-ያዕቀብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖትን ያለ አካባቢያዊ አድሎ
ለማስተዳደር በማሰብ ከግብጽ አቡን በማስመጣት እልባት ለመስጠት ቢፈልጉም ቅሉ በዚያው
መጠን ደግሞ ግብፅ ውስጥ ላሉት ክርስቲያን አባቶችና ተከታዮቻቸው ተቆርቋሪና መብት አስከባሪ
የነበሩ መሆኑ ይታወቃል:: ለዚህ ረጅም የማስፈራሪያ ኃይልና የመከራከሪያ ጉልበት ምንጭ ሆኖ
ያገለገለው ደግሞ የተፈጥሮ ሃብታችን ዐባይ ወንዝ ዋነኛው ነበር:: ለአብነት ያህል "Zara
2
Yaeqob pointed out that he was to punish his numerous Muslim subjects,
who, unlike the Copts in Egypt, enjoyed full freedom and also reminded
Egypt's ruler that he controlled the sources of the Nile." [Ibid p. 31].
የሁለቱን አገሮች የበፊት የፍጥጫ ታሪክ ለግዜው ለታሪክ እንተወውና ግብጽ በምሥራቁ የአገራችን
ክፍል በኩል ሱማሌን በመጠቀምና በተለያዩ ግዜአት በምፅዋ በኩል የሞከረቻቸው ዜጎቻንን
የማስለምና የቀጥታ ወረራ ጦርነቶ በሚገባ ይታወቃሉ:: በተለይም የኤርትራ ነጻ አውጭ
የሚባሉትን በማሰልጠንና እስከ አፍንጫቸው በማስታጠቅ የተጨወቱት ኢትዮጵያን የማዳከም
ሁለንተናዊ ሚና ምንግዜም ቢሆን ትውልድ የሚረሳው አይሆንም!! በቅርብ እንኳን በባድሜ
ጦርነት ግዜ ግብጽ ለሻቢያ ጦር መሳሪያና ፈንጅ በማቀበል የተጫወተችው መጠነ-ሰፊ ሚና
የዚያው የረጅሙ አፍራሽ ታሪካቸው ቅጽያ መሆኑ ነው - - - ጎጠኛው ወያኔ ከሻቢያ የክፋ
የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት መሆኑን ባለማወቋ!!
እናም ዛሬ በዐባይ ወንዝ አጠቃቀም ጉዳይ ላይ ከግብፅ ጋር የሚደረጉ ውይይቶችና ስምምነቶች
እነዚህን ታሪካዊ ችግሮች ሁሉ መሠረት በማድረድ የሚከናወኑ መሆኑ ሲገባቸው ወያኔ ለምን
በሚስጢር መያዝ ፈለገ? እርግጥ ነው በታሪክ አጋጣሚ ወያኔ ከግብፅ ጋር በዐባይ ጉዳይ
ለመደራደር መቅረቡ እጅግ በጣም ያሳዝናል!! ያውም ወያኔ በረጅሙ የ24 ዓመታት የጎሳ ወረራ
አስተዳደሩ አንድም ቀን እንኳ ኢትዮጵያዊ ባልሆነበት ሁኔታ እንዴትስ የኢትዮጵያ አንጡራ
የተፈጥሮ ሀብት በሆነው ዐባይ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም በማስጠበቅ መደራደር ይችላል?
የግብፁ መሪ ፕሬዜዳንት አል-ሲሲ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ማርች 23 ቀን 2015)
የመርህ ስምምነት ተፈጠመ ወደ ተባለበት የካርቱሙ ውይይት ከመምጣታቸው በፊት
መግባቢያው ሰነድ ላይ የተለያዩ ግብፃውያን ባለሙያዎችን (ከመሃንዲስ እስከ ደኅንነት ኃላፊዎች
ጭምር) ባሳተፈ መልኩ በቂ ግንዛቤ የጨበጡበትና በተቻለ መጠን የግብፅን መብት በማስጠበቅ
ረገድ ሰነዱ አስቀድሞ እንዲስተካከል ማድረጋቸው በሚገባ ከመታወቁ ባሻገር በመጨረሻም
የሆነው የግብፅን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ላይ የተደረሰ ስምምነት ነበር የሆነው::
ለዚህም ኢትዮጵያ ከግድቡ በሚወጣው ውኃ የመጠቀም መብቷን ሙሉ በሙሉ የገፈፈ ብቻ
ሳይሆን መጀመሪያውንም ወደ ግድቡ በሚገባው ውኃ መጠንና የግዜ ገደብ ላይ የግብፅን ፈላጎት
መሠረት ያደረገ እንዲሆንና በዐባይ ገባር ወንዞች ላይም ኢትዮጵያ እንዳትጠቀም ያደርጋታል::
ከዚያም አልፎ ግብፅ ኢትዮጵያ በውኃው አጠቃቀም ላይ ጎድታኛለች ብላ ቅሬታ ብታቀርብ
ኢትዮጵያ ለግብፅ ካሳ የመክፈል ግዴታ አለባት ይላል::
እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ ወያኔዎች ዛሬ ለሱዳን አሳልፈው የሰጡት የኢትዮጵያ ሰፊ መሬት
ከሱዳን መንግሥት ጋር የተናጠል ቋሚ ወዳጅነት የሚፈጥርላቸው መስሏቸው የአንድ ሳንቲም
3
ሁለት ገጽታዎች ተፈጽሮአዊ ባሃሪና አካልነት ካላቸው አንድም ሁለትም ከሚሆኑ ከሱዳንና
ከግብጽ ጋር ያለ ዐባይ ተፋሰስ አገሮች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ለውይይት ማቅረባቸው ለተንኮል
ካልሆነ በወሳኝ ውሳኔዎች ላይ በድምፅ እንደሚበለጡ (ወያኔዎች) ጠፍቷቸው ነውን?
እንደ መርህ መግባቢያ ስነዱ ስምምነት ከሆነ ከአሁን በኋላ በዐባይ ላይ የሚወሰኑት መሠረታዊ
ጉዳዮች ላይ ወሳኙ በሦስትዮሽ የሚቋቋመው ኮሚቴ በመሆኑ ኢትዮጵያ ምን ግዜም ቢሆን በወሳኝ
ጉዳዮች ላይ አንድ ለሁለት (በ2/3 ድምፅ እየተረታች) ለዘመናት የተከፈለበትን የነጻነት ታሪክ
ፍትሃዊ ባልሆነ የድምፅ ብልጫ እያስረከበች እንድትገባ እያደረጓት መሆኑ ዳግም እየታየ ነው::
ለዚህ ደግሞ የወያኔ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ተጻሮ በመቆም ኤርትራን ያለ ሕጋዊ አግባብ የሕግ
ሽፋን በመስጠት በድብስብስ እንድትነጠል ማድረጉና በኋላም በታሪክ አጋጣሚ ዳግም በአልጀርስ
ውይይት ላይ ተጨማሪ ታሪካዊ ክህደት መፈጸሙን ለዋቢነት ይጠቅሳሉ!! ይህን ክእደቱን ነበር
ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ሳይቀር ወያኔ የኢትዮጵያን ቋሚ ጥቅም አሳልፎ በመስጠት "ትራክ ሪከርዱ"
ይመሰክራል ብለው ለማስረጃ ለVOA ጠያቂ ወያኔ ከሱዳንና ግብፅ ጋር ያደረገው ስምምነት አደጋ
ሊኖረው እንደሚችል አስቀድመው ስጋታቸውን በይፋ የገለፁ!!
ወያኔዎች ከላይ በአጭሩ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ብቻ ሳይሆን ሁለቱ አገሮች እንዲወስኑ ያደረጉ
በዋናው የግድቡ የዕለት ከዕለት ድርጊት (including the Dam’s day to day operation)
ሳይቀር ሙሉ መብት አጎናጽፏቸዋል!! የወያኔ እድሜ እንዲረዝም ከፈቀድንለት ወደፊት ደግሞ
ለሁለቱ አገሮች የባለቤትነት መብት ቢሰጣቸው ሊደንቀን ነውን?
ግብፅ ከ550 ኪ.ሜ ባላነሰ ርዝማኔ ላይ በተንጣለለው የአስዋን ግድብ ላይ ሕዝቧ ይህን እርዝማሌ
ተከትሎ ከኢትዮጵያ የሚሄደውን ለም የደለል አፈር በመጠቀም እጅግ በጣም መጠነ ሰፊ ምርት
ያመርቱበታል:: በዓለም ገበያ የሚታወቀው የግብፅ የጥጥ ምርትና ራሳቸውን ከመመገብ አልፈው
ጥራጥሬና አትክልት ሳይቀር ለውጭ ገበያ በስፋት የሚያቀርቡ መሆናቸው እንዳለ ሆኖ ለዚህ
ጽሁፍም መነሻ የሆነኝ አዲሱ የግብፅ ፕ/ዳንት አል-ሲሲ (under the patriotic leadership
of Former Military General Abdel Fattah al-Sisi) የዐባይን ወንዝ በመጠቀም በአዲስ
መልክ ሊገነቡ ያቀዱትን መጠነ ሰፊ ፕሮጀክት በአጭር ለመዳሰስ ነው::
ወያኔ ከሱዳን ድንበር ላይ ስለጀመረው (ደህንነቱ አስተማማኝ ስላልሆነው) የኃይል ማመንጫ
ግድብ ብዙ ሲያወራና ሲያስወራ ለመሆኑ ግብፅ በዚች ሰኮንድና ደቂቃ በዐባይ ወንዝ ላይ ምን
እያደርረገች እንድሆን ወያኔ ያውቃልን?
ፕ/ዳንት አል-ሲሲ እ.ኤ.አ በጁን 2014 የፕሬዘዳንትነቱን በትረ-ሥልጣን ጨብጠው ሁለት ወር
ባልሞላ ግዜያት ውስጥ ወዲያው የገማል አብድል ናስርን (1956 - 1970) የግባታ ፈለግ
በመከተል አዲሱን የስዊስ ካናል ሽንቁር ግንባታ መርሃ-ግብር (the New Suez Canal
4
Corridor Development Project) የመሠረት ድንጋይ በጣሉ ማግስት 7500 ግብጻዊያን
በቀጥታ ወደ ግንባታው ሥራ ተሰማሩ:: ለዚህ የሚያስፈልገውን ወጭ የግብፅ ተወላጆች ብቻ
በራሳቸው ፈቃድ (USA $8.5 billion dollar) በ8 ቀናት ብቻ በሽሚያ አዋጡት (as source
of reliable investment for Egyptian Citizens):: በመልካም ሁኔታ የተጀመሪው ሥራ
በአንድ ዓመት መጠናቀቅ ያለበት የሥራ እቅድ ከአሥራ አንድ ወራት ባነስ ግዜ መጠናቀቁ ደግሞ
አስገራሚ ነበር:: ይህም ጅምር ወደ ፍጣሜ በሚደርስበት ግዜ ግብፅ በሲውስ ካናል ላይ እጅግ
በጣም ብዛት ያላቸውን መርከቦች ያለ ትራፊት መጨናነቅ በፍጥነት ለማስተናገድ የሚያስችላት
ሲሆን አስዋን ግድብ በማስፋትና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመዘርጋት እጅግ በጣም ዘመናዊ የሆኑ 8
ከተሞችን ለመገንባት የሚያስችላትን መርሃ ግበር ጀምራለች:: ይህ ፕሮጀክትም የእስራኤልን
የበርሃ ማልማት እውቀትና ልምድ በመጠቀም ሲና በርሃንና ሌሎችን ሙሉ በሙሉ የማልማት
እጅግ በጣም ሰፊ መርሃ-ግብር ሲሆን ዐባይ ለሁሉም መርሃ-ግብሮች ዋናው የተፈጥሮ ሀብታቸው
አድርገው ለመጠቀም እቅዱ ተይዟል::
ይህ ቶሻካ (Toshka) ተብሎ የተሰየመው ፕሮጀክት ወደ 42,000 ሄክታር በረሃን ከአስዋን ግድብ
በመጠቀም (በዐባይ ወንዝ በመጠቀም) ሙሉ በሙሉ ወደ አረንጓዴነት የሚለውጥ ሲሆን ሊገነቡ
በታሰቡት እጅግ በጣም ዘመናዊ 8 ከተሞች ላይም የዘመኑ አዳዳሲ ቴክኖሎጅ ግንባታን
በመጠቀም - ፈጣን ዘመናዊ የባቡር መስመሮች - ዩንቭርሲቲዎችና ሌሎችም ልማቶችን
ይዘረጉበታል:: ሁሉም ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ በግብጻዊያን እውቀትና ገንዘብ እንዲሁም ጥሬ
ሃብት እንዲገነቡ ጽኑ እምነት ያለ ቢሆንም ቅሉ ፕሮጀክቱን ለማገዝ ተብሎ የቻይናው የውጭ
ጉዳይ ምኒስቴር ዋንግ ዪ (Wang Yi) አል-ሲሲን በግንባር በማነጋገር ፕሮጀክቱን በኒውክለር
ግንባታና ዘመናዊ ቴክኖሎጅን በመገንባት ለማገዘ አገራቸው ቻና ወደ ኋላ የማትል መሆኗን
አረጋግጠውላቸዋል:: ይህም የቻይናው የግንባታ መር ዓይነት "One Road, One Belt"
የሚለውን Deng Xiaoping 1976 የእዳሴ ልማትና የጥንቱን የቻይናውያን መሪ Confucius
ትብብራዊ ዕድገት መርህን ተግባራዊ በማድረግ የግብፅን ዘመናዊ እድገት ማፋጠን ያስችላል
ብለዋቸዋል::
የግብፅ ቶሻካ (Toshka) ፕሮጀክት ተብሎ የሚታወቀው ጅምር እቅዱ እ.ኤ.አ 1997 የወጣ
ቢሆንም ቅሉ ይህን ተቋርጦ የቆየን እቅድ እንደገና በአዲስ መልክ በስፋትና በጥልቀት በመንደፍ
ያዘጋጁት እውቁ ግብጻዊ-አሜሪካዊው ናሳ አፖሎ 11 ን ከጨረቃ ላይ እንዲያሳርፍ በእቅዱ ላይ
ሰፊ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ፋሮክ ኤል-ባዝ (Professor Farouk El-Baz) ሲሆኑ
የፕሮጀክታቸውን አወዳደቅ በወረቀት ላይ ላዬ የግብፅን ትንሣኤ ዳግም ያወጀ መሆኑን ለመገንዘብ
ሲያስችለው በዚያው ልክ ደግሞ የወያኔ ከንቱ ድንፋታ ከግብጽ አዲስ የግንባታ መርሃ ግብር ጋር
ላወዳደረ ዐባይን በጭልፋ ነው የሚሆንበት!! ያውም ወያኔ የዐባይን ግድብ እየሰራሁ ነው
5
የሚለው የራሱ ጎሳ ፖለቲካ ስለቦቹና ካምፓኒዎች የሥራ መስክ ለመፍጠር ብሎ ከሚያደርገው ጎን
ለጎን ደግሞ ታላቋ ትግራይን ለመፍጠር ተጨማሪ ግብአት አድርጎ እየወሰደው መሆኑ አጀማመሩ
በሚገባ እያሳየ ነው!!
ለዚህም የጎጃም ክ/አገር አውራጃ በሆነው በመተከል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አማራዎችን
ከመሬታቸው በማባረርና ያፈሩትን ንብረት በመዝረፍ በምትኩ አዳዲስ ነዋሪዎችን ከትግራይ
በማምጣት ማስፈሩና የትግራይ ተወላጆች ከሚያከናውኑት ዘመናዊ የእርሻ ሥራ ጎን ለጎን ከ3500
በላይ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች የተለያዩ ቋሚ የንግድ ተቋም ባለቤቶች እንደሆኑ በራሳቸው
በትግራይ ተወላጆች አንደበት በይፋ እየተነገረ መሆኑን በዋቢነት ማቅረብ ይቻላል::
የትግራይ ተወላጆች እንደማንኛው ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሚመቻቸው ቦታ ተንቀሳቅሰው ሰርተው
ንብረት የማፍራትና የመኖር ሙሉ መብት ያላቸው ቢሆንም ቅሉ ወያኔ ታሏቋ ትግራይን
እገንባለሁ በሚል መጥፎ አባዜ አልፎ እየከነዳ ነዋሪውን ኢትዮጵያዊ እየገደለና እያፈናቀለ
የሚያሰፍርባቸውን መሬት ሁሉ የትግራይ አካል ነው (ወይም መሆን አለበት) እያሉ የወያኔ ተባባሪ
መሆን ግን ለዘለቄታው ፍጹም ደም የሚያቃባ መሆኑን አስቀድሞ በመገንዘብ ይህ የባንዳ ልጆች
ስብስብ አካሄድ የኋላ ኋላ ለትግራይ ሕዝብም ጦሱ የሚተርፍ ነውና እጅግ በጣም የዘገየ ቢሆንም
እንኳ አሁንም ቢሆን ወያኔን በጋራ ሆነን በቃህ ልንለው ይገባል:: ወያኔ የትግራይን ታሪካዊ
የተከዜን ድንበር ተሻግሮ ከሁመራ እስከ መተማ ባለው የጎንደር ክ/አገር ግዛት ውስጥ እየፈጸመ
ያለውን ዘር የማጥፋት ድርጊት አንስቶ መዘርዝር ይከብዳል::
እኛ ኢትዮጵያውያንም በሕዝብ የተመረጠ ሁነኛ መሪ በሚኖረን ግዜ አንድ ግድብ መገደብ ብቻ
አይደለም አሥር ሌላ ግድብ መገደብ የሚችል ንብረትና እውቀቱ እንዳለን ለግብፅና ለዓለም
ሕዝብ ማሳየት እንችላለን!! እናም አሁን ግዜው የሚጠይቀው ወያኔን በቃህ በማለት ሕዝባዊ
አመጹን መቀስቀስና በጽኑ እምነትና ቆራትነት ትግሉን መምራት እንጅ ወያኔ ሳይወዳደር ባቸነፈው
የምርጫ ድራማ አዳማቂ መሆንን አይደለም!! በዐባይ ላይም ቢሆን ወያኔ የኢትዮጵያን ጥቅም
የማስጠበቅ ተወጥሮአዊ እድገቱና ጎሰኝነት አደረጃጀቱ ስለማይፈቅድለት ወግድ ልንለው ይገባል!!
ግብፅም ቢሆን ኢትዮጵያን ለማዳከም ያልፈነቀለችው ድንጋይ ባይኖራትም እስልምናውን ግን
እንደ አንድ ቋሚ እስትራቴጅ አድርጋ ከመውስድ ወደ ኋላ አላለችምና እሷንም ቢሆን ልክ እንደ
በፊቱ ሁሉ “አገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው” ብለን በአንድ የአገር ልጅነት ስሜት በቃሽ
ልንላት ይገባል!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

No comments:

Post a Comment