Friday, May 8, 2015

ኤሎሄ ኤሎሄ…አቤቶ ሰማን


ኤሎሄ ኤሎሄ… አቤቶ ሰማን
አማኝ ሕዝቦችህን ስለ ምን ተውከን።
በአምሳልህ ፈጥረህ አንተን ያአስመሰልከን
በ እጆች ሰርተህ ውበትን ያአደልከን
አንተ ነህ እግዚአብሔር የአምላኮች አምላክ
በፍጥረቶችህ ላይ …እኛን ያሰለጠንክ።
ፈቃድክን ሳያገኝ … ማን በማን ይደርሳል
የአራዊቶች ንጉሰ መች አንበሳ ያገሳል
የማን ክንድ ፈርጥሞ እማን ላይ ይነሳል
ሀያል አንተ ብቻ …ወደር የለህ አቻ
በፍኖተ ሎዛ ያዕቆብ ከአንተ ታግሎ
እንቢኝ አለቅህም ካልባረከኝ ብሎ
በፍቅር አሸነፈህ እሰራኤል ተብሎ።
ዘሩን ባረክለተ በከንዓን ምድር
እያፈሰስክለት ወተትና ማር።
ልጆቹ በድለው አንተ ብትቆጣ
ረሀብ ችግር ሆነ መሰደድም መጣ
በግብድ ባርነት እሰራኤል ተቀጣ
ራሔል አለቀሰች ልጅዋን በእግርዋ ረግጣ።
ያኔም የወገንህን ጩከት ሰማህና
ወርደህ አዳንካቸው ከፈርኦን ጫና።
ታዲያ እንዴት ኢትዬዽያን ጨክንህ ዝም አልካት
ከክብርዋ ተዋርዳ… አህዛብ ሲአሰካካባት
ያረመኔ መንጋ …ግፍ ሲፈድምባት
የክርሰትያን ጠላት ልጆችዋን ሲያረድባት
ምነው? የማረያም ልጅ… ያልተመለከትካት።
የዮዲት ጉዲት ግፍ፤ የመሃመድ ሰይፍ
የአክራሪዎች ሜንጫ፤ የባእዳን ጡጫ
ከአረማዊያን ሃገር … ሳውዲ አረብያ
በደቡብ አፍሪካ የመንና…ሊብያ
የተፈዸመብን በአንተ ዘንድ ይታያ
አሜን ሃሌ ሉያ፡ አሜን ሃሌ ሉያ።
ምን ቃል አለን ለሰው አውሬ
ዘግናኝ ግብሩ… የዓለም ወሬ
በእውነተኛ ሃይማኖት ድናት ጥንካሬ
በኦርቶዶክስ እምነት ሰማእትነት ፍሬ
ወንጌል በደማቸው ለአህዛብ የሰበኩ
ሀዲስ ሃዋርያት በጌታ የተመኩ
በብር ብንደለል…በእሳት ብንቃጠል
ታንቀን ብንሰቀል…ታርደን ብንገደል።
ማህተብ አንበጥስም…ሃይማኖት አንክድም
ከክርስቶስ ፍቅር ማንም አይለየንም ።
ብለው ያለፉትን የኦርቶዶክስ ጀግኖች
እንዘክራለን የተዋህዶ ልጆች።
አንፈራም አንሰጋም …ለሥጋዊ ሞት
አስተምረውናል ሆነው አብነት።
ኤሎሄ ኤሎሄ …አቤቶ ስማን
ለአንተ ያለንን ፍቅር…በሞት አሳየን
ይሄ ዓለም ጠልቶናል…ብቻ አትተወን።
እማማ ኢትዩዽያ ሃገረ እግዚአብሔር
እጆችዋን ዘርግታ …ሰትል ሕዝቤን ማር
ሰማዕት ልጆችዋ ሆነው ምሰክር
አረ ፍረድላት…በእኛ አትማረር።
ቴዎድሮስ እራሱን ከመግደሉ በፊት
ኢትዮዽያ እንዳታቅስ…አጥብቆ ነገራት
ሠላም ፍቅር አጥታ …ነገ እንባ እንዳያጥራት
አቡነ ዼጥሮስም… ገዝተው ሞቱላት።
ያ የአባቶች ራዕይ ፤ ዛሬ ደርሶ ሊታይ
እንባ በእንባ …ዋይ ዋይ፤ እንበ በእንባ ዋይ ዋይ።
ፍቅር አንድነት ጠፍቶ፤ መተሳሰብ ቀርቶ
መለያየት ሰፍቶ፤ ዘረኝነት ደርቶ።
አጉል መጠላላት፤ እርስ በእርስ መባላት
በላይዋ ላይ ሰፍኖ…ኢትዮዽያን ዝም አልካት።
ኤሎሄ ኤሎሄ አቤቶ ስማን
ችግር፤ስደት፤እልቂት…ስቃይ በዛብን
የሠርዊት አምላክ በምህረት ጎብኘን
በአዛኝቱ ማርያም ብለህ ተለመን
ሰቆቃችን ያብቃ ፍርድህን ስጠን
ኤሎሄ ኤሎሄ አቤቶ ሰማን።
ለሊበያ ሰማዕታት መተሰቢያ
ከሰባኪ ወንጌል ሽመልሰ ተሊላ ሚያዝያ 12 2007 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment