Friday, February 1, 2013

ህወሀት ከኔ ጋር ነው ያለው፤አደረጃጀቱም ከኔ ጋር ነው ያለው…(አቶ ስብሀት ነጋን )Dereje Habtewold


 

Sebehat  Nega(aboye)
ያልገባኝ ጥያቄ
ስለ ህወሀት መከፋፈል በስፋት እየተነገረ ባለበት ሰዓት ፍኖተ ነፃነት በጉዳዩ ዙሪያ አቶ ስብሀት ነጋን አናግሯቸዋል።
አቦይም፦<<በዚህ ምድር ላይ ሊሆን ከማይችል ነገር አንዱ የህወሀት መሰንጠቅ ነው። …ህወሀት ከኔ ጋር ነው ያለው፤አደረጃጀቱም ከኔ ጋር ነው ያለው…>> የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል፤ ወይም ለማስተባበል ሞክረዋል።
በመቀሌ ተበትኗል በተባለው ወረቀትም ሆነ ዛሬ ፍኖተ-ነፃነት ባጠናቀረው ዘገባ እንደተመለከተው በነአቶ ስብሀት ቡድን እና በነ አቶ አባይ ወልዱ ቡድን መካከል የጎላ ልዩነት የተፈጠረው፤ እነ አቶ ስብሀት (ስዩም፣አባይ፣ቅዱሳን ወዘተ)- ቀደም ሲል ከህወሀት የተባረሩት የድርጅቱ የቀድሞ አመራሮች መመለስ አለባቸው” የሚል አጀንዳ በማራመዳቸው ነው።
እዚህ ላይ ያልገባኝ ነገር ህወሀት ለሁለት በተከፈለ ጊዜ ፦”አንጃ”ተብለው በአቶ መለስ ቡድን ከድርጅቱ የተባረሩት ሰዎች ”ወደ ድርጅታችሁ ተመለሱ”ቢባሉ ለመመለስ ፈቃደኛ ይሆናሉ ? እነ አቶ ስብሀት በዚህ አቋም ምክንያት እስከመቃቃር የደረሱትስ ከተባረሩት ጋር ስምምነት ላይ ከደረሱ በሁዋላ ነው? ወይስ “እኛ እንስማማ እንጂ እነሱ መመለሱን ይፈልጉታል” ከሚል ግምት ተነስተው? “የተባረሩት ይመለሱ” ሲባልስ ከመካከላቸው የተወሰኑት (እነሱ እንደሚሉት ነፍጠኞች ጉያ ያልገቡት እነ ስዬና ገብሩን ሳይጨምር) ተመርጠው ነው? ወይስ “ሁሉም ይመለሱ” ነው እየተባለ ያለው? እንበልና ህወሀት በስምምነት “ይመለሱ”ቢልስ በእርግጥ የተባረሩት የቀድሞው አመራሮች ይመለሳሉ? ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

staff reporter | January 31, 2013 at 1:03 pm | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-1oy
Comment  

            


No comments:

Post a Comment