Tuesday, September 29, 2015

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ (ጥላዬ ታረቀኝ)



ሰንደቅ አላማ የአንድ ሀገር ህዝቦች ተስማምተውበት ይወክለናል ቢውለበለብ ይገልፀናል ብለው ለቀለማቱ ትርጉም በመስጠት ከምንም በላይ ክብራቸውን የሚገለፀበት የሀገር ውክልና የሚወስድ ወይም የሚገልፅ የሀገር ንብረት ወይም መግለጫ ነው ። ሰንደቅ ሀገራት ከሀገራት የሚለዮበት ትልቅ ምልክት ነው። ሀገራት ወይም ሰንደቅ አላማ ትልቅ ዝምድና አላቸው በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያለች ድንቅ ሀገር ለሰንደቅ አላማ ያላት ክብር ከፍተኛ ነው ። ሰንደቅንና ኢትዮጵያዊ የተቆራኞት ሀገሪቱ በንግስና መተዳደር ከጀረችበት ግዜ አንስቶ ትውልድ ለትውልድ እያስረከበ ለባንዲራ ያለው ፍቅር ከአያቶች እየተማረ ለልጆች እየተላለፈ የመጣበት ሁኔታ ነው። የነበረበው ሄደቱ ሳይቆራረጥ በዚያ ሰአት የነበረው ትውልድ ሲረከብ ሲያስረክብ ይዘቱን ቀለሙን ሳይቀየር ቢጎዝም በንግስና ግዜ የነበረው መሀል ላይ የሞሀ አንበሳ ምልክት ከሀይማኖት አንፃር ቢነሳም ቀጣይ የነበረ የባንዲራ ፈተናዋች የበዙ ቢሆንም ባንዲራዋ ግን ቀለሞን ሳትቀይር እዚህ ደርሳለች ።
የትውልድ ቅብብሎሽ ባንዲራዋን እዚህ ቢያደርሳትም ያኔ የነበረ ትውልድና አሁን ያለው ትውልድ ለባንዲራ ያለውን ክብር ከማወቃችን በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ለባንዲራ ያለውን ፍቅር መግለፅ ማስቀደሙ ሊገልፀው ይችላል። ብዬ በማሰቤ ይቺን ላስቀምጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመከራ ለችግር ለደስታ እንዲሁም ለሀገራዊ ክብር በአላት ላይ ይውለበለባል ሀገራችን ዳር ድንበሮ ተሰብሮ በተወረርንበት ግዜ አባቶች ህዝቡን ሲያነቁ ባንዲራህ ተደፎርል ድንበርህ ተጥሶል ለክብርህና ለባንዲራ ውጣ ብለው ያዙ ነበር። በዚያ ግዜ ለባንዲራ ያላቸውን ነገር ብንገልፅበት ሊገልፀው ይችላል ብዬ ያስብኩትን ይቺን እንመልከት ሸንጎ (.ፍርድ) ሲቀርቡ ሰው ሲበድላቸው እረ በባንዲራ ብሎ ከለመነ ጥፍተኛውም ጥፍቱን ያርማል በዳይም በደሉን ይቅር ይላል ተበዳይም የተጠራው #ባንዲራ በመሆኑ!!!
ለሀገራችንን ኢትዮጵያ ባንዲራ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መልስ ሊሆነው የሚችለው ባንዲራ ወይም ሰንደቅ አላማ ማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ዘውድ ወይም ደም ማለት ነው። ይሄ ለኢትዮጵያ ህዝብ መገለጫ የሆነው ሰንደቅ አላማ አሁን ላለው ትውልድ ምን ቦታ አለው ብለን መፈተሽ ተገቢ ነው ባይ ነኝ በነገራችንን ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ መንግስታት ሲቀያየሩ በመሳሪያ ስለሆነ ሁሉም ሲመጡ የህዝብን የሚውክለውን ሳይሆን የህዝብን ፍላጎት ሳይሆን እነሱ ይመቸናል ስልጣናችንን ሊያራዝምልን ይችላል ብለው ያመኑትን ከህዝብ ፍላጎት ውጪ ምልክት በመጨመር የስልጣን እድሜን ማርዘሚያ እንጂ ለሀገር ፍቅር ወይም ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ የለም ሁሉም ለራሱ በማሰብ እንጂ የፀና የኢትዮጵያን ባንዲራ የለም መንግስትም ቢወርድ ቀጣይነት ያለው ባንዲራ ባለመኖሩ የአሁን ትውልድ የኔ ነው ብሎ ሳይቀበል ያንተ ነው ተቀበለው ተብሎ ስለተቀበለው ጥቂት የዚህ ትውልድ ወጣቶች የባንዲራ ትምህርት ትርጉም ባይገባቸውም ለባንዲራ ያላቸውን ፍቅር ይሄ ነው ብሎ ለመተንበይ ያስቸግራል የአባቶቻቸው መሰረት ተቀይሮ ስላገኙት ይሄን ደግሞ ለዚህ መሰረት መናጋት ዋናው ተጠያቂ አስተዳዳሪ ሆኖ ራሱን የሾመው የህውሀት ኢህአዲግ መንግስት ነው ።
ከህዝብ ጋ ሆድና ጀርባ ሆኖ በራሱ ፍቃድ ትርጉም ሊሰጥ የማይችል ተጨማሪ ባእድ ከእምነት ከሀገሪቱ ነባራዊ ሆኔታ ጋ የማይገናኝ ለትውልድ መከራ የሚያመጣ እርስ በእርሶ እንዳይተማመን መልካም ያልሆነ የባንዲራውን ፎርም ወይም መልክት ያጠፉ የሰይጣን ምልክት ነው። የተባለወን መሀል ላይ በመሰንቀር ባንዲራውን ከህዝብ በመነጠል የራሱ በማረግ የባንዲራውን ትርጉም በማዛባት በሀገሪቱ የነበረውን የባንዲራ ቁጥር ከአንድ ወደ አስራ ምናምን ያሳደገ የህውሀት መንግስት ለባንዲራ የነበረውን ክብር ዝቅ አድርጎታል ።

በዚህም የተነሳ የአሁን ትውልድ የባንዲራ ትርጉም ጉራማይሌ እንዲሆን አድርጎል ከአስራ ምናምን ውጪ የሀገሪቱ ባንዲራ በሁለት በመክፈል
1 አረንጎዴ ቢጫቀይ (ንፁህ) ቀደም
2 አረንጎዴ ቢጫ ቀይ (መሀል ላይ ኮከብ በማረግ የሀገሪቱን ባንዲራ በሁለት በመክፈል የባንዲራ ፍቅር ይሁን የባንዲራ ትርጉም በማጥፍት ግንባር ቀደም ተወቃሽና ተከሳሽ ይህ ሀገሪቱን እየመራ ያለው መንግስት ነው ።
አሁን በህይወት የሌሉት ጠቅላይ ሚኔስተር አማካኝነት የባንዲራን ክብር ዝቅ በማድረግ ጨርቅ ነው እስከማለት ደረጃ ደርሶ የነበረበት ወቅት ሁሉ ነበር ይሄን የነበረ የሀገር ባንዲራ ትርጉም በማሳጣት ደረጃ ከፍተኛውን ሚና በመጫወት አሁን ሀገሪቱን በመሳሪያ ሀይል እየመራ ያለው ህውሀት ኢህአዲግ አስራ አራት ባንዲራዋችን በአንድ ሀገር ላይ እንዲውለበለቡና በአለም አቀፍ ደረጃ ሁለት ባንዲራዋች በዜጎች ደረጃ እንዲውለበለቡ ከፍተኛ አስተዋፅ አበርክቶል የስርአቱ ደጋፊዋች ባለአርማውን ወይም ሰይጣን የሰይጣን ምልክትን ያካተተውን ሲያውለበልቡ በዚህ አመት የሰይጣን ቤተመቅደሴ ነው በማለት ያስተዋቀውን ማስታወስ በቂ ነው በዋሽንግተን ዲሲ ሰሞኑን ቤተ መቅደሴን ከፍቻለሁ ምልክቴም ይሄ ኮከብ ነው።


በማለት ለቢቢሲ ይፍ በማድረግ በአለም ዜናውን አሰራጭቶል ይህ የሰይጣን ምልክት ደግሞ በኢትዮጵያ ባንዲራ መሀል ላይ ተለጥፎ ይገኛል በመሆኑም ሀገር ውስጥ በሀይል በህግ በህገወጥ መልኩ በማሰፈራራት እንዲውለበለብ ቢያረግም ከሀገር ውጪ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ግን ባንዲራውን አይቀበሉትም በብዛት ህዝብ የሚቀበለው አርማ የሌለወን .#አረንጎዴ #ቢጫ #ቀይ ሲሆን ብዛት ያለውተቀባይነትም አለው ይሄም ህዝቡን ይወክላል ።ይሄ ሆኖ ሳለ እውነቱ ስርአቱ ግን የብሄረሰቦችን እኩልነት እንዴት እንደሚወክል በፍጹም የማያሳየውን አና ታማኝነት የሌለው ከሃገሪቱ ሃይማኖታዊ ባህላዊ አና ማህበራዊ ዘይቤ ጋር የማይገናኘው ይህ ኮከብ ያለበትን ባንዲራ ሰንቅሮ ሃገራችን ላይ በፍቃድ ያውለበልባል በመሆኑም እኛን የሚወክለን መሀል ላይ ምንም የሌለበት አረንጎዴ ቢጫ ቀይ ነው ሰንደቅ ኣላማ መሃልላይ ያለው ባእድ ምስል መነሳት ኣለበት ::
ህዝብ ሀይል ነው በቅርብ ይቺ ንፁህ የኢትዮጵያ ባንዲራ ትውለበለባለች
ድል የህዝብ ነው #ባንዲራየ #አረንጎዴ #ቢጫ #ቀይ ቅን አሳቢው .#ጥላዬ #ታረቀኝ

No comments:

Post a Comment