Tuesday, September 8, 2015

የኢትዮጵያ አገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን ምሥረታ በማስመልከት የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ


http://ethsat.com/video/2015/09/07/esat-breaking-news-four-ethiopian-forces-formed-a-united-front-sep-07-2015/
September 8, 2015
…በጋራ አብሮ በመታገል የሚገኘው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የገባቸውና ካለፈው ተደጋጋሚ የታሪክ ስህተት የተማሩ፣ በአገራችን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት በምድር ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ አራት ድርጅቶች በጥምረት ተባብረው በጋራ ለመታገል ወስነዋል። እነዚህ አራት ድርጅቶች ለብዙ ዓመታት የአብሮ መታገል ፍላጎት እንቅፋት የሆነውን የገዢ መደቦች የከፋፍለህ ግዛው ሴራ በጣጥሰዋል። ይህ ዛሬ በጥምረት የተጀመረው ትብብር እያደገ ሄዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ውህደት እንዲያድግ ይደረጋል። ከዚህም በተጨማሪ ንቅናቄው ከሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ከሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይገፋበታል።
በዚህም መሠረት፣
1ኛ) የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ
2ኛ) የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ
3ኛ) የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ፣ እና
4ኛ) የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ
የኢትዮጵያ አገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ (በአጭሩ “የአገር አድን ንቅናቄ”) የሚባል ድርጅት ዛሬ በአዲስ ዓመት መባቻ ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ፈጥረዋል። የንቅናቄውን ምክርቤት፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የተለያዩ መምሪያዎችን ከማቋቋሙም በላይ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ሊ/መንበር፣ አቶ ሞላ አስግዶምን ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። [ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]
United Movement for the Salvation of Ethiopia through Democracy

No comments:

Post a Comment