Friday, March 1, 2013

ሰበር ዜና- የፓትርያርክ ምርጫው ተከናወነ ስድስተኛው ፓርትርያሪክ ተመረጡ by staff reporter

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያሪክ ኾኑ!!!
የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢትየጽያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ፡፡ ከ806 ድምጽ 500 ውን በማግኘት ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ለረጂም ጊዜ አጨቃጫቂ የነበረው ይሄው የምርጫ ስርአት በአቡነ ማትያስ ወደ መንበሩ በመምጣት ተጠናቋል ለበለጠ መረጃ ዝርዝሩ እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡

የድምፅ ቆጠራው ውጤት ታውቋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በ500 ድምፅ አሸናፊ ! ! !
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – በ98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – በ70 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – በ98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – በ39 ድምፅ
photo 4
ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ
በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚሾሙ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ይኾናሉ፡- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት !!!
በዛሬው የመራጮች መዝገብ 808 መራጮች ተመዝግበዋል፡፡
806 መራጮች መርጠዋል፡፡
15 ድምፆች ዋጋ አልባ ኾነዋል፡፡
አንድ ባዶ የድምፅ መስጫ ወረቀት ተገኝቷል፡፡
ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ንግግር አድርገዋየምርጫውን ውጤት እንደሚቀበሉ ገልጸዋል፡፡
እሑድ በዓለ ሢመቱ ከተፈጸመ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ተመልክቷል፡፡
ለምርጫው በአጠቃላይ ብር 3,650,000 ወጪ መደረጉን የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ተናግረዋል፡፡
ከምርጫው ውሎ ጋራ የተያያዙ ተጨማሪ ዘገባዎችንና ትችቶችን ከቆይታ በኋላ እናቀርባለን፡፡ ሐራ ዘተዋሕዶ  ከልብ እናመሰግናለን፡፡

staff reporter | February 28, 2013 at 7:34 am | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-1uc
Comment 

No comments:

Post a Comment