Thursday, March 7, 2013

“ድህነታቸውን ህዝቡ ላይ አራግፈው ለራሳቸው ባለፎቆች ሆነዋል..” ስማቸው ያልተገለጸ እናት



 

 
Gudu Kassa
ሉሉ
ከበደ(ጋዜጠኛና ደራሲ)
ሰሞኑንከአገርቤትአንዲትእናትልጃቸውንሊጠይቁመተውነበር።ልጃቸው የባለቤቴ ጓደኛነች።..የኔምጓደኛ! ...እኒህ አናት አንደበተርቱ እና ተደምጠው የማይጠገቡ ጨዋታ አዋቂ ቀልደኛምናቸው።ሑሉም ነገር የገባቸው ፍጹም ፖለቲካ አዋቂ ብሩህ እናት ናቸው። ጨዋታቸውንግግራቸው  ሁሉ ይማርካል። ሰማንያ አመት አይሞሉም። ጥንክርያሉ፤የነቁ ፍጹም ጤናማእናት ናቸው።
ወይንቢጤገዛሁናባለቤቴድፎዳቦጋግራ (እናቶችአዚህአገርሲመጡድፎዳቦሲቀርብላቸውደስእንደሚላቸውታውቃለች)እንኳንደህናመጡልንልሄድን።
 ለሁለትሰአትያህልአብሬስቆይከናታችንየገበየሁትትምህርትናቁምነገርበቀላልየሚገመትአይደለም።የኢትዮጵያህዝብእየጠላቸውዛሬስልጣንላይየተጣበቁትየወያኔደናቁርት፤የኢትዮጵያንህዝብምንምአያውቅምብለው፤የሚገምቱትናየሚንቁት፤ወደታችወደህብረተሰቡዝቅብለው፤ስለነሱአገዛዝ፤ስለመልካምአስተዳደርያለውንግዛቤቢረዱምንያህልከህብረተሰቡኋላኋላእየሄዱእንመራሀለንእንደሚሉበተረዱናባፈሩይበጃቸውነበር።
 እኒህእናትድህነትንእኩልያካፈለንደርግተሻለነውነውየሚሉት፤“እነዚህድህነታቸውንህዝቡላይአራግፈውለራሳቸውባለፎቅሆነዋል።ደርግአንዱንልጅአንዱንእንጀራልጅአላደረገንም።ቢበድለንምአልለያየንም።”
 ጎዳናላይለፈሰሱለማኝህጻናትናወላጆችዘወትርያለቅሳሉኑሮአቸውንየከተማውቆሻክምርላይየመሰረቱወላጆችናልጆችያስለቅሷቸዋል።“ይሄሁሉፎቅይገነባል።የእያንዳንዱንፎቅባለቤትአስርአስርልጅከጎዳናወስዶእንዲያሳድግቢያስገድዱትጽድቅነበር።ላለውሰውምንምማለትአይደለም”ይላሉ።
ስለቤተሰብስለዘመድአዝማድ፤ስአየርንብረትናሌላትንሽከተጨዋወትንበኋላወዲያውነበርስለሀገርጉዳይየተነሳው።
“ኑሮአንዴትነው?.. እትዬ... አገርቤት ” አልኩ።
 “...አየ... ልጄ .. ምንኑሮእንዴትነውትለኛለህ? ...ወያኔውእንዴትአደረጋችሁበለኝእንጂ? ...”
አነጋገራቸውያስቃል።ሁላችንምሳቅን።ሳቄንገታአደረኩና.. “ወያኔውምንአደረገ?.. እስቲያለውንነገርያጫውቱኝ...” አልኩ።
 “ ከየቱጋእንደምጀምርልህአላውቅምልጄ....ያላየነውታሪክየለም...በነዚህሰዎችዘመንያየነውጉድብዙነው።”
“ ምንጉድአለባቸው?”
 “ደግጠይቀኸኛልልጄ...ምንጉድአለባቸውአልከኝ? .... ይሔውልህእኔያንተእናት...ሶስቱንምመንግስትበልቻለሁ።.. አንድነገርልንገርህ ..ጃንሆይንክፉ ...አድሀሪስትሉ..ክፉመንግስትስትሉ ...ደርግመጣናክፉመንግስትምንአይነትእንደሆነአሳየን..ደርግንክፉስንልስንጠላ..ስንጠላ..እነዚህመጡናየባሰክፉመኖሩንአሳዩን..” ድንገትአቁዋረጥኳቸውና...
“የነዚህክፋትምንድንው?”
 “ደግብለሀልልጄ... የነዚህክፋት..ደርግወንበሬንቀናብላችሁአትዩብሎነበርያንሁሉሰውየፈጀው፤...አማራአላለም፤...ትግሬአላም።እስላምክርስትያንአላለም።ደርጉይልየነበረው፤አገራችሁንጠብቁ፤ተስማምታችሁአንድሆናችሁኑሩ፤ወንበሬንግንቀናብላችሁአትዩ...”
ፊቴንትኩርብለውእያዩ
 “..ያኔእናንተምበየከተማውጦርነትከፈታችሁበት..እሱምጦርነትከፈተ...ያሁሉበልቶያልጠገበልጅአለቀ።ቀድሞውንምያኔወይጫካሂዳችሁበተዋጋችሁትደግ...ወይአርፋችሁበተቀመጣችሁ... ያንንሁሉየልጅሬሳአናይምነበር..በኢሀፓጊዜ...”
 “..እነዚህመጡ ...ያገሬሰውተረተ። ... ‘ምንሽርልገዛወይፈኔን ሳስማማ፤መጣየትግሬልጅበነጠላጫማ’... ገናሲመጡጀምሮየወደዳቸውምየለ...እግዚአብሄርያመጣውንፍርጃመቀበልእንጂ  የሚደረግየለም...መጡልህናወንበራችንንምቀናብላችሁእንዳታዩ፤ለራሳችሁምእንዳትትያዩ...በየዘራችሁተበታተኑአሉ።ለሁሉምበየዘሩማህበርአበጀለትናሁልህምበዚህቀንበርውስጥትገባለህ..ግባአለው።”
“ማንነውያለው?’’
“ሟቹ...”
 “አልገባምያለ፤እነሱንየሞገተ፤የጥይትእራትይሆንጀመር።አንድምሰውጠመንጃአንስቶየተኮሰባቸውየለም።በያለበትሰውመግደልሆነስራቸው።አንዱንካንዱማባላት፤አሉባልታውሸትበራዲዮን፤በቴሌቭዥንሲነዙመዋልሆነ።እንዲህእንዲህአድርገውሰዉንሁሉአደናግረውሲያበቁ፤አስፈራርተውሲያበቁ፤...የራሳቸውንሰውሁሉ ቦታቦታውንአስያዙ።ዛሬያለነሱነጋዴየለም።ያለእነሱየቢሮአለቃየለም።ያለነሱየቀበሌአለቃየለም።ያለእነሱፎሊስየለም።ሰውሁሉሀሞቱፈሶእነሱንእየፈራመኖርየዟል።....ወንዱምሴቱም....ታዲያልጄደርጉእንደዚህባይተዋርአድርጎናል?”አሉናበንዴትእራሳቸውንእየነቀነቁጠየቁኝ።
 “ልማቱስእትየ?...አገሩንአልምተዋልይባልየለእንዴ?”
 “ሀሰት!..ሀሰትልጄ!...አገርቢለማ፤አገሬውሁሉከነልጁለልመናጎዳናላይይፈስነበር?...ልማቱንስቢሆንእነሱእንጂሌላውሰውየታለ?..የታለጉራጌባለፎቅ?..የታለአማራ?..የታለኦሮሞ?....ያፎቅየማነውስትል...እነሱ....ያፎቅየማነውስትልእነሱ.....ልጄከየትአመጡትያሰኛልእኮ?እነሱናአላሙዲእንጂሀብታምአለእንዴዛሬ?..”
 “ዛሬአንድሺህብርይዘህገበያወተህ.....አንዲትዘንቢልሞልተህአትመለስምእኮ!...ልማትማለትድህነትናእራብነውእንዴ?...ጦሙንየሚያድረውህዝብተቆጥሮአያልቅምእኮ.... እዚችውአዲስአበባ.....”
“...ጭራሽጥጋባቸው... ቤትዘግተው፤ዊስኪአውርደውሲጨፍሩየሚያድሩእነሱ...ጠግበውበሽጉጥሲታኮሱየሚያድሩእነሱ...መጠጥቤትየፈለጋቸውንደብድበውአድምተውየሚሄዱእነሱ....”
 “...የኛሰፈርመደዳውንቡናቤትነው።...አንድቀንጠዋትወደክፍለሀገርአውቶብስተራልሄድአስርሰአትተነስቼታክሲስጠብቅ....አንዲቷንድሀጸጉሩዋንይዞመሬትለመሬትእየጎተተበግንባሯያዳፋታል፤ከቡናቤትአውጥቶአስፋልትላይይረግጣታል።..ኡኡእያለች...ገደለኝእያለች...ሊገላግላትየመጣወንድጠፋ።ሰውሁሉሰምቶእንዳልሰማእየሆነብቅአላለም።በስካርመንፈስእንኳእነዚህንሰዎችየሚደፍርጠፋ?አልኩናእንባዬንእርግፍአድርጌአለቀስኩ።ልጄድሮሴትልጅድረሱልኝብላስትጮህእንዲህ ነበርእንዴ?..”
 “..ወዲያውኑአንድታክሲሲበርመጣ... አስቆምኩናገብቼ... እንዳውልጄይህንሰውየእላዩላይንዳበት!...ንዳበት!...ገደላትእኮ...ንዳበት!አልኩት።ለካንስያምባለታክሲየነሱሰውኖሯል...አንዳንድደግመቸምአለ...ሽርርርአደረገናመኪናዋንእላዩላይ አቁሞ፤ወርዶ፤እንደብራቅጮኸበትአልኩህ።ተጯጯሁ..ተጯጯሁ..ተሰዳደቡ፤ተሰዳደቡ..በግርግርእሷእመርአለችልህናደሟንእያዘራችተነስታአመለጠች...ያምከባለታክሲውጋርእየተሰዳደበወደመሄጃየአቀናን...”
 “..ዛሬአሁንየፈለገነገርቢመጣየአዲስአበባሰውቤትለነሱአያከራይም....”
“ለምን?” አልኩ።
 “ለምንማለትደግ..ይኽውልህልጄቤትታከራያቸውየለም?...ልቀቁስትልአይለቁም፤ ...ወደየትም ሄደህከሰህአታስለቅቃቸውም።...አንዲቷእንዳደረገችኝልንገርህ..” አሉናፎቴውላይእየተመቻቹ፤የተደረበላቸውንብርድልብስወደላይእየሰበሰቡ፤ “...እግዚአብሄርብድሩንይክፈላቸውናልጆቼቤትሰሩልኝብየህአልነበር?...”
ውድአንባቢያንወደጨዋታችንመጀመሪያላይልጆቻቸውቤትእንደሰሩላቸውነግረውኝ ነበር።አምስትልጆችአሏቸው።ሁሉምበየአለሙተበትነውይገኛሉ።ኖርዌይ፤ጀርመን፤አሜሪካ፤ካናዳ..እናሁሉምእንደየአቅሙአዋቶአራትዋናዋናክፍሎችከየመኝታቤትያላቸውባለአንድፎቅሰርተውላቸውነበር።እሳቸውአሮጌውቤትእየኖሩይህንቤትአከራይተውበሚያገኙትገቢስድስትየእህትየወንድምልጅከገጠርአስመጥተውእያስተማሩያሳድጋሉ።እናምልጆቻቸውእንደገናገንዘብእንስጥሽብለውእንዳይቸገሩበማለትለነሱያልነገሯቸው፤ነገርግንከቤቱኪራይቆጥበውምድርቤትባንዱክፍልምግብናመጠጥሊነግዱሀሳብአላቸው።ዛሬነገእጀምራለሁሲሉአንዱንቤትአላከራዩትምነበር።ኋላላይግንለማከራየትወሰኑ።
“...ቤትሰሩልኝብየህአልነበር?...ታዲያያችንአንዷንየቀረችውንለአምስትወርምቢሆንላከራይአልኩልህና....አንዱደላላአንዲቷንወያኔሴትይዞመጣ።ቤቱመንገድዳርነውለንግድይመቻል...አንባሻናሻይቡናልሸጥነውአለችኝ።.....አይልጄእኔምእንዲህ፤እንዲህላደርግሀሳብአለኝ።...ባከራይሽምለአምስትለስድስትወርነው።ከፍተሽየምትዘጊውንግድምንምአያደርግልሽም።ሌላብትፈልጊይሻልሻልአልኳት።”
 “...ሞቼእገኛለሁ።ልቀቂባሉኝቀንእለቃለሁ።እንደውእትዬ..እትዬ..” አለች።
“ኮሎኔልወንድምአላትአሉ።እሱነውካገሯያስመጣት።ላገሩምእንግዳነች።አይእንግዲህእለቃለሁካለችትግባብየበሰውፊትተዋውለንገባች።”
 “እርግጥጎበዝሴትናት።የኛሰፈርአላፊ አግዳሚውይበዛል።በጠዋትተነስታቄጠማውንጎዝጉዛ፤አጫጭሳ፤ቡናውንአቀራርባ፤ሞቅሞቅስታደርገው፤ መንገደኛውሁሉቁርሱንበልቶቡናውንጠጥቶላትወደየስራውይሰማራል።”
 “..እንዲህእንዲህእያለያችአምስትወርደረሰች።አይይችሰውአሁንእንዲህገበያውደርቶላትልቀቂብላትትቀየመኝይሆን?አልኩልህናእኔውተጨንቄአረፍኩት።...እሷምቤትልፈልግአላለች፤እኔምትንሽትቋቋምብየሶስትወርጨመርኩላት።ከዚያበኋላደሞሶስትወርአስቀድሜቤትእንድትፈልግነገርኳት።እሺአለች።ወርአለፈ።ሁለተኛውምአለፈ።ሶስተኛውተገባደደ።እየፈለኩነውትላለች።ወሩአለቀ።ቤቴንመልቀቅየፈለገችአትመስልም።...በይእንግዲህካጣሽእኔውእፈልግልሻለሁአልኩናከኔቤትወረድብሎሌላአገኘሁላትናበይበዚህወር መጨረሻላይቤቱንእፈልገዋለሁአልኳት።ወሩሲሞላደህናየነበረችውሴትዮድንገትተለዋወጠችብኝናአልወጣምሂጂክሰሽአትለኝመሰለህ?...አበስኩገበርኩ...አልኩናያዋዋሉንንሰዎችጠራሁናይችንሽፍታገላግሉኝአልኩ።ጭቅጭቋንቀጠለች።አንድአስራአምስትቀንስታምሰንከረመችአልኩህ...በኋላአንድቀንጠዋትወደዚሁቤትስመጣሌሊትእቃታግዝነበርሲሉኝአምላክበሰላምሊገላግለኝነውአልኩናገብቼቤቴንአየዋለሁ....ልጄአፍርሳዋለችአልኩህ...ግርግዳውንሁሉቧጣ፤ቧጣቧጣ.....እንደውልጄበምንይሆንስትቧጥጠውያደረችው?...ሸንትራ፤ሸንትራ፤ግርግዳውንልጅያረሰውመጫወቻደጅአስመስላዋለች።ሽንትቤቱንሰባብራአግማምታ፤አበስብሳው፤የአንድወርየቤትኪራይሳትከፍለኝኮተቷንሰብስባውልቅአለች።ክሰሻትአሉኝ።ማንላይነውየምከሳት?...ጭራሽአሸባሪትብየእኔውልታሰር?...”
 የእናታችንጨዋታፈርጀብዙነበር።አንዱንጨርሰውወደሌላውሲያልፉአንደበተርቱእነታቸውናለዛቸውአፍያስከፍታል።
 “..አንድጉድደሞላጫውትህ....ስራአጥተውችግርርርርያላቸውአስርየሚሆኑየሰፈራችንወጣቶችተሰበሰቡልህናስራፈጠሩ።ምንድነውስራውብትለኝ...ሆቴልቤቶችሞልተዋልብየሀለሁሰፈራችን....ከባለቤቶቹጋርይነጋገሩልህና በቀንሶስትጊዜቆሻሻመድፋት፤በቀንአንድጊዜግቢመጥረግ፤ይህንለመስራትተዋውለው....ባለሆቴሎቹምሁሉደስብሏቸው....ሲሰሩየሚለብሱትልብስምገዝተውላቸው...ጋሪምገዝተውላቸውስራጀመሩ።የሰፈሩሰውሁሉደስአለው።ልጆቹገንዘብአገኙ፤እናትናአባታቸውንማልበስለራሳቸውምደህናደህናነገርመልበስጀመሩ።ስራቸውንምእያስፋፉበቁጥርአስራአምስትደርሰው፤በሰላምተረጋግተውበመስራትላይእንዳሉ፤ህገወጥስራነውየምትሰሩትአቁሙይላቸዋልአንዱ...”
“ ማን? “
“ እዚያውቀበሌውስጥ ....የምንትስሀላፊነውያሉትትግሬ...”
“ ለምንአስቆማቸው?”
 “ስራውንቀበሌውሊሰራውበእቅድየያዘውስለሆነበቀበሌታቅፋችሁነውመስራትያለባችሁ።ቀበሌለናንተይከፍላል።ግብርለመንግስትመክፈልአለባችሁ፤ፍቃድያስፈልጋችኋል....አለናአስቆማቸው።ልጆቹምለምንድነውእኛየፈጠርነውንስራየምንከለከለውብለውሲጨቃጨቁሁለቱንአስረው፤የቀሩትንአስፈራርተውበተኗቸው።”
 “...ትንሽቆየትይሉልህና...ልጆቹንአደናግረውአስፈራርተውከበተኗቸውበኋላያንኑስራበቀበሌውየማይኖሩየራሳቸውንወጣቶችሰብስበው....
 “የራሳቸውንወጣቶችማለት?” አቋርጨጠየኩ።
 “ትግሬዎቹን... ሰበሰቡናከመጀመሪዎቹሁለቱንቀላቅልውስሩአሏቸው...እነዚያሁለቱደሞጓደኞቻችንተባረውእኛአንሰራምብለውትተውላቸውሄዱ።ባለሆቴሎቹቀድሞየሚያስጠርጉትንልጆችሲያጡ፤ምንድነው ነገሩብለውቢያጠያይቁ፤የመጀመሪያዎቹልጆችየሆነውንሁሉነገሯቸው።ባለሆቴሎቹምአደሙ።ቆሻሻችንንእኛውእንደፋለንእንጂአናስጠርግምአሉ።የተተኩትንልጆችስራየለንምእያሉመለሷቸው።”
 “ያአለቃተብየውቀበሌሰዉንሰብስቦአሉ...ጸረልማትሀይሎችእያለሲሳደብከረመአሉ።ባለሆቴሎቹምእንዳደሙቀሩ።ሗላላይሥሰማበመጀመሪያያጸዱላቸውየነበሩትንልጆችሁሉንምተከፋፍለውቀጠሯቸውአሉ።እነዚያምጋሪያቸውንናጓዛቸውንይዘውወዴትእንደሄዱአላውቅምእልሀለሁ.....ልጄ..ወያኔእንዲህእያመሰንነውእልሀለሁ.....”እንደመተከዝአይኖቻቸውንወለሉላይተክለውለአፍታዝምምአሉ።
 ውድአንባቢያንየህብረተሰብደህንነትየሚረጋገጠው፤እያንዳንዱክፍለህዝብከህዳጣንእስከብዙሀንምልአተህዝቡንየገነቡብሄረሰቦችሁሉእኩልመብትናነጻነትሲኖራቸው፤በሀገራቸውእኩልየባለቤትነትስሜትሲኖራቸው፤አንባገነንምይሁንዲሞክራሲያዊ..ያለውንመንግስትየኛነውሲሉት፤በባህላቸው፤በቋንቋቸው፤በሀይማኖታቸው፤የተነሳምንምአይነትመገፋትእንደሌለሲያረጋግጡዜጎችደህንነትይሰማቸዋል።
የናታችንንጨዋታለማጫርይችንጥያቄጣልአደረኩ።
 “ወያኔ..ወያኔይባላል... ኢህአደግነውመባልያለበት... አይደለምእትየ?”
 ከትአሉናሳቁ።ሳቃቸውአስቆንሁላችንምፍንድትአለን።
 “አየህልጄ...በቆሎእሸትታውቃለህአይደል?..በቆሎእሸት..” አሉእጃቸውንቀናቀጥአድርገው፤“..በቆሎእሸትየምትሸለቅቀውልባሱአለ።ያልባሱገለባነው።ይጣላል።ዋናውበቆሎውነው።ፍሬው።እነዚህኢህአደግ ያልካቸውገለባናቸው (ሶስቱንየወያኔፍጡራንድርጅቶችማለታቸውነው፡ኦህዴድ፤ብአዴን....)ዋናዎቹትግሬዎቹናቸው።ገባህልጄ...
በአዎንታራሴንነቀነኩ።
 “..የአማራውነን፤የኦሮሞውነን፤ማነውይሄደሞየበየነጴጥሮስአገር...ብቻሁሉምከነሱጋርያሉትገለባዎቹአሽከሮቻቸውናቸው።ማፈሪያዎችናቸው፤.....እንዳይመስልህልጄ...ጌቶቹትግሬዎቹናቸው፤....የአህያባልከጅብአያስጥልምእነዚህኢህአደግያልካቸውከምንምአያስጥሉንም......”
 ውድአንባቢያንያለፈአንድአመትአካባቢአንዲትሌላእናትእንዲሁመተውለመጠየቅሄጄዘጠናበመቶማለትይቻላልተመሳሳይአይነትጨዋታአጫውተውኝነበር።ካንድሰውብቻየተገኘኢንፎርሜሽንለሌላውማስተላለፍያስቸግራል፡፡ሁለትይማይተዋወቁሰዎች፤የተለያየአካባቢየሚኖሩ፤በተለያየጊዜአንድአይነትነገርከተናገሩእውነትነትያለውጉዳይአለማለትነው።
 ይህስርአትመለወጥእንዳለበትዜጎችይስማማሉ።ሰላማዊየስልጣንሽግግርየሚታሰብነገርአልሆነም። እንዴትነውእነዚህንሰዎችከስልጣንየምናስወግደውነውጥያቄው፤መላመምታትየእያንዳንዱዜጋግዴታናፈንታነው።እናታችንንጠይቄአቸውነበር።
 “ይህንንመንግስትለመለወጥምንቢደረግየሚበጅይመስሎታልእትየ?”
 “መተኮስ....መተኮስነዋ!...እነሱተኩሰውአይደልለዚህየበቁት?.....ግንእኮልጄ...ወንዱሁሉሀሞቱፈሰሰ...በጥቁርአህያነውአሉያስደገሙብን...የሱዳንመተትቀላልእንዳይመስልህልጄ...ሱዳንአልነበረየሚኖሩት...ያኔአሉ....ሲገቡ፤ሕዝቡሁሉእንዲፈዝላቸው......ወንዱሁሉወኔውእንዲሰለብ.... በጥቁር አህያ አድርገው አስደግመው ገቡ አሉ።ይኸውሀያሁለትአመት....አገርመሬቱንሲሸጡ፤እስላምክርስቲያኑንሲያምሱ፤ሲገሉ....ቤትሲያፈርሱ.. ንብረት ሲቀሙ...ማንወንድሸፍቶአስደነገጣቸው?.....ሀያሁለትአመት...ሀያሁለትዓመት... መተኮስ ... መተኮስ ነው ልጄ...”  lkebede10@gmail.com
maleda times | March 6, 2013 at 9:50 pm | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-1w4

  

 

No comments:

Post a Comment