Tuesday, March 12, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ የተሰረዘበትን ምክንያት ሲነገር ያለውን ቪዲዮ ይዘናል

Gudu  Kassa

መንግስት ጣልቃ የገባበት እና የ እራስት ግብዣ ፕሮግራሙ እንዳይከናወን የታገደው የዋቢሸበሌ እራት ፕሮግራም በምን ምክንያት እንደሆነ አለመጠቆሙ አሳፋሪ ነው ሲሉ በ እራት ግብዣው ላይ የተገኙት እንግዶች ገለጹ ።ባለፉት ቀናት መሰረዙን አስመልክተን የዘገብነው ይሄው ፕሮግራም ዛሬም ድረስ አነጋጋሪ እንደነበር እና በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደፈጠረ ተናግረዋል።  ሆኖም እንደዚህ ከመንግስት ሃይሎች ጋር በመስራት የሚተባበሩትን ባለ ሃብቶች እና ድርጅቶች በአድማ ስራቸውን ካላሳጣናቸው ከ እንደዚህ አይነት እኩይ ተግባር አይታቀቡም ብለው የተናገሩት አንድ ግለሰብ ማናቸውም ባለ ሃብቶችን ለሚሰሩት መጥፎ ስራ ለሃገራችን ጠቃሚ ስለማይሆኑ ከስራቸው ሊውገዱ የሚችሉበትን መንስኤ መፍጠር አልብን ሲሉ ለማለዳ ታይምስ ገልጸዋል ። ከስር የምትመለከቱት ከዋቢሸበሌ ሆቴሎች አስተዳደር ጋር የተደረገ ጭቅሽቅ ነው።


የመንግስት ጣልቃ የገባበትን ዋነኛ ምክንያት ያልገለጹት የዋቢ ሸበሌ ባለቤት ፣ጉዳዩን በግልጽ ለማውጣት ባለመቻላቸው የወደፊት ደንበኞቻቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ተገልጾላቸዋል ።የአፓርታይድ ስራትን ትደግፋለህ ይህ ነጻነታችንን ነው የነፈከን እንዲሁም እቤትህ መጥተን አትበሉም ብለህ እንደመለስከን ነው የምንቆጥረው በማለት የመለሱት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች እና ደጋፊዎች እንዲሁም የተለያዩ እንግዶች ሲሆኑ በአመራር ደረጃ ላይ ያሉት እንደ እነ ፕሮፌስር መስፍን ምንም ለመናገር አለመቻላቸው ከውስጣቸው ማዘናቸውን እና የዋቢ ሸበሌን ባለቤት ላለማስከፋት ያደረጉት ጥረት ይመስላል ።እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ሲከናወን ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የፕሮግራሙን መሰረዝ መናገር ሲገባቸው ወዲያው ዉጡልኝ ማለት ይህ አሳፋሪም እንደ ገናም ወልጀል ሲሆን የሰውን ልጅ ጊዜ ጉልበት እና ገንዘብ ማክሰር እንደሆነ ሳንጠቁም አናልፍም ።ሆኖም ይህንን አስመልክቶ የሰማያዊ ፓርቲ ላጠፉት ጊዜ ገንዘብ እና የሰውልጅ ጉልበት የካሳ ክፍያውን ከባለቤቱ በግዴታ የመቀበል እድል ይኖራቸዋል
 
maleda times | March 12, 2013 at 6:38 am | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-1xs
Comment   See all comments

No comments:

Post a Comment