Saturday, August 1, 2015

አቶ በረከት ስምዖን የት ሂደው ጠፉ??



ከታማኝ  የሀገር ውሥጥ መረጃ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ  መሰረት
በአንዳርጋቸው ጽጌ ስም ሊወጣ የታቀደውን መጽሀፍ ያዘጋጁት አቶ በረከት ስምዖን መሆናቸው ታወቀ:: ከብአዴን ቁልፍ ባለስልጣናት የተገኘው ጥብቅ መረጃ ላይ እንደተብራራው አቶ በረከት መጽሀፉን እንዲያዘጋጁ ከተወሰነ በሁዋላ ከመንግስት መደበኛ ስራም ሆነ ከመድረክ ለረጅም ወራት ጠፍተዋል:: መጽሀፉ በጥንቃቄ እንዲዘጋጅ ከፍተኛ ሃላፊነት የተሰጣቸው አቶ በረከት ከደህንነት መስሪያ ቤቱ ጋር በመሆን መረጃዎችን ሲሰበስቡ ከርመዋል:: የአቶ አንዳርጋቸውን ግላዊ ህይወት ከማጥናት አንስቶ የቤተሰባቸውን ሁኔታ በኤርትራ የነበራቸውን ቆይታ በአጠቃላይ የአቶ አንዳርጋቸውን የአጻጻፍ ስልት ሳይቀር በማጥናት የሰዉን ጥርጣሬ በ�ሚያጠፋ መልኩ እያዘጋጁት እንደሆነም የተገኘው መረጃ ያመለክታል:: የግንቦት ሰባት አመራር ውስጥ የነበሩና ሀገር ቤት የገቡት(ቪላ ቤት ተሰጥቷቸው እየተቀለቡ ያሉት) 3 ግለሰቦች የድርጅቱን መረጃና በኤርትራ የአቶ አንዳርጋቸውን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ምን እንደነበረ መረጃውን በዝርዝር ለአቶ በረከት እንዳቀበሉም ይነገራል:: የመጽሀፉን ይዘት በተመለከተ በዝርዝር መረጃው የሚወጣ ይሆናል:: አቶ አንዳርጋቸውን በተቆራረጠ ምሥልና ድምጽ መጽሀፉ የራሱ መሆኑን ሲገልጽ የሚያሳይ ቃለመጠይቅም ሊዘጋጅ እንደታቀደም ከውስጥ የመጣው መረጃ ያመለክታል:: ዝርዝር ጉዳዮችን ከሰሞኑ እናቀርባለን::

No comments:

Post a Comment