Monday, July 13, 2015

ግልጽ ደብዳቤ ለፖፕ ፍራሲስ ቫቲካን ኢጣሊያ። ኢትዮጵያ ለደረሰባት ፍጅት ፍትህን ትጠይቃለች

 

opening-graziani-memorial
የግራዚያኒ ሀውልት ሲመረቅ
በኢትዮጵያ ስለ ተፈጸመው የፋሺሽት የጦር ወንጀል ዓለም አቀፍ ተቃውሞ
የካቲት 12 ቀን 2005 ዓ/ም (February 19, 2013) በዓለም አቀፍ ደረጃ በ30 ከተሞች በሚከናወኑት የተቃውሞ ሰላማዊሰልፎችና ስብሰባች በአዲስ አበባ ከተማ፤ በየካቲት 1929 ዓ/ም የተጨፈጨፉት 30000 ኢትዮጵያውያንና፤ በቫቲካንድጋፍ የኢጣልያ ፋሺሽቶች ከ1928-33 ዓ/ም ስለ ፈጸሙት የጦር ወንጀል ይታሰባል።
የፋሺሽት ጦር ወንጀሎች በኢትዮጵያ፤በኢትዮጵያ የተፈጸሙት የኢጣልያ የጦር ወንጀሎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ከባድ ጥፋቶች አስከትለው ነበር፤
1. በዓለም አቀፍ ሕግ በተከለከለ በብዙ የኢጣልያ አውሮፕላኖች በተነሰነሰ የመርዝ ጋዝና በሌላም የጦር
መሣሪያዎች በመጠቀም አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈዋል፤
2. 2 000 ቤተ ክርስቲያኖችና 525 000 ቤቶች ተደምስሰዋል፤
3. 14 ሚሊዮን እንስሳትን ጭምር ያወደመ የአካባቢ ብክለት ተከስቷል።
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፤ እንደሚባለው፤ የኢጣልያ መንግሥት በቅርቡ አፊሌ በምትሰኝ ከሮም ከተማ ወደ ደቡብበምትገኝ ሥፍራ፤ ለፋሺሽቱ የጦር ወንጀለኛ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ አንድ መካነ መቃብርና መናፈሻ አቋቁሞለታል። እ.ኤ.አ.በ1947 ኢጣልያ ለኢትዮጵያ የከፈለችው 6 ሚሊዮን ስተርሊንግ ፓውንድ ካሣ፤ ፍጹም የማይመጥን፤ ሌላው ኢፍትሐዊድርጊት ነው።
በፋሺሽቶች የተሰቀሉ የኢትዮጵያ አርበኞች የኢጣልያ ፋሺሽቶች ከቆረጡት የኢትዮጵያዊ አርበኛ ራስ ጋር ሲታዩ
ቫቲካን ለፋሺሽቶች ያበረከተችው ድጋፍ፤በጊዜው በፖፕ ፓየስ 11ኛ፤ ቀጥሎ በፖፕ ፓየስ 12ኛ ትመራ የነበረችው ቫቲካን በፋሺሽቱ የጦር ወንጀል ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ ነበረች። ይህንንም ከሚያረጋግጡ ብዙ ማስረጃዎች ውስጥ የሚከተሉትን መመልከት ይቻላል፤
1ኛ/ታዋቂው “ኒው ዮርክ ታይምስ” (New York Times) ጋዜጣ፤ይህ በዓለም-አቀፍ ደረጃ ታዋቂና ታማኝነት ያለው ጋዜጣ፤ የካቲት 6 ቀን 1929 ዓ/ም (February
13, 1937) ስለ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ባወጣው ዜና ከዚህ እንደሚከተለው ዘግቧል፤
“Earlier today the Pontiff had given his recognition of Italian sovereignty over
Ethiopia by bestowing his apostolic benediction upon Victor Emmanuel as “King
Of Italy and Emperor of Ethiopia.” (ትርጉም፤ ቀደም ሲል ዛሬ አቡኑ “ለኢጣልያ
ንጉሥና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት”፤ ለቪክቶር ኢማኑኤል፤ ቅዱስ ቡራኬያቸውን በመስጠት
ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ስላላት ሉዓላዊነት እውቅናቸውን ገልጸዋል።) ሙሉውን ዘገባ ከዚህ በታች ካለው
መመልከት ይቻላል፤
http://www.globalallianceforethiopia.org/piusxi.pdf
2ኛ/ ማንቸስተር ጋርዲያን (Manchester Guardian)የካቲት 5 ቀን 1922 ዓ/ም (February 12, 1929) በወጣው በዚህ ጋዜጣ ዘገባ የሚከተለው ጽሑፍ ይነበባል፤
“Pope Pius XI is credited with much admiration for Mussolini. That the Italian clergy as a
whole are pro-Fascist is easy to understand, seeing that Fascism is a nationalist,
authoritarian, anti-liberal, and anti-Socialist force.” (ትርጉም፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ለሙሶሊኒ ስላላቸው
ክፍተኛ አድናቆት ይነገርላቸዋል። የፋሺሽት ሥርዓት አምባገነናዊ፤ ብሔርተኛ፤ ፀረ-ዲሞክራሲና ፀረ-ሕዝባዊ ኃይል
ስለ ሆነ የኢጣልያ ካሕናት በአጠቃላይ የፋሺሽት ደጋፊ መሆናቸውን በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።)
3ኛ/ አቭሮ ማንሐታን (Avro Manhattan) የተሰኘው ጸሐፊ፤ “The Pope in World Politics” በተሰኘው መጽሐፉ፤ የፋሺሽቱ ጦር አዲስ አበባ ሲደርስ ፖፕ ፓየስ 11ኛ የሚከተለውን የደስታ መልእክት አስተላልፈው ነበር፤
“The triumphant joy of an entire, great and good people over a place
which, it is hoped and intended, will be an effective contribution and
prelude to the true place in Europe and the World.” (ትርጉም፤
ለአውሮፓና ለዓለም መልካም ጅማሮና ሁነኛ ደረጃ ተገቢ አስተዋጽኦ እንዲሆን ለታቀደና ተስፋ ለተጣለበት ቦታ (ኢትዮጵያን ማለት ነው) የታላቅና ግሩም ሕዝብ (ኢጣልያኖችን ማለት ነው) ከፍ ያለ ደስታ።)
4ኛ/ የቱራኖ ጳጳስ በሚከተለው ገለጻ በኢትዮጵያ ላይ የተከናወነውን የፋሺሽት የጦር ወረራ ባርከው ነበር፤
“The war against Ethiopia should be considered as a holy war, a crusade”
(as Italian victory would) “open Ethiopia, a country of infidels and
schismatics, to the expansion of the Catholic Faith.” (ትርጉም፤ በከሐዲዎቹ
ሐገር፤ በኢትዮጵያ፤ የካቶሊክን ሃይማኖት ለማስፋፋት ስለሚጠቅም በኢትዮጵያ ላይ
የተፈጸመው ጦርነት እንደ ቅዱስ ጦርነት፤ መንፈሳዊ ዘመቻ መቆጠር አለበት።)
የቫቲካን ካሕን የፋሺሽቱን ጦር ሲባርኩፍትሕ ለኢትዮጵያ፤በቫቲካን ድጋፍ፤ በኢትዮጵያ ላይ ለተፈጸሙት የጦር ወንጀሎች ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገው ፍትሕ የሚከተለው ነው፤
1ኛ/ ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
2ኛ/ የኢጣልያ መንግሥት፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገቢውን ካሣ እንድትከፍል፤
3ኛ/ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመውን የጦር ወንጀል በመዝገቡ እንዲያውል፤
4ኛ/ የኢጣልያና የቫቲካን መንግሥቶች ይዘውት የሚገኙትን የተዘረፈ ንብረት ለኢትዮጵያ እንዲመልሱ፤
5ኛ/ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ ከሮም ከተማ በስተደቡብ በምትገኝ አፊሌ በምትሰኝ ሥፍራ የተቋቋመውን
የሮዶልፎ ግራዚያኒን መካነ መቃብርና መናፈሻ የኢጣልያን መንግሥት እንዲያፈርስ።
የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት ለሮዶልፎ ግራዚያኒ የተቋቋመው መካነ መቃብር ሲመረቅ
ለተጨማሪ ማስረጃ፤
Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044, USA
Tel: (214)703 9022; Email: info@globalallianceforethiopia.com
http://www.globalallianceforethiopia.org
አባሪ ፩ ፡ የሚካፈሉ ከተሞች ዝርዝር
1ዋሺንግቶን ዲሲ
2ኒው ዮርክ
3ዳላስ ፎርት ዎርዝ
4አትላንታ
5ሳን ሆሴ
6ሲያትል
7ላስ ቬጋስ
8ሎስ ኣንጀለስ
9ዴንቨር
10ሁውስቶን
11ቺካጎ
12ቦስቶን
13ዴትሮይት
14ፊላደልፊያ
15ሚያሚ
16ታምፓ
17ቶሮንቶ
18ሎንዶን
19ስቶኮልም
20ሮም
21ጄነቫ
22ብራስልስ
23በርሊን
24ፍራንክፈርት
25አምስተርዳም
26ሞስኮ
27ጀሩሳሌም
28ሲድኒ
29ጆሃንሱቡርግ
30ናይሮቢ
31ካምፓላ
32ኪንግስቶን
33ሉሳካ
34አውስትራሊያ
35ቶክዮ
36ጀሩሳሌም
37ኣዲስ አባባ
38ዋሺንግቶን ዲሲ

No comments:

Post a Comment