Thursday, July 9, 2015

እነተስፋለም ወልደየስ ተፈቱምክንያቱ የፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የጉዞ እቅድ ነው ተባለ

Zelalem_zone9_1safe_image278LG8IB_tesefalem1
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ፣ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ጦማሪ ዘላለም ክብረት፣ማህሌት ፋንታሁንና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ዛሬ ማምሳውን በፍትሕ ሚኒስቴር ውሳኔ መፈታታቸው የታወቀ ሲሆን ከቤተሰብ መቀላቀላቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ገለጹ።የቀሩት በእስርና በስደት ያሉ አምስት ጦማሪያን ጉዳኢ በተጀመረው የክስ ሂደት ይቀጥላል ቢባልም ቁርጥ አለ ውሳኔ አለመሰጠቱ ታውቋል። በክሱ ላይ ብኢን ለመስጠት ከመጪው ቀጠሮ ሐምሌ 13 ቀን 2007 በፊት ይፈቱ ዌኢ እንደተባለው ክሱ ቀጥሎ ብይን ይሰጥ አልታወቀም።
ከአስሩ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መካከል የክስ ሂደታቸው ይቀጥላል የተባለው የክሱ መዝገብ በስሟ የተከፈተውን ሶሊያና ሽመልስ ፣ አቤል ዋበላ ሱጌቦ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሃይሉ እና አጥናፉ ብርሃኔ ጉዳይ መታየቱ እንደሚቀጥል ከፍርድ ቤቱ የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
የፍትህ ሚኒስቴር የፌደራል ተቋማትን ስልጣን እና ተግባር ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀፅ 16 መሰረት በማናቸውም ሰዓት የተጀመረ ምርመራ እና ክስ የማቋረጥ እና የማንሳት ስልጣን እንዳለው ይታወቃል ያለው አንድ የአገዛዙ ሚዲአ ፍቺውን ሕጋዊ ላማድረግና በሕግ መሰረት የተሰራ ለማስመሰል ሞክሯል። በዚህ መዝገብ አቃቤ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ምስክሮችን ማሰማቱን ተከትሎ ችሎቱ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 13 ቀን 2007 መቅጠሩን አስቀድመን መዘገባችን ይታወሳል።
የዞን ዘጠኝ ጦማሪአንም ሆኑ ሌሎች በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች በፈጠራ መንግስትን በሀይል ለመታልና በሽብር በሚል ተከሰው ያለ በቂ ማስረጃ በትዕዛዝ የተፈረደባቸውና ጉዳያቸውን እተከታቱ ያሉት መጨረሻ ለጊዜው ባይታወቅም የፕ/ት ኦባማ የኢትዮጵያን ጉዞ ዕቅድ በምሳሌነት የሚያነሱ መደመጥ ጀምረዋል።
ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግልጽ ደብዳቤ የጻፈውን ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀን ጨምሮ ክሳቸው ይቀጥላል የተባሉት አምስቱ ጦማሪያን ጉዳይ ከሐምሌ 13 ቀተሮ በፊት ይቋጭ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ድርጅት በተለያየ ደረጋ ያሉ መሪዎች፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም ጉዳይ በተመለከተ አገዛዙ የሰጠው መግለቻ የለም።

ባለፈው ሰኔ 8/2007 ቀጠሮ አንደኛዋን ተከሳሽ ሲሊአና ሽመልስን ይመለከታል የተባለው <ሲ.ዲ >> በግልጽ ችሎት ይታያል ተብሎ ሲጠበቅ ዳኞች ያለ አንዳች ማብራሪያ በግልጽ ችሎት አይታይም በማስረጃነት ተቀብለነዋል ማለታቸው ይታወሳል።
የጦማሪያኑ መፈታት ከፕ/ት ኦባማ ጉዞ ጋር ይያያዝ ዌኢም በሌላ ምክንያት እስካሁን የሚታወቅ ባይኖርም አንዳንዶች የኦባማ ጉዞን እቅድ በምክንያትነት ያነሳሉ።
maleda times | July 8, 2015 at 9:44 pm | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-6Vu
Comment   See all comments

No comments:

Post a Comment