Tuesday, July 14, 2015

የጥቁሩ ውሻ "የመለስ ዜናዊ" ሕይወት ታሪክ

 

በጣሊያን ወረራ ጊዜ የወያኔው መለስ ዜናዊ አያት አቶ አስረስ ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት የመጡትን ጣሊያኖች እየመሩ አርበኞችን ሲያስጨፈጭፉ የነበሩ ባንዳ ስለነበሩ፣ ፋሽስት ጣሊያን በአርበኞች ተጋድሎ ድል ተነስቶ ነፃነትን ካስመለሱ በኋላ፤ የአገሬው አርበኛ እና ሕዝብ ተሰባስቦ "ለአቶ አስረስ ሚስት የዳረ ጥቁር ውሻ ይውለድ" ተብሎ ቢማማሉባቸውም አቶ አስረስ የመለስን አባት አቶ ዜናዊ አስረስን ወለዱ። ከዚያም ጥቁር ውሻ ውለዱ የተባለው እርግማን በአቶ ዜናዊ አስረስ ደርሶ፤ አቶ ዜናዊ አስረስ ከወ/ሮ አረጋሽ ገብረልዑል በግንቦት 1 ቀን 1947 ዓ.ም. ጥቁሩን ውሻ መለስ ዜናዊን ወለዱ።ጥቁሩ ውሻም /መለስ ዜናዊ/ ከባንዳ ቤተሰቡ በወረሰው ቂም በቀል፣ በዘር ጥላቻ አጋንንት እና መርገም ተለክፎ አደገ። መሰል ባንዳ ጓደኞቹ ጋርም ጫካ ገባ። የዋሁ የኢትዮጵያ ሕዝብም የባንዳዎቹ ጩኸት እውነት መስሎት ድጋፉን ሰጣቸው እና ጥቁሩ ውሻ ለስልጣን በቃ። በእስስታዊ አስመሳይነቱ የተካነም ጥቁር ውሻ ሆነና "ኢትዮጵያ የምትባልን አገር፣ ኦርቶዶክስ የሚባልን ሃይማኖት፣ አማራ የተባለን ብሔር"፤ ቢቻል ከምድረ ገጽ ለማጥፋት፣ ካልሆነም አንኮታኩቶ ለመጣል የበቀል ሰይፉን ጀመረ፤
• ለዘመናት በቋጠረው ቂም በቀል መሰል ዘረኛ ጓደኞቹን ሰብስቦ፣ የጎሳ ፖለቲካውን መርዝ በመንዛት፣ አገር የሚያስገነጥል እና የአንድ ጠባብ ጎሳን የበላይነት የሚያረጋግጥ፣ የጥላቻ እና ዘረኛነት ልክፍት ያለበት፣ በተለይ አማራውን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ፣ "ትግራይ እስክትለማ - ሌላው አገር ይድማ" ብሎ የተነሳና የቀሪውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕድገት እና ብልጽግና የሚያኮስስ፣ ለማይተባበሩት የትግራይ ተወላጆች እንኳ ግድ የሌለው፣ ሕወሃት የተባለ የአንድ ጠባብ ጎጠኛ እና ፋሽስታዊ ዘረኛ ኤምፓየር መሠረተ፣
• ጥቁሩ ውሻ እና አውሬው ሕወሃትም ከጉዲፌቻ አባታቸው ከሻዕቢያ በሚሰጣቸው መመሪያ መሠረት፤ ከ3000 ዓመት በላይ የታሪክ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን - ታሪኳን እንደ ድንበሯ ቆራርጠው የ100 ዓመት ብቻ አደረጉት፣ ያገኙትን የታሪክ አሻራ የሆኑ ማሥረጃዎች እና ቅርሶች በቻሉት መጠን አወደሙ፣ 
• ጥቁሩ ውሻም ለኖህ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን፣ የምህረትና የሰላም ቃልኪዳን ምሳሌ የሆነችውን፣ አያት ቅድመ አያቶቻችን ኢትዮጵያውያን አርበኞች፤ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍስሰው ከፋሽስትና ከጠላት ጠብቀው ያቆዩዋትን፤ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማችንን፤ ከባንዳ አያቱ በወረሰው የፋሽስቶች የጥላቻ ስድብ እና ንቀት "ጨርቅ" ብሎ አንቋሸሻት፣
• ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የመበታተን ተግባሩን ኤርትራን በማስገንጠል አንድ ብሎ ጀመረ፣ 
• ቀጥሎም በፊት የወሎ ክፍለ ሃገር አካል፣ በኋላም በራስ ገዝነት ራሷን ችላ ትተዳደር የነበረችውን አሰብን አስገንጥሎ፤ ኢትዮጵያን ያለ ወደብ አስቀረ፣ ዛሬ ለጅቡቲ በቀን ከ 3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለወደብ ኪራይ ይከሰከሳል፣ ከአሰብ ጅቡቲ ከ300 ኪሜ በላይ ስለሚርቅም ተጨማሪ የመጓጓዣ ወጭ እና የኑሮ ውድነት አስከትሏል፣
• አሰብ የነበረውንም የነዳጅ ማጣሪያ አብሮ ከአሰብ ወደብ ጋር ለእናቱ ዘመዶች ለኤርትራ በማስረከቡ፤ የነዳጅ ድፍድፍ በርካሽ እየተገዛ ይጣራ የነበረውን የነዳጁም ተረፈ ምርት ለአስፋልት ሬንጅ እና ለሌሎች ዕቃዎች ምርት ይውል የነበረውን፤ ዛሬ ኢትዮጵያ የተጣራ ነዳጅ እና ሬንጅ በውድ ዋጋ በዶላር እንድትገዛ በመገደዷ የነዳጅ ዋጋ እየናረም የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፣ 
• በእምየ ምኒሊክ ጥረት ከጅቡቲ-አዲስ አበባ የተዘረጋው የምድር ባቡር እድሜ ሳይገድበው እየተንገዳገደ ከ100 በላይ ባለተሳቢ መኪኖች የሚያጓጉዙትን ቁሳቁስ በአንድ ጊዜ በአድ መኪና ወጭ ጠቅልሎ ያመጣልን የነበረውን ባቡር በማኮላሸት፣ በትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ ስም የሚንቀሳቀሱት የሕወሃት የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪኖች እንዲሸቅሉበት እና የሸቀጦች የትራንስፖርት ዋጋ እንዲንር እና የኑሮ ውድነት እንዲከፋ አስደረገ፣ 
• አማራው ላይ የቋጠረውን ቂም ለመበቀል በአርባ ጉጉ እና በበደኖ በፕላን የተቀነባበረ የእጅ አዙር የጅምላ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ አስደረገ፣
• አማራውን ነፍጠኛ እና ትምክህተኛ እያለ የሌላው ጎሳ እንዲነሳበት፣ የበሬ ወለደ የጥላቻ ዘመቻ በአፄ ሚኒሊክ ላይ በሰፊው በመክፈት እና በሰፈራ ሄደው የሚኖሩትን ዜጎች የአማራ ተወላጆችን አስወጡ በማለት ከተለያዩ ክልሎች በቅርቡም በ2004 ዓም. ከደቡብ ክልል እንዲፈናቀሉ ከአስደረገ በኋላ አማራዎች አይደሉም ምሥራቅ ጎጃሞች ናቸው አለ፣ ቀደም ሲልም በአማራው ላይ ነፍጠኛ ትምክህተኛ የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶ የጥላቻ መርዙን ከረጨ በኋላ ሰሜን ሸዋዎችን ነው ብሎ ለመከፋፈል ሞከረ፣ 
• በሰሜን ምዕራብ ጎንደር እና በወሎ ክፍላተ ሃገራት በኩል ያሉትን ሰፋፊ እና ለም ወረዳዎች ቆርሶ ተወላጁን እና ነዋሪውን አማራ በግዴታ አፈናቅሎ ወደ ትግራይ ክልል አጠቃለለ፣ 
• በምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል በቦታው ያሉትን ኢትዮጵያውያንን፣ በተለይም አማራውን በማፈናቀል፤ ለአማራ ብሔር ጥላቻ ባለው የሕወሃት ዘረኛው የጎሳ ፓርቲ ታዛዥ በሆነው የአገው ተወላጁ በደመቀ መኮነን ፈራሚነት፤/በወቅቱ የአማራ ክልል ም/ፕሬዚዳንት ስለነበረ እና ለዚያ አገር ቆርሶ የመሸጥ ውለታው የሚኒስቴርነት አሁን ደግሞ የም/ጠ/ሚኒስቴርነት ምዕረግ የተሰጠው/ ከ60 ኪሜ በላይ ወደ ውስጥ ከ1000 ኪሜ በላይ ርዝማኔ ያለው ለም የእርሻ መሬት እና አፄ ዮሐንስ አንገታቸውን የተሰየፉላትን የዮሐንስን ከተማ ጨምሮ ለሱዳን ገፀ-በረከት ሰጠ፣
• ደርግ የሠራውን ወያኔ እያፈረሰበት እና በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር ወጭ እያወጣ፣ ያለምንም እርዳታ እና ብድር የሠራውን በፓዌ የጣና በለስን፣ በጋምቤላ የአልዌሮን እንዲሁም በጎዴና ሌሎች አካባቢዎች የሠራቸውን ሰፋፊ የመስኖ ፕሮጀክቶች 21 ዓመት ሙሉ በከንቱ እንዲፈስሱ እና የእርሻ መሬቱ በጫካ እንዲወረር፣ በአገሪቱም የምርት እድገት እንዳይኖር አደረገ፣ 
• ዘረኛው የሕወሃት ፓርቲ ሥልጣን ሲይዝ ከ18 ዓመት በታች ዕድሜ የነበራቸው የገበሬ ልጆች በወቅቱ መሬት አላገኙም ነበር። ዛሬ ቢያንስ 38 ዓመት ይሆናቸዋል። ከዚህ ዕደሜ በታች ያለው እና ጎጆ ወጥቶ የሚኖር አርሶ አደር በሙሉ የሚያርሱት መሬት አጥተው፣ በጋምቤላ እና ፓዌ የሚገኘውን ሰፊ የመስኖ ቦታ ለአረቦች እና ለህንዶች ሰጠ - ለዚያውም ምርቱ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ለማይውል እና የጋምቤላ እና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰያምኑበት እና ሳይቀበሉት፣
• የዘረኛ ፖለቲካየን አልተቀበላችሁም በሚል በሽህዎች የሚቆጠሩ የአማራ አርሶ አደሮችን "ቢሮክራት" የሚል ቅጽል ስም በመስጠት መሬታቸውን ነጥቆ፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ጦም እንዲያድሩ ፈረደባቸው፣ 
• ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ እንዳይኮራ "ለወላይታው የአክሱም ሃውልት ምኑ ነው" ብሎ ዘረኛነቱን በይፋ አሳወቀ፣
• ከትግራይ ብሔር ውጭ ያለውን የንግዱን ማህበረሰብ በግብር ሰበብ አዳክሞ የንግድ እንቅስቃሴው በአንድ ጎሳ እጅ ውስጥ እንዲወድቅ አደረገ፣
• በ17 ዓመት የትጥቅ ትግል ወቅት በወያኔ እና በደርግ በኩል ያልሞተ የወታደር ቁጥር በባድሜ ሰበብ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 ሽህ በላይ ንፁሃን ዜጎችን ከአስጨፈጨፈ በኋላ፣ ለኤርትራ እንዲሰጥ አስደረገ - ለዚያውም ኢትዮጵያ ልታሸንፍበት የምትችለውን ማስረጃ አልቀበልም ብሎ የወደቀ እና በአድዋ ጦርነት የተሻረ የጣሊያንን ማሥረጃ በመምረጥ- ለዚያውም ኢትዮጵያ በይገባኝ የመጠየቅ መብት እንዳይኖራት አስቀድሞ ፍርዱ ይግባኝ እንዳይኖረው በመማፀን - ለዚያውም ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሙያዎች ጥብቅና በነፃ እንቁም እያሉ በብዙ ሽህ ዶላር ለኢትዮጵያ ደንታ የሌለው ሰላቶ ጥብቅና እንዲቆም በመግዛት፣
• በሳሊኒ አማካይነት ጎጃም ድንበር የነበረውን የጣና-በለስን ከፍተኛ የመስኖ ፕሮጀክት በማፈራረስ ማሽነሪውን ዘርፎ ሱር ኮንስትራክሽን ብሎ ካምፓኒ መሠረተ፣ ለመስኖ ሥራው ደጋፊ ቱቦ ማምረቻ የነበረውን የፕላስቲክ ፋብሪካ በፕራይቬታይዜሽን ስም ወረሰው፣ በተመሳሳይ መልኩ በመላ አገሪቱ /በተለይም ጎንደር በጎጃም በወሎ በወለጋ በከፋ በአርሲ ክፍላተ ሃገራት/ ሜካናይዝድ እርሻ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ጀምረው የነበሩትን የገበሬዎች አምራቾች የህብረት ሥራ ማኅበራት እና የመንግሥት እርሻዎች አፈራርሶ ማሽነሪዎቹን ወደ ኤርትራ በማጓጓዝ ኢትዮጵያ ወደ ጥንታዊውና ኋላቀሩ የማረሻ እርሻ እንድትመለስ እና የተጀመረው ዘመናዊው የግብርና ዘዴ 21 ዓመት ወደ ኋላ እንዲሄድ አደረገ፣
• የማያነቡ ዓይኖች የማይጽፉ እጆች አይኖሩም ብሎ ደርግ የጀመረውን የመሠረተ ትምህርት ዘግቶ ማይምነት እንደገና እንዲስፋፋ አደረገ፣ የትምህርት ፖሊሲውንም ደረጃ በማውረድ "ዓላማችንን ተቀብሎ ያሳካልን እንጅ ዘበኛም ቢሆን ሚኒስቴር አድርገን እንሾማለን" ብሎ ደንቆሮ የትምህርት ሚኒስቴር በመሾም ደንጋይ ፈላጭ የምሁር ደንቆሮ ያስፈለፍል ጀመረ - ደንጋዩዋ /ኮብል ስቶንዋ/ እንኳ ባቅሟ የተማረ ይጥረበኝ ትበል
• የሚሠሩ እጆች እንጅ የሚሰርቁ እጆች አይኖሩም ብሎ መንጌ ቢፎክር በስርቆት እና በውንብድና ስልጣን ላይ ፊጢጥ ያለው መለስ ዜናዊም "መሥረቅም ሥራ ነው" በማለት በይፋ በማወጅ እና በሙስና የተካነ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለይስሙላ አቋቁሞ አገሪቱን ለዘራፊዎች ዳረጋት፣
• አፄ ሚኒልክ ጊዮርጊስን አብረው አስሸክመው ወደ አድዋ በመዝመት ጣሊያንን ድል ማድረጋቸው ያንገበገበው የባንዳው የልጅልጅ "ለአማራው -ነፍጠኛ የሚል ስያሜ፣ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ደግሞ የነፍጠኛ ምሽግ" እያለ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማጥፋት ከኦርቶዶክስ እምነተ - አምልኮ ውጭ የሆኑ "ድንግል ማርያም ከአዳም የተወረሰው የውርስ ሃጢያት አለባት" ብለው የሚያምኑ፣ የጣሊያን ባንዳዎችን እምነት የሚያራምዱ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ እና ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች አሿሿም ሥርዓት ውጭ፣ ዘረኛ ፓትርያርክ ሾሞ፤ መጽሐፍ ቅዱስ በቀላል አማርኛ ይተርጎም በሚል ሰበብ የኦርቶዶክስን እምነት በሚበርዝ መልኩ የትርጉም ለውጥ አስደረጉ፣ ይህንን የተቃወሙትን ታላላቅ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንት አስደዱ፣ በስውርም አስገደሉ፣ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት እንዲቃጠሉ፣ ንዋዬ ቅድሳት እንዲዘረፉ አስደረጉ፣ በልማት ሰበብ የዋልድባ ገዳም እና በአካባቢው የሚገኙ ቤተክርቲያናትን ለማፈራረስ ሥራ አስጀመረ፣ መነኮሳቱን አስደበደበ፣ አሳሰረ፣ አስሰደደ፣ 
• ከ1997 ምርጫ በኋላ የትግራይ ተወላጆች ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር ተከባብረው እና ተስማምተው ሲኖሩ በጥላቻ ቅናት በመብገን "መርካቶ ገጀራ ተወደደ - ምክንያቱም ትግሬዎችን ለመጨፍጨፍ" በማለት መለስ የተለመደ የኢንተር- ሃምዌይ ሽብር ፈጠራ በማውራት፣ ይህም ትልቅ ዜና ሆኖ የቪኦኤዋ አዳነች ፍሥሓዬ አወያይ ሆና "እንዴት አንድን ጎሳ ለማጥፋት እንዲህ ይደረጋል" የሚል ተከታታይ ፕሮግራም እንድትሠራ ተደርጎ የትግራይን ሕዝብ ከወገኑ ከኢትዮጵያውያን እንዲነጠል ሞከረ፣
• አረመኔው መለስ ዜናዊ፤ እንደ እነሱ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ያልጠላ ትግሬዎች ላይ የተቀነባበረ የጥፋት ዘመቻ በማካሄድ ሃውዜንን በደርግ ጀቶች በማስደብደብ ንጹሃን ዜጎችን /ሕፃናትን፣ እናቶችን፣ አባቶችን/ በጭካኔ አስደበደበ፤ በ1977 ድርቅ ጊዜ የትግራይን ሕዝብ በግድም በውድም ወደ ሱዳን ሄደው እንዲሰፍሩ አስደርገው፣ ለነፍስ ማዳን የመጣውን የእርዳታ ምግብ ሰርቀው በመከዘን፣ ሕዝብ በረሃብ እየረገፈ እህሉ ለብልሽት እንዲዳረግ፣ የተረፈውንም በመሸጥ የትራንስፖርት መኪኖች ገዝተው በህዝቦች ህይዎት ላይ ነገዱበት፣
ግን ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የቃል ኪዳን አገሩ ነችና ሊጎበኛት ፈቀደ እና ቀንደኛ ነቀርሳዎቿን ጥቁሩን ውሻ መለስ ዜናዊን እና ተጋዳላይ ጳውሎስን ነቅሎ ጣላቸው አሁንም ኢትዮጵያውያን በርትተው በጸልዩ እና ፈጣሪያቸውን ቢማፀኑ ጠላቶቻቸውን ይበታትንላቸዋል።
ብሔራዊ እርቅ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ ዕድገት እና ብልጽግና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች!!!
ጥቁሩን ውሻ የነቀለ ሃያሉና ሕያው እግዚአብሔር ኢትዮጵያ
የ21 ዓመት ፀረ-ኢትዮጵያዊ፣ ፀረ-ኦርቶዶክስ እና ፀረ-ብሔረ አማራ አምባገነናዊ እና ዘረኛ አመራር

No comments:

Post a Comment