ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ የጀመሩትን ታሪካዊ ሀገር የማዳንን ትግል ዳር ለማድረስ ወደ ኤርትራ መግባታቸው ተዘገበ
July 19, 2015
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከቃሊቲ እስር ተፈተው ቀደም ሲል ይኖሩበት ወደነበረው አሜሪካን ሀገር ከተጓዙ በኋላ አፍታም ሳይቆዩ ነበር የሁለገብ ትግልን አስፈላጊነት መናገር የጀመሩት። ዶ/ር ብርሃኑ ወዲያውም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ከሌሎች ሃሳባቸውን ከሚጋሩ ስመጥር ፖለቲከኞች እና የለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄን መሰረቱ፣ በወቅቱ ዶ/ር ብርሃኑ የእርሳቸውን እና በግንቦት 7 ዙሪያ የተሰባሰቡ ጓዶቻቸውን ቁርጠኛነት ሲያስገነዝቡ “ዘረኛውን የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድ የማንፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም” ነበር ያሉት።
https://www.youtube.com/watch?t=16&v=b-upNBStOVM
https://www.youtube.com/watch?t=16&v=b-upNBStOVM
ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ 7 ጠንካራግንቦት የተዋጊ ሃይል ማቋቋም የቻለ ሲሆን ለጥቆም ቀደም ሲል ጀምሮ ወያኔን ማስወገድ የሚቻለው በሃይል ብቻ ነው በማለት መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ከነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጋር በመዋሃድ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄን መፍጠር ተቻለ።
ዛሬ በወያኔ እጅ ወድቆ የሚገኘው በሳሉና ቆራጡ ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስካሁን ግንቦት 7 በተጓዘባቸው የስኬት ጎዳናዎች ሁሉ አሻራው እንዳለበት በቅርብ አብረውት ሲታገሉ የነበሩ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይመሰክራሉ።
በወጣት አርበኞች የተገነባውና እራሱን ለውጊያ ብቃት ሲያደራጅ የሰነበተው አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ክንዱን ማሳረፍ በጀመረ ማግስት ነው እንግዲህ የንቅናቄው መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም አመራሮች በአካል የትግሉን ጎራ ለመቀላቀል ወደ ሜዳ የወረዱት።
የዶ/ር ብርሃኑ ነጋንና የሌሎች አመራሮችን የትግሉን ጎራ በአካል መቀላቀል አስመልክቶ ንቅናቄው ባሰራጨው አጭር መልዕክት እንደገለጸው፣
“የተቀደሰ አላማን ያነገብን እርኩስ አላማን በሚያራምዱት ላይ ድልን እንቀናጃለን፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም የንቅናቄው አመራሮች የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ነጻነት፣ የፍትህ እና የዴሞክራሲ ጎዳና እንደሚመሩት ጥርጥር የለንም” ብሏል።
አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም የንቅናቄው አመራሮች በአካል ከአርበኞቹ ጎን መገኘት ከፍተኛ ሞራል እና መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአለም አቀፍ ህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጨነት ያላቸው የሰላምና የዴሞክራሲ ግንባር ቀደም ታጋይ ናቸው። ይህን ችሎታቸውም ኢትዮጵያን ወደ ነጻነት ለመውሰድ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
No comments:
Post a Comment