Monday, September 30, 2019

ማንነት ሲጋለጥ ታምራት ታረቀኝ 1999 ዓ.ም [ከመዐሕድ እስከ ቅንጅት] የልደቱ አያሌው ሴራ



"ይህን መፅሃፍ በማንበብ ስለ ልደቱ አያሌው ማንነት ለብዙ አመታት በቅርብ ከሚያውቀው ሰው ለመረዳት በመቻሌ ተደስቻለሁ። መፅሁፉ ስለ ልደቱ የነበሩኝን ጥርጣሬዎች ይበልጥ አረጋግጦልኛል።

አሁን ስለ ልደቱ ያለኝ ግንዛቤ ቀደም ብሎ ቢኖረኝ ኖሮ የኢዴአፓ-መድህን አባል ባልሆንኩ ፣ የአቶ ልደቱና መሰሎቻቸው መጠቀሚያ ባልሆንሁ ነበር።
በመፅሀፉ አንባቢያን ስለ ልደቱ ይበልጥ እንዲያውቁ በማድረጉ አቶ ታምራትን በጣም አመሰግናለሁ።
>>
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ
<<
እንዴት አታምነንም? ቃለ ጉባኤ ሰነድ አይደለም ወይ? ይህንንም አላምንም ካልክ አዚሁ እንፈርምልሃለን። የብዕር ፊርማችንንም አላምንም ካልክ ጣታችንን ቀለም እየነከርን እንፈርምልሃለን ፣ ይህንንም አላምን ካልክ ጣታችንን እያደማን በደማችን እርምልሃለን።
>>
ከመዕሃፉ የተወሰደ
(የቅንጅት አመራሮች ዶ/ር ኃይሉ እና ዶ/ር አድማሱ)
--------------------------------------
"ልደቱ አያሌው አይበቃኸም?"
(በታምራት ታረቀኝ)
===================
በድንገተኛ ስሜት ተስቤ ኢ ኤን ኤን ቲቪ ላይ የሰማሁት የቀድሞ ወዳጄ ቃለ ምልልስ በዝምታ የማይታለፍ ሆኖብኝ የጀመርኩት ጽሁፍ ትውስታ ትውስታን እየቀሰቀሰ ለዚህ ለክፍል ሁለት አድርሶኛል፡፡ ዋና ዋናዎቹን ብቻ በማንሳት በዚሁ ለመቋጨት እሞክራለሁ፡፡
1- እኛ፤ ንግግሩ በሙሉ እኛ ነው፤ እኛ የወል መጠሪያ እንደመሆኑ ለብዙ ነገር ያመቻል፡፡ ስለሆነም ልደቱ እኛ የሚላቸው ኢዴአፓ መድህንን ወክለው የቅንጅት ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የነበሩትን 5 ሰዎች፤ የም/ቤት አባል የነበሩትን 18 ሰዎች ወይንስ ከውህደት በፊት የነበረውን የኢዴአፓ መድህን ሥራ አስፈጻሚና ምክር ቤት አባላት ወይንስ ከውህደት በኋላ ከቅንጅት አፈንግጦ በእሱ ሊቀመንበርነት የቀጠለውን አመራር፡፡ እኛ ሲል ብቻየን አልነበርኩም ማለት ነውና እኛ የሚለው መሸፈኛ መገለጥ ይኖርበታል፡፡ አሁን ደግሞ በዶ/ር ጫኔ እና በእሱ መካከል ክፍፍሉ ለይቶለት ኢዴፓን አፍርሰነዋል ብሎ አውጇል፡፡ እናም ለአስር አመት ሙል እኛ ሲል እነማንን ጨምሮ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡
2- በወቅቱ አቋማችንን ለማስረዳት ሚዲያ አልነበረንም፡፡በምርጫ 97 ወቅት ለአቅመ ፖለቲካ የደረሳችሁ ወገኖች ሁሉ ለአፍታ በአይነ ልቦና መለስ በሉና 1998 ዓ.ም አስታውሱ፡፡ አየቅንጅት አመራሮች እስር ቤት ሆነው ከእስር የተረፉትም እንኳን አደባባይ ወጥተው ሊናገሩ በየቤታቸው ለመኖር ምጥ በሆነበት እና ማንም መልስ የሚሰጠው ባልነበረበት ወቅት በወቅቱ በነበሩት የመንግስት መገናኛ ብዙኃን እንደልቡ ሲጠቀም አልነበረምን፡፡ እኔ እስር ቤት ሆኘ አየውና እሰማው ነበርና ሌላው ቢቀር ሁለት ነገሮች አይረሱኝም፡፡ አንደኛው ዛሬም ድረስ እንደሚያደርገው ራሱን ነጻ አድርጎ እስር ቤት ያነበሩትን አመራሮች ይወነጅል የነበረበት ሁለተኛው በቅርቡ ከእስር የተፈታው ወዳጄ አቶ አንዱዓለም አራጌ መስከረም 11/98 በኢዴአፓ መድህን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተናገረውን ለእሱ በሚፈልገው ሁኔታ ቆርጦ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ያስተላለፉለት ነው፡፡ እዚህ ድረስ መገናኛ ብዙኃንን የተጠቀመ ሰው ዛሬ በወቅቱ አቋማችንን ለማስረዳት ሚዲያ አልነበረንም ሲል መስማት ምን ሊባል እንደሚችል ቸገረኝ፡፡ ጋዜጠኞቹም በበቂ ተዘጋጅተው የሚጠይቁ ባለመሆኑ በየመድረኩ እውነት ትረገጣለች፡፡
3- ወጣት አስጨረስክ የሚሉኝ እኛ ነን እንደውም የታደግነው፤ እኛ እነማን እንደሆኑ የማይታወቅ በመሆኑ እኔ እሱን ብቻ የሚመለከተውን እና የአይን ምስክር የነበርኩበትን ነው የምገልጸው፡፡ ዛሬም ከአስር አመት በኋላ እውነት ተቀብራ የቀረች ይመስል ራስን ነጻ ሌላውን ወንጀለኛ ለማድረግ ከመቸገር የጥፋት ደረጃችን ያንስ ይበዛ እንደሁ እንጂ በዛን ወቅት ከሆነው ማናችንም ነጻ ልንሆን አንችልም፡፡ ስለሆነም በእኔ በኩል ለሆነው ሁሉ የቅርታ እጠይቃለሁ ማለቱ ነበር ሊያስከብር የሚችለው። ይህ ሳይሆን ሲቀርና ዛሬ የተነገረው ትናንት ከሆነው ጋር የማይገናኝ ሲሆን ነገሩን በቅርብ የምናውቅ ሰዎች በስሜት ሳይሆን በእውነት በአሉባልታ ሳሆን በማስረጃ ገልጸን የማሳየት የህሊና ግዴት አለብን፡፡ እናም እነሆ፤
ሀ- የምርጫውን ውጤት ተከትሎ በየፓርቲዎችም በቅንጅትም ውይይት ሲደረግ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻውን ውጤት ካሳወቀ በኋላ ካልተስማማን ምን እናደርጋለን ተብሎ እንደ አንድ አማራጭ በቀረበው ፍርድ ቤት መሄድ አለመሄድ ጉዳይ የኢዴፓ ም/ቤት ሲወያይ ልደቱ ያቀረበው ሀሳብ አስደንጋጭም አጠራጣሪም ነበር፡፡ “ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ለውጦ ኢህአዴግን አሸናፊ ቢያደርገው ፍርድ ቤት ሄደን የተለየ ነገር ስለማናገኝ የተጭበረበረውን የህዝብ ድምጽ ለማስመለስ ህዝብ ለተቃውሞ እንጠራለን፣ ኢህአዴግ በለመደው መንገድ ይህን የህዝብ ተቃውሞ ሰዎችን በመግደል ያከሽፈዋል፣ ከዚህ በኋላ እኛ ይህንኑ አጋልጠን ያገኘነውን ወንበር ይዘን በፓርላማ ትግላችንን እንቀጥላለን ነበር ያለው፡፡” (ይህን አባባሉን ከውህደት በፊት በነበረውና እኔ አባል ባልነበርኩበት የቅንጅት ምክር ቤትም ማቅረቡን ሰምቻለሁ)፡፡ ሁለቱም ቦታ የነበሩ ሰዎች ከጥቂቶች በስተቀር ዛሬም በህይወት አሉ፡፡
ለ- አኩርፎ ከመቅረቱ በፊት የቅንጅት የህዝብ ግንኙነት ሥልጣንኑ በመጠቀም በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድምጽህን አስቀምተን አንቀመጥም የኢትዮጵያ ህዝብ ቅንጅት ለሚያደርግልህ ጥሪ ተዘጋጅተህ ጠብቅ ማለቱን በወቅቱ የእለት ሁኔታን ይከታተል የነበረ ሁሉ የሚያውቀው በድምጽም በመስልም ተቀርጾ ያለ ነገር ነው፡፡ ከሌላ ቦታ ቢጠፋ ከኢቲቪ መደርደሪያ ላይ አይጠፋም ይህ አባባል ህብረተሰቡን የሚያረጋጋ ወይንስ የሚያነሳሳ?
መ- በክፍል አንድ ላይ የገለጽኩት መስከረም 29/ምሽት የፓርላማ መግባት አለመግባትን ጉዳይ ከወሰነው የምክር ቤት ስብሰባ በኋላ በተሰጠ መግለጫ ላይ ህዝቡ የመረጠን ፓርላማ ገብተን ወንበር እንድናሞቅ አይደለም በማለት የተናገረውም ቢሆን የሚያረጋጋ ሳይሆን የሚያናጋ ነው፡፡
ሰ-የቃሊቲው የፌዝ ችሎት የአቃቤ ህግ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በተመለከተበት ግዜ በስመ አቃቤ ህግነት የቀረበው ሽመልስ ከማል የማስረጃ ጭብጥ ያለውን ሲያሰማ ህገ መንግስታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፍረስ አቅደው ህዝቡን ለዚህ ዓላማቸው ለማነሳሳት ያደረጉትን ቅስቀሳ ያሳይልኛል ይልና ቪዲዮው ሲታይ የተባለውን ሲናገር የሚታየው ልደቱ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ችሎቱን የሚከታተለው ታዳሚ እነ ሽመለስ ከማልን እያየ ያጉረመርማል ግማሹም ፈገግ ይላል፡፡ መሳቅ በችሎት ማወክ ያስቀጣል ተብሎ ማስጠንቀቂያ በመሰጡት እንጂ ብዙዎች ከትከት ብለው ይስቁ እንደነበር ሁኔታቸው ይናገር ነበር፡፡ ከዳኞቹ ፊት ላይ ደግሞ የመገረም ስሜት ሲነበብ አጃቢ ፖለሶች ስክሪን ላይ የሚያዩትን ሰው ከመካከላችን ይፈልጋሉ፡፡ታዲያ ችሎቱ ተነስቶ ስንመለስ እንዴት ነው ነገሩ ቪዲዮው ላይ ያየነው ሰው ከመካከላችሁ የለም አልተከሰሰም ማለት ነው ወዘተ እያሉ ይጠይቁን ነበር፡፡
4- ትናንት ኢህአዴግን ደገፋችሁ ተብለን ተጠላን ዛሬ ሁሉም የኢህአዴግ ደጋፊ ሆነ፤ ይህን ስሰማ ለወዳጄ በእጅጉን አዘንኩለት፤ የት ይደርሳል ብለን በጉጉት ስናየው የነበረ ልጅ መሀል መንገድ ላይ አይሆኑ መሆኑ ሲገርም እንዲህ እስከ ማሰብ መድረሱ የሚያሳዝን ነው፡፡ እኔ እስከሚገባኝ ከተሳሳትሁ ለመታረም ግጁ ነኝ ህዝቡ የደገፈው ኢህአዴግንም ዶ/ር አብይንም ሳይሆን የታገለለትን የናፈቀውን የተመኘውን የለውጥ ጅማሮ ነው፡፡ ለውጥ ያለ ሰው ስለማይታሰብ ዶ/ር አብይም ሆኑ ቲም ለማ ድጋፍ ያገኙት የለውጡ ተዋናይ በመሆናቸው ነው፡፡ እነርሱ ወደ ሥልጣን መጥተው ለውጥ ባይታይ የሚገጥማቸው ምስጋና ሳይሆን ተቃውሞ እንደነበረ መረዳት ለልደቱ የሚሳን አይመስለኝም፡፡ ነገሩ ወሎዬ ሲያንጎራጉር አላህ ሲቆጣ ብትር አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም የሚለው ሆኖ እንጂ፡፡
5- ይቅርታ ጠይቀው ከተፈቱ በኋላ፤ ይህንንም ያነሳው በአዎንታዊ መልኩ አይለም፡፡ ይህ ግልጽ የሚሆነው የመፈረማችን ዜና ከፕ/ር ኤፍሬም ጋር በተስማማንበት መሰረት ሳይሆን መለስ በሚፈልገው መንገድ በመገናኛ ብዙኃን ተነግሮ ገና ሳንፈታ አቶ ልደቱ ተሸቀዳድሞ በመገናኛ ብዙኃን ብቅ በማለት እኛንም ይቅርታ ይጠይቁን ማለቱን ስናስታውስ ነው፡፡ አሁን ግዜ ተለውጧልና ፕ/ር ኤፍሬም ወደ ሞት ከመሄዳቸው በፊት እውነቱን ይናገራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ እባካችሁ ጋዜጠኞችም ጠይቁቸው፡፡ በመጨረሻው ሰአት ላይ ተዋቂው የህግ ባለሙያ አቶ ታምሩ ወንድምአገኘሁም ነበሩበት፡፡
6-የአሉባልታ ፖለቲካ ይሄ እውነት ነው፤ ፕ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ የሚሉት አደረገው እንጂ፡፡ ለአንድ ዓላማ ተሰልፈው፤ በአንድ ህግ ሊገዙ ቃል ተገባብተው፣ እስከ ሞት አብሮ መዝለቅ የሚጠበቅባቸው የአንድ ፓርቲ ሰዎች የሀሳብ የበላይነት ማግኘት ሲያቅትና በመረጃና ማስረጃ መሞገት ዳገት ሲሆን ቀላሉና አቋራጩ መንገድ አሉባልታ ነው፡፡ይህን የተቃውሞውን ጎራ ድክመት በተለይም በመሪነት ቦታ የሚቀመጡትን ሰዎች ከወንበር በላይ ማሳብ አለመቻል የተረዳው ወያኔ አሉባልታ እየፈበረከ፣ የፍረጃ መርዝ እየቀመመ ይረጫል፡፡ በዚህ ወቅት ወንበሩ ላይ ያሉት ሰከን ብለው ለማጣራት ከመሞከር ይልቅ የማይፈልጉትን ሰው ከአጠገባቸው ለማራቅ በቂ ድጋፍ እንዳገኙ ይቆጥሩትና የበለጠ ያራግቡታል፡፡ ከዛም አባራሪና ተባራሪ ብሎም አዲስ ፓርቲ ይፈጠራል፡፡
የሚገርመው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአመራር ቦታ ተቀምጦ አሉባልታና ፍረጃ ያልነካው ቢኖር የታደለ በጣም ጥቂት ሰው ነው፡፡ ዛሬ በሌሎች የተፈረጀ አሉባልታ የተወራበት ሰው ነገ እሱ በተራው ሌሎችን ይፈርጃል አሉባልታ ያስወራል፡፡ ይህ አሌ የማይባል እውነት ሆኖ አጠያያቂውና አስጠያቂው ልደቱ ራሱን ከደሙ ንጹህ አድርጎ ማቅረቡ ነው፡፡ ግዮን ሆቴል አቅራቢያ ከሚገኘውና የእሱ ልዩ ምሽግ ከነበረው(ይህን ያልኩበት ምክንያት አለኝ) ቢሮ እየተፈበረኩ ይወጡ የነበሩ አሉባልታዎችን እየተቀመሙ ይረጩ የነበሩ ፍረጃዎችን አላውቃቸውም እኔን አይመለከቱኝም ይል ይሆን?
የልደቱን ልዩ የሚያደርገው በፊት ለፊትም ሰው ለማጋጨት የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ማህተም አላደርግም ብሎ እነ ዶ/ር አለማየሁ አረዳ ሽምግልና ተልከው እነርሱም በነገራቸው አምነው ሊያስረዳ በተገኘበት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ አላምናችሁም አለ፤ ስለምን ቢባል ከምርጫው በፊት ዶ/ር ብርሀኑና ፕ/ር መስፍን ምርጫው ይለፍ እንጂ ሀይሉን እናነሳልሀለን ብለውኝ ነበር ሲል ተናገረ፡፡ ኢ/ር ኃይሉ ከተሰብሳቢው መሀል ነበሩና ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው ወንበሩን ነው የምትፈልገው፤ አትችለውም እንጂ ከቻልከው ዛሬውኑ ውሰደው አሉት፡፡ ያሰበው ነገር አቅጣጫውን ሳተበት፡፡
7-የሚቃወሙን ፖለቲካን ምርጫ 97 የጀመሩ ናቸው፤ ይህን ምን ትሉታላችሁ፤ እኛ የምትለው የወል መጠሪያ መገለጥ ያለባት እዚህ ጋር ነው፡፡በወቅቱ የኢዴአፓ መድህን ም/ቤት ሙሉ ለሙሉ ባይባልም አብዛኛው የእሱ ደጋፊ አልነበረም፡፡የውህዱ ቅንጅት ም/ር ቤት አባል ከነበርነው 18 ሰዎች አስራ ሰባታችን ማህተም አላደርግም በማለቱ ምክንያት ስብሰባ አድርገን በነበረ ግዜ የዘጠኙን ድጋፍ ማግኘት ችሎ ነበር፤ ከላይ በገለጽኩት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ዶ/ር አለማየሁ አረዳ ተነስተው ቃለ ጉባኤ ሰነድ አይደለም ወይ እንዴት አታምነንም፤ በብእር ካለመንህ ጣታችን ቀለም እየነከርን በአሻራችን እንፈርምልህ፤ይህንንም ካላመንህ ጣታችንን እያደማን በደማችን እንፈርምልህ፣ አለ የምትለውን ነገር ሁሉ በአጀንዳ መወያየት እንችላለን ወዘተ ብለውት አሻፈረኝ ሲል ከዘጠኙ ውስጥ የነበሩት ወ/ሮ ላቀች ደገፉ አቶ ጎሹ አውደው( ነብስ ይማር ሁለቱም ሞተዋል) መምህር ወንድ ወሰን ተሾመ (አሁን በዶ/ር ጫኔ በሚመራው ኢዴፓ ውስጥ ናቸው፡፡) በየተራ እየተነሱ ከዚህ በላይ ምን ይፈለጋል ማህተሙን ልታደርግ ይገባል ሲሉት ነበር ከዚህ በላይ አልችልም ብሎ ሹልክ ብሎ ወጥቶ የሄደው፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ፖለቲካን በምርጫ 97 የጀመሩ ናቸው ማለት ነው፡፡ ያሳዝናል አሁንም ጥሩ መካሪ ያገኘ አይመስለኝም፡፡በየቦታው የመናገር ምቹ ሁኔታ ማግኘቱን ዳግም እንደማንሰራራት ቆጥሮት ከሆነ ንግግሩ ሲበዛ ስህተቱ ይጨምራል የሚለውን አባባል ማስታወሱ ሳይበጅ አይቀርም፡፡
“መከበርና መዋረድህ ከቃልህ የተነሳ ነው፤ የሰው መከራው በአንደበቱ ከተናገረው የተነሳ ነው፡፡” መጽኃፈ ሲራክ 5/14 ይጠቅም ከሆነ አንድ ዓላማዊ አባባልም ላክል፡፡ “በዚህ ዓለም ማንም ሰው ለውድቀት የሚያበቃ ዕቅድ የሚያወጣ የለም፤ ትክክለኛ ዕቅድ ባለማውጣታቸው ግን እነዚህ የተባሉት ይሆናሉ፤ ትክክለኛ ዕቅድ አለማውጣት ራስን ለውድቀት ማዘጋጀት

Friday, August 9, 2019


The basic skills of facilitator
====================


we often experience moods of anger & joy .we do have remarkable ability to learn and memorize events .We often notice powerful effect of leaders on behaviour of followers .
While we interact in groups we often experience conflict and cooperation.
At times we suffer from depression hyper anxiety . All of us remain curious to know about the causes of these happenings and try to make sense in own ways .
The knowledge gathered in this way cannot be used to formulate theories or to solve problems faced by peoples in their lives . We need dependable and relatively & accurate understanding the principles of describing the working human mind and behaviour.
The basic skills of facilitator following good meeting practices , timekeeping and minimizing self bias
Accuracy and Bias in self Perception
--------------------------------------------------------------
Self insight or accuracy of self perception, has been an issue of longstanding concerns to philosophers and social scientists . Among contemporary psychologists ,two different points of view predominant . According to one view, perception of self are based on socially shared reality ensue from the same processes the perception of others are best thought as accurate of behaviour and experience.
According to others view self perception is fundamentally distorted, self serving , and more consistent by self serving, and more positive than is justified by the perception of others .
Some psychologists discuss illusory self-enhancement if it were general law of human behaviour applicable to all normal psychologically healthy individual
Normal human thought is marked not by accuracy but by positive self enhancing illusions "the healthy person is prone to self deceptive s positively"
The team-building Overview
--------------------------------------------------------
Team building activities exercises that help teams building cohesion and work through common group issues and provide opportunities for participants to combine individual talents and abilities with awareness of the need to develop cooperation and trust within a group.
As people interact, they form relationship based on their own motivations and understanding of the other parties intentions & desires. Similarly people who represent an organization, political party or a group of people must bridge relationship when interacting with others. The corner stone of creating a constructive and working relationship among people whether they are representatives of something greater or not , is understanding that all parties involved have desire outcome . In most cases the desired outcomes of or motives of the other involved parties . With the later in mind ,individuals can improve their chance of successful working relationships if they understand where they themselves are coming from and where they are going.

Monday, January 7, 2019

"በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ


Sunday, January 6, 2019

ያልተገራው የማንነት ፖለቲካችን እና አደጋው (ተበጀ ሞላ (PhD)


The Poison of Ethnic Federalism in Ethiopia’s Body Politic
መግቢያ
በሀገራችን የዘውጌ ፖለቲካ ያለ ልክ ጦዟል።  በየማዕዘኑ ዘውጌ-ተኮር አፍራሽ ፉከራ እና ዲስኩር እየሰማን ነው። ፖለቲካኞቻችንም ሃሳብ ከመሸጥ ይልቅ ስሜት መግዛት ላይ አትኩረዋል።  በግዜ እልባት ካላገኘ ይሄ አካሄድ ሀገር አልባ እንዳያስቀረን ያስጋል። ለመሆኑ የዘውጌ ፖለቲካ ታሪካዊ መሰረቱ ምንድነው? ከኛ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃርስ አክራሪ ዘውጌነት ምን አደጋ አለው? አሳታፊ የሆነ የዜግነት ፖለቲካ እዉን እንዲሆን ምን የተሻለ መንገድ አለ? ይህ አጭር መጣጥፍ እነዚህን ነጥቦች በጨረፍታ ይዳስሳል። በፅሁፉ ዉስጥ ዘውጌ፣ ዘውግ እና ብሔር የሚሉት ቃላት እንደ ቅደም ተከተላቸው ethnic፣ ethnicity እና nation የሚሉትን የእንግሊዝኛ ቃላት ይተካሉ።  ሃሳቤን ማንነትን በማብራራት እጀምራለሁ።
ማንነት ምንድን ነው?
ማንነት ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት በቡድንም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ራሳችንን የምንገልፅበት መለያችን ነው። በዋናነት ማንነት ለራስ በሚሰጥ እይታ ይገለፃል። ማንነት ዘርፈ-ብዙ ነው።  ነጠላ ማንነት ያለው ሰው የለም። አንድ ግለሰብ በፆታው፣ በሃይማኖቱ፣ በቋንቋው፣ በዘውጉ፣ በሙያዉ፣ በፖለቲካ እምነቱ እና አሰላለፉ፣ ወዘተ ማንነቱን ሊገልፅ ይችላል። ከሁለንተናዊው ሰውነቷ ባሻገር ሶፊያ  ባንድ ግዜ ሙስሊም ፣ መምህር፣ ስልጤ፣ ኢትዮጵያዊት፣ የአፍሪካ ሴት ልትሆን ትችላለች። በመሆኑም ‘ይህ ቡድን ወይም ያ ግለሰብ የተለየ ማንነት አለው’ ሲባል የግድ ስለ ዘዉግ አያወራን ላይሆን ይችላል። በሌላ አነጋገር ማንነት እንደ ቀይ ሽንኩርት ተደራራቢ ነው። አንዱን ንብር ልጦ ጥሎ (ረስቶ) ሌላውን መብላት (ማስጮህ) የባለቤቱ ምርጫ ነው።
ሰው ነን እና ኑሯችን ከሌሎች ጋር የተቆራኘ ነው። ስዉር በሆነው የግል ማንነታችን እና ሁለንተናዊ (universal) በሆነው ሰዋዊ ተፈጥሯችን መካከል ራሳችንን በበርካታ የጋርዮሽ እርከን እናገኘዋለን። ከቤተሰብ ጀምረን ከፍ ስንል በዘመድ አዝማድ ከዛም ሲያልፍ በጎሳ (clan)፣ በዘውግ (ethnicity)፣ በነገድ (tribe)፣ በብሔር (nation) እና በዘር (race) ማንነታችንን እንገልፃለን። አንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ደግሞ የዉጭ ሰዎች በብሔራዊ ማንነታችንን (national identity) ይለዩናል።
በሊብራል ዲሞክራቲክ ሃገራት እንደ አዲስ ያቆጠቆጠውን አክራሪ ብሄርተኝነት ተከትሎ ስለ ማንነት ፖለቲካ ብዙ ትንታኔ አየተሰጠ ነው። እዉቁ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ፍራንሲስ ፍኩያማ እና አፍሪቃዊው ፈላስፋ ክዋሜ አፕያህ በቅርቡ በማንነት ላይ ያሳተሟቸው መፅሃፍት ተጠቃሽ ናቸው።  እንደ ፍኩያማ እምነት የሰው ልጅ ለእዉቅና (recognition) የተለየ ቦታ አለው። ለማንነት የሚሰጥ እዉቅና ከክብር ጋር ይያያዛል። ማንነቴ ተገቢዉን እዉቅና ዋጋ አላገኘም ብሎ ያመነ ግለሰብም ሆነ ቡድን ይደራጃል፣ ይታገላል። አፕያህ በበኩሉ ማንነት እንደ ዘረመል (gene) የሚወረስ ሳይሆን እንደ ፀጉር በቅጥ ተሰርቶ ማድመቂያ የሚሆን ስሪት ነው ሲል ይከራከራል ። የዘውጌ ማንነት በዋናነት ተወራሽ መለያወችን (primordial characteristics) መሰረት ያደረገ ነው። አባላቱ ‘እኛና እነሱ’ ብለው የሚለዩባቸው ቋንቋ ፣ ወግና ልማድ እንዲሁም ግዛት (ancestral territory) ይጋራሉ። ሆኖም ማንነት ተፈጥሯዊ አይደለም — ሰው ሰራሽ ነው።  አዲስ ግዛት በመዉረር፣ ባህልን በማሻሻል እና ታሪክን ለራስ በሚመች መልኩ በመከለስ የዘውጌ ማንነት ይፈጠራል። ለዚህ ደግሞ የፖለቲካ ኃይል፣ ትውፊት እና ዲስኩር ዋና መሳሪያዎች ናቸው።  ካለፉት 30 አመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር እየሆነ ያለዉን ያስተዋለ ይህን እዉነታ  አይስተውም።
የብሔር ፖለቲካ አመጣጥ በጨረፍታ 
ብሔር እና የብሔር ፖለቲካ መነሻ አዉሮፓ ነው። በዘርፉ ጥልቅ ምርምር ያደረገው ሊህ ግርንፈልድ እንደሚለው nation (ብሔር) የሚለው ፅንሰ-ሃሳብ ምንጩ natio የሚለው የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም ‘የተወለደ’ ማለት ነው። የጥንት ሮማዉያን ቃሉን ካንድ አካባቢ የመጡ የዉጭ ሃገር  ሰዎችን ለመግለፅ ይጠቀሙበት እንደነበር ተዘግቧል። በዋናነት መጤነትን ስለሚገልፅ ትርጓሜው የክብረነክነት ባህሪ ነበረው። ሁላ በመካከለኛው የአዉሮጳዉያን ታሪክ ብሔር የሚለው ስያሜ በቋንቋ ወይም በትዉልድ ቦታ  ከሚመሳሰሉ አካባቢዎች የመጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመግለፅ ይዉል ነበር ። ተማሪዎቹም የትዉልድ ቄያቸውን መሰረት አድርገው መተጋገዝ እና በክርክርም ወቅት አንድ ላይ መቆም መለያቸው ስለነበር ብሔር የሚለው ስያሜ ያንድ አካባቢ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ሃሳብ እና ዓላማ ለሚጋሩ ማህበረሰቦች (communities) መጠሪያ ሊሆን በቃ።  ቆይቶም ሃሳቡ ወደ ቤተክህነት ጉባኤ ዘልቆ ገባ እና ሌላ ትርጉሙ አገኘ: ልሂቃንን ለመግለፅ ዋለ። በ16ኛው ዘመን እንግሊዞች  ብሔርን እና   ‘ሕዝብ’ን በእብረታ (አንድ ላይ) መጠቀም እንደጀመሩ  ይነገራል። ይህ ለውጥ ሃገራዊ ብሄርተኝነት (civic nationalism) የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም እንዲሆን ርሾ የጣለ ነበር።
ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ግን ብሔር የሚለው ቃል ‘ልዩ ሕዝብ’ የሚል ትርጉም ያዘ። በፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ሩስያ ቃሉ ዘውግን፣ ግዛትን እና የፖለቲካ ታማኝነትን አጣምሮ የያዘ ማህበረሰብ የሚገልፅ ሆነ።  በተለይ ደግሞ በፈረንሳይ አብዮት ማግስት የተቀነቀነው ‘የብሔር ጥያቄ’ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ  ጀምሮ በግራ-ዘመም ፖለቲከኞች ቁልፍ አጀንዳ ለመሆን በቅቷል።  ብሔር እና ብሔረሰብን ዋና የፖለቲካ ጉዳይ  አድርጎ ለመጀመርያ ያቀረበው የሶቪየቱ መሪ ጆሴፍ ስታሊን ማርክሲዝም እና የብሔር ጥያቄ በሚለው ፅሁፉ (1913 እአአ) ብሔር መሰረቱ የግድ ዘር፣ ነገድ ወይም ዘውግ ላይሆን ይችላል ይላል። በዋንናነት የኦቶ ባወርን (በወቅቱ ስመ-ጥር የነበረ ኦስትርያዊ ፖለቲከኛ) ሥራ መሰረት አድርጎ፣ ስታሊን   ብሔር ማለት ታሪካዊ ሂደት፣ ቋንቋ፣  አሰፋፈርና ስነ-ልቦና የሚጋራ እና የምጣኔ ሀብት ትሥሥር ያለው ማህበረሰብ ነው ሲል አብራርቷል።
በዚህ መልኩ ቅርፅ የያዘው የብሔር ፖለቲካ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማግስት ጀምሮ  ከአዉሮጳ ወደ ሌሎች ክፍለ-ዓለማት በሰፊው ተዛመተ። የአፍሪካ ልሂቃን በሌላ አዉድ ስለ ብሔር የተፃፈውን እና የተነገረውን ሁሉ ገልብጠው ለዘውግ ፖለቲካ አዋሉት።  የኛዎቹ ዋለልኝ መኮንን እና መለስ ዜናዊም ይህንኑ ነበር ያደረጉት። ሃሳቡን ሲዋሱ አግባበ ነገሩን ግን አላገናዘቡም። ከላይ እንደተባለው ብሔር (nation) የሚለው ቃል በታሪክ ሂደት ብዙ ግዜ ትርጉሙ ተለዉጧል፥ ለሮማዉያን የመጤ ሰዎች መጠሪያ ነበር። ቆይቶ  ሃሳብ እና ዓላማ የሚጋሩ ስብስቦችን ለመግለፅ ዋለ።  ኋላ ደግሞ የሃይማኖት እና ማህበራዊ ልሂቃን ስያሜ ተደረገ። ከዛም እንግሊዞች ‘ሉዓላዊ  ሕዝብ’ የሚለውን ፖለቲካዊ ትርጉም አስያዙት። በዘመነ አብዮት ደግሞ ብሔር ማለት ‘ልዩ ሕዝብ’ ማለት ሆነ። የ ‘ያ ትውልድ’ ዘውጌዎች እና የዛሬዎቹ ደቀመዝሙሮቻቸው ‘ብሔር’ ነን ሲሉ “ሌሎች ጋር ምንም የማንጋራ ‘ልዩ’ ሕዝብ ነን” ማለታቸው ነው። ኢትዮጵያን በቅጡ ለሚያውቅ እሳቤው የተዛባ ነው። ከሀገራዊ ብሔርተኝነት (civic nationalism) እደገት እና ታሪክ አንፃር ሲታይ ብሔር ማለት እጣ ፈንታው አንድ የሆነ፣ ከሚያለያዩት የዘውጌና ሌሎች ማንነቶች ባለፈ ጠንካራ የጋራ እሴቶች ያሉት ሕዝብ ማለት ነው። ስለዚህ ፖለቲካችን በብሔር ደረጃ ከሆነ የምናወራው ስለ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ስለ ዘውጌ ማንነት ሊሆን አይችልም።
የኢትዮጵያ “ብሔር” እና “ብሔረሰብ” እነማን ናቸው?
እንደማንኛውም መድብለ-ዘውጌ ማህበረሰብ (multi-ethnic society) በኢትዮጵያ ከዘዉዳዊዉ ስርዓት ግርሰሳ ጀምሮ፣ በተለይ ደግሞ ኢሕአዴግ ወደ ስልጣን ከወጣ ወዲህ ‘የብሔር ጥያቄ’ ዋና የፖለቲካ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። የሶቭየትን (1936/1977 እአአ) እና ዩጎስላቪያን (1946/1974 እአአ) ህገ-መንግስቶች ፈለግ ተከትሎ ወታደራዊው ስርዓት በሕገ-መንግስቱ (አንቅፅ 2) ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች ሀገር መሆኗን አስቀምጦ ነበር። በተመሳሳይ አራተኛው (አሁን በሥራ ላይ ያለው) ህገ-መንግስት በሀገሪቱ  ሉዓላዊ  የሰልጣን ባለቤቶች  ‘ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች’ ናቸው ይላል። ነገር ግን በሕገ-መንግስቱ የሰፈሩት አንዳንዶቹ  የፖለቲካ ቃላት አስማሚ እና ግልፅ ብያኔ የላቸውም። ለምሳሌ ስታሊን ለብሔር የሰጠውን ብያኔ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ‘ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን’ የሚለውን ፈርጅ (category) ለመግለጽ ተጠቅሞበታል። አንቅፅ 39(5) ‘ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ’ ማለት “ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የማንፀባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክዓምድር የሚኖሩ ናቸው” ብሎ ይፈታዋል።  ፅንሰ-ሃሳቡ በቀጥታ ከስታሊን ፍች አለያም ከመሰል ምንጭ የተቀዳ በመሆኑ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ማን ብሔር፣ ማን ብሔረሰብ፣ ማን ሕዝብ እንደሆነ በግልፅ አልተቀመጠም። በ1984 ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድሮችን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ (ቁጥር 7/1984) ደግሞ ብሔርና ብሔረሰብ ተተካኪ እንደሆኑ አድርጎ አስቀምቷቸዋል። አንቅፅ 2(7) “‘ብሔር’ ወይም ‘ብሔረሰብ’ ማለት በአንድ ኩታ ገጠም መልክዓ ምድር የሚኖር አንድ የመግባብያ ቋንቋና የአንድነት ስነልቦና ያለው ሕዝብ ነው” ይላል። በተመሳስይ መልኩ የሚድያ ባለሙያዎች እና ፖለቲከኞች ብሔርና ብሔረሰብ የሚሉትን ቃላት የዘውጌ ቡድኖችን (ethnic groups) ለመግለፅ ይጠቀሙበታል።
የዘውጌ ማንነትን የተረዳንበት እና ፖለቲካዊ ጥያቄውን ምላሽ ለመስጠት የሄድንበት መንገድ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያልተዛመደ በመሆኑ አሁን ላለንበት ችግር ደርሰናል። የክልል መንግስታት ምስረታና ስያሜ ጥሩ ማሳያ ነው ። ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት በትግራይ ክልል ትግራዋይ፣ ኩናማና ሳሆ የሚባሉ የዘውጌ ቡድኖች ይኖራሉ። በደቡብ ትግራይ ያሉ ራያዎችም አማርኛ፣ ኦሮምኛና አገዉኛ ይናገራሉ። በአማራ ክልልም እንዲሁ የአማራ፣ አገው፣ ኦሮሞ፣ አርጎባ እና ሌሎች ማሕበረሰቦች ይኖራሉ። ኦሮምያም በዉስጡ በርካታ የዘውጌ ማንነት ያላቸው ህዝቦች ይዟል።  የጋምቤላ እና  የቤንሻንጉል  ጉሙዝ ክልሎችም  የተለያዩ የዘውጌ ቡድኖች መኖርያ ናቸው።  ነገር ግን የክልላዊ መንግሥታት ስያሜ እና ክለላ ይህን የብዝሃነት እዉነታ አያንፀባርቅም። የትግራይን ክልላዊ መንግስት  “ብሔራዊ ”  በሚል  ከፍታ አስቀምጦ  ጋምቤላን “የብሔረሰቦችእና ህዝቦች“  ክልል ብሎ መሰየም  የምስቅልቅሉ ሁነኛ ማሳያ ነው።  ከፊት ለፊት ሲታይ ችግሩ  የፅንሰ-ሃሳብ ግልፅነት (conceptual clarity) ሳይኖር ህገ-መንግስቱ በመተርጎሙ የመጣ ይመስላል። ሸፍጥ የለበትም ብሎ መደምደም ግን አይቻልም።
በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ ዊል ኪምሊካ የተባለ የዘርፉ ተመራማሪ በመድብለ-ዘውጌ ማህበረሰብ  ዉስጥ በቁጥር እና ንቃተ-ህሊና ከፍ ያሉ የዘውጌ ቡድኖች ብሔር ሲባሉ ቀሪዎቹ ብሔረሰብ (nationality) ተብለው ሊሰየሙ ይቻላል ይላል። ነገር ግን ፍረጃው ሳይንሳዊ አይደልም፣ አያሳምንም። አንድ ዘውግ አናሳ የሚባለው መቼ ነው? ሰያሚውስ ማነው? ፖለቲካዊ ንቃተ-ሕሊናስ በምን ይለካል? ኢትይጵያ ዉስጥ ኦሮሞ እና አማራን ብሔር፣ ጋሞ እና ስልጤን ደግሞ ብሔረሰብ ብሎ ለመለየት አሳማኝ ቀመር የለም።
 አክራሪው የዘውጌ  ፖለቲካችን  የሳታቸው አምስት ቁምነገሮች 
በሰው ልጅ ታሪክ ለረጅም ግዜ ፖለቲካዊ ቅቡልነት (legitimacy) ምንጩ እግዚአብሔር ወይም ስርወ-መንግስት ነበር። ባንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች አሁንም የስልጣን ምንጭ ደም ወይም ፈጣሪ ቢሆንም በአብዘሀኛው ዘመናዊ ፖለቲካ መሰረቱ በማንነት ዙሪያ የተሰባሰበ ሕዝብ ነው። የሙያ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ጥቁሮች ፣ ወግ አጥባቂዎች ወዘተ በፖለቲካው ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩት በማንነት ስም በሚሰበስቡት ድምፅ ነው። በኢትዮጵያም የስልጣን ምንጭ እግዜር ነበር። ቆይቶ ርዕዮተ-ዓለም ሆነ። አሁን የሁሉም ነገር ምንጩ ዘውግ ሆኗል። መጀምርያ የስታሊንን የብሔር ፖለቲካ የሸመደዱ የ1960ቹ ተማሪዎች የዘውዱን ስርዓት በብሔር እና መደብ ጭቆና ስም ታገሉት።  የመደብ ጭቆናው በወታደራዊ መንግስት ሲመለስ ዘውጌዎቹ የብሔር ጥያቄ አንጠልጥለው በረሃ ገቡ፣ አሸነፉበትም። አሸናፊዎቹ በተራቸው ፍላጎታቸውን በሌሎቻችን ላይ ጫኑ። ተጨቋኞቹ ሌላ ዙር ትግል አድርገው ዛሬ ላይ ደርሰናል። አሁንም የፖለቲካ ችግራችን እንደተወሳሰበ ነው።  በኔ እይታ ያልተገራ እና መሬት ያልያዘ  የዘውጌ ፖለቲካ ለችግራችን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። አምስት መከራከርያ ነጥቦችን ላንሳ።
አንደኛ ማንነት ሰው ሰራሽ እንደመሆኑ ቋሚ አይደልም። የታሪካዊ ግስጋሴ (historical progress)  በህዝቦች ዉህደት እና የባህል ዉርስ ይገለፃል። ለምሳሌ ብሔር የአዝጋሚ እድገት (evolution)  ዉጤት ነው። ለረጅም ጊዜ በሚዘልቅ  ጥልቅ የህዝቦች መስተጋብር ምክንያት ቤተሰብ ወደ ጎሳ፣ ጎሳም ወደ ዘዉግ፣ ዘዉግም ወደ ብሔር ያድጋል። ቁሳዊ ልማት እና የባህል ሽግግርም እንዲሁ ወሳኝ ነው። በነዲክት አንደርሰን ‘ብሔር ምናባዊ ማሕበረሰብ’ ነው ሲል ስሪትነቱን ለመጠቆም ነው።  ዛሬ ጥቁር፣ ነጭ፣ ምስራቃዊ (oriental) ወዘተ የምንላቸው የሰው ዘር ፈርጆች እንኳ ከሁለት ሚሊንየም በፊት አልበሩም። በምዕራብ አዉሮፓም ጎሳ፣ ዘውግ እና ነገድ  ታሪካዊ ሂደቱን ተከትሎ ወደ ብሔር አድጓል ።  ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እና ጣልያን የመሳሰሉት ሃገራት የግዛት ወሰናቸውን ከብሔር ክልል ጋር በማጣጣም ወጥ መንግስታዊ  አስተዳደር ወይም ብሔረ-መንግስት (nation-state) መስርተዋል።  የፈረንሳይ ብሔር ጉዓል፣ ሮማን፣ ብርቶን፣ ተኦቶን የመሳሰሉ ነገዶችን እና ጎሳዎችን በሂደት አዋህዶ የተፈጠረ ነው። የጣልያን ብሄርም እንዲሁ ሮማን፣ ኢትራስካን፣ ተኦቶን፣ ግሪክ እና አረብ ዘር ያላቸውን ህዝቦች ያዋሐደ ነው። በሌላ በኩል የህዝቦች መስተጋብር ዉስን በሆነባቸው፣ ለረጅም ግዜ ጎልቶ የወጣ ጠንካራ የፖለቲካ ማሕበረሰብ ባልተፈጠረባቸው እና በቁሳዊ ልማት ወደ ሁላ በቀሩ የኤሽያ እና የአፍሪካ ሃገራት ዉስጥ ለቁጥር የሚያታክቱ ጎሳዎች እና ዘውጌ ማህበረሰቦች መኖራቸው ማኅበረሰባዊ አዝጋሚ ለዉጥ ከቦታ ቦታ እንደሚለያይ ይጠቁማል። ለምሳሌ በኢንዶነዢያ ከ700 የሚበልጡ እንዲሁም በናይጄሪያ ከ500 የሚልቁ የዘውጌ ቡድኖች ይገኛሉ። የነዚህ ህዝቦች መስተጋብር ፍጥነት እና ዉጤት የሚወስነው በትምሀርት፣ በባህል ና በፖለቲካው ዘርፍ  በሚሰሩ የጋራ እሴት ግንባታ ስራዎች ይሆናል። የሀገራችንም ዕጣ ፈንታ ከዚህ የተለየ አይደለም።
ሁለተኛ ለአክራሪ ዘውጌዎች የመገንጠል መብት (አንቅፅ 39)  ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ነው፣ ግዜውን ጠብቆ እንደሚበትንነን አልታያቸውም፣ አልያም ብንበተን ግድ አይላቸውም። ጎርፍ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንዲሉ፣ ከኛ ቀድመው በሃሳቡ ላይ ሙክረት (experiment) ያደረጉ ከስህተታቸው ለመማር እንኳ ዕድል ሳያገኙ ጠፍተዋል። ፕሬዚደንት ጆሲፕ ቲቶ በ1974 (እአአ) የብሔሮች እና ብሔረሰቦች የመገንጠል መብት በሕገ-መንግስት እንዲረጋገጥ ሲያደርግ ሃገሩ ዩጎዝላቪያ ከ17 ዓመታት ቡሁላ እንደምትበተን አልተረጠረም። የሶቭየት መሪዎችም በ1977 (እአአ) ባሻሻሉት ህገ-መንግስት የህብረቱ አባላት ባሻቸው ግዜ የመገንጠል መብት እንዳላቸው ሲዉጁ ከ14 ዓመታት ቡሁላ ግዛታቸው ከ15 ቦታ እንደሚፈረካከስ አልታያቸውም። ሃሳቡ እነሱን እንዳጠፋቸው እያወቅን ራሳችንን ለማዳን ሌላ አማራጭ መንገድ አለመከተላችን ግራ ያጋባል (የኛ ህገ-መንግስት ሲጸድቅ ከዩጎዝላቪያ እና ሶቭየት ህብረት ፍርስራሽ አዳዲስ ሃገራት እየተመሰረቱ እንደነበር ልብ ይሏል)። ሌላው አስገራሚው እና ከንካኙ ነገር ደግሞ ከ80 በላይ የዘውጌ  ቡድኖች በሚኖሩባት ሀገር የመገንጠል ሀገ-መንግስታዊ መብት  የተረቀቀው ሁለት ቡድኖች ብቻ በሚወክሉት ህወሓት እና ኦነግ ነበር። ብዙሃኑ ድምፅ አልበረውም። ዳግም ዕድል ሊሰጠው ይገባል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርሻ እንዳለው በተግባር መገለፅ አለበት።
ሶስተኛ አክራሪ የዘውጌ ፖለቲካ ለዉህድ፣ ንዑስ እና ተደራቢ ማንነት ቦታ የለውም፤ ትኩረቱ ነጠላ፣ ጠባብ እና ‘ንፁህ’ ማንነት ላይ ነው። ከዘውግ ባሻግር ሕልዉና ያላቸውን እንደ አዲስ አበባዉያን ያሉ ኮስሞፖሊታን ማህበረሰቦች እና የተውልድ ሃረጋቸውን ከተለያዩ የዘውጌ ቡድኖች የሚስቡ ግለሰቦችን ፍላጎትና ምርጫ አያስተናግድም።  አንድ ተጨባጭ ምሳሌ ላንሳ፣ በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚኖር ራያ የሚባል ማህበረሰብ አለ። በታሪክ አጋጣሚ በትግራይ እና አማራ ክልሎች ለሁለት ተከፍሎ ይኖራል። በቅርቡ የራያን ሕዝብ ወደ አንድ አስተዳደራዊ መዋቅር ለማምጣት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ሁለት ኃይሎች ፅንፍ ይዘው ቆመዋል። ህወሓት “ራያ የሚባል ማንነት የለም፣ ራያ ትግሬ ነው” ሲል፣ አብን (አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ) ደግሞ “ራያ የሚባል ማንነት የለም፤ ራያ አማራ ነው” ብሎ ሌላ ጫፍ ይዟል። የራያን ኦሮሞነትም የበለጠ ለማጉላት የሚጥሩ የዘዉጌ ፖለቲከኞች አሉ። እዉነታው ግን ራያ ከአማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አፋር እና አገው የሚወለድ ሕብራዊ ዉህድ ማንነት ያለው ሕዝብ ነው። ከማህበረሰቡ  ባህላዊና ታሪካዊ መስተጋብር አንፃር ለራያ የሚስማማው ዜግነትን መሰረት ያደርገ ብሄርተኝነት ነው። የማንነት ሁሉ መለክያ የግድ ዘውግ ብቻ መሆን ስለሌለበት የራያ ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ባነሰ ማንነት ራሱን ይግለፅ ከተባለ ራያ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። ከዚህ ዉጭ በአንድ ዘውግ ወይም ‘ብሔር’ ስም ይጠራ  ቢባል የዘውግ ሃረጋቸውን  ከሌላ አቅጣጫ የሚስቡ የማህበረስቡን ክፍሎች ማግለል ይሆናል።  የዚህ ክትለት (implication) ግልፅ ነው፡ ራያን የመሰሉ ዉህድ ኢትዮጵያዉያን በማንነት ፖለቲካ ባግባቡ አይስተናገዱም፣ ይጠባቸዋል።
አራተኛ አክራሪ የዘውጌ ፖለቲካ ሃገራዊ ብሔርተኝነትን እንደመዳረሻ አያይም። ይባስ ብሎም የትግል ኢላማው ለአንድነት በሚሰሩ የፖለቲካ ኃይሎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የኦሮሞ፣ የትግራይ እና የአማራ ዘውጌዎች  ኢትዮጵያዊነትን ማዕከል አድርገው በተነሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ የሚያደርጉት አፍርሽ ቅስቀሳ የዚሁ ችግር ማሳያ ነው። በመሰረቱ ሃገራዊ ብሄርተኝነት እና የዘውጌ (ethnic) ማንነት አይቃረኑም። በብልሃት ከተያዙ ተመጋጋቢ ሆነው መኖር ይችላሉ። ዮሩባው ናይጄሪያዊነቱን፣ ፑንጃቢው ህንዳዊነቱን እንዳልጣለ ሁሉ ኦሮሞውም ሆነ አማራው ኢትዮጵያዊነቱን እና ንዑስ ማንነቱን አስማምቶ  መኖር ይቻለዋል። መሬት ላይ ያለው እውነታም ይህንኑ እንድናደርግ ያስገድደናል። ከፖለቲካው ዲስኩር ባሻገር፣ በተግባር ሀልዉናችን የተሳሰረ ነው።
በመጨረሻም የማንነት ፖለቲካ ‘የኔ’ ከሚለው ቡድን ያልተገደበ እሽታ ይጠብቃል። ልዩነትንና   የሃሳብ ፍጭትን አያስተናግድም። ይህ አጉል ተስፋ ከሰዋዊና ማህበረሰባዊ ተፈጥሯችን ጋር አይገጥምም።  የሰው ልጅ ከራሱ ጋር እንኳ  ፍፁም አንድነት መፍጠር አይችልም። የ10 ደቂቃ ጥሞና  (meditation) ለማድረግ የተቀመጠን ይህን እዉነታ በተግባር እናውቀዋለን። እንደ ነፋስ የሚበተነውን ሃሳባችንን ሰብስበን ማቆም ፈታኝ ነው። ይህ እንግዲህ ከራስ ጋር ለመግባባት የሚደረግ ትግል ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ ጃቆስ ላካን the mirror stage በሚለው የሰውን ልጅ እድገት  ባብራራበት ንደፈ ሐሳቡ ዉስጣዊ ስሜት እና ዉጫዊ ስሌት ብዙውን ግዜ አይጣጣሙም፣ እንዲያ ሲሆን ጭንቀት ይፈጥራል ይላል። ለምሳሌ ዘውጌ-ተኮር የፖለቲካ እንቅስቃሴ ግለሰቡ ራሱን የሚያይበት ማህበራዊ መስታዉት ነው። እንደ አባል ተስፋውን እና ምኞቱን ይገልፅበታል፣ ያነብበታል። እንደግለሰብ ደግሞ መስታዉቱ የማያሳይለት ዉስጣዊ ፍላጎት እና ትግል ይኖረዋል። የዉስጡን እና የዉጩን  ሙሉ ለሙሉ  ማገጣጠም የሚቻል አይደለም።  ፖለቲካዊ አንድምታው በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ ከሌሎች ፍፁም አንድነትን መጠበቅ እንደሌለብን ነው። ዘውጌዎች ይህን እዉነታ አይቀበሉም። የነሱን ቋንቋ የሚናገር ሁሉ እንደነሱ እንዲያስብ፣ እንዲሰማው እና እንዲያደር ይጠብቃሉ።
ከዚህ ወዴት? 
ዘግይቶም ቢሆን ኢህአዴግ ሃገራዊ ማንነትን ችላ ማለት የሚያስከትለው አደጋ ተገልጦለት ነበር። በስልጣን ላይ የነበሩት ኃይሎች ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ ራዕይ በምትባል የንድፈ-ሃሳብ መፅሄታቸው በኢትዮጵያዊነት ተኮትኩቶ ያላደገ ወጣት የዘውጌ ወጀብ ቀስቅሶ ሊያጠፋቸው አንደደረሰ ተናዘዋል። የፈሩት አልቀረም፣ ድምፅ አልባው አብዮት ገፍቶ ዳር ጥሏቸዋል። ዉጤቱም ተስፋና ስጋት ወልዷል። በደቡብ ማቆምያ የሌለው የክልልነት ጥያቄ፣ በሰሜን የምናየው እልህና ፍጥጫ፣ በምስራቅ በኩል ሕይወት የቀጠፈው የወሰን ግፍያ፣ በምዕራብ የሚርመሰመሰው ደም አፍሳሽ አማጺ፣ በመሃል የሚራገበው ፅንፈኛ ዘውጌነት ወዘተ ከለት ወደለት የለውጥ ተስፋችን በስጋት እንዲደበዝዝ አድርጎታል። በግዜ ካተገራ በየአቅጣጫው የጦዘው ግለኝነት ሃገር ሊያፈርስ ይችላል።
ከዚህ ስጋት በመነሳት  ይጠቅሙ ይሆናል ያልኳቸውን ሶስት ነጥቦች አንስቼ ሃሳቤን ላጠቃል። አንደኛ በኔ እይታ ለኛ የሚሻለን በመድብለ-ዘውጌ ዴሞክራሲ (multi-ethnic democracy) ማዕቀፍ ሀገራዊ ብሄርተኝነትን ኮትኩቶ ማሳደግ ነው። በህንድ እና መሰል ሃገራት ተተግብሮ እንዳየነው መድብለ-ዘውጌ ዴሞክራሲ ሃገራዊ እና የዘውጌ ማንነቶችን ሚዛን ጠብቆ የመያዝ ብቃት አለው። የግለሰብ እና የቡድን መብቶችን አጣጥሞ ያስተናግዳል። መርሆው ተጓዳኝ እና ተደራቢ ማንነት ያላቸውን የተለያዩ የማህበረሰቡ አባላት በእኩል ዜግነት የሚያስተናግድ የፖለቲካ ስርዓት እዉን ማድረግ ነው። አካታችነቱ እንዳለ ሆኖ ስኬታማ መድብለ-ዘውጌ ዴሞክራሲ ለጋራ እሴቶች ግንባታ እና ጥበቃ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። በስምምነት የሚፈጠር የጋራ እሴት ማዕከላዊ ይሆንና የዳርቻውን ማንነት  በአዝጋሚ ስበት ያስገባል። በሂደቱም በማንነት ላይ ሳይሆን መርህ ላይ የቆመ፣ የግለሰብና  የቡድን መብቶችን አማዝኖ የሚያስተናግድ  የዜግነት ፖለቲካ እዉን ይሆናል።
ሁለተኛ በዜግነት ፖለቲካ የተቃኘ መድብለ-ዘውጌ ዴሞክራሲ ለመገንባት ህገ-መንግስቱን ማሻሻል ቁርጠኝነት የሚጠይቅ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። ከማሻሻያው ሥራ በፊት ግን ሕዝባዊ ምክክር ያስፈልጋል። ልሂቃኑ  የሃሳብ መሪነቱን ድርሻ ይዘው አወዛጋቢ የሆኑት ጉዳዮች በስፋት ዉይይት ቢደረግባቸው ህዝቡ በእዉቀት ተመስርቶ ለማሻሻያው ድጋፍም ሆነ ተቃዉሞ ማድረግ ይችላል። ሁሉም ባለድርሻ አካልት (ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን ወዘተ) ቁልፍ በሆኑ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ ባደባባይ ሲሟገቱ  አስተፃምሮው (the synthesis) ለዉሳኔ የሚጠቅም አሳማኝና አስተማማኝ እዉቀት ይፈጥራል። የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ለማስጠበቅ በእዉቀት ላይ ተመርኩዞ የሚሰራ ፖለቲካ አማራጭ የለውም።
በመጨረሻም በፖለቲካ መግለጫችን፣ ትንታኔችንና ዲስኩራችን የምንጠቀማቸው ቃላት እና ፅንሰ-ሃሳቦች ግልፅና አግባቢ መሆን ይኖርባቸዋል። ዓለም በቃል ይፈጠራል ነውና በትርጉም ካልተግባባን በተግባር መተላለፋችን የግድ ነው። ለምሳሌ ከላይ እንደጠቀስኩት ህገ-መንግስቱ ‘ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ’ ብሎ የሚጠራቸው ስብስቦች በተጨባጭ እነማን እንደሆኑ ግልፅ አይደልም። ፅንሰ-ሃሳቡ ከነፍቹ ከዉጭ ተቀድቶ የገባ በመሆኑ ከኛ እውነታ ጋር አልገጠመም። ሌላም የተለመደና ችግር ያለበት አባባል አለ። ከተለያየ የዘውጌ ቡድኖች (ethnic groups) ብንወለድም ኢትዮጵያውያን ዘራችን አንድ ነው፣ ጥቁሮች ነን።  ስለዚህ በተለምዶ እንደሚባለው በሽታችን  ዘረኝነት ሳይሆን አክራሪ ዘውጌነት (ethnic extremism) ነው።  ችግራችንን በትክክለኛ ስሙ  መጥራት አንድ እርምጃ ወደ መፍትሔው ስለሚያቀርበን የፖለቲካ እና የፖሊሲ  ውይይታችን ለጠራ ሃሳብና አመንክዮ ትኩረት መስጠት አለበት።

Sunday, December 16, 2018

ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እና የሠራተኛው መደብ አምባገነንነት ፅንስና በኢትዮጵያ ውስጥ ያስከተለው ሰቆቃ በነገሰ ጉተማ




                                                                                     መግቢያ
The TPLF.ይህ ፅሁፍ  ስለአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ምንነትና  አመጣጥ እንዲሁም  ባለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕልውናና እድገት ላይ ያሳደረውን  የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የባህላዊ  ተጽእኖ  ይዳስሳል።  በማጠቃለያውም ተቃዋሚ  ፓርቲዎችና ዴሞክራሲያዊ  ድርጅቶች  ያለባቸውን  ታሪካዊ  ኃላፊነት በአንድነት እንዲወጡ ይጠይቃል። ጠለቅ ያለ ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉ በማጣቀሻዎች ሥር ያሰፈርኳቸውን  መፃሕፍትና ድረገጾች መመርመር ጠቃሚ ነው።
ካርል ማርክስ፣ ቭላድሚር ሌኒን እና የ”ሠራተኛው መደብ (ፕሮሌታሪያት)” አምባገነናዊ መንግሥት   አመሠራረት
በ1917 ዓ. ም.  እ.አ.አ. በቭላድሚር ሌኒን የሚመራው የሩሲያ ኮሚኒስት ፓርቲ (ቦልሼቪኮች) በጥቅምቱ አብዮት (ኦክቶበር ሬቮሉሽን) የሩሲያውን ዳግማዊ ኒኮላስን መንግሥት ከሥልጣን በማውረድ “የሠራተኛውን (ፕሮሌታርያት) መንግሥት” መሠረተ። ሶቪየት ሕብረትም ተፈጠረች። በጊዘው በቦልሼቪኮች የተመራው አብዮት“ሠራተኛውን መደብ ወይም ፕሮሌታሪያቱን” ሥልጣን ላይ ቢያመጣም የሩስያው ሠራተኛ (ፕሮሌታርያት)ብዛት፣ ጥንካሬና የንቃት ጥልቀት እንደሌሎቹ ካፒታሊዝም የጎለመሰበት የአውሮፓ ኡገሮች ሠራተኞች ስላልነበረ በሌኒን የሚመራው የሩሲያ ኮሚኒስት ፓርቲ  የሠራተኛው መደብ ፊታውራሪ (Vanguard of the proletariat) ሆኖ የሠራተኛውን ጥቅም እንዲያስጠብቅ ሞግዚት ሆኖ ራሱን ሾመ። ምንም እንኳን በ1840ዎቹ የሠራተኛውን አምባገነናዊነት ፅንሰ-ሀሳብ የቋጨው ካርል ማርክስ፣ ማንኛውም በሥልጣን ላይ ያለ መንግሥት አምባገነን ስለሚሆን ፕሮሌታርያቱም ሥልጣን ከያዘ የሠራተኛው አምባገነንነት (Proletariat Dictatorship) ይፈጥራል ብሎ ነበር። ሆኖም በሩስያው የጥቅምት 1917 አብዮት አምባገነንነቱ የፕሮሌታርያቱ መደብ መሆኑ ቀርቶ የፊታውራሪው  ሞግዚት የኮሚኒስት ፓርቲው  ተቆናጠጠ። ከአብዮቱ በፊት በኮሙኒስት ፓርቲ ምሥረታ ወቅት አንዱ ውይይት የነበረው ሩሲያ ገና ከፊውዳል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ስላልተላቀቀችና ሩስያ ውስጥ ጠንካራና ብቁ ፕሮሌታርያት ባለመኖሩ ማርክሳዊ ርእዮተአለምን ሙሉ በሙሉ መተግበር አይቻልም በሚለው ሃሳብ ዙርያ ነበር።  የነሌኒን ውሳኔውም በሩሲያ ውስጥ በቅድሚያ የፕሮሌታሪያቱን አምባገነናዊ ሥርዓት በመመሥረት አብዮቱ በሁለት ደረጃዎች ተካሂዶ  ወደ ኮሚኒዝም መሸጋገር አለበት የሚል መርሆ ተከተሉ። ለዚህም የሚሆን የተለየ ድርጅት መመሥረት እንዳለበትና ይህም ድርጅት “የሠራተኛውና የጭሰኛው አብዮታዊ  ዴሞክራሲያዊ አምባገነንነት” እንዲሆን ተደነገገ። በዚህ ፅንሰ ሃሳብ፣ ፓርቲው በማዕከላዊ ቁጥጥር የጠነከረ እንዲሆንና አመራሩም በርዕዮተ አለሙ ባመኑ አብዮተኞች ብቻ እንዲሆን ተወሰነ። እነዚህም አብዮተኞች በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ተደራጅተው መዋቅሮች ዘርግተው በገበሬውና በፋብሪካ ሰራተኞች ውስጥ ሰርገው  በመግባት ትግሉን ይመራሉ ብሎ በማሰብ ነበር። ይህም ሥርዓት የሠራተኛውን (ፕሮሌታሪያቱን) የሥልጣን በላይነት አስጠብቆ ወደኮሚኒስት ሥርዓት ለመሸጋገር ያዘጋጀዋል ተብሎ ታምኖበት ነበር። ሌኒንና የኮሚኒስት ፓርቲው ጨቅላው የሠራተኛው መደብ በተደራጁ የቀድሞው መንግሥትና ፀረ-አብዮተኞች (አድሃርያን) በቀላሉ ሊገለበጥ ይችላል የሚል ፍርሃት ነበራቸው።
ከምሥረታውም ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ዴሞክራሲን ለሁሉም ሕብረተሰብ ያለአድሎ ለመተግበር ሳይሆን በሥልጣን ላይ ላለው ድርጅት አምባገነናዊ አገዛዝን ለማመቻቸት ነው። በተጨማሪም በፓርቲው ውስጥም ሆነ በፓርቲው ሥር ባሉ ድርጅቶች ውስጥ ነጻ የሆነና የተለያዩ ወይም የሚቃረኗቸው ሐሳቦች መወያየት ፓርቲውን ይከፋፍለዋል የሚል እምነት ስለነበረ የፓርቲውን የበላይነት ለመጠበቅ ሲባል ተቃራኒ ሃሳቦችንና ተቃዋሚ አንጃዎችን አይፈቅዱም።
በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት(አምባገነንነት) ሥር የፖሊቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሚሊታሪ መዋቅሮች ተጠያቂነታቸው ለገዥው ፓርቲ ወይም መሪ ነው። በዚህ ሥርዓት ውስጥ የገዢ ፓርቲው ወይም መሪው እነዚህን መዋቅሮች የራሱን አምባገነንነት እና ህልውና ለማረጋገጥ እንደፈቀደው የማዘዝና በተቃወሙትም ላይ ሽብር መፍጠር  እንደተገቢና እንደመብቱ ይቆጥረዋል። ሌሎችንም በሥሩ የፈጠራቸውን መዋቅሮች እንደዚሁ ርእዮተ ዓለሙንና የፖለቲካ መስመሩን ለማስከበርና ተቃዋሚዎችን ለመጨቆን ይጠቀምባቸዋል። በእውነተኛ ዴሞክራሲ ላይ የተመሰረተ ሥርዓት የህዝቡን ሰብዓዊ መብቶች ልዑላዊነት ሲያረጋግጥ፣ የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ያለምንም ተፅዕኖ ሃሳብን መግለፅን፣ በፈለጉበት እንዲኖሩ፣ ተወካዮቻቸውን ያለመንግሥት ተፅዕኖ እንዲመርጡ ሲያከብርና ሲጠብቅ በማዕከላዊነት ላይ የተመሠረተው “ዴሞክራሲ” ደግሞ የገዢው መንግሥት ፍፁማዊ አገዛዝ ያስከብራል።
ቀዝቃዛው ጦርነት፣ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እና  የቅኝ ሐገራት ነፃነት እንቅስቃሴ 
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድምደማ በኋላ በሶቪየት ሕብረት የሚመሩ የሶሻሊስት ሐገሮች በአንድ ወገን፤ በአሜሪካ መሪነት የተሰማራው የምዕራቡ የካፒታሊስት ሐገሮች ደግሞ በሌላው ወገን በመሆን እስከ 1990ዎቹ  የቆየ የቀዝቃዛው ጦርነት (cold war)  ያካሄዱ ነበር። በዚህም ጦርነት ጊዜ ሶቪየት ሕብረት የምስራቅ ብሎክ (Eastern Bloc) ወይም የኮሚኒስት ብሎክ የሚባል ቡደን ፈጥረው የዴሞክራቲክ ሶሻሊዝም ንቅናቄዎችን ለማስፋፋትና ኮሚኒዝምን የዓለም ሥርዓት ለማድረግ (ስለዚህም ኢምፔሪያሊዝምን ለማጥፋት)  ራዕያቸውን ሲተገብሩ በአሜሪካ የሚመራው የካፒታሊስት ሐገሮች ቡድን ደግሞ የምዕራብ ብሎክ (Western Bloc) ተብሎ የሶቪዬት መስፋፋት ለመግታት ተሰልፈው ነበር። ሁለቱም ኃያላን ቡድኖች በዚሁ ጊዜ ዘመናዊ የጦር መሳርያ መገንቢያና ማከማቻ፤ የጦር ሰራዊታቸው  ማሰልጠኛና ማጠንከሪያ፤ የፕሮፓጋንዳና የስለላ ጦርነት ማካሄጃ አደረጉት። ሁለቱም ጎኖች ለሚደግፉት ሃገር ወይም ተዋጊ ግንባር ገንዘብ በመስጠትና መሳርያ በማስታጠቅ ጦርነታቸውን በወኪል ተዋጊዎች (Proxy Warriors) ማድረጉን መረጡ።
በዚሁ የቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ብዙዎች በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ የአፍሪካ፣ የእስያና የደቡብ አሜሪካ ሐገሮች የነፃነት ትግል ሲያካሂዱ ርዳታ ያገኙት ከሶቪዬት ሕብረት ነበርና ከነፃነት በኋላ ብዙዎቹም የሶቪየት ሕብረትን ፈለግ በመከተል አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሶሻሊዝም በመገንባት ላይ ተሰማሩ። አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሶሻሊዝም  የፖለቲካ ኃይል በጥቂቶች እጅ አከማችቶ በማዕከላዊነት ላይ የተመሰረተ አምባገነናዊ አገዛዝን አሰፈነ።   እነዚህም ሐገሮች ከአፍሪቃ አንጎላን፣ ዚምባብዌን፣ ሞዛምቢክን፣ ሳኦ ቶሜ ፕሪንሲፕ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ናሚቢያ፣ ጊኒ ቢሳዎና የመሳሰሉትን ሲጨምር፤ ከደቡብ አሜሪካ ኩባ፣ ኒካራጉዋ፣ ግሬናዳና የመሳሰሉት ሆነው፤ ከእስያ ደግሞ ኢንዶቻይና የመሳሰሉት ነበሩ። ቻይናም በኮሚኒስት ፓርቲው በኩል የሯሳን ማኦይስት ሞዴል መሥርታ እነኮሪያ፣ ቬትናም፣ አልባኒያና የመሳሰሉትን ከኋላዋ አስከተለች።
ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትና የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አፈጣጠር የአንድን ድርጅት የበላይነት ለማረጋገጥ ነው።
ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በደርግ ዘመን
ኢትዮጵያ እንደሌሎቹ የአፍሪቃ ሐገሮች በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር ባትወድቅም ብዙ የአውሮፓ መንግሥታት ቅኝ ሊያደርጓት ብዙ ሞክረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጣሊያን ከሐገራችን ተባርሮ የመልሶ ግንባታው ሲጀመር የኢኮኖሚ አርዳታና የመከላከያ ኃሎቿን መገንቢያ ከምዕራብ ሐገሮች ስታገኝ ቆይታ ከ1966 አብዮት በኋላ ሥልጣን የተቆናጠጠው “ጊዜያዊ” ወታደራዊ መንግሥት በማርክሲዝም-ሌኒኒዝም ርዕዮተ ዓለም በመጠመቁ ከምዕራብ ፊቱን ወደሶቪዬት ሕብረት  አዞረ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም የእርዳታና መሳርያ ምንጩ የምስራቁ ብሎክ ሆነ፣ አገዛዙም እንደዚሁ። ውጤቱም ሐገሪቷ በወታደርዊ አምባገነንነትና በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ማጥ ውስጥ ለ17 ዓመታት ማቀቀች። ይህም የ17 ዓመታት አባዜ ሐገሪቷን በሁሉም ዘርፍ አድክሟት ለሕወሐት ሰለባ ዳረጋት። የተገላቢጦሽ ደግሞ የሕወሐት አማካሪ፣ ደጋፊና መሳሪያ አቀባይ የምዕራቡ ብሎክ ሐገሮች፣ በተለይም አሜሪካ ሆነች። ከደደቢት ጀምረው አዲስ አበባ እስከገቡ ድረስ በአሜሪካው የስለላ ድርጅት እንክብካቤነት አድገው  የደቀቀች ኢትዮጵያን ወረሩ ።
አምባገነናዊ ማዕከልነት በሕወሐት-ኢሕአዴግ እጅ እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ እያየን ነው። የሕወሐት-ኢሕአዴግ ስንኩል ሕገመንግሥትም በሕዝብ ፊት “ሕጋዊነትን” እንዲያገኝ ይህንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አምባገነንነት መሥርቶ ላለፉት 27 ዓመታት ሕዝቡን የመከፋፈያና የራሱን ሕይወት ማራዘሚያ አድርጎታል። በነዚህ ዓመታት የሠራተኛውም ሆነ የገበሬው መደብ ሥልጣን መያዝ ቀርቶ ስማቸውም አይጠቀስም። ለሰብዓዊ መብት ታጋዩ ፕሮፈሰር አለማየሁ ገብረማርያም ይህንኑ የሕወሐት አምባገነንነት “… a thugocracy privatelymanaged and operated for theexclusive benefit of bloodthirsty thugtators.” (6) ብሎ ሰይሞታል።
ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት :- የሕወሐት-ኢሕአዴግ ቆርጦ ቀጥል ሥርዓት
የሕወሐት-ኢሕአዴግም መንግሥት የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን አገዛዝ የሚደግፉትን መሾሚያ፣ የሚቃወሙትን  መደፍጠጫ፣ ሕዝቡን በዘርና በጎሳ መከፋፈያ መሳሪያ አድርጎታል። በሥሩም የተፈጠሩት የተለያዩ ድርጅቶች የሕወሐት-ኢሕአዴግ አምባገነናዊነት ምሰሶ ከመሆን ሌላ እውነተኛ ዴሞክራሲን የሚያሳድጉ ተቋሞች መሆን አይችሉም። ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊት ኢ-ዴምክራሲያዊ ስለሆነ የመድብለ ፓርቲንና ሁሉን የሕብረተሰብ ክፍሎች የያዘ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በተግባር አይቀበልም። ሕግ አውጭው፣ ሕግ ተርጓሚውና ሕግ አስፈፃሚው አንድ ሲሆን የሚያገለግለውም በሥልጣን ላይ ያለውን ፓርቲ ነው። ሕጉንም የሕወሐት-ኢሕአዴግ መንግሥት አንዳመቸው ሲለውጠውና አዲስ ሕግም ሲደነግግ ነበር። በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እነዚህ ሦስት አውታሮች አብሮ መሥራት ብቻ ሳይሆን እርስበርስ በመቆጣጠር የአገሪቷን ሕጋዊ ጉዳዮች ያካሂዳሉ። በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ሦስቱም አውታሮች እንደአሻንጉሊት ክሮች የሚስበው የሕወሐት-ኢሕአዴግ መንግሥት ነው። በተጨማሪም የተለያዩ የኢኮኖሚው አውታሮችን፣ ምክር ቤቱን፣ የደህንነት ጥበቃውን፣ የመከላከያ ሰራዊቱን እና የመሳሰሉትን ለራሱና ለደጋፊዎቹ ጥቅም ያውላል።
ዶክተር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ሕልሞች – የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ” በተሰየመው መጽሐፋቸው ውስጥ የኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የፈጠራቸውን (ያስከተላቸውን) ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታም ሆነ ለልማት ብልፅግና አንቅፋት የሆኑትን አሥር ነጥቦችን በትክክል አስፍረዋል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ነጥብ “… የኢህአዴጉ ‘አብዮታዊ ደሞክራሲ’ ከሁሉም በላይ መንግሥትንና የመንግሥት ተቋማትን የአንድ ፓርቲ የግል ሃብት የሚያደርግና የመንግሥት ተቋማት ዋና ሥራቸው መሪዎችን ሥልጣን ላይ ለማቆየትና በሕግ የሚታወቀውን መንግሥትን ተክቶ የሚሠራ መንግሥት መፍጠሩ ነው። የዚህ ሁሉ ችግሮች እናት ሁሉ….. ደግሞ ከኢህአዴግ ‘አብዮታዊ ዴሞክራሲ’ የሚመነጨው የአንድ ፓርቲ የበላይነት (hegemony) ሕልም ነው።”(1)
ሕወሐት ለራሱ አመቻችቶ የፈጠረውን ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊ አምባገነንነት የ1968ቱን ማኒፌስቶ እቅድ ከግብ ለማድረስ እየተጠቀመበት ነው። ኢትዮጵያን በዘር ከከፋፈሏትና የሕዝቡንም አንድነት ካዳከሙት የሕወሀት-ኢሕአዴግ ተግባሮች ጥቂቶቹን ከዚህ በታች ቀርፌ አቅርቤአለሁ።
አንደኛ – ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን በመጠቀም እንደ ደቡብ አፍሪቃው አፓርታይድ ሥርዓት ሕዝቡን በጎሳ፤ በቋንቋ፤ በክልል ከፋፍለው በማዳከም፤ የጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔሮች ግንኙነት ፈጥረው የሐገሪቷን አንድነት አቃወሱት። ይህም ሕወሐት የራሱን ክልል ለማልማትና ሌሎቹ፣ በተለይም አማራውና ኦሮሞው፣ ኦሮሞውና ሱማሌው፣ ደቡቦችም እርስበርስና ከጎረቤቶቻቸው ደም አንዲፋሰሱ በማድረግ ብዙ ችግሮችን ፈጥረዋል። በሕወሐት-ኢሕአዴግ የተፋፋመው የዘር ክፍፍል ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ህመም መሆኑ እንደማይቀር አይጠረጠርም።
ሁለተኛ – የሥርዓቱን የብዝበዛና የሌብነት መርበብ ዘርግተው የሐገሪቷን ሐብት ለግላቸውና ለደጋፊዎቻቸው መበልፀጊያ አድርገው የኢትዮጵያን ሕዝብ በኢኮኖሚያዊ ገደል አፋፍ ተንጠልጥሎ እንዲሰቃይ አደረጉት። ያለገደብ አንዲያድጉና እንዲዘርፉ የተለቀቁት እንደ ሜቴክ፣ ኤፈርት፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽንና የሌሎችም ትላልቅ ኩባንያዎች የዝርፊያ መናኸሪያዎች ሆነው የባለሥልጣናትን፣ የዘመዶቻቸውንና የአጎብዳጆቻቸውን የውስጥና የውጭ ባንኮች አካውንቶች አንዲሞሉና የቅምጥል ኑሮ እንዲኖሩ አድርገዋል።
ሦስተኛ – ከማዕከላዊ መንግሥት ውጭ ለመሥራት የሞከሩ፣ ሥርዓቱን በተቃወሙ፣  አረመኔያዊ ተግባራቸውን ለዓለም ለማጋለጥ የታገሉት ጦማሮችን፣  ዓይን ባወጣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሽብርተኝነት ወንጀል ሰብስበው በየእሥር ቤት ከተቱ፤ ገረፉ፤ ሰለቡ፤ አሰደዱ፤ ገደሉ። ይህንንም ግፍ ሲፈፅሙ በአስቸኳይ ጊዜያዊ አዋጅና በፀረ-ሽብር ሕግ ጥላ ሥር ተደብቀው ነው። የሕወሐት ፀረ ሽብር ሕግ በ1967 ዓ. ም. ከታወጀው የደቡብ አፍሪቃው ፀረ ሽብር ሕግ ጋር ተመሳሳይ ነው። የፕሪቶሪያው ዘረኛ መንግሥት እነዊኒ ማንዴላንና ሌሎችንም አፓርታይድን የሚዋጉ አካሎች በዚህ ሕግ ተጠቅመው ነበር ሲያስሯቸው፣ ሲገርፏቸውና ሲገድሏቸው የነበረው።(2)
አራተኛ – ሕወሐት-ኢሕአዴግ በወታደራዊ ትጥቅ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስና፣ በምክር ርዳታ ሰጥተው ለሥልጣን ያበቋቸውን የምዕራብ ሃገሮችን ለማስደሰት ሲሉ የነፃ ገበያን (free market) ከዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊ አምባገነንነት  ጋር አዳቅለው መላቅጡ የጠፋበት የኢኮኖሚ መዋቅር ፈጠሩ። በኢትዮጵያ ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ከነፃ ገበያ ጋር ለማደባለቅ መሞከር አምባገነኖች ጡንቻ ለማጠንከርና ከላይ በተጠቀሱት የመንግሥት ሞኖፖሊዎች መበዝበዝን መርዳትና  ሌላውን የግል ነጋዴዎችን እንዳይንሰራፉ ለማድረግ ነው። ያልተገደበ ዴሞክራሲያዊ ነፃነት (የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ እንደልብ የመንቀሳቀስና በንግድ ሥራ መሠማራት) በሌለበት ሁኔታ ከራሱ አምባገነናዊ ጥቅም ውጭ የማይፈቅድን ሥርዓት ነፃ ገበያን በተግባር ላይ ሊያውል አይችልም(1,5)።
አምስተኛ – የምርጫ ቦርዱን እንደራሳቸው መሳርያ በመጠቀም የምርጫ ውጤቶችን በማስለወጥ ሲሸነፉ በማጭበርበር አሸናፊ ሆኖ መቅረብ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትን በማሰርና በመግደል እውነተኛና አድልዎ የሌለበት ምርጫ እንዳይካሄድ አድርገዋል። ይህም የማጭበርበሪያ የምርጫ ቦርድ በነሱ ቁጥጥር ሥር ሆኖ  የነሱ ዕድሜ ማርዘሚያ  አንጂ ገለልተኛና አድልዎ የሌለበት ምርጫን ለማስተግበር አልነበረም። በዶክተር መረራ አገላለጽ የምርጫው ቦርድ ለሕወሃት ሥልጣን ላይ መቆያ ከሆኑት ሁለት ምርኩዞች አንዱ ሆኖ ቆይቷል። ሁለተኛው ምርኩዝ የጠመንጃ አፈሙዝ ነው።
ስድስተኛ – በካድሬዎቻቸውና በስለላ መርበቦቻቸው በሰፈርና በቤተሰብ ውስጥ ጠልቀው በመግባትና ሕዝቡን ለረጅም ዘመናት ያስተሳሰረውን የባሕል “ድርና ማግ” በመበጣጠስ፤ የሕዝብን መሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች በመወንጀል ከሥልጣን አውርደው የራሳቸውን ካድሬዎችና ታማኞች በመትከል፤ ሕዝቡ እርስ በርሱ እንዳይተማመንና በጥርጣሬና በፍርሃት እንዲጠላላ አድርገውታል። ይህ ዓይነቱ የከፋፍለህ ግዛ ተንኮልና የራሳቸውን ጎሳ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የባህል ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን በመያዝ የበላይነትን እንዲያገኙ የማድረግና የሌላውን ሕዝብ በነዚሁ አውታሮች የበታች እንዲሆኑ በመጨቆን፣ ቀድሞ የነበረውን የሕብረተሰብ ክፍል በማባረር ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በመተካት ከፍተኛ የህብረተሰባዊ  ምህንድስና (ሶሻል ኢንጂነሪንግ) በማከናወን ላይ ተሰማርተዋል። በዘርና በብሄር ለይቶ ሰውን የበላይነትና የበታችነት  መፍጠር የባርያ ሥርዓት ባሕርይ ነው።
የለውጥ ጭላንጭል
ኢትዮጵያና ሕዝቧ ከ40 ዓመታት በላይ በፈጀ አምባገነናዊ አገዛዝ ሥር ተቆራምተው ብዙ መቶ ሺዎች ሕዝብ ካለቀ በኋላና ያንኑም ያህል በስደት ከተበታተነ በኋላ አሁን የለውጥ ጭላንጭል እየታየ ነው። ይህም የለውጥ ጭላንጭል ሊመጣ የቻለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የረጅም ጊዜ ትግል  በተለይም ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደማይመለስበት ደረጃ (critical juncture) ላይ በመድረሱና ምንም ዓይነት ጊዜያዊ አዋጅም ሆነ የጠመንጃ ጋጋታ ሊያቆመው አለመቻሉ ነው።  ይህም ሕዝባዊ አመጽ የገዢውን ፓርቲ ከመሠረቱ አናግቶት የጠቅላይ ሚንስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝን በ”ፈቃደኝነት” ከሥልጣን  መውረድን አፋጥኖ የዶክተር አብይ አሕመድን  ወደሥልጣን መምጣት ጥርጊያ መንገድ ከፍቷል።
ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አሕመድ ድርጅታቸው ቢወድም ባይወድም ያለፉትን የሕወሐት-ኢሕአዴግን አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የመንግሥት ሽብርተኝነት አምኖ በግልፅ ጥፋቱን በመቀበል ራስን የማነፅና ሥሕተቶችን የማረም ጉዞ ጀምሯል። ይህ ሂደት በራሱ የኢትዮጵያን ሁኔታ ልዩ ያደርገዋል። አንድ  አምባገነናዊ ገዢ ፓርቲ በምንም ዓይነት ሁኔታ ቀጥቅጦ ሲገዛው ለኖረው ሕዝብ እራሱን አጋልጦና ስህተቱን በግልፅ አምኖ ይቅርታ በመጠየቅና ለውጦች ለመተግበር የተነሳበት ሁኔታ በታሪክ ጥቂት ነው።
የክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢደገፍም ከራሱም ፓርቲ ውስጥ ተቃውሞ ደርሶበታል፤ በአደባባይ የግድያና የመፈንቅለ መንግሥት  ሙከራዎች ተደርገውበታል። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህንን ለውጥ ከግቡ ለማድረስ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። እሱና ደጋፊዎቹ ለለውጡ መቆማቸውን በወሰዱት እርምጃዎች አሳይተዋል፤ እያሳዩም ናቸው። በግፍ የታሰሩ ተቃዋሚዎችንና የሚዲያ ሰዎችን ፈተዋል፤ ሰብዓዊ መብትን የጣሱና የኢትዮጵያን ሕዝብ ያሰቃዩትን ሰብስበው በሕግ ተጠያቂ ማድረግ ጀምረዋል፤ የካቢኔና የአመራር ለውጥም እያካሄዱ ነው። ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ድርጅቶች እንዲመለሱና የዴሞክራሲያዊ  ሥርዓት መመሥረቱ ላይ እንዲሳተፉ በሩን ከፍተዋል፤ የሐገሪቷን የመከላከያ ኃይልም ከአንድ ፓርቲ አገዛዝ ለማላቀቅ አየሠሩ ነው፤ በሌብነት ሐገሪቷን ያራቆቱትንም እያሳደዱ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃም ብዙ የሚያረኩ ድርጊቶችን አስመዝግበዋል።  ከ18 ዓመታት በላይ የፈጀውን የኤርትርያና የኢትዮጵያን ፍጥጫ ወደሰላም አድርሰዋል።
በተቃራኒውም ጥቅማቸው የተነካባቸው የገዢው ፓርቲ ተጠቃሚዎችና ደጋፊዎቻቸው አንዲሁም ከሐገሪቷ ውጭ ሆነው ሃገሪቷን ሊበታትኑ የሚፈልጉ ድርጅቶች ለውጡን ለመቀልበስ ሌት ተቀን እየጣሩ ናቸው። ፀረ-አንድነት ወሬዎችን በአስመሳይ ሶሻል ሚድያ በመዝራት፤ ገንዘብና ትጥቅ በመስጠት ሐገሩን በዘርና በቋንቋ ለያይተው ለማጋደል እየሠሩ ናቸው።  የሕወሐት አባላትና ሎሌዎቻቸውም የአብዮታዊ ዴሞክራሲና ሕገመንግስቱ ይከበር እያሉ እያለቀሱም ናቸው። በዚህም ለቅሷቸው ምን ለማለትና ለማድረግ እንደሚፈልጉ ማወቅ አያዳግትም።  ግምገማና ተሃድሶ! እያሉም ደጋግመው የሚጮሁ የሕወሐት ሰዎችም እስከዛሬ ድረስ በዚያው በግምገማና ተሃድሶ ሕዝቡን ሲያታልሉት ኖረው የሃገሪቷን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ሰብዓዊ መብቶችን ተሰምቶ ከማይታወቅበት አሳፋሪ ዝቅጠት ውስጥ ከተውታል። ከመጀመሪያው በተጣመመ መሠረት ላይ የተገነባውን መዋቅር ምንም ዓይነት ግምገማና ተሃድሶ ሊፈውሰው እንደማይችል ለማየት ተስኗቸዋል። እነሱ ግምገማና ተሃድሶ ባደረጉ ቁጥር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ እየባሰበት እንጂ እየቀነሰለት አልሄደም። ለሕወሐት ደላሎችና ካድሬዎች ግምገማ እናድርግ ማለት “ጨቁነናችሁ አላበቃንምና ዘይቤያችንን አድሰን ለበለጠ ብዝበዛ እንድንመለስ ሌላ ዕድል ስጡን” ማለት ይመስላል።
መዘንጋት የሌለብን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ወይም ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አሁንም የሕወሀት-ኢሕአዴግ መንግሥት አምባገነናዊ የአገዛዝ ስልት ሆኖ እንዳለ ነው። የአሁኑም  አምባገነናዊ ሥርዓት በእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መተካትና  ሕገመንግሥቱ ዴሞክራሲን እንዲደግፍ መሻሻል ወይም መለወጥ ይኖርበታል። ስለዚህም ይህን ለውጥ ወደፊት ማራመድና እውነተኛው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲፈጠር ተግቶ መሥራት  የሁላችንም ሃላፊነት ነው።
ይድረስ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ድርጅቶች
ቁጥራችሁ የበዛ አገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲዎች ተደራጅታችሁ እንዲሁም ሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ተሳትፋችሁ የሕወሐት-ኢሕአዴግን መንግሥት ስትጋፈጡት  ቆይታችኋል። ለዚሁምበድርጅትም ሆነ በግለሰብአስከፊ ስቃይ ተቋቁማችሁ ለአገራችሁም ፍቅር ከፍተኛ ዋጋ ከፍላችኋል። በተቃራኒውም ሲታይ ልዩነቶቻችሁ የጠነከረ ድርጅት አንዳትፈጥሩና በሕብረት እንዳትታገሉ እንቅፋት ሆኖባችኋል። ይህም እውነታ ሕዝቡንም በመከፋፈል በጠነከረ አንድነት አንዳይታገል አድርጓል። ይህንንም ድክመት የሕወሐት-ኢሕአዴግ መንግሥት የራሱን ሥልጣን ላይ ማራዘሚያ አድርጎ ተጠቀሞበታል። አሁንም ልዩነታችሁን ወደጎን አስቀምጣችሁ ይህን  የለውጥ ዕድል ተጠቅማችሁ ጠንካራ ድርጅት በመመሥረት ለሐገራችን ዴሞክራሲያዊ  መንገድ መቀየስ ይኖርባችኋል። ይህንም ማድረግ ባትችሉና የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደገና ለጭቆና ቀንበር አሳልፋችሁ ብትሰጡ ውርደቱ የናንተና የናንተ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም ይፋረዳችኋል። በዶክተር አብይና ረዳቶቹ በሩ ተከፍቷል። ለምን ጊዜ ያህል ተከፍቶ እንደሚቆይ የሚወሰነው በእናንተና በኢትዮጵያ  ሕዝብ ነው።  በምንም መንገድ የ97ቱም ሆነ የ2002ም ሆነ የ2007 የምርጫ ቀውሶች መደገም የለባቸውም። ከአሁን ወድያ የምርጫ ሳጥኖች ተስፋ በቆረጠ ሕዝብ “የስድብና የተበላሹ የምርጫ ወረቀቶች”(5)ተሞልተው ማሸነፍ የሌለበት ፓርቲ የሚያሸንፍበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ኢትዮጵያ ወደፊት የመራመድ እንጂ ወደኋላ የመመለስ ምርጫ የላትም።
ማጣቀሻዎች፡
  1. ዶክተር መረራ ጉዲና – የኢትዮጲያታሪክና የሚጋጩ ህልሞች – የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ, እ ኢ አ 2008 እትመት
  2. Nelson Mandela – Long Walk to Freedom
  3. ኤርሚያስ ለገሠ – የመለስ ልቃቂት
  4. በተለያዩ አከባቢዎች ለሚቀሰቀሱግጭቶች ህወሓቶች እና አክቲቪስቶች ተጠያቂ ናቸው! Seyoum Teshome October 27, 2018 – https://ethiothinkthank.com/2018/10/27/the-role-of-tplf-elites-and-activists-in-inciting-ethnic-conflict/
  5. ሀብታሙ አያሌው – ከህወሓት ሰማይ ሥር, 3ኛ እትም
  6. ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም – “The End of Thugtatorship and Rise of the Rule of Law in Ethiopia”. November 19, 2018.  https://ecadforum.com/2018/11/19/the-end-of-thugtatorship-and-rise-of-the-rule-of-law-in-ethiopia/
  7. Daren Acemoglu & James A. Robinson -Why Nations Fail –
  8. https://www.britannica.com/topic/democratic-centralism
  9. http://nazret.com/blog/index.php/2006/12/10/ethiopia_tplf_revolutionary_democracy
  10. https://www.opride.com/2017/12/29/ethiopia-eprdf-ditch-democratic-centralism-avoid-civil-war/
https://yefiyefitun.wordpress.com

Wednesday, November 7, 2018

Mycobacteriosis in fish(By Rodrigo Orrego)










Mycobacteriosis in fish is a disease that is difficult to detect and therefore often underdiagnosed. For the same reason, information about the effects of this disease on the fish farming industry has been limited
The development of two diagnostic tests has led to the discovery of a mycobacterium which causes disease in both cod and salmon and has never been detected in Norway before. Reports submitted to the authorities of mycobacteriosis (tuberculosis) in fish have been sporadic and have only stemmed from aquarium fish or wild fish, not farmed fish. This is probably due to underdiagnosis. Adam Zerihun’s doctoral research has led to the development of two methods of diagnosis based on real-time PCR and immunohistochemistry respectively. The tests are extremely sensitive and have been instrumental in detecting a mycobacterium that has never been found in Norway before. The bacterium was found both in farmed salmon and in burbot and experimental infection showed that Atlantic cod was very susceptible to the bacterium and became diseased. The isolated bacterium was identified as Mycobacterium salmoniphilum.In cod and burbot infected with M. salmoniphilum, Zerihun discovered serious nodules, while only small or no such changes were found in infected Atlantic salmon. The formation of nodules in cod was shown to undergo several phases of development. The identification and characterization of these different stages are important for the appraisal of disease development and in order to estimate the time of infection. Zerihun’s study indicates that the occurrence of the disease in farmed Atlantic salmon and in cod is more widespread than previously thought, both with regard to the range of host and climate variations.Since the formation of nodules is not a typical symptom in salmon infected with M. salmoniphilum, it is highly probable that many cases of tuberculosis in salmon remain undiscovered. Fish that lose weight without there being any apparent disease or specific cause are classified in fish farming as “lost fish”. A mycobacterial infection can be lurking behind various different symptoms, where weight loss is one characteristic.
For this reason, many salmon infected with tuberculosis can be the undetected reason for losses in the industry. The stress that arises when many fish are kept in closely packed surroundings weakens their immune system and allows mycobacteria to reproduce in many individuals. These factors are known to promote the occurrence of mycobacteriosis.DVM Mulualem Adam Zerihun defended his doctoral research on 11th January 2013 at the Norwegian School of Veterinary Science with a thesis entitled: “Mycobacteriosis in marine and freshwater fishes: characterization of the disease and identification of the infectious agents”. Biography: Mulualem Adam Zerihun was born in Ethiopia and qualified as a veterinary surgeon at Humboldt University in Berlin, Germany in 1989. He has worked as a district veterinary surgeon, ranch manager and researcher in Ethiopia and as a researcher at the Norwegian Veterinary Institute in Oslo since 2004, where he was a research fellow from 2006-2010. Contact information: Mulualem Adam Zerihun Tel.: + 47 67 53 92 95 Tel. work: + 47 23 21 64 40 Mobile: + 47 415 09 453 Email: adam.zerihun@vetinst.no Magnhild Jenssen, Information Officer at NVH Tel.: +47 77 66 54 01 Mobile: +47 957 94 830 Email: magnhild.jenssen@nvh.no

Wednesday, September 26, 2018

ከሰሞኑ የከሸፈው የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ሚስጢሮች ( ዳነኤል)


የጠ/ሚ አብይ መንግስትን የመገልበጥ ሙከራ እንቆቅልሽ!

የመንግስት ግልበጣ ውጥን ነበር ከሽፏል! ፥,አሁንም ያልከሸፈው ከግልበጣው ጀርባ ያለው ፓለቲካዊው ቁማር ነው:: ይህም ቀጥሏል::
የመንግስት ግልበጣው መሃንዲስ ህወሃት ሲሆን የሴራው ተባባሪዎቹ አክራሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦነጋውያን(OLF)ና አክቲቪስቶች ናቸው:: 


A). የመንግስት ግልበጣ ጠንሳሾች የጋራ አላማና አንድነት bበአጭሩ:-

1. ህወሃት(TPLF) አፓርታይዳዊ የህዳጣን ሥርዐቱን ለመመለስ፣ ይህ  ደግሞ ካልተሣካ ኢትዮጵያን ለመበታተን

2. የጠ/ሚ አብይና የፕ/ት ለማ መገርሣን  ኢትዮጵያዊ ቀመር በሁለቱም ሃይሎች አለመወደድ

3. አክራሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦነጋውያን(OLF)ና አክቲቪስቶች አንድም ኦሮሚያን የመገንጠል ይህ ካልሆነ የብዝሃን ጎሣ አምባገነን መንግስት (multiethnic government)መመስረት ህልም ለመተግበር

4. የአርበኞች ግንቦት 7 መምጣትና ይህን ተከትሎ በትላልቅ ከተሞች ላይ የታየው የኢትዮጵያዊነት መንፈስ መነቃቃት፣ ማበብና ማንሰራረት ለህወሃትም ይሁን ለአክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች (OLF, TPLF).ምቾት ስለነሳቸውና በነዚሁ ከተሞች ያለው ሕዝብ እንደማይመርጣቸው ማወቃቸው ዋነኛው ምክንያት ነው::

 የመንግስት ግልበጣው ሴራና ዕቅድ!


ሀ). የመንግስት ግልበጣው ቅድመ ዕቅድ (pre-coup d’etas Contingency plan)

በድሬዳዋ፣ ቡራዩ፣  አዋሣና አሰላ የዘር ጭፍጨፋ በማድረግ ሕዝቡ በቁጣ ገንፍሎ የፕሮፓጋንዳቸው ሠለባ ማድረግና ለአመፅ መገፋፋትና የጠሚ አብይን መንግስት ከቁጥጥሩ በላይ የሆነ ክስተትን መቆጣጠር አልቻለም የሚል ግንዛቤን በሕዝብ ውስጥ በማስረፅ ለቀጣይ ዕቅድ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነበር::
ለ). የመንግስት ግልበጣ ድህረ ዕቅድ
(post - coup d’etas Contingency plan)

1. አዲስ አበባ አቀፍ ሰልፍ መጥራትና በሰልፈኞቹ መንገድ  በመዝጋትና ማህበራዊና የንግድ አገልግሎትን ማሰናከል

2. ኢቲቪ*ETV(ና ፋና ሬዲዮ ጣቢያን መቆጣጠር

3. ኦሮሚያ ባህል ማዕከልን፣ ባንክ ፣ ኢንሹራንስ መንግስታዊና የግል የንግድ ተቋማትን በመቆጣጠር፣ በመዝረፍና በማቃጠል የአካባቢውን የኦሮሞ ገበሬን በቁጣ በመቀስቀስ ከተማዋን ማስወረር የትግራይ ተዎላጆችን ንብረት የሆኑትን ህንፃን መዝረፍና ማቃጠል

4. የ"ጎሣ ፌደራሊዝምን" (ethnic federalism)እና የተዎሰኑ ብሔረሰቦችን  ነጥሎ በመፈክር በማውገዝና በመዝለፍ  ሰንደቅ          ዓላማ  በመቀየር "ህገ መንግስቱ ተጣሰ" በሚል ሴራ  ሐገራዊ ድጋፍን ማሰባሰብ
5. "ሥራዓት አልበኝነት በሃገሪቱ ነግሷል" በሚል ሽፋን "ሕዝብን ከእርስ በርስ እልቂት ለመከላከል ፣ለመጠበቅና ወንጀልን                 ለመከላከል" ጦሩ ጣልቃ ገብቷል የሚል በድርጊት የታገዘ ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ከዓለም አቀፋዊ ማህበረሰብ ድጋፍን              ማሰባሰብ
6. ህወሃት በሚስጥር ባሰረጋቸውና በአዲስ አበባ የሚገኙ የደህንነትና የጦር ሃይሉች አማካኝነት የጠሚ አቢይን መንግስት ሁኔታው      ከቁጥጥሩ ውጭ ነው በሚል ዶር አቢይን ከስልጣን ማውረድና የጠቅላይ /ሚኒስተር  የለውጥ ቡድን(team Lemma)ና              አጋሮዎቸን ማፈስና ማሰርና (Replacement of incumbent leaders with another)
7. የገቡ የለውጥ ሃይሎችን ሃገር ጥለው እንዳይወጡ የአየርና የምድር ትራንስፖርት በማገድ በቁጥጥር ስር ማዋል

8. የመንግስት ግልበጣው ውጥን የተነደፈው በግንቦት 7 እንደሆነ በማስመሰል ጦሩም ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ጣልቃ       እንዲገባ ማድረግ የድራማው ክፍል ነበር::

C). የመንግስት ግልበጣው እንዴት ከሸፈ?

የመንግስት ግልበጣው ውጥን ከሰላማዊ ሰልፉ ጥሪ ጋር የተያያዘ ነው:: ሠልፉን የጠራው ይህ የግልበጣ ቡድን ነው:: ውጥኑንም በቅድሚያ የደረሰበት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የደህንነት አታሼ ሲሆን የግልበጣውን ዝግጅት
ለጠ/ሚ አብይ መንግስት በጊዜው አሣወቋል:: ለግልበጣውም መክሸፍ አይነተኛ ሚና ተጫውቷል:: የግልበጣው ጠንሳሾች ታውቀዋል:: የጠ/ሚ አብይን  መንግስት ቀጥተኛ እርምጃ ለጊዜው በነዚህ ሐይሎች ላይ እንዳይወስድ ኤምባሲው ጫና አሳድሯል:: በግልበጣው ጠንሳሾች ላይ የሚወሰድ እርምጃ የሚያስከትለውን ፓለቲካዊና ወታደራዊ አንደምታና መዘዝ የጠ/ሚ አብይን መንግስት መመከት አሁን የማይችል በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ስልት እንዲነድፍ በተለይም በወታደራዊውና በደህንነት ዘርፉ ላይ የፍፁም የበላይነትን አቅም ፈጥኖ እንዲፈጥር መክሯል:: ይህ ምክንያታዊም ይመስላል::

D).ከግልበጣው ጀርባ ያለው ፓለቲካዊው ቁማርና ሚስጥር!

የመንግስት ግልበጣው ውጥንና ዕቅድ  ከሸፈ እንጂ የፓለቲካው ሴራና አሻጥሩ ቀጥሏል:: የሀገራችን እጣ እጅግ ፈታኝና አደገኛ አዙሪት ውስጥ ገብቷል::

የመንግስት ግልበጣው መክሸፍ በሁዋላ ሁለት ዓይነት መንግስት አንድ ሐገርን እያስተዳደረ ነው:: አንደኛው የጠ/ሚ አብይ እና ቡድናቸው ነው:: ሁለተኛው በጃዋር
(team Jewar)፣ እዝቅኤልና በቀለ ገርባና በፀጋዬ አራርሳ አማካሪነት የሚመራውና በህወሃት የሚታገዘው የለሌውና  ቤተ መንግስት ያለው "የቄሮ መንግስት" ነው:: ተከታዩን ማየት ይበጃል::

ሀ). የጠ/ሚ አብይና ቡድናቸው (de jour)

ይህ ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ ያለ ነገር ግን  የኢትዮጵያ 
ብቸኛው ሕልውና ተስፋ ነው:: ይህ ቡድን በህወሃት ሰራሹ ፓርላማ ውስጥ ማህበራዊ መሠረቱን ኦህዴድን (ኦዴፓ) አድርጎ በደህዴንና በብአዴን ድጋፍ የቆመ መንግስት ነው  ነገር ግን ከኢትዮጵያዊያንና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ አለው:: ስለዚህም ይህን መንግስት የሚደግፉት ድርጅቶች አባላት አንዱ የሆነው ህወሃታውያንና የመኖር ህልውናቸው በጎሣ ፌደራሊዝም ታማኝነት ላይ የተገነባ ነው:: ኢትዮጵያውያኑ "የጎሣ ፌደራሊዝም" በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲተካ የሚፈልጉ ናቸው:: የጠ/ሚ አብይና ቡድናቸው በእነዚህ ፍላጎቶች መካከል የሚወዛወዝ ነው:: በመንግስት የስልጣን እርከን ውስጥ እራሱን ለማቆም በአንድ በኩል በህወሃት በሌላ ጎኑ አክራሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ  ኦነጋውያን ድርጅቶች(OLF)ና አክቲቪስቶች ፈተና የሚሰጠውም  በእነዚህ ምክንያት ነው::

ለ). በጃዋር፣ እዝቅኤልና በቀለ ገርባና በተልዕኮ በፀጋዬ አራርሳ አማካሪነት የሚመራ፣ በህወሃት የሚታገዘው የኢሊሊው ሆቴልን ቤተ መንግቱ ያደረገው "የቄሮ መንግስት" (de facto government )

ይህ "የቄሮ መንግስት" መንግስት ያልሆነ ግን እንደ መንግስት የሚሰራና የሚወስን (non-state actor) ነው:: በጠ/ሚ አብይ መንግስት ውስጥ ያሉ ባለስልጣኖችን፣ የፓሊስና ወታደራዊ አዛዦችን በጎሣ ምንነት ሰርጎ ገብቶ የጠ/ሚ አቢይንና ቲም ለማን(team Lemma) ቡድን የሚያዳክም ነው:: ሕዝብ አዋኪ የጥፋት አጀንዳዎችን የሚነድፍም ነው:: በቀጥታም ለነዚህ ሹመኞች ትዕዛዝ እየሰጠ የአዲስ አበባን ወጣቶች በመንግስት ግልበጣ ሰበብ ዴሞክራሲያዊውን ጎራ ለማዳከም እያሣሰረም ነው:: ቡራዮ እንደታየው ግጭቶችን በመፍጠር ጭፍጨፋን የሚተገብርም ነው:: የዚህ ቡድን ድንጋጤ የተከሰተው በአዲስ አበባ በጳጉሜ 4/2010 ዓ.ም ግንቦት 7ን ለመቀበል ናዝሬት፣ አርባምንጭ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ ሸዋና ድሬዳዋ ሕዝቡ በኢትዮጵያዊነት ደምቆና ገዝፎ መውጣት እረፍት ነስቶታል:: በዋነኛ ከተሞች ውስጥ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አብላጫ ድምፅ እንደማያገኝ ስለተረዳ ቢችል የከተሞቹን ጎሣዊ ስብጥር ለማዛነፍ የጎሣ አባላቱን ለማስፈርና ግጭቶችን በመቆስቆስ ነዋሪዎቹን  ለቀው የሚወጡበትን የማፈናቀልና የጭፍጨፋ ዕቅድ የሚነድፍም ነው:: በዚህ ዕቅዱም ደስተኛ የሆኑ የኦህዴድ ባለስልጣናትና አባላትም ይተባበሩታል:: እየተባበሩም ነው:: የቡራዮ ገዳዮችን ትተው ግድያውን የተቃወሙ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ያፍሳሉ:: ይህ ኢ-ፍትሃዊ ብቻ ሣይሆን መዘዝ ያለው ግፍ ና ወንጀል ነው::

E). የጠ/ሚ አብይና ቡድናቸው ብቸኛ ምርጫ!

የመንግስት ግልበጣው ከሽፏል ማለት እንደገና አይጠነሰስም ማለት አይደለም:: ሀገር በሁለት መንግስት አትመራም:: 

የጠ/ሚ አብይና ቡድናቸው የተኩት የኢህአዴግን መንግስት እንጂ በመንግስት ውስጥ ያለውን የህወሃት መንግስት አልነበረም:: አሁንም የጠ/ሚ አቢይና ቡድናቸው የኢህአዴግ መንግስት ይሁኑ እንጂ በመንግስት ውስጥ የተሠራ የአክራሪዎቹ የእነጃዋር 'በመንግስት ውስጥ ያለ መንግስት (Deep State)' አለ:: ይህ ለጠ/ሚ አቢይና ቡድናቸው ይሁን ለሐገራችን ኢትዮጵያ የህልውና ችግር ነው:: ይህ የነጃዋር ቡድን ባለስልጣኖችን እያዘዘና እየተጠቀመ በራሱ ወንጀል የህዝብን ልጆች እያሣፈሰ መንግድታቸውን ሕዝብ እንዲጠላው እያረገ ነው:: ከመደመሩ ማዕቀፍ ውስጥ በአስቸኳይ ተቀንሰው ለፍርድ መቅረብና በOMN የሚሰጡትን አፍራሽ ቅስቀሳ ማቆም አለባቸው:: ህወሃት ቆሰለ እንጂ አልሞተም:: ህወሃትን እያከሙ ያሉት እነዚሁ አክራሪዎች ናቸው:: ለእራት እያሰቧችሁ ነውና ቀድማችሁ ቁርስ አድርጉዋቸው:: ህወሃት ሲያገግምም እናንተውኑ ይበላል::

F). የኢትዮጵያንውያን ብቸኛ ምርጫ!

በመንታ መንገድ ላይ ያለች ሐገራችንን ከመፈረካከስ ለማዳን ያለን ብቸኛ ምርጫ በኢትዮጵያዊነት ከኢትዮጵያውያን ጋር በሕብረት መቆም ነው:: ከዳር ሆነን ከምንተች መሃል ገብተን ለመለወጥ በተለይም ይደረጋል የተባለው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዳይደናቀፍ መስራት አለብን: