"ይህን መፅሃፍ በማንበብ ስለ ልደቱ አያሌው ማንነት ለብዙ አመታት በቅርብ ከሚያውቀው ሰው ለመረዳት በመቻሌ ተደስቻለሁ። መፅሁፉ ስለ ልደቱ የነበሩኝን ጥርጣሬዎች ይበልጥ አረጋግጦልኛል።
አሁን ስለ ልደቱ ያለኝ ግንዛቤ ቀደም ብሎ ቢኖረኝ ኖሮ የኢዴአፓ-መድህን አባል ባልሆንኩ ፣ የአቶ ልደቱና መሰሎቻቸው መጠቀሚያ ባልሆንሁ ነበር።
በመፅሀፉ አንባቢያን ስለ ልደቱ ይበልጥ እንዲያውቁ በማድረጉ አቶ ታምራትን በጣም አመሰግናለሁ።
>>
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ
>>
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ
<<
እንዴት አታምነንም? ቃለ ጉባኤ ሰነድ አይደለም ወይ? ይህንንም አላምንም ካልክ አዚሁ እንፈርምልሃለን። የብዕር ፊርማችንንም አላምንም ካልክ ጣታችንን ቀለም እየነከርን እንፈርምልሃለን ፣ ይህንንም አላምን ካልክ ጣታችንን እያደማን በደማችን እርምልሃለን።
>>
ከመዕሃፉ የተወሰደ
(የቅንጅት አመራሮች ዶ/ር ኃይሉ እና ዶ/ር አድማሱ)
እንዴት አታምነንም? ቃለ ጉባኤ ሰነድ አይደለም ወይ? ይህንንም አላምንም ካልክ አዚሁ እንፈርምልሃለን። የብዕር ፊርማችንንም አላምንም ካልክ ጣታችንን ቀለም እየነከርን እንፈርምልሃለን ፣ ይህንንም አላምን ካልክ ጣታችንን እያደማን በደማችን እርምልሃለን።
>>
ከመዕሃፉ የተወሰደ
(የቅንጅት አመራሮች ዶ/ር ኃይሉ እና ዶ/ር አድማሱ)
--------------------------------------
"ልደቱ አያሌው አይበቃኸም?"
(በታምራት ታረቀኝ)
===================
(በታምራት ታረቀኝ)
===================
በድንገተኛ ስሜት ተስቤ ኢ ኤን ኤን ቲቪ ላይ የሰማሁት የቀድሞ ወዳጄ ቃለ ምልልስ በዝምታ የማይታለፍ ሆኖብኝ የጀመርኩት ጽሁፍ ትውስታ ትውስታን እየቀሰቀሰ ለዚህ ለክፍል ሁለት አድርሶኛል፡፡ ዋና ዋናዎቹን ብቻ በማንሳት በዚሁ ለመቋጨት እሞክራለሁ፡፡
1- እኛ፤ ንግግሩ በሙሉ እኛ ነው፤ እኛ የወል መጠሪያ እንደመሆኑ ለብዙ ነገር ያመቻል፡፡ ስለሆነም ልደቱ እኛ የሚላቸው ኢዴአፓ መድህንን ወክለው የቅንጅት ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የነበሩትን 5 ሰዎች፤ የም/ቤት አባል የነበሩትን 18 ሰዎች ወይንስ ከውህደት በፊት የነበረውን የኢዴአፓ መድህን ሥራ አስፈጻሚና ምክር ቤት አባላት ወይንስ ከውህደት በኋላ ከቅንጅት አፈንግጦ በእሱ ሊቀመንበርነት የቀጠለውን አመራር፡፡ እኛ ሲል ብቻየን አልነበርኩም ማለት ነውና እኛ የሚለው መሸፈኛ መገለጥ ይኖርበታል፡፡ አሁን ደግሞ በዶ/ር ጫኔ እና በእሱ መካከል ክፍፍሉ ለይቶለት ኢዴፓን አፍርሰነዋል ብሎ አውጇል፡፡ እናም ለአስር አመት ሙል እኛ ሲል እነማንን ጨምሮ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡
2- በወቅቱ አቋማችንን ለማስረዳት ሚዲያ አልነበረንም፡፡በምርጫ 97 ወቅት ለአቅመ ፖለቲካ የደረሳችሁ ወገኖች ሁሉ ለአፍታ በአይነ ልቦና መለስ በሉና 1998 ዓ.ም አስታውሱ፡፡ አየቅንጅት አመራሮች እስር ቤት ሆነው ከእስር የተረፉትም እንኳን አደባባይ ወጥተው ሊናገሩ በየቤታቸው ለመኖር ምጥ በሆነበት እና ማንም መልስ የሚሰጠው ባልነበረበት ወቅት በወቅቱ በነበሩት የመንግስት መገናኛ ብዙኃን እንደልቡ ሲጠቀም አልነበረምን፡፡ እኔ እስር ቤት ሆኘ አየውና እሰማው ነበርና ሌላው ቢቀር ሁለት ነገሮች አይረሱኝም፡፡ አንደኛው ዛሬም ድረስ እንደሚያደርገው ራሱን ነጻ አድርጎ እስር ቤት ያነበሩትን አመራሮች ይወነጅል የነበረበት ሁለተኛው በቅርቡ ከእስር የተፈታው ወዳጄ አቶ አንዱዓለም አራጌ መስከረም 11/98 በኢዴአፓ መድህን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተናገረውን ለእሱ በሚፈልገው ሁኔታ ቆርጦ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ያስተላለፉለት ነው፡፡ እዚህ ድረስ መገናኛ ብዙኃንን የተጠቀመ ሰው ዛሬ በወቅቱ አቋማችንን ለማስረዳት ሚዲያ አልነበረንም ሲል መስማት ምን ሊባል እንደሚችል ቸገረኝ፡፡ ጋዜጠኞቹም በበቂ ተዘጋጅተው የሚጠይቁ ባለመሆኑ በየመድረኩ እውነት ትረገጣለች፡፡
3- ወጣት አስጨረስክ የሚሉኝ እኛ ነን እንደውም የታደግነው፤ እኛ እነማን እንደሆኑ የማይታወቅ በመሆኑ እኔ እሱን ብቻ የሚመለከተውን እና የአይን ምስክር የነበርኩበትን ነው የምገልጸው፡፡ ዛሬም ከአስር አመት በኋላ እውነት ተቀብራ የቀረች ይመስል ራስን ነጻ ሌላውን ወንጀለኛ ለማድረግ ከመቸገር የጥፋት ደረጃችን ያንስ ይበዛ እንደሁ እንጂ በዛን ወቅት ከሆነው ማናችንም ነጻ ልንሆን አንችልም፡፡ ስለሆነም በእኔ በኩል ለሆነው ሁሉ የቅርታ እጠይቃለሁ ማለቱ ነበር ሊያስከብር የሚችለው። ይህ ሳይሆን ሲቀርና ዛሬ የተነገረው ትናንት ከሆነው ጋር የማይገናኝ ሲሆን ነገሩን በቅርብ የምናውቅ ሰዎች በስሜት ሳይሆን በእውነት በአሉባልታ ሳሆን በማስረጃ ገልጸን የማሳየት የህሊና ግዴት አለብን፡፡ እናም እነሆ፤
ሀ- የምርጫውን ውጤት ተከትሎ በየፓርቲዎችም በቅንጅትም ውይይት ሲደረግ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻውን ውጤት ካሳወቀ በኋላ ካልተስማማን ምን እናደርጋለን ተብሎ እንደ አንድ አማራጭ በቀረበው ፍርድ ቤት መሄድ አለመሄድ ጉዳይ የኢዴፓ ም/ቤት ሲወያይ ልደቱ ያቀረበው ሀሳብ አስደንጋጭም አጠራጣሪም ነበር፡፡ “ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ለውጦ ኢህአዴግን አሸናፊ ቢያደርገው ፍርድ ቤት ሄደን የተለየ ነገር ስለማናገኝ የተጭበረበረውን የህዝብ ድምጽ ለማስመለስ ህዝብ ለተቃውሞ እንጠራለን፣ ኢህአዴግ በለመደው መንገድ ይህን የህዝብ ተቃውሞ ሰዎችን በመግደል ያከሽፈዋል፣ ከዚህ በኋላ እኛ ይህንኑ አጋልጠን ያገኘነውን ወንበር ይዘን በፓርላማ ትግላችንን እንቀጥላለን ነበር ያለው፡፡” (ይህን አባባሉን ከውህደት በፊት በነበረውና እኔ አባል ባልነበርኩበት የቅንጅት ምክር ቤትም ማቅረቡን ሰምቻለሁ)፡፡ ሁለቱም ቦታ የነበሩ ሰዎች ከጥቂቶች በስተቀር ዛሬም በህይወት አሉ፡፡
ለ- አኩርፎ ከመቅረቱ በፊት የቅንጅት የህዝብ ግንኙነት ሥልጣንኑ በመጠቀም በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድምጽህን አስቀምተን አንቀመጥም የኢትዮጵያ ህዝብ ቅንጅት ለሚያደርግልህ ጥሪ ተዘጋጅተህ ጠብቅ ማለቱን በወቅቱ የእለት ሁኔታን ይከታተል የነበረ ሁሉ የሚያውቀው በድምጽም በመስልም ተቀርጾ ያለ ነገር ነው፡፡ ከሌላ ቦታ ቢጠፋ ከኢቲቪ መደርደሪያ ላይ አይጠፋም ይህ አባባል ህብረተሰቡን የሚያረጋጋ ወይንስ የሚያነሳሳ?
መ- በክፍል አንድ ላይ የገለጽኩት መስከረም 29/ምሽት የፓርላማ መግባት አለመግባትን ጉዳይ ከወሰነው የምክር ቤት ስብሰባ በኋላ በተሰጠ መግለጫ ላይ ህዝቡ የመረጠን ፓርላማ ገብተን ወንበር እንድናሞቅ አይደለም በማለት የተናገረውም ቢሆን የሚያረጋጋ ሳይሆን የሚያናጋ ነው፡፡
ሰ-የቃሊቲው የፌዝ ችሎት የአቃቤ ህግ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በተመለከተበት ግዜ በስመ አቃቤ ህግነት የቀረበው ሽመልስ ከማል የማስረጃ ጭብጥ ያለውን ሲያሰማ ህገ መንግስታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፍረስ አቅደው ህዝቡን ለዚህ ዓላማቸው ለማነሳሳት ያደረጉትን ቅስቀሳ ያሳይልኛል ይልና ቪዲዮው ሲታይ የተባለውን ሲናገር የሚታየው ልደቱ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ችሎቱን የሚከታተለው ታዳሚ እነ ሽመለስ ከማልን እያየ ያጉረመርማል ግማሹም ፈገግ ይላል፡፡ መሳቅ በችሎት ማወክ ያስቀጣል ተብሎ ማስጠንቀቂያ በመሰጡት እንጂ ብዙዎች ከትከት ብለው ይስቁ እንደነበር ሁኔታቸው ይናገር ነበር፡፡ ከዳኞቹ ፊት ላይ ደግሞ የመገረም ስሜት ሲነበብ አጃቢ ፖለሶች ስክሪን ላይ የሚያዩትን ሰው ከመካከላችን ይፈልጋሉ፡፡ታዲያ ችሎቱ ተነስቶ ስንመለስ እንዴት ነው ነገሩ ቪዲዮው ላይ ያየነው ሰው ከመካከላችሁ የለም አልተከሰሰም ማለት ነው ወዘተ እያሉ ይጠይቁን ነበር፡፡
4- ትናንት ኢህአዴግን ደገፋችሁ ተብለን ተጠላን ዛሬ ሁሉም የኢህአዴግ ደጋፊ ሆነ፤ ይህን ስሰማ ለወዳጄ በእጅጉን አዘንኩለት፤ የት ይደርሳል ብለን በጉጉት ስናየው የነበረ ልጅ መሀል መንገድ ላይ አይሆኑ መሆኑ ሲገርም እንዲህ እስከ ማሰብ መድረሱ የሚያሳዝን ነው፡፡ እኔ እስከሚገባኝ ከተሳሳትሁ ለመታረም ግጁ ነኝ ህዝቡ የደገፈው ኢህአዴግንም ዶ/ር አብይንም ሳይሆን የታገለለትን የናፈቀውን የተመኘውን የለውጥ ጅማሮ ነው፡፡ ለውጥ ያለ ሰው ስለማይታሰብ ዶ/ር አብይም ሆኑ ቲም ለማ ድጋፍ ያገኙት የለውጡ ተዋናይ በመሆናቸው ነው፡፡ እነርሱ ወደ ሥልጣን መጥተው ለውጥ ባይታይ የሚገጥማቸው ምስጋና ሳይሆን ተቃውሞ እንደነበረ መረዳት ለልደቱ የሚሳን አይመስለኝም፡፡ ነገሩ ወሎዬ ሲያንጎራጉር አላህ ሲቆጣ ብትር አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም የሚለው ሆኖ እንጂ፡፡
5- ይቅርታ ጠይቀው ከተፈቱ በኋላ፤ ይህንንም ያነሳው በአዎንታዊ መልኩ አይለም፡፡ ይህ ግልጽ የሚሆነው የመፈረማችን ዜና ከፕ/ር ኤፍሬም ጋር በተስማማንበት መሰረት ሳይሆን መለስ በሚፈልገው መንገድ በመገናኛ ብዙኃን ተነግሮ ገና ሳንፈታ አቶ ልደቱ ተሸቀዳድሞ በመገናኛ ብዙኃን ብቅ በማለት እኛንም ይቅርታ ይጠይቁን ማለቱን ስናስታውስ ነው፡፡ አሁን ግዜ ተለውጧልና ፕ/ር ኤፍሬም ወደ ሞት ከመሄዳቸው በፊት እውነቱን ይናገራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ እባካችሁ ጋዜጠኞችም ጠይቁቸው፡፡ በመጨረሻው ሰአት ላይ ተዋቂው የህግ ባለሙያ አቶ ታምሩ ወንድምአገኘሁም ነበሩበት፡፡
6-የአሉባልታ ፖለቲካ ይሄ እውነት ነው፤ ፕ/ር መረራ የቡዳ ፖለቲካ የሚሉት አደረገው እንጂ፡፡ ለአንድ ዓላማ ተሰልፈው፤ በአንድ ህግ ሊገዙ ቃል ተገባብተው፣ እስከ ሞት አብሮ መዝለቅ የሚጠበቅባቸው የአንድ ፓርቲ ሰዎች የሀሳብ የበላይነት ማግኘት ሲያቅትና በመረጃና ማስረጃ መሞገት ዳገት ሲሆን ቀላሉና አቋራጩ መንገድ አሉባልታ ነው፡፡ይህን የተቃውሞውን ጎራ ድክመት በተለይም በመሪነት ቦታ የሚቀመጡትን ሰዎች ከወንበር በላይ ማሳብ አለመቻል የተረዳው ወያኔ አሉባልታ እየፈበረከ፣ የፍረጃ መርዝ እየቀመመ ይረጫል፡፡ በዚህ ወቅት ወንበሩ ላይ ያሉት ሰከን ብለው ለማጣራት ከመሞከር ይልቅ የማይፈልጉትን ሰው ከአጠገባቸው ለማራቅ በቂ ድጋፍ እንዳገኙ ይቆጥሩትና የበለጠ ያራግቡታል፡፡ ከዛም አባራሪና ተባራሪ ብሎም አዲስ ፓርቲ ይፈጠራል፡፡
የሚገርመው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአመራር ቦታ ተቀምጦ አሉባልታና ፍረጃ ያልነካው ቢኖር የታደለ በጣም ጥቂት ሰው ነው፡፡ ዛሬ በሌሎች የተፈረጀ አሉባልታ የተወራበት ሰው ነገ እሱ በተራው ሌሎችን ይፈርጃል አሉባልታ ያስወራል፡፡ ይህ አሌ የማይባል እውነት ሆኖ አጠያያቂውና አስጠያቂው ልደቱ ራሱን ከደሙ ንጹህ አድርጎ ማቅረቡ ነው፡፡ ግዮን ሆቴል አቅራቢያ ከሚገኘውና የእሱ ልዩ ምሽግ ከነበረው(ይህን ያልኩበት ምክንያት አለኝ) ቢሮ እየተፈበረኩ ይወጡ የነበሩ አሉባልታዎችን እየተቀመሙ ይረጩ የነበሩ ፍረጃዎችን አላውቃቸውም እኔን አይመለከቱኝም ይል ይሆን?
የልደቱን ልዩ የሚያደርገው በፊት ለፊትም ሰው ለማጋጨት የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡ ማህተም አላደርግም ብሎ እነ ዶ/ር አለማየሁ አረዳ ሽምግልና ተልከው እነርሱም በነገራቸው አምነው ሊያስረዳ በተገኘበት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ አላምናችሁም አለ፤ ስለምን ቢባል ከምርጫው በፊት ዶ/ር ብርሀኑና ፕ/ር መስፍን ምርጫው ይለፍ እንጂ ሀይሉን እናነሳልሀለን ብለውኝ ነበር ሲል ተናገረ፡፡ ኢ/ር ኃይሉ ከተሰብሳቢው መሀል ነበሩና ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው ወንበሩን ነው የምትፈልገው፤ አትችለውም እንጂ ከቻልከው ዛሬውኑ ውሰደው አሉት፡፡ ያሰበው ነገር አቅጣጫውን ሳተበት፡፡
7-የሚቃወሙን ፖለቲካን ምርጫ 97 የጀመሩ ናቸው፤ ይህን ምን ትሉታላችሁ፤ እኛ የምትለው የወል መጠሪያ መገለጥ ያለባት እዚህ ጋር ነው፡፡በወቅቱ የኢዴአፓ መድህን ም/ቤት ሙሉ ለሙሉ ባይባልም አብዛኛው የእሱ ደጋፊ አልነበረም፡፡የውህዱ ቅንጅት ም/ር ቤት አባል ከነበርነው 18 ሰዎች አስራ ሰባታችን ማህተም አላደርግም በማለቱ ምክንያት ስብሰባ አድርገን በነበረ ግዜ የዘጠኙን ድጋፍ ማግኘት ችሎ ነበር፤ ከላይ በገለጽኩት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ዶ/ር አለማየሁ አረዳ ተነስተው ቃለ ጉባኤ ሰነድ አይደለም ወይ እንዴት አታምነንም፤ በብእር ካለመንህ ጣታችን ቀለም እየነከርን በአሻራችን እንፈርምልህ፤ይህንንም ካላመንህ ጣታችንን እያደማን በደማችን እንፈርምልህ፣ አለ የምትለውን ነገር ሁሉ በአጀንዳ መወያየት እንችላለን ወዘተ ብለውት አሻፈረኝ ሲል ከዘጠኙ ውስጥ የነበሩት ወ/ሮ ላቀች ደገፉ አቶ ጎሹ አውደው( ነብስ ይማር ሁለቱም ሞተዋል) መምህር ወንድ ወሰን ተሾመ (አሁን በዶ/ር ጫኔ በሚመራው ኢዴፓ ውስጥ ናቸው፡፡) በየተራ እየተነሱ ከዚህ በላይ ምን ይፈለጋል ማህተሙን ልታደርግ ይገባል ሲሉት ነበር ከዚህ በላይ አልችልም ብሎ ሹልክ ብሎ ወጥቶ የሄደው፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ፖለቲካን በምርጫ 97 የጀመሩ ናቸው ማለት ነው፡፡ ያሳዝናል አሁንም ጥሩ መካሪ ያገኘ አይመስለኝም፡፡በየቦታው የመናገር ምቹ ሁኔታ ማግኘቱን ዳግም እንደማንሰራራት ቆጥሮት ከሆነ ንግግሩ ሲበዛ ስህተቱ ይጨምራል የሚለውን አባባል ማስታወሱ ሳይበጅ አይቀርም፡፡
“መከበርና መዋረድህ ከቃልህ የተነሳ ነው፤ የሰው መከራው በአንደበቱ ከተናገረው የተነሳ ነው፡፡” መጽኃፈ ሲራክ 5/14 ይጠቅም ከሆነ አንድ ዓላማዊ አባባልም ላክል፡፡ “በዚህ ዓለም ማንም ሰው ለውድቀት የሚያበቃ ዕቅድ የሚያወጣ የለም፤ ትክክለኛ ዕቅድ ባለማውጣታቸው ግን እነዚህ የተባሉት ይሆናሉ፤ ትክክለኛ ዕቅድ አለማውጣት ራስን ለውድቀት ማዘጋጀት
No comments:
Post a Comment