Wednesday, December 30, 2015

ኢትዮጵያ የማን ናት? ከአንተነህ መርዕድ

 

 

"ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው" ( ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ)

"ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም" (ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ)

ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት የብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የልብ ህመም ሆኖ የቆየው የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ዛሬም በኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ጥያቄ ቢኖር የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሆነ በጨለማ ለመግዛት የተነሱት ጣልያንም ሆነ ወያኔ ለአላማቸው ማስፈፀምያ የዚህን ታላቅ ህዝብ ጥያቄ ነበር ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚጠቀሙበት። ከላይ በጥቅስ ያስቀመጥኋቸውን ሃሳቦች የተናገሩት በኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ ትፅዕኖ ፈጣሪና ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከአስራ አራት ዓመት በፊት በሞት የተለዩን ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳን ንግድ ማተምያ ቤት አጠገብ ባለው መኖርያ ቤታቸው ለጦቢያ መጽሄት ቃለ መጠይቅ ልናደርግላቸው አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ጋር ሄደን ነበር። ሜጫና ቱሉማን በመመስረትና ለኦሮሞ መብት በመታገል ኢትዮጵያዊ መፍትሄ እንዲያግኝ በመልፋት የሚታወቁት እኒህ አንጋፋ አባት አመሻሽ እድሜአቸው ላይ ሆነው ያዩት ሁሉ አላስደሰታቸውም።

አክራሪ ፅንፍ የያዙ የኦሮሞ ኤሊቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን መለየትን እንደመፍትሄ በግልፅ በሚሰብኩበትና ለተግባራዊነቱ በሚገፉበት፤ ወያኔም ይህንኑ አጀንዳ አስጨብጦ በሚያራግብበት ፈታኝ ወቅት ነበር የሄድንባቸው። አምቦ አካባቢ ግንደበረት ተወልዶ ከማደጉም በላይ የኦሮሞን ህብረተሰብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጋሽ ሙሉጌታ ከኮሎኔሉ ጋር ያላቸውን መግባባትና መከባበር ስመለከት ተገርሜያለሁ። በርካታ አገራዊና የግል ጥያቄዎችን ያቀረብንላቸው ቢሆንም በቁጣ ስሜት የመለሱት ለኦሮሞ ችግር ከኢትዮጵያ መገንጠል መፍትሄ ይሆናልን? የሚለውን ጥያቄአችንን ነበር። "ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው?" በማለት ነበር ጥያቄአችንን በጥያቄ የመለሱት።

ኦሮሞ የኢትዮጵያ እምብርት ብቻ ሳይሆን ከሰሜን ጫፍ እስከ ትግራይ፣ በደቡብ እስከ ኬንያ፤ በምስራቅ ኦጋዴንን ነክቶ በምዕራብ ሱዳን ድረስ ሲያጣቅስ በመሃል ከአብዣኛው ኢትዮጵያውያን ተዛንቆ፣ ተዋልዶ፣ ተዋህዶ በመኖሩ እድሉ የኢትዮጵያ ባለቤት መሆን እንጅ ጊዜው እንደወለዳቸው ፖለቲከኞች ቁራሽ መሬት ይዞ መወሰን አይደለም የህዝቡ ፍላጎት። ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳም የገለፁት ይህንኑ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት ነበር። ቃለ መጠይቁን ለህትመት አብቅተን ኮሎኔል ዓለሙን ደግመን ስናገኛቸው ያየሁትና የሰማሁት ለብዙ ጊዜ አሳዝኖኛል። የጊዜው የፖለቲካ አራጋቢዎች ትልቅ የመንፈስ ስብራት ፈጥረውባቸው ነበር። "ዛሬ በሽምግልናዬ ቤት ውስጥ ተወስኜ ሞቴን በጸጋ በምጠብቅበት ሰዓት የአገር ጉዳይ ጠልቆ ያልገባቸው ወንድሞቼ በእኔና በቤተሰቤ ያሳደሩብኝ ጫና ቀላል አይደለም። ቀሪ ጊዜዬን በሃዘን እንዳልቋጨው ታገሱኝ" አሉን። እኛም ታገስናቸው።

ዛሬ ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳና አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት የሉም። ጋሽ ሙሉጌታ ሊለየን ትንሽ ሰዓታት ሲቀረው "ለዘመናት ወጣቱ ላይ የነበረኝን ወቀሳ አንስቻለሁ፤ አገሩን የሚታደግ ወጣት በማየቴ ኮርቻለሁ። በሉ ተነሱ ሰልፍ የጀግና ነው፣ ድል የእግዜብሄር ነው" ሲል ተስፋውንና ጥሪውን ገልፆ አልፏል። የኦሮሞ ህዝብና ቀሪው ኢትዮጵያዊ ባንድ ቁሞ ታላቋን ኢትዮጵያን የመገንባቱ ተስፋ እየለመለመ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ባለቤት ለመሆን አገራዊ አጀንዳ ይዞ እየተነሳ ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች (ኤሊቶች) እንደ ኦሮሞ ህዝብ ሰፊ ልቦናና ኢትዮጵያዊ ባለቤትነትን ካላቀፉ ለጠባቡና ለጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ ራሳቸውን ወስነው መነሳት እንደማያዋጣቸው የተረዱ ይመስላል። ከአንጋፋ ፖለቲከኞች ሌንጮ ለታና ጓዶቻቸው፣ ከወጣቶቹም ጁአር ሞሃመድና ሌሎችም ሰሞኑን ያሳዩት ሁሉን አቃፊ (አኮሞዳቲቭ) አቋም ያየ፤ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የኦሮሞን ህብረተሰብ በሚመጥን ደረጃ ለመገኘት መንቀሳቀሳቸውን ወይንም መፈለጋቸውን ይገነዘባል። ያድርግልን። ከሰሞኑ የህዝብ አመፅ በኋላ የአማራውና የኦሮሞው አንድነት ጥሪ በሰፊው ተሰብኳል። አመፁን ተከትሎ የመጣ በረከት ይመስላል (ፈረንጆች ኤ ብሌሲንግ ኢን ዲስጋይዝ እንደሚሉት)። አመፁን ወደ እውነተኛ አንድነት እንዲያድግ ከተፈለገ አጀንዳው ከክልላዊነት ወጥቶ ወደ አገራዊነት መለወጥ አለበት።

ለኢትዮጵያ ህልውናና እድገት የህዝቦቿ መተባበር፤ በተለይም የኦሮሞውና የአማራው በአንድነት መቆም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጠው ለመግዛት የሚያልሙ የውጭ ሆነ የውስጥ ጠላቶች እነዚህን ጉልህ የህዝብ

ክፍሎችን የጥቃታቸው ኢላማ የሚያደርጉት። አድዋ ላይ አባቶቻችን ያንበረከኳትና በዓለም ፊት ያዋረዷት ጣልያን የሽንፈቷ ምክንያት የኢትዮጵያውያን ህብረት መሆኑን ከውድቀቷ ተምራለች። ከአርባ ዓመት በኋላ ቂም ቋጥራ ዳግም ስትመጣ፤ መጀመርያ የተሰማራችው ተባብረው የደቆሷትን አማራና ኦሮሞን በመለያየት ላይ ነው። ብዙ ክፍተት ለጊዜው ብትፈጥርም እንዳልተሳካላት ሌላውን የኦሮሞ የጀግንነት ምሳሌ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ታሪክእንቃኝ። የበጋው መብረቅ የሚባሉት የጀግናው የጄኔራል ጀጋማ ኬሎ አጎት ናቸው። ፊታውራሪ አባዶዮ ዋሚ ገሮ ይባላሉ። አባ ዶዮ የፈረስ ስማቸው ነው። ጣልያን አማራንና ኦሮሞን ለመከፋፈል በሰፊው ሠርቶ ስለነበር፤ ይህ ሰበካ እውነት የመሰላቸው ታላላቅ ሰዎች የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮን ምክርና ይሁንታ ለመሻት ቤታቸው ሄዱ። "አማራ የሚበድለን ስለሆነ ከአካባቢያችን ልናስወጣ አስበናል ምን ይመክሩናል?" የሚል ሃሳብ አቀረቡላቸው። እንግዶቻቸውን አብልተው አጠጥተው፣ በነገሩም አሰላስለው ቆዩና ለእያንዳንዳቸው እፍኝ እፍኝ ሙሉ ሰርገኛ ጤፍ እንዲሰጣቸው አዘዙ። ጤፉም ለእንግዶቹ ተሰጠ። "በሉ ቀዩን ከነጩ ጤፍ ለዩልኝ" አሏቸው። ግራ የተጋቡት እንግዶች "አባ ዶዮ ይሄማ እንዴት ይቻላል?" በማለት እንደማይሆን ነገሯቸው። "ያቀረባችሁልኝ እኮ እንዲህ ያለ ጥያቄ ነው። ከአማራ ያልተጋባ፣ ያልወለደ፣ ያልተዛመደ ማን አለ? እንዝመት ካላችሁ በራሳችን፣ በቤታችን እንጀምር። ይህንን ደግሳ ያበላቻችሁ የልጆቼ እናት አማራ ናት። ልጆቼንና ልጆቿንም፣ እሷንም ጭምር ግደሉ፤ እናንተም በየቤታችሁም ሂዱና የአማራ ደም ያለበትን አጥፉ። ይህ እንዲሆን አይደል የምትጠይቁኝ" አሏቸው። በርግጥም ከአማራ ያልተዛነቀ ኦሮሞ፤ ከኦሮሞ ያልተዋለደ አማራ ጥቂት ነው። ጥፋታቸውን የተረዱት መልዕክተኞች የጣልያንን ተልዕኮ አከሸፉ። በነገራችን ላይ ዶክተር መረራ ጉዲናም አንዳንድ ፅንፈኛ የሆኑትን ፀረ አማራ የሆኑ የኦሮሞ ልሂቃንን "ማታ ቤታቸው አማራ ሚስቶቻቸውን ታቅፈው እያደሩ ቀን ስለእነዚህ ትልልቅ ህዝቦች መለያየት ይሰብካሉ" ሲሉ ከሃያ ዓመት በፊት መተቸታቸውን አስታውሳልሁ።

ታሪኩ በዚህ አያበቃም። የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮ ወንድም የአባ ኬሎ ገሮ ልጅ ጀጋማ ኪሎ ጣልያንን ገና በአስራ አራት አመታቸው ጀምሮ ነው በጥይት እየቆሉ መውጫ መግቢያ አሳጥተው ነፃነታችንን ያጎናጸፉን። የጣልያንን ሴራ ብቻ ሳይሆን ሰላቶን ከነባንዳው አይቀጡ ቅጣት የቀጡት ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ ከአምሳ አምስት ዓመት በኋላ የባንዳ ልጆች የሆኑ የወያኔ መሪዎች በአማራውና በኦሮሞው ልዩነት ፈጥረው ለማፋጀት ሲነሱ አጎታቸው ዘንድ ለምክር እንደሄዱ መልዕክተኞች የህወሃትን መርዝ ይዘው ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ሲያቀነቅኑ ልባቸው በሃዘን ተነክቷል። አዛውንቱ ፖለቲከኛ ቡልቻ ደመቅሳ "ለኦሮሞ መገንጠል ይበጀዋል ወይ?" ብለው ለጠየቋቸው "ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም" ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይገነጠልም ብለው እንደመለሱላቸው ሰምቻለሁ። ዛሬ ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ የ95 ዓመት አዛውንት ናቸው። የኦሮሞ አድባር፣ የኦሮሞ ዋርካ፣ የአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ዋርካ በህይወት እያሉ ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ስንት ጊዜ ተጠቃች? ስንት ጊዜ አፈር ልሳ ተነሳች?

አብዛኞቹ የህወሃት መሪዎች ለጣልያን ያደሩ የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ከገብረመድህን አርዓያ የበለጠ ምስክር አንሻም። Rኡቅ ሳንሄድ የህወሃት ሴራ ባለቤት የመለስ ዜናዊ አያት የጣልያኑ ደጃዝማች አስረስ በርካታ ህዝብ ያስፈጁ አገር የሸጡ ባንዳ መሆናቸውን ሁሉም ያውቀዋል። ታድያ እነመለስና ጓደኞቻቸው ከአባቶቻቸው የተማሩት አገርን መታደግ ሳይሆን ማፍረስ ነው። ጀግናው አፄ ዮሃንስ ከበርካታ የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋር(የትግራይን ጨምሮ) አንግታቸውን የተሰውበትን መሬት ሳይቀር ለሱዳን ሲሰጡ ሃፍረት የማያውቁ ከሃዲ ወንጀለኞች ናቸው። በመሆናቸውም ነው መሃል ኢትዮጵያን አፍኖ ለመግዛት አማራና ኦሮሞን ለመለያየት የባንዳ አባቶቻቸውን ጌቶች ፖሊሲ የተከተሉት። ይህ ተንኮል ከጣልያን የበለጠ ለእነሱ ሰርቷል። ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከሁለቱ ህዝብ ፅንፈኛ የሆኑና ለፍርፋሪ የሚያድሩትን በማግኘታቸው ዙፋናቸው ላይ እስከአሁን ተደላድለዋል።

አማራው በየሄደበት እንደ አውሬ ታድኗል። ዐይኑ እያየ ገደል ላይ ተጥሏል። ይህንን ደግሞ ሃውዜን ላይ በትግራይ ህዝብ ሲፈፅሙት የተካኑ በመሆናቸው በፊልም እየቀረፁ "ኦሮሞው አማራውን እንዲህ አድርጎ ነው የገደለው" ብለው በአደባባይ በማሳየት እስከዛሬ የሠራላቸውን የመከፋፈል ሴራ ውጤታማ አድርጎታል። ተንኮላቸው በሁለት በኩል ስለት እንዳለው ቢላዋ ባንድ በኩል ኦሮሞውን ከአማራ ለመለያየት ሲያገለግላቸው፤ ሌላኛው ስለት ኦነግን የፖለቲካ ሞት እንዲሞትላቸው ማድረጋቸውን የዚህ ተንኮል መሃንዲስ ከሆነው መለስ ዜናዊ ጋር በቅርብ የሠሩትና አጥርተው የሚያውቁት ሊንጮ ለታ ዛሬ በአዛውንት እድሜአቸውና በሰከነ አእምሮአቸው ቢመሰክሩ ደስ ይለናል። ለትናንት የፖለቲካ ዓላማ ባይጠቅምም፤ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ ትምህርት ይሆነዋል።

ኦሮሞው በየቦታው ሲሰደድ፣ ሲገደልና የአገሪቱን እስር ቤቶች ሲያጨናንቅ፤ አድር ባይ ልጆቹ ወያኔ የሰጣቸውን የመቶ ዓመት ታሪክ ሲቆፍሩና ተጠያቂ ሲፈልጉ፣ ዛሬ የሚፈጸመውን ዐይን ያወጣ በደልና ግፍ እነሱም ዐይተው እንዳላዩ፣ ህዝቡም እንዳያይ ብዙ የከፋ ወንጀል ሠርተዋል። ቢዘርፉ የማይጠረቁ የወያኔ መኳንንት አዲስ አበባን ጨርሰው የአካባቢውን ገበሬ ሲያፈናቅሉ "የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ" በሚል ጅል ተመክሮአቸው ህዝቡን አጥንቱ እስኪቀር ትንሽ ፍርፋሪ እያገኙ አስግጠውታል። ዛሬ ፅዋው ሞልቶ ሲፈስና ህዝቡ ከዳር ዳር ሲነሳ በድንገት ባነኑና የህዝብ ደጋፊ ነን ለማለት በአዳራሽ ተሰብስበው ወያኔ ላይ መፎከራቸውን ከኢሳት ሰምተናል። ልጃገረዷ አረገዘች የሚል ሃሜት ሲናፈስ "እስቲ ታገሱ፤ እህል ከሆነ ይጠፋል፣ ሽል ከሆነም ይገፋል" እንዳሉት ኦህዴዶቹ ከልባቸው ከሆነ የምናየው ነው። ጌታቸው ወያኔ ሳይቀድሙት በመቅደም አባዜ የተካነ ነውና ቀበቶአቸውን ጠበቅ ሊያደርጉ ይገባል። የስምንት ዓመት ልጅ በጥይት ከሚደፋ፣ አስከሬን ለወላጅ በሺህ ብር ከሚሸጥ፣ አገርን ቆርሶ ከሚቸበችብ አምባገነን ጋር ከመስራት የከፋ ወንጀል አለ? ርህራሄ የሌለው ህወሃት ለዚህ ድፍረታቸው በመቶ ሺዎች አሳልፈው ከሰጧቸው፣ እስር ቤት ከሚገኙ ወንድሞቻቸው ጋር ለማጎር አይሳሳም። ደርግ መኢሶንን ተጠቅሞበት ደመኛ ጠላቶቹ ከሆኑት ኢህአፓዎች ጋር በአንድ እስርቤትና በአንድ ጉድጓድ እንዳገናኛቸው ሁሉ ወያኔም ይህንኑ እንደሚያደርግ ግልፅ ነው። ኦህዴድ ሆይ! በአገሪቱ በተለይ በኦሮሞው ላይ ለተሠራው ሁሉ ወንጀል ሃላፊነቱን በግልፅ በመውሰድና ከህዝብ ጎን በመቆም ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት ካልታገላችሁ ይህ ሙት ስርዓት ይዟችሁ ይሞታል።

የኦሮሞ ህዝብ ልበ ሰፊ ነው። አስተዋይና አዋቂም ነው። ይህንን ትልቅነቱን ሰሞኑን በሚገባ አሳይቷል። በውስጡ ያሉትን አማሮችና ሌሎችንም እንዲተነኩስ ዘረኞች ቢሰብኩትም በልበ ሰፊነት ሰላማዊ ትግል እያደረጉ ልጆቹ ለሰላምና ለፍቅር ሲሉ ወድቀዋል። አምናም ዘንድሮም የወደቁ ጀግኖች የኢትዮጵያ ሰማዕታት ናቸው። ለጠባብ አላማ አልወደቁም። ይልቅስ ገዳዮቻቸው ወራዳ ታሪክ ፈፅመዋል። የኦሮሞ ህዝብ በትልቅነቱ ልክ አባቶቹ በደማቸው የአቆዩአትን አገር ባለቤት ሆኖ ነፃ ሊያወጣት ከወንድሞቹ ጋር ይሰለፋል እንጂ ፖለቲከኞች በሰፉለት አርቲፊሻልና ጠባብ ዓላማ ራሱን ወደ ትንሽነት አይቀይርም። ለዚያውም የትግራይን ህዝብ የካዱ የባንዳ ልጆች መጠቀምያ አይሆንም። ለኦሮሞ ህዝብ እንኳን ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካ ትጠበዋለች። "ኢትዮጵያ የማን ሁና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው" ያሉት ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ ዛሬ በህይወት ቢኖሩ ምንኛ ተስፋቸው በለመለመ። "ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም" ያሉት ጀግናው ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ እንደልብ መስማት ባዳገታቸው በዚህ የሽምግልና ወቅት አሁን በምልክትም ቢሆን የኦሮሞን ህዝብ እንቅስቃሴ መረዳታቸው አይቀርምና የመጨረሻ ዘመናቸው በሃዘን እንዳይቋጭ መትጋት ያስፈልገናል።

የእኛ ያልሆነን ሶሻሊዝም ለማፅደቅ የብዙ ኢትዮጵያውያን ደም ፈስሶ ስር ሳይሰድ ቀርቷል። የልዩነትና የጎሳ ፖለቲካም አፍላው ያለፈበትና የመሸበት አስተሳሰብ መሆኑን እንደሶሻሊዝሙ ብዙ ከፍለንበት ተምረናል። ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ካለንበት ጨለማ ለመውጣት በጋራ ካልተነሳን ተስፋ የለንም። በተለይም ከአማራውና ከኦሮሞው የወጡ ጽንፈኞች በህዝቡ ስም በመነገድ አምባገነኑና ዘረኛው የውያኔ አገዛዝ እድሜ እንዲኖርው ከማገዝ እንዲቆጠቡ በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል። በዘውግ ፖለቲካ ተጨፍነን እያለ፣ ለከተማ መሬት ስናዝን፣ የአግሪቱ ለም መሬት ለሱዳን እየተሰጠ ነው። በጉርሻ ስንጣላ የህልውናችን መሰረቱ ራትና ምሳችን ሊሄድ ነው። መተማ ላይ የአፄ ዮሃንስን አንገት የቀላ ሰይፍ ድንበሯን አናስነካም ያሉትን ንፁሃን በመቁረጥ ላይ ነው። ሰይፉ ከሁለት አቅጣጫ ተደቅኖብናል። ከሱዳንና ከህወሃት። ሰሞኑን የሱዳኑ መሪ አልበሽር ሰራዊታቸው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲንቀሳቀስ አዝዘዋል። በኢትዮጵያ ምንግስት በኩል ደግሞ ኃይለማርያም ደሳልኝ ኢትዮጵያውያንን ሱዳንን የሚያጠቁ ሽፍቶች ሲሉ በፓርላማው ፊት ወንጅለዋል። ይህም ይህወሃት ሰራዊት ከሱዳን ጋር ተባብሮ ዜጎቹን ለመውጋት መዘጋጀቱን ያመለክታል። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደዚህ ያለ ለህልውናዋ ጠላት የሆነ መንግሥት አጋጥሟት አያውቅም።

ይህን ጽሁፍ በማጠቃለል ላይ እያለሁ ወያኔዎች በቀለ ገርባንና ሌሎችንም እያደኑ ማሰራቸውን ሰማሁ። ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ እጣ መሆኑን ያላወቀ ካለ አንድም የዋህ ነው፣ ያለዚያም የስርዓቱ አገልጋይ ነው። በቀለ ገርባን የመሰለ የተረጋጋ፣ ሰላም ፈላጊና ትልቅ የዓላማ ሰው አገሪቷ እንዳይኖራት ወያኔ ተግቶ መሥራት የጀመረው አሁን አይደለም። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አሰፋ ማሩን፣ ተስፋዬ ታደሰን….ገድሏል፤ የቅንጅት መሪዎችን፣ አንዱዓለም አራጌንና ሺህ የኢትዮጵያ ተስፋዎችን አስሯል። በአራቱም ማዕዘናት ወጣትና ሽማግሌ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል። አገርንና ህዝብን እንደጠላት ኢላማ አድርጎ ከተነሳ ስርዓት በጎ ነገር የመጠበቅ የዋህነት አብሮ የመግደልን ያህል ወንጀል ከሆነበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያውያን ሌት ተቀን መስራት ያለብን በቀለ ገርባንና ተመስገን ደስአለኝን ከመሰሉ ጀግኖች ጎን መቆምና

እነሱን የመሰሉ ሺዎችን ከመካከላችን ማፍራትና መንከባከብ መሆን አለበት። ዳር ቆሞ ሌሎችን በመተቸት የተጠመደው ልሂቃን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ተገቢ ዋጋ እየከፈሉ ባለበት ሰዓት የጥርጣሬና ያለመተማመን ዲስኩሩን ያቁምና የትግሉ አካል ይሁን።

ኢትዮጵያ የቅን ልጆቿ ሁሉ የጋራ ናት!

በሁሉም አቅጣጫ መስዋዕት በሚከፍሉ ልጆቿም በቅርቡ ጨለማው ይገፍላታል!!

በአንድነት የተነሱ ታጋዮቿ ይታደጓታል!!

Amerid2000@gmail.com

Wednesday, October 21, 2015

Report of the Conference on the Future of Eritrea and Ethiopia


October 21, 2015
EROn Sunday October 18, 2015 a successful one-day long conference was held at Georgetown Marriott Hotel, 1221 22nd St NW, Washington, DC 20037. The theme of the conference was on the present and future relationship between Eritrea and Ethiopia and had conflict prevention and resolution threads. The panelists range from former United States diplomats and State Department officials to former government officials of Ethiopia, senior academics, authors, professionals and social and political activists. The conference was organized by Vision Ethiopia, a network of Ethiopian academics and professionals residing in the United States and Japan, in collaboration with the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT).  The number of people who attended the conference was at full hall capacity.   The audience had ample opportunities to ask and express diverse view points on a variety of current and sensitive issues affecting Ethiopia and Eritrea.  The full conference audio and video is available and will be transmitted to the people of Eritrea and Ethiopia very soon.  Although there were four panel sessions scheduled only three sessions were delivered because of lack of time. They all focused on historical, social, cultural and professional dimensions of building and rebuilding trust between the two related people, the role of super powers and regional powers in the Ethio-Eritrea relationship, and the risks and opportunities of establishing fraternal relationship between the Government of Eritrea and the Ethiopian political organizations.

The Master of Ceremonies, W/t. Birtawit Girmay, Manager of  ESAT Washington DC studio, opened the conference at 10:15. She outlined the objectives of the conference and laid out the conduct and procedure of the conference. After clarifying on important issues of housekeeping, W/t Birtawit invited Ato Gizaw Legesse of Vision Ethiopia and ESAT producer to make the formal opening remarks about the purpose, importance and timeously nature of the conference.
The first of the three panel sessions was moderated by Professor Getachew Begashaw. The four panelists were Mr. Tariku Debretsion, Mr. Gashaw Gebre, Dr. Assegid Habtewold, and W/t Lulit Mesfin. They all presented their well researched and documented papers that were well received by the audience. As a prelude to the ensuing two sessions, drawing on their vast experiences of engagements and studies, these four panelists talked on the roles of Ethiopian and Eritrean Community leaders in building people-to-people relationship at different levels, how much the basic principles of peaceful co-existence of nations can be foundations for peace between the two countries and the region as a whole, and how social and professional organizations, including but not limited to churches, mosques, professionals and men and women of the Arts can create useful links and elevate  the relationship to an even higher level.
The second session was moderated by Professor Minga Negash.  The theme of the session was on the roles and interests of foreign powers in the regional peace, security and stability. On the panel were former senior diplomats of the United States, Ambassador Herman Cohen, Former Assistant Secretary of State and Ambassador David Shinn. Their tenure at the State Department coincided with the collapse of central government of Ethiopia and the takeover of Addis Ababa and Asmara by the TPLF/EPRDF and EPLF in 1991, and the 1998-2000 war between Ethiopia and Eritrea. They were joined by the veteran critical scholar of Ethiopia, Professor Emeritus Mesfin Wolde Mariam.  There was a candid discussion about the United States’ policy failure towards Ethiopia and Eritrea. Ambassador Cohen revealed that Eritrea’s relation with the United States is unlikely to change during the term of office of President Obama.
He was also open about what transpired in 1991. He revealed that the crisis in Somalia is a threat to the United States and its policy appears to be driven by a singular concern for security. For Ambassador Cohen Ethiopia must accept the boundary commission’s ruling and start engaging Eritrea on all other matters. He underscored that both governments do not trust one another.  As regards to the lifting of the UN sanctions against Eritrea he informed that it was only the the United States that used its veto power to block the lifting. He also revealed his efforts to engage in second tier diplomacy and organizing expert level discussion between the two countries.
Drawing from his experience as an Ambassador, Dr. Shinn went on straight to the identification of the powers that have interest in the region. He classified them into a two tier countries and acknowledged the United States’ influence must be examined in light of other countries’ interests. For Ambassador Shinn accepting the boundary commission’s ruling was evident and did not spend time on that. He was more cautious about the prospect of peace and urged that more work needs to be done to prevent another cycle of conflict. The European Union, China, and regional powers are also important and noted that much of what happens in Ethiopia is influenced by regional powers.
repo Er


Professor Mesfin was unforgiving in letting his audience know that successive Ethiopia governments, including the current regime, were clients of super powers, and Eritrea is being punished for resisting dominance by the United States. The old Ethiopian ethos of not bending to foreign powers and pride exists only in Eritrea, as manifested by the behavior of the Eritrean government and in contrast to the behavior of the regime in Addis Ababa in relation to foreign powers, Professor Mesfin Woldemariam asserted.
As a peace activist he regretted that the peace proposal he initiated before the collapse of central government in 1991 was not supported by the United States. He highlighted the double standards of the United States, and compared Ethiopia and South Africa’s reconciliation.  He also urged that Ethiopians must take ownership of their own destiny and start building and rebuilding the relationship with Eritrea.  In general, there was a consensus about the successes and failures of U.S diplomacy in the area. And all the three panelists explained the economic incentives that are available from reconciliation and cooperation between the two countries.
Nine participants from the audience presented varieties of questions. Most of them were directed to Ambassador Cohen and Ambassador Shinn. There was no unanswered question that was important. The questions to Professor Mesfin were more focused on seeking his guidance. The session closed with vote of thanks and a call for the continuation this type of productive panel discussion. The session took more time than was originally planned because of the interest shown by the audience. The panel closed with a sense of satisfaction.
The third session started after a brief lunch break. The session was moderated by Professor Messay Kebede and the theme of the discussion was on relations between the Eritrean Government and the Ethiopian opposition forces.  Ambassador Dr. Kassa Kebede, former minister and diplomat of the Ethiopian Government under Dergue, Mr. Erimias Legesse, former deputy Minister of government communication under TPLF/EPRDF, Dr. Mesfin Abdi of the recently formed Oromo Democratic Front and Mr. Neamin Zeleke of the recently merged Patriotic Ginbot 7 were on the panel.
Dr Mesfin Abdi presented a carefully thought out document and indicated that the view expressed in the document is also being adopted as the official position of his party. He outlined a carefully thought out proposal and invited discussion. He emphasized the need to recognize the sovereignty and independence of Eritrea in order to have peace, stability and prosperity in the sub-region.  He further announced that his organization is planning to host a conference shortly, and called upon for participation.
Dr Mesfin was followed by former Ambassador Dr. Kassa Kebede.  Dr.  Kassa started his presentation by making few remarks on Ambassador Cohen’s presentation.  Citing early historical inscriptions he outlined the history of state formation in Ethiopia.  Ethiopians and Eritreans lived together for thousands of years and shared language, culture, religion, and geography until recently. Dr. Kassa Kebede stated that the two countries had defended the region from enemy forces and colonialists in unison. “Of course, Eritrea was under Italian colonialism for fifty years and British Military Administration (BMA) for ten years before the Federation which was abrogated during Emperor Haile Selassie’s regime, “he recalled.
He then moved to answering the questions about the feasibility of good relationships between the government of Eritrea and Ethiopian political parties. He recognized the rights of the Ethiopian opposition forces to do so by declaring that the choice must be left to the organizations themselves.  Throughout his presentation Ambassador Kassa detoured from time to time and intimated a number of important information which surprised/excited the audience. For instance, he confirmed that the relation between Eritrea and the United States might be simply explained by personality clashes between Ambassador Suzan Rice, who is now the Chief National Security Advisor of President Obama and President Isayas Afeworki, and noted that this relation is unlikely to change while President Obama is in office.  The implications of this for Eritrea is that lifting the UN sanction against Eritrea may not be possible.
Dr. Kassa Kebede cited closed door negotiations and backdoor meetings held with leaders of the Eritrean People’s Liberation Front (EPLF) during his time as a top official and Ambassador in under the PDRE/WPE regime. He told the audience that President Isaias Afeworqi has an unbending belief in the existence of a united Ethiopia and that he is a living witness to this belief held by the Eritrean President.
Mr. Ermias Legesse presented the TPLF/EPRDF’s policy towards Eritrea. He explained the differences between what are discussed in EPRDF internal documents and what are published in its ideological magazine, using pennames.  Ethiopia’s policy and party official statements, including Prime Minister Haile Mariam public pronouncements are exact extracts from the party’s ideological magazine which were written by the late Prime Minister Meles Zenawi and Minister Bereket Simon.  According to Ermias, the policy of containment, isolation and undermining the Eritrean government and eventual regime change is the strategy of the government of Ethiopia.
The fourth panelist was Mr. Neamin Zeleke. Although he did not prepare a formal presentation, he made few general remarks about the nature of the government in Ethiopia and provided the rationale for his organization’s   actions. He told the audience that there are thousands of political refugees in Eritrea. He emphasized that Eritrea is the only safe place in the Horn of Africa where Ethiopian refugees can go.  He reported that Patriotic Ginbot 7’s relationship with the government of Eritrea has passed the initial tests of building trust and Eritrea does not interfere in his organization’s internal affairs.
There were a total of eight questions and views from the audience; and some from both sides of the Eritrean political divide. There were some views coming from different angles from the Ethiopian side as well. Some of the views regarding Eritrea include call for democracy in Eritrea and how Ethiopia can be helpful. This view was not well received by Ethiopians in that Ethiopians acknowledge the fact that this must be left for Eritreans. The comments from the Ethiopian side include the reliability of the government of Eritrea in committing itself to the unity of Ethiopia, what Ethiopian political organizations may have to give in order to get Eritrea’s support, and Ethiopia’s right to own the port of Assab.
Mr. Neamin stated unequivocally that his party has no mandate to negotiate on the future of Ethiopia with any government or international body and only an elected and properly constituted future government of Ethiopia would take the matter forward. He, however, said that they see the current relationship, not as a tactical one, but as a groundwork for building confidence, trust, and a springboard to chart a new era of peace, stability prosperity within a framework of a comprehensive and strategic partnership with the state of Eritrea that should include economic, security, and other vital interests such as the question of ports and access to the sea.
The panelists agreed that at present the focus must only be on building trust between The Eritrean government and the Ethiopian opposition forces.
Vote of thanks and concluding remarks were delivered by Dr Assegid Habtewold and the conference was closed at 6:30 pm.
Note: the moderators’ session, scheduled to be the last one, “Quo Vadis? Where are we going to? The un-answered Questions”, was to be presented by Professors Messay Kebede, Minga Negash, and Getachew Begashaw.

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጀርባ

አርበኞች ግንቦት 7
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጀርባ  ከሁለት አመት በፊት በቂ ህዝባዊ ምክርና ውይይት ያልተካሄደበት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባር ላይ ለማዋል የተደረገው ሙከራ በበርካታ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ እንደገጠመውና በየኮሌጁ በተነሱ ተቃውሞዎች ሳቢያ በርካታ ወጣቶች በወያኔ እንደተገደሉ ብዙዎች በእስር እየማቀቁ እንዳሉ ይታወቃል። ግጭቱ የፈጠረው ቀስል ገና ባላገመ ማግስት በአሁኑ ወቅት የህወሃቱ አባይ ጻሀይ በውድም በግድም ፕላኑ “ይተገበራል” ብሎ በዛተው መሰረት ተግባር ላይ ለማዋል ሰሞኑን ሽር ጉድ ተይዟል። 
ከዚህ ማስተር ፕላን በስተጀርባ የተደበቀው የህወሃትና ጀሌዎቹ አላማ በአግባቡ አለመተንተኑ የፕላኑ ተቃዋሚዎች ኦሮሞዎች ብቻ በመሆናቸው ጥያቄው የግዛት ስፋትና ጥበት ወይም ባለቤትነት ጉዳይ መስሎ ይታይ እንጂ ነገሩ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስቆጪና ተቃውሞ ሊያስነሳ የሚገባው ደባ ነው። ከህወሃት/ ወያኔ ማስተር ፕላኑ ጀርባ የመሬት ዝርፊያ እቅድ እንዳለው አርበኞች ግንቦት 7 ከእስከ አሁኑ ተመክሮና ባህሪያቸው በግልጽ ማየት ይቻላል ብሎ ያምናል።
     እስከዛሬ ባለን ተመክሮ ከተማውን በማስፋፋት ስምና መሬት የመንግስት ነው የሚለውን ሰበብ በመጠቀም ድሃ ገበሬዎችን በማፈናቀል የተዘረፈውን መሬት ልብ ማለትና ማስታዎስን ያሻል።
     በሀገራችን ቅጽበታዊ ሚሊየነር የሆኑት የወያኔ ሹማምንት፣ ዘመዶቻቸውና ባለሟሎቻቸው ዋናው የሃብታቸው ምንጪ ድሆችን በማፈናቀል በገፍ እየዘረፉ የሸጡትና የተቆራመጡት መሬት ነው። የአዲስ አበባ መሬት የወያኔ የወርቅ ማእድን ጉድጓድ ከሆነ ቆይቶል። በየከተማው ዙሪያ ያሉ ምስኪን ገበሬዎች የረባ ካሳ እንኮን ስላላገኙ ከግብርና ወጥተው ወደኩሊነትና የቀን ሰራተኝነት ተበታትነው ቤታቸው ፈርሶ ይገኛል።
     የወያኔ መንግስት ይህን ማስተር ፕላን ስራ ላይ ለማዋል የሚስገበገብበት ዋናው ምክንያት የሀገርና ከተማ ልማት ጉዳይ አይደለም። የከተማው መሬት ተዘርፎ በማለቁ ሌላ በገፍ የሚዘረፍ መሬት ለማመቻችት ብቻ ነው። ችግሩ ለምን ፕላን ኖረ፣ አዲስ አበባ በአግባቡ ማደግና መልማት የለባትም የሚል አይደለም። ቁምነገሩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በቅጽበት እያፈናቀለና እየደኸዩና ቤተሰብ እየፈረሰ፤ በጥቂት ህገ ወጥ ባለስልጣናት የሚደረገው ሀፍረት የለሽ ዝርፊያ ነው ችግሩ። በመሆኑም ይህን የዝርፊያ ተግባር ብሄረሰብ ሳንለይ ሁላችንም ልንቃወም ይገባል። ይህ ማስተር ፕላን የህግ የበላይነትና ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ ስራ ላይ በአግባቡ ስራ ላይ መዋል አይችልም። በፕላኑ የተጠቃለለውን ህዝብና አካባቢ ሊጠቅም የማይችል ፕላን ሊሆን የሚችለው የዝርፊያ ፕላን ብቻ ነው።
      የወያኔ መንግስት በሰፈራ ሁኔታ ባካሄደው የከተማ ቦታ ዝርፊያ ነው ዛሬ በየመሸታ ቤቱና በየከተማው ዋና ዋና መዝናኛ ቦታዎች ብር እንዳሻቸው የሚነዙ የወያኔ ቱባ ባለሟሎች  የተፈጠሩት። ወያኔ ሌላው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ዘረኝነት በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን።
     መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን በማር የተላወሰ መርዛማ ፕሮጀክት አጥብቆ እንዲታገል አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
በሀገራችን ጥቂቶች እያረፉ የሚከብሩበት ድሃ ወገኖቻችን ይበልጥ እየደኸዩ የሚሄዱበት ዘመንና ስርአት አለንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወገድ ወጣቱ አርበኞች ግንቦት 7ን ባለበት ይቀላቀል። ትግላችን እስከመጨረሻው ድል ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7

Report of the Conference on the Future of Eritrea and Ethiopia

by Vision Ethiopia and ESAT


Conference on the Future of Eritrea and EthiopiaOn Sunday October 18, 2015 a successful one-day long conference was held at Georgetown Marriott Hotel, 1221 22nd St NW, Washington, DC 20037. The theme of the conference was on the present and future relationship between Eritrea and Ethiopia and had conflict prevention and resolution threads. The panelists range from former United States diplomats and State Department officials to former government officials of Ethiopia, senior academics, authors, professionals and social and political activists. The conference was organized by Vision Ethiopia, a network of Ethiopian academics and professionals residing in the United States and Japan, in collaboration with the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT). The number of people who attended the conference was at full hall capacity. The audience had ample opportunities to ask and express diverse view points on a variety of current and sensitive issues affecting Ethiopia and Eritrea. The full conference audio and video is available and will be transmitted to the people of Eritrea and Ethiopia very soon. Although there were four panel sessions scheduled only three sessions were delivered because of lack of time. They all focused on historical, social, cultural and professional dimensions of building and rebuilding trust between the two related people, the role of super powers and regional powers in the Ethio-Eritrea relationship, and the risks and opportunities of establishing fraternal relationship between the Government of Eritrea and the Ethiopian political organizations.
The Master of Ceremonies, W/t. Birtawit Girmay, Manager of ESAT Washington DC studio, opened the conference at 10:15. She outlined the objectives of the conference and laid out the conduct and procedure of the conference. After clarifying on important issues of housekeeping, W/t Birtawit invited Ato Gizaw Legesse of Vision Ethiopia and ESAT producer to make the formal opening remarks about the purpose, importance and timeously nature of the conference.
The first of the three panel sessions was moderated by Professor Getachew Begashaw. The four panelists were Mr. Tariku Debretsion, Mr. Gashaw Gebre, Dr. Assegid Habtewold, and W/t Lulit Mesfin. They all presented their well researched and documented papers that were well received by the audience. As a prelude to the ensuing two sessions, drawing on their vast experiences of engagements and studies, these four panelists talked on the roles of Ethiopian and Eritrean Community leaders in building people-to-people relationship at different levels, how much the basic principles of peaceful co-existence of nations can be foundations for peace between the two countries and the region as a whole, and how social and professional organizations, including but not limited to churches, mosques, professionals and men and women of the Arts can create useful links and elevate the relationship to an even higher level.
The second session was moderated by Professor Minga Negash. The theme of the session was on the roles and interests of foreign powers in the regional peace, security and stability. On the panel were former senior diplomats of the United States, Ambassador Herman Cohen, Former Assistant Secretary of State and Ambassador David Shinn. Their tenure at the State Department coincided with the collapse of central government of Ethiopia and the takeover of Addis Ababa and Asmara by the TPLF/EPRDF and EPLF in 1991, and the 1998-2000 war between Ethiopia and Eritrea. They were joined by the veteran critical scholar of Ethiopia, Professor Emeritus Mesfin Wolde Mariam. There was a candid discussion about the United States’ policy failure towards Ethiopia and Eritrea. Ambassador Cohen revealed that Eritrea’s relation with the United States is unlikely to change during the term of office of President Obama.
He was also open about what transpired in 1991. He revealed that the crisis in Somalia is a threat to the United States and its policy appears to be driven by a singular concern for security. For Ambassador Cohen Ethiopia must accept the boundary commission’s ruling and start engaging Eritrea on all other matters. He underscored that both governments do not trust one another. As regards to the lifting of the UN sanctions against Eritrea he informed that it was only the the United States that used its veto power to block the lifting. He also revealed his efforts to engage in second tier diplomacy and organizing expert level discussion between the two countries.
Drawing from his experience as an Ambassador, Dr. Shinn went on straight to the identification of the powers that have interest in the region. He classified them into a two tier countries and acknowledged the United States’ influence must be examined in light of other countries’ interests. For Ambassador Shinn accepting the boundary commission’s ruling was evident and did not spend time on that. He was more cautious about the prospect of peace and urged that more work needs to be done to prevent another cycle of conflict. The European Union, China, and regional powers are also important and noted that much of what happens in Ethiopia is influenced by regional powers.
Professor Mesfin was unforgiving in letting his audience know that successive Ethiopia governments, including the current regime, were clients of super powers, and Eritrea is being punished for resisting dominance by the United States. The old Ethiopian ethos of not bending to foreign powers and pride exists only in Eritrea, as manifested by the behavior of the Eritrean government and in contrast to the behavior of the regime in Addis Ababa in relation to foreign powers, Professor Mesfin Woldemariam asserted.
As a peace activist he regretted that the peace proposal he initiated before the collapse of central government in 1991 was not supported by the United States. He highlighted the double standards of the United States, and compared Ethiopia and South Africa’s reconciliation. He also urged that Ethiopians must take ownership of their own destiny and start building and rebuilding the relationship with Eritrea. In general, there was a consensus about the successes and failures of U.S diplomacy in the area. And all the three panelists explained the economic incentives that are available from reconciliation and cooperation between the two countries.
Nine participants from the audience presented varieties of questions. Most of them were directed to Ambassador Cohen and Ambassador Shinn. There was no unanswered question that was important. The questions to Professor Mesfin were more focused on seeking his guidance. The session closed with vote of thanks and a call for the continuation this type of productive panel discussion. The session took more time than was originally planned because of the interest shown by the audience. The panel closed with a sense of satisfaction.
The third session started after a brief lunch break. The session was moderated by Professor Messay Kebede and the theme of the discussion was on relations between the Eritrean Government and the Ethiopian opposition forces. Ambassador Dr. Kassa Kebede, former minister and diplomat of the Ethiopian Government under Dergue, Mr. Erimias Legesse, former deputy Minister of government communication under TPLF/EPRDF, Dr. Mesfin Abdi of the recently formed Oromo Democratic Front and Mr. Neamin Zeleke of the recently merged Patriotic Ginbot 7 were on the panel.
Dr Mesfin Abdi presented a carefully thought out document and indicated that the view expressed in the document is also being adopted as the official position of his party. He outlined a carefully thought out proposal and invited discussion. He emphasized the need to recognize the sovereignty and independence of Eritrea in order to have peace, stability and prosperity in the sub-region. He further announced that his organization is planning to host a conference shortly, and called upon for participation.
Dr Mesfin was followed by former Ambassador Dr. Kassa Kebede. Dr. Kassa started his presentation by making few remarks on Ambassador Cohen’s presentation. Citing early historical inscriptions he outlined the history of state formation in Ethiopia. Ethiopians and Eritreans lived together for thousands of years and shared language, culture, religion, and geography until recently. Dr. Kassa Kebede stated that the two countries had defended the region from enemy forces and colonialists in unison. “Of course, Eritrea was under Italian colonialism for fifty years and British Military Administration (BMA) for ten years before the Federation which was abrogated during Emperor Haile Selassie’s regime, “he recalled.
He then moved to answering the questions about the feasibility of good relationships between the government of Eritrea and Ethiopian political parties. He recognized the rights of the Ethiopian opposition forces to do so by declaring that the choice must be left to the organizations themselves. Throughout his presentation Ambassador Kassa detoured from time to time and intimated a number of important information which surprised/excited the audience. For instance, he confirmed that the relation between Eritrea and the United States might be simply explained by personality clashes between Ambassador Suzan Rice, who is now the Chief National Security Advisor of President Obama and President Isayas Afeworki, and noted that this relation is unlikely to change while President Obama is in office. The implications of this for Eritrea is that lifting the UN sanction against Eritrea may not be possible.
Dr. Kassa Kebede cited closed door negotiations and backdoor meetings held with leaders of the Eritrean People’s Liberation Front (EPLF) during his time as a top official and Ambassador in under the PDRE/WPE regime. He told the audience that President Isaias Afeworqi has an unbending belief in the existence of a united Ethiopia and that he is a living witness to this belief held by the Eritrean President.
Mr. Ermias Legesse presented the TPLF/EPRDF’s policy towards Eritrea. He explained the differences between what are discussed in EPRDF internal documents and what are published in its ideological magazine, using pennames. Ethiopia’s policy and party official statements, including Prime Minister Haile Mariam public pronouncements are exact extracts from the party’s ideological magazine which were written by the late Prime Minister Meles Zenawi and Minister Bereket Simon. According to Ermias, the policy of containment, isolation and undermining the Eritrean government and eventual regime change is the strategy of the government of Ethiopia.
The fourth panelist was Mr. Neamin Zeleke. Although he did not prepare a formal presentation, he made few general remarks about the nature of the government in Ethiopia and provided the rationale for his organization’s actions. He told the audience that there are thousands of political refugees in Eritrea. He emphasized that Eritrea is the only safe place in the Horn of Africa where Ethiopian refugees can go. He reported that Patriotic Ginbot 7’s relationship with the government of Eritrea has passed the initial tests of building trust and Eritrea does not interfere in his organization’s internal affairs.
There were a total of eight questions and views from the audience; and some from both sides of the Eritrean political divide. There were some views coming from different angles from the Ethiopian side as well. Some of the views regarding Eritrea include call for democracy in Eritrea and how Ethiopia can be helpful. This view was not well received by Ethiopians in that Ethiopians acknowledge the fact that this must be left for Eritreans. The comments from the Ethiopian side include the reliability of the government of Eritrea in committing itself to the unity of Ethiopia, what Ethiopian political organizations may have to give in order to get Eritrea’s support, and Ethiopia’s right to own the port of Assab.
Mr. Neamin stated unequivocally that his party has no mandate to negotiate on the future of Ethiopia with any government or international body and only an elected and properly constituted future government of Ethiopia would take the matter forward. He, however, said that they see the current relationship, not as a tactical one, but as a groundwork for building confidence, trust, and a springboard to chart a new era of peace, stability prosperity within a framework of a comprehensive and strategic partnership with the state of Eritrea that should include economic, security, and other vital interests such as the question of ports and access to the sea.
The panelists agreed that at present the focus must only be on building trust between The Eritrean government and the Ethiopian opposition forces.
Vote of thanks and concluding remarks were delivered by Dr Assegid Habtewold and the conference was closed at 6:30 pm.
Note: the moderators’ session, scheduled to be the last one, “Quo Vadis? Where are we going to? The un-answered Questions”, was to be presented by Professors Messay Kebede, Minga Negash, and Getachew Begashaw.

Wednesday, October 7, 2015

የቤተ-አምሃራ ክርስቲያኒያዊና እስላማዊ ስልጣኔዎች ከኦሮሞ ወረራ በፊት በጨረፍታ አምደጺዮን ዘ ተጉለት

ፈጠጋር (አሩሲ )
በ 7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በመካከለኛው ምስራቅ የእስልምና ሃይማኖት ማንሰራራትን ተከትሎ የአክሱም መንግስት በቀይ ባህር የንግድ መስመር ላይ ይዞት የነበረውን የበላይነት ቀስ በቀስ እየተነጠቀ በመምጣቱና በኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ መስኩ የነበረው ጥንካሬ ክፉኛ በመሸርሸሩ በሰሜናዊ ግዛቱ በተደጋጋሚ ይቃጣበት የነበረውን የዘላን ማህበረሰቦች ወረራና ጥቃት መቋቋም ተስኖት የመንግስቱን መቀመጫ ከአክሱም ከተማ በማንሳት ወደ ደቡባዊ የግዛቱ አቅጣጫ እንዲያዞር ተገድዶ ነበር:: ከ7 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በአክሱም መንግስት ላይ ተደጋጋሚ ወታደራዊ ድልን በመቀዳጀት ከመረብ ወንዝ ማዶ ያሉትን ሰፊ ሰሜናዊ ግዛቶች(የዛሬውን ኤርትራ) በመውረር በሰፈራ የተቆጣጠሩት የበጃ ዘላን ማህበረሰቦች አካባቢው በዛግዌ መንግስት አማካኝነት ተመልሶ ወደ ኢትዮጵያ እንዲጠቃለል ከተደረገ በኋላም እስከ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ በማእከላዊ መንግስት ስር ሆነው አካባቢውን በበላይነት ማስተዳደር ችለው ነበር(Taddesse Tamrat, Ethiopia the red sea and the horn, p.100; Abir, Ethiopia and the red sea, p.42):: ከ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ በዘላን ማህበረሰቦች ወረራና የተፈጥሮ ሃብት መመናመን ገፊነት የአክሱምን ከተማ በመልቀቅ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ ማፈግፈግ የጀመረው የአክሱም መንግስት በ9 ኛውና 10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመንግስቱ መቀመጫ አድርጎ የተጠቀመባት የ “ኩባር” ከተማ በቀድሞው ቤተ-አምሃራ በዛሬው ወሎ ክፍለ ሃገር ውስጥ በሃይቅ አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ ነበረች:: ለዚህም አስረጅ የሆኑ የጽሁፍና አርኬዎሎጂካል መረጃዎችን እናገኛለን:: በወሎ ሃይቅ አካባቢ የተገኙ የአክሱማዊ ነገስታትን ሰፈራዎች የሚያመላክቱ ጥንታዊ ቅርሶች በወቅቱ የነበረው የአረብ ታሪክ ጸሃፊ ኣል-ያቁቢና(872-89) የኣስረኛው ክፍለ ዘመን የአረብ አሳሽ ኣል-ማሱዲ “ኩባር” በማለት የገለጿትን የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መቀመጫ በቤተ-ኣምሃራ ውስጥ ለይተው የጠቆሙ ጠቃሚ የታሪክ መረጃዎች ናቸው:: የአህመድ ግራኝ ዜና መዋዕል ጸሃፊ እንደመዘገበው ከሆነ የሙስሊም ወራሪ ጦር በ 1532 እ.ኤ.አ. ያወደመው በሃይቅ አቅራቢያ ይገኝ የነበረ ታላቅ ቤተ መቅደስ ከመውደሙ ከ720 አመታት ቀደም ብሎ የተገነባ ነበር:: ይህም ቤተ መቅደሱ የተገነባበትን ዘመን ወደ 812 እ.ኤ.አ. ይወስደዋል:: በሃይቅ እስጢፋኖስ ገዳም የሚገኝ ድርሳን እንደሚያወሳው ገዳሙ በሃይቅ አቅራቢያ ሰፍሮ በነበረ አክሱማዊ ንጉስ በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገነባ ነበር(ዓጼ አንበሳውድም?):: የቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ዘብሄረ ቡልጋ(1215-1313) ቀደምት አባቶች በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ከቤተ-አምሃራ እምብርት ተነስተው ኋላ የቤተ-አምሃራ ደቡባዊ አውራጃ በሆነው ሰሜን ሸዋ መስፈራቸውን እንዲሁም ከዚህም በጣም ቀደም ብሎ በ9 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የአቡኑ ዘሮች ከአክሱም ወደ ቤተ-አምሃራ መፍለሳቸውን ገድላቸው ያወሳል:: የአክሱም መንግስት በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሃይቅ አቅራቢያ ተረጋግቶ እንዲመሰረት ያስቻለው ቀደም ብሎ ከ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ በአካባቢው የተጀመረው ወታደራዊ ሰፈራና እሱን ተከትሎ በሂደት የተካሄደው የአክሱም ማህበረሰብ ፍልሰት የፈጠረው መደላድል እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ይቻላል:: እነዚህ የአክሱም ገዥ መደቦች የሆኑ ሰፋሪ ንጉሳዊ ቤተሰቦች፣ መኳንንትና ካህናት እንዲሁም ወታደሮች፣ ባለ እጆችና ገበሬዎች ለሶስት መቶ አመታት ያህል ማለትም ከ700-1000 ባሉት ዘመናት በተከዜ ወንዝና በምስራቅ የሚገኙ የአባይ ገባር ወንዞች ሸለቆ መካከል ባለው ለምና ሰፊ ግዛት ሰፍረውና ተስፋፍተው እንዲሁም ከነባሩ የአገው ማህበረሰብ ጋር ተዋህደው ሲኖሩ “አምሃራ” የተሰኘ አንድ ወጥ የባህልና የቋንቋ ማንነት በመፈጠሩ ከ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን(1000-) ጀምሮ በመጡት ዘመናት አምሃራ የተሰኘ ነገድ በውጭ ሃገራትና በቤተ-አምሃራ አጎራባች ሱልጣኔቶች በተጻፉ ድርሳናት ውስጥ በስም መጠቀስ እንደጀመረ እንመለከታለን::
በዘመነ አክሱም ሰፊ ሰሜናዊ ግዛታቸውን በዘላን ማህበረሰቦች የተነጠቁት የአክሱም መንግስት ወራሾች የሆኑት የቤተ-አምሃራ መስራቾች ቀድሞ ይኖሩበት የነበረው አካባቢ የተፈጥሮ ሃብት በመሟጠጡና ህብረተሰቡን በተገቢው መልኩ መደገፍ የማይችልበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ ጋር ተደራርቦ በተፈጠረባቸው ከፍተኛ ችግር ምክንያት መከተል የጀመሩት ወደ ደቡብ የመስፋፋት ፖሊሲ በተደጋጋሚ ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር ከፍተኛ ጥፋቶችን ወዳስከተሉ ግጭቶች ውስጥ ከቷቸዋል:: አክሱም ውስጥ በቄስ ገበዝ ተክለሃይማኖት ተሰብስበው ከሚገኙ ድርሳናት በአንደኛው ውስጥ እንደተዘገበው 150 ቀሳውስትን ከአክሱም ወደ ቤተ-አምሃራ በመውሰድ ደብተራ ብሎ የሰየማቸውና ለመጀመሪያ ግዜ በቤተ-አምሃራ “ወይና ደጋ”(ኩባር?) በተሰኘ አውራጃ መንግስታቸውን የመሰረቱት ዓጼ ደግናዣን(825-845) ሸዋን በመሻገር እስከ አዋሽ ሸለቆ ድረስ ባደረጓቸው የጦር ዘመቻዎች የታወቁ ሲሆን በ 845 በሃገሪቱ ምእራብ አቅጣጫ ይዘው ከዘመቱት 100,000 የጦር ሰራዊት ጋር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሰው ህይወታቸው አልፏል:: ይህ ወታደራዊ እልቂት የአክሱምን መንግስት ክፉኛ አዳክሞ ቀደም ሲል በአክሱማዊያን ተስፋፊነትና እሱን ተከትሎ በመጣው የክርስትና ሃይማኖት መስፋፋት የተቆጣው የዮዲት ጉዲት መንግስት ለከፈተው ወረራና ጭፍጨፋ አመቻቸው:: የአስረኛው ክፍለ ዘመን አረብ የታሪክ ጸሃፊ ኢብን ሃውቃልና(977) የአሌክሳንድሪያ ፓትሪያርኮች ግለ ታሪክ ጸሃፊዎች የነበሩት ኮስማስ(933-42) እና ፊላቴዎስ(979-1003) መዝግበው እንዳቆዩልን ዮዲት ጉዲት(ባኒ ኣል-ሃምዊያ) ከደቡባዊ የሃገሪቱ ግዛት ተነስታ ክርስቲያን አምሃሮችን በመጨፍጨፍና ቤተ ክርስቲያኖችን በማቃጠል አረመኔያዊ አገዛዟን ለአርባ አመታት ያህል አስፍና ቆይታለች:: በዚህ ከፍተኛ ወረራና ጥፋት ወቅት ዓጼ አንበሳውድም(885-905) መንግስታቸውን በሰሜን ሸዋ አድርገው በመከላከል የክርስቲያን ቤተ-አምሃራ ስልጣኔን ከፈጽሞ ጥፋት ታድገዋል:: በገድለ እየሱስ ሞዓ ተጽፎ እንደሚገኘው ዓጼ አንበሳውድም የዮዲት ጉዲትን ሞት ተከትሎ በስደት ተሸሽገው ከቆዩበት ሸዋ ተመልሰው ከአቡነ ሰላማ ጋር በመሆን 300 ካህናትን ከአክሱም በማስመጣት በሃይቅ ዙሪያ የደብረ ነጎድጓድ ቤተ ክርስቲያንንና ዝነኛውን የቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳምን አቋቁመዋል:: በዚህ ገድል መሰረት ከዚህ በተጨማሪ ንጉሱ ከሸዋ በተመለሱ በሰባት አመታቸው በሃይቅ ዙሪያ ቤተ መንግስታቸውን አሳንጸዋል( ይህ መረጃ በሃይቅ ዙሪያ ከተገኙ የአርኬዎሎጂካል ግኝቶች ጋር የክፍለ ዘመኑን የንጉሰ ነገስት መቀመጫ ከተማ ለይቶ በመጠቆሙ ረገድ ስምምነት አለው):: የዓጼ አንበሳውድም ልጅ የነበሩት ዓጼ ድልነአድ(905-915) በበኩላቸው የሚካኤል አምባ ውቅር ቤተ ክርስቲያንንና አክሱም ጺዮንን በትግሬ አስገንብተዋል:: በሌላ በኩል የ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በሸዋ ደቡባዊ ምስራቅ አካባቢ የእስላማዊ ሱልጣኔቶች የሚያቆጠቁጡበት ዘመን ስለነበር እነዚህ ሁለት ተስፋፊ ሃይሎችን (የሙስሊም ሱልጣኔቶችንና ቤተ-አምሃሮችን) ለብዙ መቶ አመታት የሚቆይ ግጭት ውስጥ የከተተ የግዛት፣ የሃይልና የንግድ የበላይነት ፉክክር የተለኮሰበት ወቅት ነበር:: አምሃሮች በ1108 እ.ኤ.አ. ከተስፋፊው የሸዋ እስላማዊ ሱልጣኔት ጋር የመጀመሪያውን ጦርነት ማድረጋቸውን እንዲሁም በ1128 እ.ኤ.አ. ወርጂህ ከሚባለው ሃገር መባረራቸውን በወቅቱ በአረብኛ የተጻፈውና በ1941 እ.ኤ.አ. በኤንሪኮ ሴሩሊ የተተረጎመው የሸዋ ሱልጣኔት ዜና መዋዕል ያወሳል:: ወርጂህ ዘላን ማህበረሰብ ሲሆኑ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሸዋ በምስራቅ በኩል በአዋሽ ሸለቆ ሰፍረው ይኖሩ የነበሩ ናቸው:: ቤተ-አምሃሮች ከጎጃምና ከበጌ ምድር አገዎችም ጋር እንዲሁ የግዛት ግጭት ውስጥ በመግባታቸው ብዙ አገዎች ለስደት ስለተዳረጉ በተክለ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ዜና መዋዕል ላይ ሰፍሮ እንደሚገኘው “አማራ ሲለምድ አገው ሲሰደድ” የሚለው የአማርኛ አባባል ሊነገር ችሏል:: በ16 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የደቡብ ጎጃም አገዎች ከግራኝ አህመድ ወራሪ ጦር ጋር ወግነው ቤተ-አምሃሮችን እንዲያጠቁ የገፋቸው ምክንያት ግዛታቸው የነበረውን ምስራቅ ጎጃምን ቤተ-አምሃሮች ከዛ በቀደሙት ዘመናት ነጥቀዋቸው ስለሰፈሩበት በመቆጣታቸው እንደነበር በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል(Tadesse Tamrat, Ethiopia, the red sea and the horn, p.176):: በዚህ መልኩ ከሰሜን ወደ ደቡብ በመፍለስና በመስፋፋት መልሶ የተቋቋመው የቤተ- አምሃራ አክሱማዊ ነገድ የመስፋፋት ፖሊሲው አዳዲስ ለሰፈራ የሚያገለግሉ ለም ግዛቶችን ቢያስገኝለትም መንግስቱ ከአቅም በላይ በመለጠጡና ከአካባቢው ሃይሎች ጋር ለተደራራቢ ግጭቶች በመዳረጉ ሃይሉ ስለተዳከመ የመንግስት ስልጣኑን በላስታ አገዎች በሃይል ሊነጠቅ ችሏል::
ሃይቅ(ኩባር) ላይ የነገሱ የቤተ-አምሃራና ሌሎች ንጉሰ ነገስታትና ንግስተ ነገስታት(825-915):-
ዓጼ ዳግናዣን (825-845) ፣ ዮዲት ጉዲት(ትርዳ ንግስት፣ እሳቶ)(845-885) ፣ ዓጼ አንበሳውድም (885-905)፣ ዓጼ ድልነዓድ (905-915)
የዛግዌ ስርወ መንግስት ከተመሰረተ በኋላ በሰሜን ሸዋ የተቀመጡ የቤተ-አምሃራ ነገስታት ዝርያዎች(915-1270):-
ዓጼ ድል ነዓድ(ስልጣናቸውን በዛግዌዎች ከተነጠቁ በኋላ ወደ ሰሜን ሸዋ የሸሹት)፣ ማህበረ ውድም፣ አግብዓጺዮን፣ ስንፈአርድ፣ ነጋሽዛርኤ፣ አስፍሃ፣ ያቆብ፣ ባህርአሰግድ፣ እድምአሰግድ፣ ዓጼ ይኩኖ አምላክ(በ1270 እ.ኤ.አ. ዓጼ ተብለው የነገሱ)
የ10ኛውና 11ኛው መቶ ክፍለ ዘመናት ቤተ-አምሃሮች የተዳከሙባቸው ወቅቶች ስለነበሩ በተለያዩ አካባቢያዊ ሃይሎች ለወረራና ጥቃት በመጋለጣቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቤተ-አምሃራ ምርኮኞች የመንን ጨምሮ ወደተለያዩ ሃገራት በባርነት ተሽጠዋል(ይህ ዘመን ከዮዲት ጉዲት ወረራና ከዛግዌ ስርወ መንግስት መነሻ ጋር ይገጣጠማል):: ወደ የመን በግዞት የተወሰዱት ቤተ-አምሃሮች በየመን ከፍታ ቦታዎችና በቀይ ባህር መካከል ባለው መሬት ከወደቡ 27 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ጢሃማ ውስጥ በዛቢድ ከተማ ላይ ነባሩን የአረብ ዚያዲድ ስርወ መንግስት ገልብጠው “የሃበሻ ማምሉክ ስርወ መንግስት” በመባል ይታወቅ የነበረ እስላማዊ የቤተ-አምሃራ ስርወ መንግስት በ1021 እ.ኤ.አ.( ከሂጅራ በኋላ 412) መስርተው ነበር:: ይህን እስላማዊ ስርወ መንግስት የመሰረተው ሰው የዚያዲድ ስርወ መንግስት ቤተ መንግስት የመጨረሻ ከንቲባ አገልጋይ የነበረ “ናጃህ” የተባለ ቤተ-አምሃራ ሲሆን የስርወ መንግስቱ ገዢዎች የነበሩት ከእሱ ተከታትለው የነገሱት ዝርያዎቹ “ናጃሂዶች” በመባል ይታወቁ ነበር:: መስራቹ ናጃህ ዛቢድን ከ1021-1060 እ.ኤ.አ. ድረስ አስተዳድሯል:: ስርወ መንግስቱ ከኢትዮጵያ በባርነት ተሽጠው የሄዱና የአረብን ባህል የወረሱ ሀበሾች ድጋፍ የነበረው ነው:: ቤተ-አምሃሮቹ ናጃሂዶች በቋሚነት የሚገጥሟቸውን ግጭቶችና አመጾች ተቋቁመው ለ138 አመታት ዛቢድን ማስተዳደር ችለው ነበር:: ይህ የቤተ-አምሃራ ማምሉክ ስርወ መንግስት
ከ1021-1159 እ.ኤ.አ. ( ከሂጅራ በኋላ 412-554) ባሉት ዘመናት ውስጥ 8 ነገስታትን አንግሶ ያለፈ ሲሆን ከነዚህ ነገስታት ውስጥ “ካኢድ አቡ ሙሃመድ ሱሩር አምሃራ ኣል-ፋቲቅ” የተሰኘው እጅግ በጣም ዝነኛው ነበር:: በግዜው የነበረ ኢብን ካልዱን የተሰኘ ጸሃፊ ስለዚህ ገናና ገዥ ሲጽፍ “ካኢድ አቡ ሙሃመድ ሱሩር አምሃራ ኣል-ፋቲቅ 'አምሃራ' ከተሰኘው የአቢሲኒያ ነገድ የተገኘ ሲሆን እኔ ስለእርሱ ታላቅነት መጻፍ የምችለው ከውቂያኖስ ውስጥ ጠብታ ያህሉን ብቻ ነው” ብሏል:: ይህ የናጃሂድ ንጉስ በ1156 በተገደለ በሶስት አመታት ውስጥ ዛቢድና በስሯ ያሉ አካባቢዎች በዓሊ ኢብን መህዲ በመያዛቸው የአምሃራ ማምሉክ ስርወ መንግስት ፍጻሜ ሊሆን ችሏል:: ዛቢድ ከተማ የኤደንና መካ ከተማን በሚያገናኘው መንገድ ላይ የምትገኝ እንደመሆኗ መጠን በግዜው ታላቅ የንግድ ማእከል ሆና ታገለግል ነበር:: ኢድሪሲ የተባለው ጸሃፊ በበኩሉ የዛቢድ ከተማ ሃብታምና ብዙ ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ እንደነበረች ገልጾ በከተማዋ የሚሸጡት ሸቀጦች የሚመጡት እንደ ሂጃስ፣ ኢትዮጵያና ግብጽ ካሉ ቦታዎች በመርከብ ተጓጉዘው እንደነበር ጽፏል:: የናጃሂድ ገዢዎች ዝርዝር እንደሚቀጥለው ነው:-
ሙዓያድ ናጃህ(1021-1060)፣ ዓሊ ዳዒ ሱላይሂድ(1060-1062) (ናጃሂድ ያልነበረ)፣ ሰዒድ አህዋል ቢን ናጃህ(1062-1080)፣ ጃያሽ ቢን ናጃህ(1080-1089)፣ ፋቲቅ ጃያሽ(1089-1104)፣ መንሡር ቢን ፋቲቅ(1104-1109)፣ ፋቲቅ(2ኛ) መንሡር(1109-1123)፣ ፋቲቅ(ሳልሳዊ) ቢን ሙሃመድ ቢን መንሡር(1136-1159) ናቸው::
በዛግዌ ስርወ መንግስት ዘመንም የቤተ-አምሃራ የመስፋፋት እርምጃዎች ተጠናክሮ ቀጥሎ በላይኛው ተከዜ፣ በባሺሎና በጣና ሃይቅ መካከል ያለው ግዛት በቤተ-አምሃራ ስር ተጠቃሎ ሊያዝ ችሏል:: በዚህ ወቅት የአዋሽና የቀሰም ወንዞች መነሻዎች ድረስ ያሉ ክርስቲያን ማህበረሰቦች አደፋ ለሚገኘው የዛግዌ ንጉስ ይገብሩ ነበር:: ከዓጼ ድልነአድ(905-915) የዘር ግንዳቸው የሚመዘዘው የቤተ-አምሃራ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩት መስፍን ይኩኖአምላክ የመንግስታቸው መቀመጫ ከነበረችው የቤተ-አምሃራ ደቡባዊ አውራጃ ተጉለት(ሰሜን ሸዋ) በመነሳት በታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ የኢትዮጵያ ወርቃማ ዘመን ተብሎ የሚታወቀውን የመካከለኛውን ዘመን ያስተዳደረውንና በስፋትና በጥንካሬ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አቻ የማይገኝለትን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ግዛት የመሰረተውን ገናና ሰሎሞናዊ ስርወ መንግስት(1270-1632) በ1270 እ.ኤ.አ. በቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት እረዳትነት መስርተዋል:: በዚህ ስርወ መንግስት የአማርኛ ቋንቋ የምስራቅ አፍሪካ የመግባቢያ ቋንቋ መሆን እንደቻለም ከታሪክ እንገነዘባለን ( ለዚህ ትልቅ ማስረጃ የሚሆነን የታሪክ መዝገብ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግራኝ አህመድ በህንድ ውቂያኖስ ጫፍ ሰፍረው ከሚገኙ የሱማሌ ዘላን ጎሳዎች የተውጣጡትን ወታደሮቹን ወደ ክርስቲያኖች ግዛት ለስለላ በሚልክበት ወቅት የአማሮችን አለባበስ በመልበስ አማርኛ ቋንቋ ብቻ እየተናገሩ እንዲገቡ ያስተላለፈው ትእዛዝ ሰፍሮ የሚገኝበት የአረብኛ ዜና መዋዕሉ ሲሆን የቤተ-አምሃሮች ተጽዕኖና የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት ምን ያህል ሰፊ ግዛታዊ ተደራሽነት እንደነበረው የሚመሰክር ነው::) በተጨማሪም በወቅቱ ይፋትን ጨምሮ አብዛኞቹ የመካከለኛው ዘመን የሙስሊም ሱልጣኔቶች(ደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ) በርካታ ሙስሊም አምሃራ ነዋሪዎች የነበሯቸው ሲሆን ከፈጠጋር(አሩሲ) በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ደግሞ በርካታ ክርስቲያን አምሃሮች ይኖሩባቸው ነበር(Merid, “Southern Ethiopia”, pp.42-47,46-47):: የሸዋ ቤተ-አምሃራ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ማዕከላዊ ጦር የአክሱምን የጦር አደረጃጀት የተከተለ ሲሆን በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ካሉ ማህበረሰቦች የተውጣጡ የዳሞት፣ ኢናሪያ፣ ሃዲያ፣ ይፋት፣ አምሃራ፣ አገው፣ ትግሬ፣ አዳል፣ ሃረር፣ ኦሮሞ ወዘተ ክርስቲያንና ሙስሊም ወታደሮችን ያቀፈ ነበር(Ibid, pp.81-82, 294):: ከ1270 አንስቶ እስከ 1468 ዓመተ ምህረት ድረስ በተከታታይ የነገሱት ታላላቅ የሸዋ ቤተ-አምሃራ ዓጼዎች ይኩኖ አምላክ(1270-1285)፣ አምደጽዮን(1314-1344)፣ ዳዊት(1382-1413)፣ ይስሃቅና(1414-1429)፣ ዘርዓ ያዕቆብ(1434-1468) በዘመነ አክሱም የተጀመረውን የቤተ-አምሃራን ወደ ደቡብ የመስፋፋት ፖሊሲ በማደስ በሰሜን፣ በሰሜን ምእራብ፣ በደቡብና በደቡብ ምስራቅ የሚገኙትን የአገው፣ ጎጃም፣ ዳሞት፣ ፈላሻ፣ በለው(በጃ)፣ ቢዛሞ፣ ኢናርያ፣ ማያ፣ ጉሙዝ፣ ሻንቅላ፣ ጂንጅሮ፣ ጋፋት፣ ገንዝ፣ ሞራ፣ ሸዋ፣ ሲዳማ፣ ሃድያ፣ ከምባታ፣ አላባ፣ ይፋት፣ አርጎባ፣ ፈጠጋር፣ ደዋሮ፣ አረባቢኒ፣ ሻርካ፣ ደራ፣ ባሊ፣ ሃርላ፣ አዳል፣ ሱማሌ፣ ገበል፣ ወርጂህ፣ ዶባ፣ ጉራጌና ሌሎች የአፍሪካ ቀንድ ማህበረሰቦች መኖሪያ ክልሎችንና የንግድ መስመሮችን በቁጥጥር ስር አድርገዋል:: በዚህ ዘመን የኢትዮጵያን የግዛት ክልል ቀይ ባህር፣ የኤደን ባህረ ሰላጤ፣ ህንድ ውቂያኖስና ላይኛው የአባይ ሸለቆ(ነጭ አባይ) እንደሚያዋስኑት ለማረጋገጥ ተችሏል:: በዚህ መሰረት በወቅቱ ኢትዮጵያ ዘይላ፣ ምጽዋና ሱዋኪን የተሰኙ ዋና ዋና የባህር ወደቦች ነበሯት::
ታዋቂው አሜሪካዊ የታሪክ ምሁር ዶናልድ ሌቪን የኢትዮጵያ የምንግዜም ታላቅ ንጉሰ ነገስት ሲል የገለጻቸው ዓጼ አምደ ጽዮን ከላይ ከተዘረዘሩት ነገስታት ሁሉ ታዋቂ ከመሆናቸውም በላይ በዘመነ መንግስታቸው ከተጉለት(ሰሜን ሸዋ) በመነሳት በመላው የአፍሪካ ቀንድ በክርስቲያኑም በእስላሙም፣ በአዋሙም ላይ የቤተ-አምሃራን መንግስት ማዕከላዊ የበላይ ሥልጣን በማስፈን በምስራቅ አፍሪካ ተስተካካይ የሌለው ሃያልና ገናና መንግስት ለማቋቋም ችለዋል:: ታዋቂው የአረብ ጸሃፊ ኢብን ፋደል አላህ ኦማሪ የዓጼ አምደ ጽዮንን የጦር ዘመቻዎች ተከትሎ በ1330ዎቹ ዓመታት መጨረሻ ሲጽፍ የኢትዮጵያ ዓጼ መንግስት ግዛት በደቡብ ምስራቅ ከህንድ ውቅያኖስ ጠረፍ አንስቶ በሰሜን ምእራብ እስከ ባርካ ሸለቆ ማለትም የዛሬው የኤርትራ ምዕራባዊ ክፍል ድረስ ይዘልቅ እንደነበር አረጋግጧል:: ኦማሪ ከዚህም በላይ “የንጉሰ ነገስት ሰፊ አካባቢ” በሚል የቤተ-አምሃራ ዓጼዎችን ግዛት በአጠቃላይ ገልጾታል:: በ14ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ በኢትዮጵያ ዘጠና ዘጠኝ ትንንሽ የአካባቢ ባላባትና ሃገረ ገዢዎች እንደነበሩ ይታወቃል:: ከተጠቀሱት የቤተ-አምሃራ መንግስት የአስተዳደር ክልሎች መካከል በኦማሪ መጽሃፍ ሰምሃር(ሳሆ)፣ ሃማሴን፣ ናራ(ባሪያ)፣ ትግሬ፣ ሰሐርት፣ አምሃራ፣ ሸዋ፣ ዳሞት፣ ገንዝ፣ አዳሶ፣ ሞራ ይገኙባቸዋል:: እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ ይፋት፣ ደዋሮ፣ አራባቢኒ፣ ሃዲያ፣ ሻርካ፣ ባሌና ደራ የተሰኙ እስላማዊ ግዛቶች እንደነበሩ በስም ተለይተው ተጠቅሰዋል:: የታሪክ መዝጋቢው ከተጠቀሱት በተጨማሪ በዓጼው ግዛት ውስጥ በቁጥር ሃምሳ የሚሆኑ የቋንቋ ማህበረሰቦች እንደነበሩ አረጋግጧል:: ከእስላማዊ ግዛቶቹ ውስጥ ጠንካራው ሃዲያ ሲሆን 120,000 የጦር ሃይል ሲኖረው ከነዚህም መሃል 80,000 ያህሉ እግረኛ ሲሆን 40,000 ያህሉ ደግሞ ፈረሰኛ ነው:: በተመሳሳይ ወቅት ታላላቆቹ የኑቢያና የሰናር የሰሜን-ምስራቅ አፍሪካ ክርስቲያን መንግስታት ሲወድቁና በእስልምና ሲዋጡ የሸዋ ቤተ-አምሃራ ነገስታት ከአውሮጳ ውጪ በአለም ላይ ብቸኛውንና በስፋት የአውሮጳን ሃገራት ጨምሮ በመላው አለም ወደር የሌለውን ጠንካራ የክርስቲያን መንግስት መመስረት ችለዋል:: የዓጼ አምደ ጽዮን አስደናቂና በርካታ ተደራራቢ ድሎች የንጉሱን ዝና በመላው አውሮጳ በእጅጉ እንዲናኝ አድርጎታል:: ወቅቱ የሙስሊም መንግስታት ሃይል በንግድና በወታደራዊ አቅም ያየለበት እንደመሆኑ መጠን ዓጼ አምደ ጽዮን በሙስሊም ሱልጣኔቶች ላይ የተቀዳጃቸው ታላላቅ ወታደራዊ ድሎችና በህንድ ውቂያኖስ አካባቢ ባለው ምስራቅ አፍሪካ ላይ የመሰረቱት ሃያልና ግዙፍ ክርስቲያናዊ መንግስት በተሸናፊዎቹ የክርስቲያን አውሮጳ ነገስታት ዘንድ በህንድ ውቅያኖስ ንግድ ላይ ለተመሰረተው የግብጽ ማምሉክ ሱልጣኔቶች መንግስት ተገዳዳሪ ሃይል መፈጠርና ለተዳከመው የክርስቲያን ሃይል ማንሰራራት ትልቅ ብርሃን የፈነጠቀ ክስተት ነበር:: ከዚህ በኋላ የአውሮጳ ነገስታት ኢትዮጵያን በፊት አውራሪነት የሚያሰልፍ ጸረ-እስልምና የክርስቲያን ግንባር ለመፍጠር እቅድ ማውጣት ጀመሩ:: የዓጼ አምደ ጽዮን አስደማሚ ወታደራዊ ስኬት እንዲሁ ትልቅ ተስፋን የጫረባቸው የሮማ ካቶሊክ ጳጳስም ኢትዮጵያን ካቶሊካዊት የማድረግ ፍላጎት ስላደረባቸው በአውሮጳ ነገስታት እየተነደፈ በነበረው ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ክርስቲያናዊ ግንኙነት የመፍጠር እቅድ ዙሪያ አብረው መክረው ነበር:: ከዚህ በኋላ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የአውሮጳ አምባሳደሮች፣ ነጋዴዎችና ሃገር አሳሾች የግብጽ ማምሉክ ሱልጣኖችን ጥብቅ ቁጥጥር ጥሰው እያለፉ ወደ ሸዋ-ቤተ-አምሃራ መጉረፍ ጀመሩ:: በአፍሪካ ቀንድ የህንድ ውቂያኖስና የቀይባህር ንግድንና እስላማዊ ሱልጣኔቶችን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ዓጼ አምደ ጽዮን እራሳቸው የሚመሩት ጦር ቀይ ባህር በደረሰ ማግስት ወደ ግብጽ የሚደረገውን የንግድ ፍሰት ለማወክና በግዛታቸው ስር ባሉ እስላማዊ ሱልጣኔቶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ በመዛትና የግብጽ ሱልጣኖችን እጅ በመጠምዘዝ ከረጅም ዘመን በኋላ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ፓትሪያርክ እንዲላክ አስገድደዋል:: መንግስታቸውም ለግብጽ ክርስቲያኖች ይፋዊ ተጠሪ(protectorate) በመባል ለአውሮፓውያኖች እንኳን ባልተሰጠ ታላቅ ክብር በአሌክሳንድሪያ ሊሰየም በቅቷል:: በዚህ መልኩ በምስራቅ አፍሪካ ላይ የበላይነታቸውን ያረጋገጡት በኢትዮጵያ ታሪክ ወደር የማይገኝላቸው ወታደራዊ ንጉሰ ነገስት አምደ ጽዮን፥ የአፍሪካ ቀንድ ጠንካራ መንግስታትን በሙሉ በጦር ሃይል ከማንበርከካቸውም በተጨማሪ በሃገሪቱ ነባር ግዛቶች የፈላሻና የትግሬን አመጽ በአስተማማኝ መልኩ በመቀልበስ መረጋጋትን አስፍነዋል:: “ወኪል” በመባል የሚታወቁት የንጉሱ ተላላኪዎችም ከዘይላ በመነሳት በመካከለኛው ምስራቅ እስከ ኢራቅ ድረስ እየተጓዙ የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር::
የይፋት ሱልጣኔትን አመጽ ተከትሎ ዓጼ ሰይፈአርድ(1344-1371 ) በሱልጣኔቱ ላይ በወሰዱት ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ የተቆጣው የግብጹ ገዥ ሡልጣን ኣል-ማሊክ ኣል-ሳሊህ የግብጽን ፓትሪያርክ አቡነ ማርቆስን በ1352 በማሰር የአጸፋ እርምጃ ወስዷል:: የአቡኑን መታሰር የሰሙት ዓጼ ሰይፈአርድ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ግብጻዊ ነጋዴዎችን በሙሉ ሰብስበው በማሰርና በወደብ ያለውን የግብጽ የንግድ ሸቀጥ በማገድ ምላሽ ሰጥተዋል:: ዓጼ ሰይፈ አርድ የግብጹን ፓትሪያርክ ከእስር ለማስፈታት ከነበራቸው ቁርጠኝነት የተነሳ ከላይ ከፈጸሟቸው ተጽዕኖ የመፍጠሪያ እርምጃዎች በተጨማሪ በራሳቸው መሪነት ጦራቸውን በማሰባሰብ በግብጽ ደቡባዊ ግዛቶች ውስጥ እስከ አስዋን ድረስ ዘልቀው በመግባት በወሰዱት ወታደራዊ እርምጃ ሡልጣን ኣል-ማሊክ ኣል-ሳሊህ አቡነ ማርቆስን ከእስር ለመልቀቅ ተገድዷል:: ከዚህ ወቅት በኋላ የግብጽ ማምሉክ ሱልጣኖች በክርስቲያን ዜጎቻቸው ላይ የሚፈጽሙትን ከፍተኛ በደል አጠናክረው በመቀጠላቸው ከሸዋ ቤተ-አምሃራ ነገስታት ጋር ያላቸው ግንኙነት እየሻከረ ሊሄድ ችሏል:: በግብጽ ማምሉክ ሱልጣኔቶችና በየመን ራሱሊድ ነገስታት የሚደገፈው የይፋት ወላስማ ገዢ ሃቀዲን(2ኛ) መቀመጫውን ከይፋት ወደ አዳል በማዞር ከ1360ዎቹ ጀምሮ የአመጽና የሽብር እርምጃዎችን በቤተ-አምሃራ መንግስት ላይ በመክፈቱ በ1374 በዓጼ ሰይፈ አርድ ልጅ ዓጼ ንዋየ ማርያም በጦር ሜዳ ተሸንፎ ሊገደል ችሏል:: የሃቀዲን ወንድም የሆነው ሰዓደዲን(1373-1403) የወንድሙን ፈለግ በመከተል ከቀይ ባህር ዳርቻ ጀምሮ ያሉ የእስልምናና የሌሎች እምነት ተከታይ ማህበረሰቦችን በማስተባበር በመሰረተው ግዙፍ የጦር ሃይል ከ1376 ጀምሮ በቤተ-አምሃራ ማዕከላዊ መንግስት ላይ ከዛ ግዜ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ አመጽ በመክፈት እንደ ባሊና ደዋሮ ባሉ ትላልቅ እስላማዊ ግዛቶች ላይ ዝርፊያ በመፈጸም፣ ዜጎችን በመግደልና በባርነት በመፈንገል ብሎም ቤተ ክርስቲያናትን በማቃጠል ባደረሰው ጥፋትና በማዕከላዊ መንግስት ጦር ላይ ባስመዘገባቸው መለስተኛ ድሎች በመላው አለም ሙስሊሞች ዘንድ ከፍተኛ ስምና ዝና በማትረፉ የተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ጸሃፍት በጻፏቸው መጽሃፍት ላይ በተጋነነ መልኩ በጀግንነት ተወድሷል:: በመጨረሻም ዓጼ ዳዊት(1380-1412) በ1403 በከፈቱት የተጠናከረ የአጸፋና የማረጋጋት ወታደራዊ እርምጃ አማጺያኑን ከባሊና ደዋሮ ጠራርገው ካስወጡ በኋላ ከሃረር ጀምሮ እስከ ቀይ ባህር ዳርቻ ድረስ ያሉትን ከአዳል፣ ከአረብና በኢማም ዓሊ ሰዒድ የሚመራውን የሱማሌ ጦር ጨምሮ ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድ ማህበረሰቦች የተውጣጡትን የዋላስማ ሰአደዲንን ሃይሎች ሙሉ በሙሉ ደምስሰዋል:: በመጨረሻም በተመሳሳይ አመት ሰአደዲን በዓጼ ዳዊት በተመራ ጦር በቀይ ባህር የዘይላ ወደብ ላይ ታድኖ በመገደሉ አመጹ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል:: የሸዋ-ቤተ-አምሃራ መንግስት ከዚህ ቀደም “ጨዋ” የተሰኘውን ጦር በተቆጣጠራቸው የደጋ ግዛቶች ላይ የማስፈር ልምድ ቢኖረውም በምስራቅ ያሉ የቆላ እስላማዊ ግዛቶቹ ላይ ግን የአካባቢው የአየር ንብረት ደገኛ ለሆኑት የአምሃራ ወታደሮችና የጦር አበጋዞች የማይስማማ በመሆኑ በተወካይ አስተዳዳሪዎች በኩል ከግዛቶቹ አመታዊ ግብርና የወደብ ንግድ ቀረጥ በመሰብሰብና ለብሄራዊ ግዳጅ ወታደሮችን በመመልመል የተወሰነ ፖሊሲን ብቻ ይከተል ነበር:: ከላይ በተጠቀሰው የወላስማ አመጽ ገፊነትና የሰአደዲን ልጆች የአባታቸውን ሞት ተከትሎ ወደ የመን በመሸሽ በየመን ራሱሊድ ንጉስ ናሲር አህመድ ቢን ዓሽአሪ ቢን ኢስማኤል(1400-1424) አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ብዙ የአረብ ወታደሮች ተጨምረውላቸው እንዲጠናከሩ ተደርጎ ወደ ኢትዮጵያ በመመለሳቸው የወላስማ የአመጽ እንቅስቃሴን አጠናክረው ስለቀጠሉ ከዓጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት ጀምሮ የቤተ-አምሃራ ነገስታቶች ጦራቸውንና ቤተ-አምሃሮችን ከሃረር ጀምሮ እስከ ሞቃዲሾ(ህንድ ውቂያኖስ ዳርቻ) ባሉ የቆላ እስላማዊ ግዛቶቻቸው ላይ በማስፈር አካባቢዎቹን በቀጥታ ማስተዳደር ጀመሩ:: ይህንን በተመለከተ ታዋቂው የአረብ ታሪክ ጸሃፊ ኣል-ማቅሪዚ እንደሚከተለው ጽፎ ነበር:- “የሰአደዲንን ሞት ተከትሎ የሙስሊሞቹ ሃይል ተገቶ ነበር:: አምሃሮችም ሃገራቸውን በመውረር ሰፈሩበት:: ከመስጊዶቹ ፍርስራሾችም ቤተ ክርስቲያናትን ገነቡበት:: ሙስሊሞቹም በአምሃሮች እጅ ለሃያ አመታት የደረሰባቸው ከፍተኛ ሽንፈትና ጥፋት በቃላት ሊገለጽ ከሚችለው በላይ ነው” (A.-Maqrizi, Historia Regnum islamiticorum in Abyssinia, ed. and tr. F. T. Rink (Leiden, 1790) , 27):: ዓጼ ዳዊት እየሩሳሌምን ከሙስሊሞች እጅ ነጻ የማውጣት ከፍተኛ ምኞትና ዝግጅት ስለነበራቸውና የአውሮጳውያንን ቴክኖሎጂ ወደ ሃገራቸው የማስገባት ፍላጎት ስላደረባቸው በ1392 አንቶኒዮ ባርቶሊ የተሰኘ የፍሎረንስ ተወላጅ አምባሳደራቸውን ወደተለያዩ የአውሮጳ መሪዎች በመላክ ፍላጎታቸውን አሳውቀዋል:: በሰለሞናዊያን ስርወ መንግስት ወቅት የኢትዮጵያ የጥንካሬና የሃብት ዝና በአለም ዙሪያ ስለናኘ ከመካከለኛው ምስራቅና ከአውሮጳ የሚመጡ ስደተኞች በቤተ-አምሃራ ነገስታት ጥገኝነትና ጥበቃ ይሰጣቸው ነበር:: ዓጼ ዳዊት በቡርጂ ማምሉክ ሱልጣኖች ከስልጣን ለተወገዱት የግብጽ የባህሪ ሱልጣኖች ጥገኝነት የሰጡ ሲሆን በዓጼ ሰይፈ አርድ የተጀመረውን በግብጽ ደቡባዊ ግዛቶች ላይ የተከፈተውን ወታደራዊ ዘመቻም አጠናክረው ቀጥለዋል::
ዓጼ ይስሃቅም( 1413-1430) በሰሜንና ሰሜን-ምእራብ ባሉ የአገውና የፈላሻ ማህበረሰቦች ላይ የጦር ዘመቻ በማካሄድና በማስገበር ግዛታቸውን አስፋፍተዋል:: በተጨማሪም በቀይ ባህር ጫፍ በተደጋጋሚ በመዝመት በዚህ ግዛታቸው ያሉ የአረብና የወላስማ አማጺያንን በመደምሰስ የወደብ ቁጥጥራቸውን በማጠናከር የሱማሌና የስሙር ማህበረሰቦችን አስገብረዋል (ሱማሌዎች በኢትዮጵያ ድርሳናት ለመጀመሪያ ግዜ በስም የተጠቀሱት በዚህ ዘመን በዓጼ ይስሃቅ ዜና መዋዕል ላይ ነው):: ኣል-ማቅሪዚ እንደመዘገበው በጊዜው የኢትዮጵያ የግዛት መጠን ከህንድ ውቂያኖስ በባብ ኣል-ማንዳብ እስከ ታክሩር ይደርስ ነበር:: በዚህ ወቅት ሌሎች የቱርክ ማምሉክ ስደተኞች በመሪያቸው በአልተንቡኛ እየተመሩ በ1420 ኢትዮጵያ በመድረስ ከዓጼ ይስሃቅ ዘንድ ጥገኝነት አግኝተዋል:: እነዚህ የልእለ ሃያሏ ቱርክ ጥገኞች ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ተቀጣጣይ ናፍጣን ያስተዋወቁ ሲሆን በግዜው በሸዋ-ቤተ-አምሃራ በተቋቋመው የጦር መሳሪያዎች ማምረቻ ተቋም ውስጥ ጎራዴ፣ ጦር፣ የብረት ጥሩርና ጋሻ እንዲሁም ሌሎች ዘመናዊ መሳሪያዎችን በማምረት አገልግሎት አበርክተዋል:: በተጨማሪም ለኢትዮጵያ የእግረኛና ፈረሰኛ ጦር የውጊያ ስልት ስልጠና ሰጥተዋል:: እጅግ በርካታ ቁጥር ካላቸው የግብጽ ክርስቲያን ስደተኞች መካከልም የተከበረው ፋክር ኣድ-ዳውላ ለዓጼ ይስሃቅ ግዙፍ መንግስት በንግድና አስተዳደር መዋቅር ዙሪያ የማማከር አገልግሎት ሰጥቷል:: የግብጹ ገዥ ሱልጣን ባርስባይ(1422-1438) በእየሩሳሌም ያለውን የክርስቶስ ቅዱስ መካነ መቃብር የሚገኝበትን ቤተ ክርስቲያን በማዘጋቱና የኮፕቲክ ክርስቲያኖችን በመበደሉ ዓጼ ይስሃቅ በ1424 እስከ አስዋን ድረስ ባለው የደቡባዊ ግብጽ ግዛት ላይ ወታደራዊ እርምጃ ወስደዋል:: ኣል-ማቅሪዚ እንደመዘገበው በደቡባዊ የግብጽ ግዛቶች ላይ በዓጼ ሰይፈ አርድ የተከፈተውን ወታደራዊ ወረራ ከ1380 ጀምሮ የነገሱት ነገስታት አጠናክረው ቀጥለውበት በአካባቢው የሚገኙትን ዘላን ማህበረሰቦች በማስገበር የቤተ-አምሃራን ግዛት ከህንድ ውቅያኖስ እስከ አስዋን ባለው የግብጽ ደቡባዊ ግዛት ድረስ ማስፋፋት ችለዋል (Maqrizi, according to Quatremere, E., Memoires geographiques et historiques sur l'Egypte et sur quelques contrees voisines, Paris, 1811, vol. 2, pp. 276-77; Schefer, C., Le Voyage d'outre Mer de Bertrandon de la Brocquiere, Paris, 1892, p.148) :: በተጨማሪም በዚህ ወቅት ዓጼ ይስሃቅ በምጽዋ አቅራቢያ የራሳቸውን ወደብ አስገንብተዋል:: ዓጼ ይስሃቅ በ1427 ለአራጎኑ አልፎንሶ 5ኛ እና ለዱክ ዲ ቤሪ የአውሮጳ መንግስታት መልእክተኛ በመላክ የተቀናጀ የክርስቲያን ግንባር በሚፈጠርበት መንገድ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን መሳሪያዎችና ባለሞያዎች እንዲላኩላቸውም ጠይቀዋል:: በዱክ ዲ ቤሪ ከተላኩት መሳሪያዎችና ባለሞያዎች ውስጥ የተወሰኑት ሸዋ-ቤተ-አምሃራ ሲደርሱ ከአራጎን የተላኩት ግን በግብጽ አደናቃፊነት ሳይደርሱ ቀርተዋል:: የአውሮጳ ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ከፍተኛ ጉጉት የነበራቸው ታላቁ ንጉሰ ነገስት ዓጼ ይስሃቅ በዱክ ዲ ቤሪ ከተላኩላቸው መልእክተኞች ውስጥ አንደኛውን አውሮጳዊ “በወኪልነት” በመቅጠር ተጨማሪ የዕደ ጥበብ ባለሞያዎችን፣ ግንበኞችንና መሳሪያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያመጣ መልሰው ወደ አውሮጳ ላኩት:: ይህ አውሮጳዊ የንጉስ ወኪል በ1432 በፔራ(ባይዛንቲየም) ለጌታው ባለ እጆችንና ግንበኞችን በመመልመል ላይ ነበር:: ሆኖም ሃገራቸውን ለማዘመን ከፍተኛ ቀናኢነት የነበራቸው ዓጼ ይስሃቅ ከዚህ ወቅት ቀደም ብሎ በ1430 ስለ ሃገራቸውና እምነታቸው ሲዋጉ በጦር ሜዳ ወድቀው ነበር:: ለቤተ-አምሃራ መንግስት የጦር መሳሪያዎችን በመሸጥና ሌሎች አገልግሎቶችን በመስጠት በዓጼ ይስሃቅ ዘንድ ታማኝነትን ያተረፈው የፋርስ(ፐርሺያ) ነጋዴና ሃገር አሳሽ ዓሊ ታብሪዚ በበኩሉ በንጉሱ ትእዛዝ ጽፎ ወደተለያዩ የአውሮጳ ነገስታት ባደረሰው ደብዳቤ የአውሮጳ መንግስታት የግብጽ ማምሉክ ሱልጣኖችን በባህር የሚያጠቁ ከሆነ ዓጼ ይስሃቅ በደቡብ ግብጽ ከሚገኘው የጦር ሰፈራቸው በመነሳት በእግረኛ ጦር ጥቃት በመሰንዘር በአባይ ሸለቆ ላይ የክርስትናን የበላይነት እንደሚመሰርቱ አስታውቆ ነበር::
ፈላስፋ፣ ሃይማኖተኛ፣ መሃንዲስ፣ ሊቅና በጠላቶቻቸው የሚፈሩ የተዋጣላቸው የጦር አበጋዝ የነበሩት ዓጼ ዘርዓያቆብ(1434-1438) በበኩላቸው ከግብጽ ሱልጣኖች ጋር ሰላም ለመፍጠር ከነበራቸው ፍላጎት የተነሳ በ 1437 ለግብጹ ገዥ ሱልጣን ባርስባይ ከመልካም ምኞት ደብዳቤ ጋር በጣም ውድ ዋጋ ያላቸውን በርካታ ስጦታዎችን ልከዋል:: ይህ የንጉሱ የሰላም ፖሊሲ በሁለቱ ሃገራት መሃከል የነበረውን ጸብ ለረጅም ግዜ አርግቦት ቢቆይም የሱልጣን ባርስባይን ሞት ተከትሎ የነገሰው ሱልጣን በግብጽ ቤተ ክርስቲያኖችን በማፍረሱና ክርስቲያኖችን በመበደሉ የተቆጡት ዓጼ ዘርዓያቆብ ለሱልጣኑ በላኩት ደብዳቤ ላይ በሳቸው መንግስት ስር ያሉ ሙስሊም ዜጎች በሱልጣኑ መንግስት ስር እንዳሉት ክርስቲያኖች እንደማይበደሉና ሃይማኖታቸውን በሙሉ ነጻነት እንደሚያራምዱ ገልጸው ሱልጣኑ ከተግባሩ ካልተቆጠበ በግዛታቸው ስር ያሉትን ሙስሊም ዜጎች እንደሚቀጡ በመዛትና የአባይ ወንዝ ምንጭ በሳቸው ቁጥጥር ስር መሆኑን በማስታወስ አስጠንቅቀዋል:: ይህን ተከትሎ የግብጹ ሱልጣን ወደ ኢትዮጵያ አምባሳደር በመላክ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጽመውን በደል እንደሚያቆም በማስታወቅ መልካም ግኑኝነትን ለመፍጠር ያለውን ፍላጎት ገልጿል:: ዓጼ ዘርዓ ያቆብ በዘመነ መንግስታቸው የወላስማ ሱልጣን የነበረውን ሱልጣን አህመድ ባድላይን(1432-1445) በ1445 ደዋሮ ላይ ከሞቃዲሾ(ደቡብ ሱማሌ) እስከ ቤት ማላ(ሰሜን ኤርትራ)ያሉ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦችን በሙሉ በማስተባበር ካሰለፈው ጦር ጋር ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ለቀጣዮቹ አርባ አመታት በሃገሪቱ መረጋጋት እንዲሰፍን አድርገዋል:: ዓጼ ዳዊት በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ያሉትን ሱልጣኔቶችና በቀይ ባህር ጫፍ ያሉ ዘላን ማህበረሰቦችን በጦር ሃይል ካረጋጉ በኋላ ፊታቸውን ወደ አውሮጳ በማዞር በአባቶቻቸው የተጀመረውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አጠናክረው ቀጥለውበታል:: በሮማና በኮንስታንቲኖፕል መሃል የተፈጠረውን መከፋፈል ለማስታረቅ በፍሎረንስ(ጣሊያን) ከ1439-1441 ድረስ በተደረገው ሃይማኖታዊ ጉባዔ ላይ ዓጼ ዘርዓ ያቆብ ተወካያቸውን በመላክ ተሳትፈዋል:: በ1450 በሲሲሊያዊው ፔትሮ ራምቡሎ መሪነት የቤተ-አምሃራ ተወላጅ አምባሳደሮቻቸውን ወደ አውሮጳ ልከዋል:: ይህ የልኡካን ቡድን ከአራጎን ንጉስና ከሮማ ጳጳስ ጋር በመገናኘት መክሯል:: ይህንን የልኡካን ቡድኑን ጉብኝት ተከትሎም በርካታ የዕደ ጥበብ ባለሞያዎችና የጳጳሳት ልኡካን ቡድን ከአውሮጳ ወደ ሸዋ-ቤተ-አምሃራ መጥተዋል:: በአራጎን ንጉስ የተላኩት ልኡካን በበኩላቸው ዓጼ ዳዊት የአባይን ወንዝ አቅጣጫ በማስቀየርና በግብጽ ላይ በእግረኛ ጦር በመዝመት የአራጎን መንግስት በእየሩሳሌም ላይ የሚከፍተውን የመስቀል ጦርነት እንዲያግዙ የሚጠይቅ የትብብር ደብዳቤ ለንጉሰ ነገስቱ አድርሰዋል:: ዓጼ ዘርዓ ያቆብ በአዳል ግዛታቸው ላይ ከፍተኛ ድል አስመዝግበው ከባድ የግብር ቅጣት እንዲጣልበት ከወሰኑ በኋላ ለመንግስታቸው ቋሚ የባህር ወደብ ስላስፈለገ በሰሜናዊ የቀይ ባህር ዳርቻ (ኤርትራ) ጦራቸውን በማስፈር በደጋው የኤርትራ ክፍል የሚገኘውን ማህበረሰብ በአንድ የባህረ ነጋሽ አስተዳደር ስር ካደራጁ በኋላ በምጽዋና በዳህላክ ደሴቶች ላይ የሚገኙትን የአረብና ሌሎች ሙስሊም አውራጃዎችን በማጥቃትና በማስገበር በምጽዋ አካባቢ የሚገኘውን የግራር ወደብ ጥገና እንዲደረግለት በማድረግ የደጋው ኢትዮጵያ የንግድ እንቅስቃሴ በሙሉ በወደቡ በኩል እንዲካሄድ አመቻችተዋል:: ይህም ስኬታቸው እንደ አባቶቻቸው ሁሉ በመላው አውሮጳ ከፍተኛ ስምና ዝናን በማትረፍ በአውሮጳዊያን ዘንድ የግብጽ፣ አረቢያና ሶሪያ ሙስሊም መንግስታትን ሃይል ይሰብራሉ የሚል ከፍተኛ ተስፋ እንዲጣልባቸው አድርጓል:: ዓጼ ዘርዓ ያቆብ በዘመነ መንግስታቸው ደብረ ብርሃንን(ሰሜን ሸዋ) የመንግስታቸው መቀመጫ አድርገው መስርተዋል:: በተጨማሪም በደብረ ብርሃን ግዙፍ ቤተ መንግስት ያስገነቡ ሲሆን መኳንንቶቻቸውና ካህናቶቻቸውም በዙሪያው ታላላቅ ቪላዎችንና ያጌጡ ቤተ ክርስቲያናትን ገንብተዋል:: ይህ የግንባታ ዓቢዮት ከመላው የሃገሪቱ ግዛቶች በርካታ ግንበኞችን፣ የዕደ ጥበብ ባለሞያዎችን፣ የጉልበት ሰራተኞችን፣ ገበሬዎችንና ነጋዴዎችን ሊስብ ችሏል:: በጊዜው ደብረ ብርሃን የትምህርት፣ የሃይማኖት፣ የፍልስፍናና የዕደ ጥበብ ማዕከል ሆና ከማገልገሏም በተጨማሪ የውጪውን አለም ትኩረትም በእጅጉ በመሳብ ትታወቃለች::
የዓጼ ዘርዓ ያቆብን መንግስት በመውረስ በተከታታይ የነገሱት የሸዋ ቤተ-አምሃራ ነገስታት ዓጼ ባዕደ ማርያም(1468-1478) ፣ ዓጼ እስክንድር(1478-1494)፣ ዓጼ ናኦድ(1494-1508)፣ ዓጼ ልብነ ድንግል(1508-1540)፣ ዓጼ ገላውዲዎስ(1540-1559)፣ ዓጼ ሰርጸ ድንግል(1563-1597) እና ዓጼ ሱሴኒዮስ(1607-1632) እንደ አባቶቻቸው ሁሉ በቱርኮች፣ በቱርክ ቅጥረኛ ጂሃዲስቶች፣ በኦሮሞ ጎሳዎች ወዘተ በሃገራቸው ላይ የተከፈተባቸውን ወረራ በመከላከል፣ ለስነ ጽሁፍና ስነ ህንጻ እድገት አይነተኛ ድጋፍ በማበርከትና ሃገራቸው ከውጪው አለም ጋር የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ልውውጥና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አጠናክረው በመቀጠል እስከ ዘመነ ጎንደር(1632-1769) ድረስ የመንግስታቸውን ታላቅነትና ነጻነት አስጠብቀው ዘልቀዋል:: በተለይ ዓጼ ልብነ ድንግል ከዓጼ ዘርዓ ያቆብ ዘመነ መንግስት ፍጻሜ ጀምሮ የተቋረጠውን የመስፋፋት ፖሊሲ በማደስ በሰሜንና በሰሜን ምእራብ ያሉ የሙስሊም በለው(በጃ) ጎሳዎችን በማስገበር ግዛታቸውን እስከ ሰናር(በዛሬው ሱዳን ውስጥ የሚገኝ) እና የሱዋኪን ወደብ ድረስ ማስፋፋት ችለዋል:: ፖርቹጋላዊው አልቫሬዝ ሲጽፍ በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ድንበር የሱዋኪን ወደብ ሲሆን የግብጽ ግዛት ወሰን ደግሞ ከሱዋኪን ወደብ በኋላ እንደሚጀምር ገልጿል:: አልቫሬዝ በተጨማሪም የዓጼ ልብነ ድንግል አጎት የሆነው ባህረ ነጋሽ ከዚህ የሃገሪቱ ድንበር በመነሳት በግብጽ አቅጣጫ 6 ቀናትን ተጉዞ የሚገኘው የኖቢስ(ሃማጅ፤ ሰናር ውስጥ የነበሩ ማህበረሰቦች) ሃገር ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን ጽፏል( Alvarez, vol.1, p.129; Alvarez, vol.2, p.450):: በዛሬው ሰሜን-ምስራቅ ሱዳን የሚገኙት የናይሎቲክ ገበሬዎችና የበጃ ዘላን ማህበረሰቦች መኖሪያ አካባቢዎች ለቤተ-አምሃራ መንግስት አይነተኛ የፈረስ፣ የባሪያና የወታደር ምንጭ እንደነበሩ ተመዝግቦ ይገኛል:: በደቡብና ምእራብ የሚገኙ የቤተ-አምሃራ ግዛቶችም እንዲሁ የባሪያ፣ የወርቅ፣ የከበሩ ማእድናት፣ የዝሆን ጥርስና የተለያዩ የግብርና ውጤቶች ምንጭ ነበሩ::
ይቀጥላል..........
(እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ዳግማዊት አክሱም ቤተ-አምሃራ የገናናው አክሱማዊ ስልጣኔ ተቀጽላ እንጂ አዲስ ስልጣኔ አይደለችም:: የቤተ-አምሃራ መስራች አባቶች፤ የስነጽሁፍና የኪነ ህንጻ ጥበቦች፤ ቋንቋ፤ ምግብና መጠጦች፤ አልባሳት፤ ሃይማኖት፤ ባህል፤ የጦር አደረጃጀት፤ የመኳንንት፣ የጦር አበጋዞችና የነገስታት የማዕረግ መጠሪያዎች፤ የአገዛዝና የአስተዳደር ዘይቤና መዋቅር ወዘተ በሙሉ ከአክሱም የሚቀዱ ናቸው:: በወቅቱ ይነገር የነበረው የአማርኛ ቋንቋ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ለዓጼ አምደ ጽዮን በወታደሮቻቸው በተገጠመላቸው የውዳሴ ግጥም ላይ ሰፍሮ እንደሚታየው ከዛሬው አማርኛ ይልቅ ለግዕዙ የቀረበ እንደነበር የሚታወቅ ነው:: )
ምስል1:- ከታች የቀረበው የአማርኛ ግጥም በ 1332 ለዓጼ አምደጽዮን በወታደሮቻቸው የተገጠመላቸው መወድስ ነው::
ምስል2:- በካርታው ላይ በቀይ ደምቆ የሚታየው መሬት የሰለሞናዊው ስርወ መንግስት ግዛት ነው

Tuesday, September 29, 2015

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ (ጥላዬ ታረቀኝ)



ሰንደቅ አላማ የአንድ ሀገር ህዝቦች ተስማምተውበት ይወክለናል ቢውለበለብ ይገልፀናል ብለው ለቀለማቱ ትርጉም በመስጠት ከምንም በላይ ክብራቸውን የሚገለፀበት የሀገር ውክልና የሚወስድ ወይም የሚገልፅ የሀገር ንብረት ወይም መግለጫ ነው ። ሰንደቅ ሀገራት ከሀገራት የሚለዮበት ትልቅ ምልክት ነው። ሀገራት ወይም ሰንደቅ አላማ ትልቅ ዝምድና አላቸው በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያለች ድንቅ ሀገር ለሰንደቅ አላማ ያላት ክብር ከፍተኛ ነው ። ሰንደቅንና ኢትዮጵያዊ የተቆራኞት ሀገሪቱ በንግስና መተዳደር ከጀረችበት ግዜ አንስቶ ትውልድ ለትውልድ እያስረከበ ለባንዲራ ያለው ፍቅር ከአያቶች እየተማረ ለልጆች እየተላለፈ የመጣበት ሁኔታ ነው። የነበረበው ሄደቱ ሳይቆራረጥ በዚያ ሰአት የነበረው ትውልድ ሲረከብ ሲያስረክብ ይዘቱን ቀለሙን ሳይቀየር ቢጎዝም በንግስና ግዜ የነበረው መሀል ላይ የሞሀ አንበሳ ምልክት ከሀይማኖት አንፃር ቢነሳም ቀጣይ የነበረ የባንዲራ ፈተናዋች የበዙ ቢሆንም ባንዲራዋ ግን ቀለሞን ሳትቀይር እዚህ ደርሳለች ።
የትውልድ ቅብብሎሽ ባንዲራዋን እዚህ ቢያደርሳትም ያኔ የነበረ ትውልድና አሁን ያለው ትውልድ ለባንዲራ ያለውን ክብር ከማወቃችን በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ለባንዲራ ያለውን ፍቅር መግለፅ ማስቀደሙ ሊገልፀው ይችላል። ብዬ በማሰቤ ይቺን ላስቀምጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመከራ ለችግር ለደስታ እንዲሁም ለሀገራዊ ክብር በአላት ላይ ይውለበለባል ሀገራችን ዳር ድንበሮ ተሰብሮ በተወረርንበት ግዜ አባቶች ህዝቡን ሲያነቁ ባንዲራህ ተደፎርል ድንበርህ ተጥሶል ለክብርህና ለባንዲራ ውጣ ብለው ያዙ ነበር። በዚያ ግዜ ለባንዲራ ያላቸውን ነገር ብንገልፅበት ሊገልፀው ይችላል ብዬ ያስብኩትን ይቺን እንመልከት ሸንጎ (.ፍርድ) ሲቀርቡ ሰው ሲበድላቸው እረ በባንዲራ ብሎ ከለመነ ጥፍተኛውም ጥፍቱን ያርማል በዳይም በደሉን ይቅር ይላል ተበዳይም የተጠራው #ባንዲራ በመሆኑ!!!
ለሀገራችንን ኢትዮጵያ ባንዲራ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መልስ ሊሆነው የሚችለው ባንዲራ ወይም ሰንደቅ አላማ ማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ዘውድ ወይም ደም ማለት ነው። ይሄ ለኢትዮጵያ ህዝብ መገለጫ የሆነው ሰንደቅ አላማ አሁን ላለው ትውልድ ምን ቦታ አለው ብለን መፈተሽ ተገቢ ነው ባይ ነኝ በነገራችንን ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ መንግስታት ሲቀያየሩ በመሳሪያ ስለሆነ ሁሉም ሲመጡ የህዝብን የሚውክለውን ሳይሆን የህዝብን ፍላጎት ሳይሆን እነሱ ይመቸናል ስልጣናችንን ሊያራዝምልን ይችላል ብለው ያመኑትን ከህዝብ ፍላጎት ውጪ ምልክት በመጨመር የስልጣን እድሜን ማርዘሚያ እንጂ ለሀገር ፍቅር ወይም ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ የለም ሁሉም ለራሱ በማሰብ እንጂ የፀና የኢትዮጵያን ባንዲራ የለም መንግስትም ቢወርድ ቀጣይነት ያለው ባንዲራ ባለመኖሩ የአሁን ትውልድ የኔ ነው ብሎ ሳይቀበል ያንተ ነው ተቀበለው ተብሎ ስለተቀበለው ጥቂት የዚህ ትውልድ ወጣቶች የባንዲራ ትምህርት ትርጉም ባይገባቸውም ለባንዲራ ያላቸውን ፍቅር ይሄ ነው ብሎ ለመተንበይ ያስቸግራል የአባቶቻቸው መሰረት ተቀይሮ ስላገኙት ይሄን ደግሞ ለዚህ መሰረት መናጋት ዋናው ተጠያቂ አስተዳዳሪ ሆኖ ራሱን የሾመው የህውሀት ኢህአዲግ መንግስት ነው ።
ከህዝብ ጋ ሆድና ጀርባ ሆኖ በራሱ ፍቃድ ትርጉም ሊሰጥ የማይችል ተጨማሪ ባእድ ከእምነት ከሀገሪቱ ነባራዊ ሆኔታ ጋ የማይገናኝ ለትውልድ መከራ የሚያመጣ እርስ በእርሶ እንዳይተማመን መልካም ያልሆነ የባንዲራውን ፎርም ወይም መልክት ያጠፉ የሰይጣን ምልክት ነው። የተባለወን መሀል ላይ በመሰንቀር ባንዲራውን ከህዝብ በመነጠል የራሱ በማረግ የባንዲራውን ትርጉም በማዛባት በሀገሪቱ የነበረውን የባንዲራ ቁጥር ከአንድ ወደ አስራ ምናምን ያሳደገ የህውሀት መንግስት ለባንዲራ የነበረውን ክብር ዝቅ አድርጎታል ።

በዚህም የተነሳ የአሁን ትውልድ የባንዲራ ትርጉም ጉራማይሌ እንዲሆን አድርጎል ከአስራ ምናምን ውጪ የሀገሪቱ ባንዲራ በሁለት በመክፈል
1 አረንጎዴ ቢጫቀይ (ንፁህ) ቀደም
2 አረንጎዴ ቢጫ ቀይ (መሀል ላይ ኮከብ በማረግ የሀገሪቱን ባንዲራ በሁለት በመክፈል የባንዲራ ፍቅር ይሁን የባንዲራ ትርጉም በማጥፍት ግንባር ቀደም ተወቃሽና ተከሳሽ ይህ ሀገሪቱን እየመራ ያለው መንግስት ነው ።
አሁን በህይወት የሌሉት ጠቅላይ ሚኔስተር አማካኝነት የባንዲራን ክብር ዝቅ በማድረግ ጨርቅ ነው እስከማለት ደረጃ ደርሶ የነበረበት ወቅት ሁሉ ነበር ይሄን የነበረ የሀገር ባንዲራ ትርጉም በማሳጣት ደረጃ ከፍተኛውን ሚና በመጫወት አሁን ሀገሪቱን በመሳሪያ ሀይል እየመራ ያለው ህውሀት ኢህአዲግ አስራ አራት ባንዲራዋችን በአንድ ሀገር ላይ እንዲውለበለቡና በአለም አቀፍ ደረጃ ሁለት ባንዲራዋች በዜጎች ደረጃ እንዲውለበለቡ ከፍተኛ አስተዋፅ አበርክቶል የስርአቱ ደጋፊዋች ባለአርማውን ወይም ሰይጣን የሰይጣን ምልክትን ያካተተውን ሲያውለበልቡ በዚህ አመት የሰይጣን ቤተመቅደሴ ነው በማለት ያስተዋቀውን ማስታወስ በቂ ነው በዋሽንግተን ዲሲ ሰሞኑን ቤተ መቅደሴን ከፍቻለሁ ምልክቴም ይሄ ኮከብ ነው።


በማለት ለቢቢሲ ይፍ በማድረግ በአለም ዜናውን አሰራጭቶል ይህ የሰይጣን ምልክት ደግሞ በኢትዮጵያ ባንዲራ መሀል ላይ ተለጥፎ ይገኛል በመሆኑም ሀገር ውስጥ በሀይል በህግ በህገወጥ መልኩ በማሰፈራራት እንዲውለበለብ ቢያረግም ከሀገር ውጪ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ግን ባንዲራውን አይቀበሉትም በብዛት ህዝብ የሚቀበለው አርማ የሌለወን .#አረንጎዴ #ቢጫ #ቀይ ሲሆን ብዛት ያለውተቀባይነትም አለው ይሄም ህዝቡን ይወክላል ።ይሄ ሆኖ ሳለ እውነቱ ስርአቱ ግን የብሄረሰቦችን እኩልነት እንዴት እንደሚወክል በፍጹም የማያሳየውን አና ታማኝነት የሌለው ከሃገሪቱ ሃይማኖታዊ ባህላዊ አና ማህበራዊ ዘይቤ ጋር የማይገናኘው ይህ ኮከብ ያለበትን ባንዲራ ሰንቅሮ ሃገራችን ላይ በፍቃድ ያውለበልባል በመሆኑም እኛን የሚወክለን መሀል ላይ ምንም የሌለበት አረንጎዴ ቢጫ ቀይ ነው ሰንደቅ ኣላማ መሃልላይ ያለው ባእድ ምስል መነሳት ኣለበት ::
ህዝብ ሀይል ነው በቅርብ ይቺ ንፁህ የኢትዮጵያ ባንዲራ ትውለበለባለች
ድል የህዝብ ነው #ባንዲራየ #አረንጎዴ #ቢጫ #ቀይ ቅን አሳቢው .#ጥላዬ #ታረቀኝ

Thursday, September 24, 2015

በአየር ኃይልና በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ውስጥ ያሉት በTPLF ብቻ የተያዙ ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች...





የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት
ክፍል 8

• ብ/ጀነራል መዓሾ ሀጎስ የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ደሳለኝ አበበ የአየር ኃይል የዘመቻ ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ሰለሞን ገ/ስላሴ የማዕከላዊ አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ፀጋዬ አርፋይኔ የማዕከላዊ አየር ምድብ ዘመቻ (ህወሓት)
• ሻምበል ገ/እግዚአብሄር ኃ/ስላሴ የምዕራብ አየር ምድብ 3ኛ ሚሳይል ክንፍ አዛዥ (ህወሓት)
• ሻምበል ዝናቡ አብርሃ የምዕራብ አየር ምድብ የ301ኛ አየር መቃወሚያ አዛዥ( ህወሓት)
• ኮ/ል ኪዱ አሰፋ የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ(ህወሓት)
• ሌ/ኮ ክብሮም መሃመድ የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ኃይሌ ለምለም የሰሜን አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ፀጋዬ ካህሳይ የሰሜን አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የአስተዳድርና ፋይናንስ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል አበበ ተካ የምስራቅ አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ሙሉ ገብሬ የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ኃላፊ (ህወሓት)
• ሻላቃ ፀጋዘዓብ ካሳ የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ክንፍ አዛዥ(ህወሓት)
• ሻለቃ ሀብቶም ዘነበ የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ምክትል ኃላፊ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር የስምንተኛ ታንከኛ ሻምበል አዛዥ ሻላቃ ተክላይ ወ/ገሪማ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር ምክትል የኃይል አዛዥ ብ/ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር 9ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ጥጋቡ ተወልደ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር 10ኛ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ገ/ህይወት አደራ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር የ17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል መለስ ብርሃን (ህወሓት)
• በዳርፉር የኢትዮጵያ ሰላም ማስከበር ድጋፍ ሰጭ ቡድን አስተባባሪ ኮ/ል ዮሴፍ አሮን (ህወሓት)
• በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ተክላይ ወ/ጊዮርጊስ (ህወሓት )
• በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ የዘመቻ አዛዥ ሻለቃ ሀጎስ ነጋሽ (ህወሓት )

Tuesday, September 22, 2015

ፕሮፓጋዳ ዓይን ያወጣ ውሸት ማቅረብ አይደለም።የሚሰራ መሆን አለበት። ጎብልስና ወያኔ

                              

ጎብስ_ደብረጽዮን
ፕሮፓጋዳ ዓይን ያወጣ ውሸት ማቅረብ አይደለም።የሚሰራ መሆን አለበት። ጎብልስና ወያኔ

ከቢላል አበጋዝ
ዋሽግቶን ዲ ሲ
ሰኞ ፣ ሴፕቴምበር 21 ቀን 2015
የወያኔ ትልቁን “ኩዴታ” ጥምረት ውህደትን “በሾኬ የጣለበትን” የወሬ ጋጋታ እንግዲህ አለፍነው። ተመስገን። ሰማይ አልተደረመሰም። የወያኔ ቲቪ ሰዓት እላፊ ሰራ። በዳያስፖራ ያሉ የወያኔ አሽከሮች “የፍየል ወጠጤ” ዓይነት መልክት አስተጋቡ። ወያኔን አትንኩብን አሉ። የአንድን ሰው መክዳትን ድል አድርገው ሊያደናቁሩ ተሟሟቱ። አዲስ የተሻሻለች ህወሃትን የሚሹ ምሁራንም የቆሙበት በግልጥ ታየ። ሌሎችም ጥምረት ውህደቱን ተቹ። ህብረት እንፍጠር ያላችሁ ሳይገባችሁ ነው አሉ። የሞላ መክዳትት ወሬ ጥቂቶችን አናዞ እያለፈ ነው።መጭውን የወያኔ “የረቀቀ ስለላ ውጤት” እስክንሰማ እንጠብቃለን።የሞላ አስከዶም ተገቢው ጎራ መዘነቅ ወሬው ቶሎ ከሰመ::ከዚህ የሚያልፍ አይደለም።ግን መጥኔ ለአዲሳባ!
ፕሮፓጋዳ ጥበብ ነው።ተንኮልም አለበት። ወያኔ ደግሞ በተንኮል እንጂ በጥበብ አይታማም። ፕሮፓጋዳ ዓይን ያወጣ ውሸት ማቅረብ አይደለም።የሚሰራ መሆን አለበት።ፕሮፓጋዳን በስልት ከያዙት ጋር ሲተያይ፡ ወያኔ ዛሬ ገና በድንጋይ ዘመን እየኖረ ነው።የወያኔ ፕሮፓጋዳ በመለስ አገዛዝ ይሻል ነበር።የአስራ አንድ ከመቶው “ዓመት ካመት እድገት”፤”አልሸባብ ሊወረን ነው””በቀን ሶስቴ መብላት”ትዝ የሚሉ ናቸው። ዛሬ በሞላ መክዳት የሆነውን የህወሃት ግርግር መለስን መቃብሩ ውስጥ ሆኖ የሚያወራጨው ነው።የሞላ መክዳት ጊዜ አለመግዛቱን መለስ ቶሎ ይረዳው ነበርና።አንድ የትጥቅ እንቅስቃሴ ብርታቱን የሚያገኘው ወይ በተሰዋ፤ በተሰዋች ጓድ ነው፤ወይ በከዳ፤ በከዳች ጓዲት ድርጊት የአባላት መብገን ነው። ከርእዮትና ከዓላማ ጎን ለጎን እኒህ ያሉት ተጨባጭ ክስተቶች ናቸው ትግልን ወደፊት የሚገፉት።የሞላ አስከዶም መክዳት በጊዜ መሆኑ ከፍ ካለ ጥፋት የሚሰውርና ለደምሂት ሰራዊት ጠብቆ መዋቀሪያ እድል ማስገኘቱ ይታመናል። ታች ከምናየው የፕሮፓጋዳ ሊቅ ከነበረው የአዶል ሂትለር ባለሟል አባባል ብዙ ታዝበን የወያኔንና አሽቃባጮቹን ጅል ድርጊት እንታዘባለን።ህዝባዊ ትግል የተራ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሚሆነው በህወሃቶች ጭቅላት ውስጥ ብቻ ነው።ህዝባዊ ትግል በተራ ፕሮፓጋዳ የሚገታ ቢሆን እንዴት ከየካቲት ስልሳ ስድስት አንስተን ከዚህ ደረስን? ፕሮፓጋዳንና ድንፋታ ለደርግ የእለት ተለት ተግባር አልነበረም ?እስቲ  ወደ ዮሴፍ ጎብልስ እንሂድ። እሱ እንዲህ ይላል፡
“ፕሮፓጋዳ ሰዎችን መሳብ፤ማሳመን እውነት  ነው ብየ ለተቀበልኩት፤ ይህ ነው ፕሮፓጋዳ ማለት ። ሲጀመር መግባባት አለ። ይህ መግባባት ፕሮፓጋዳን እንደ መሳሪያ ተጠቅሞ መግባባትን(ስብከትን) ወደ ፖለቲካ ይቀይረዋል።ማቸነፍ ዋናው ነገር ነው።ፕሮፓጋዳ የተራ ሰዎች ምግባር አይደም።የሙያተኞች ነው።ደስ የሚል ወይም በንድፈ ሃሳብ ትክክል መሆን የለበትም። የሚያስደንቁ፤የተዋቡ ንግግሮችን ባደርግ ሴቶችንም እምባም ባስረጭ ግድ አሰጠኝም።የፖለቲካ ንግግር ዓላማው ማሳመን ነው።እኛ ትክክል ነው የምንለውን።ክፍለ ሃገር ሆኘ የምለው በርሊን ሆኘ ከምለው ይለያል።ቤይሩት ሆኘ የምናገረው ፋረስ አዳራሽ ሆኘ ከምለው አይመሳሰልም።ይህ የንድፈ ሃሳብ ሳይሆን የተግባር ጉዳይ ነው። የጥቂት ገልጃጆች ማህበር ሳይሆን ሰፊውን ህዝብ የሚያንቀሳቅስ ነው የምንሻው።ፕሮፓጋዳን ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል። አእምሮን ማራኪ መሆን የለበትም።የፕሮፓጋዳ ተግባር ምሁራዊ እውነቶችን መፈተሽ አይደለም።እዲህ ያለው ፍተሻ የራሱ ጊዜና ቦታ አለው።እኔ እዲህ ያለውን እውነት የምፈትሸው ከቢሮዬ ተቀምጨ  እንጂ ከስብሰባ አዳራሽ ሆኘ አይደለም።”(1)
ወያኔ ህውሃት በሙስና የተዘፈቀና የተጠላ መንግስት ነው። ፕሮፓጋዳ አያሰነብተውም። ከላይ የጠቀስኩት ዮሴፍ ጎብልስ የናዚን ፓርቲ አላዳነም።ጎብልስን የጠቀስኩት ወያኔዎች የምትሰሩት የገልጃጃ ስራ እንጂ ፐሮፓጋንዳ አይደለም ለማለት ነው።ስራችሁ አያተርፍም።ዙሪያው ገደል ሆኖባችኋል። ከጭካኔአችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ በውሸታችሁ ነው የሚለያችሁ።ስለዚህ በጥቅም ከምትደልሉት በተቀር ሌላው ዛሬ በምን ይደግፋችሁ?ይህ የናተው ግዛት ሲያልፍ(በቅርቡ) “የውሸት ዘመን” የሚባል ታሪክ ይነገራል ብንል ስተት አይሆንም።የወያኔ ፕሮፓጋንዳ የቱ ይማርካል? ከህወሃት አበደን ምንም አይወጣም። ሺ ደምስ ቢለጠም ስኒ የምትሞላ አያመርትም።የህወሃት ፕሮፓጋዳ እውር ሌላውን እውር የሚመራበት ድራማ ነው።
ማንም ደካማ መንግስት በፕሮፓጋዳ አልዳነም።ወታደራዊ ደርግንም ፕሮፓጋዳ አልታደገውም።ዋንቻው  ዮሴፍ ጎብልስ እና ጌታውንም አላዳነም። ታአማኒነት ከሌለ ፕሮፓጋዳ ዋጋ የለውም። ተአማኒነት ታገኙበት የነበሩት ሃያ አራት ዓመታት አባክናችኋል።ተቃዋሚው እውነት ከሱ ጎን ስለሆነች ፕሮፓጋዳ አይነዛም።ራቡ እውነት ነው።የኑሮ ውድነቱ የሚታይ ነው።ስደቱ ምስክር አያስጠራም።መፈናቀል፤ሰቆቃ፤ግድያው ያንገሸግሻል።ህዝቡ በምቾት ተንደላቃችሁ በሙስና ተጨማልቃችሁ እንቀጥላለን በሚል ተስፋ የምትወራጩትን ህወሃቶች ይገረምባቸዋል።”እኒህ ጉዶች !” ይላል።እያለ እንደከረመው።
የሰሞኑ ወሬ መሰረት የሆነው ሞላ አስገዶም አሳዛኝ ነው።እንዴት ዓላማውን እንኳን አፍታቶ ማስረዳት የማይችል ሰው የሞቀ ኑሮውን ለዓላማው ሲል ሁሉን ትቶ በረሃ የወረደውን ይዘልፋል?እንደ አንድ ህብረተሰብ ወያኔ(መለስ) ከመጣ ወዲህ የነገሰው ጻረ ምሁርነት ውጤት ነው።ሞላም የዚህ ዝቅጠት ውጤት ነው።ወያኔ ያልተረዳው እንደ ህዝብ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከጊዜያዊ ወሬ ሸመት ማለፋችንና ውጤት ተኮር መሆናናችንን ነው።ድንበር ቆርሶ ሰጥቶ፤አርሶ አደሩን(ሃረሽታይ!)ከመሬቱ አፈናቅሎ ለውጭ ከበርቴ ቸብችቦ ስለ አገር አለማፈራረስ ማውራት እብደት ነው።እብዶች ስልጣን የያዙባት አገር ዛሬ ኢትዮጵያ ናት። ይህ ደግሞ አስጊ ነው። ለመሳለቅ አይደለም::ህወሃት በስልጣን ከቀጠለ ሊሆን የሚችለው ዘግናኝ ነው።
እስቲ ይህን እንጠይቅ።ደምሂት አስራ አራት ዓመት የፈጀ የንቧይ ካብ ነው የሞላ አስከዶም ባንዴ የሚንደው?ይህ እራሱንስ ሞላን አያስገምተውም ?እሺ ሰባት መቶ አስከትሎ ከዳ የተባለውን ብናምን አብዛኛውን ጦር ይዞ እንዳልወጣ የሚያመላክተው ወዲያው በማግስቱ ስለሌላ ውጊያ ሰማን።ገና ደግሞ ዝርዝሩን እንሰማ ይሆናል።አንድ ቀን ደግሞ አንድ የአውሮፓ ወይም የሌላ አገር ጋዘጠኛ ሁሉን ይዘረዝረው ይሆናል። ልክ ስዊድናውያኑ እነ ሺብዬ የኡጋዴኑን የወያኔ ግፍ እንደዘረዘሩት ማለት ነው።ምናልባት የሞላም ወታደራዊ ወንጀል ይዘከዘክ ይሆናል።
ሞላ ወንጀል ፈጽሟል።ለራሱ ምቾት በማድላት ጔዶቹን ከድቷል።የሞራል ብቃት፡የአስትሳሰብ እርጋታና ማጣቱና  ከቅሌት አለመራቁ በጣም አዋርዶታል።የህወሃት መሪዎች ከተዘቀጡበት ቁልቁለት ይዘውት ተንሸራተዋል።ሞላ ሌላው ቀርቶ እዚያው አስራ አራት ዓመታት አባክኖ ከሄደበት አገር የነበረው ታሪክ ያገናዘበ አልመሰለኝም።በ1980 መጀመሪያ የጀብሃ ወይም የኢልፍ ጦር ተበተነ።ትልቅ ገናና ጦር ነበር።ግን ኤርትራ የነበረውን ሁኔታን አልወሰነም።ጦርነትም አልቆመም።ታሪክ ጉዞውን ቀጠለ።እኔ እስከማውቀው በራሳቸው ድክመት የጠፉ የትጥቅ እንቅስቃሴዎች ጀብሃ፤ኢህአሰ እና የታሚል ነብር ይባሉ የነበሩ የሲሪላንካ ተዋጊዎች ነበሩ።የተቀረው ለታሪክ ምሁራን እተዋለሁ።መልእክቴ ጦር እዲህ በዋዛ አይበተንም።ነገ ጎንደር፤ትግራይ ወሎ ላይ ሲያርበደብዳችሁ የማን አገር ጦር መጣብን ልትሉ ይሆን? ይህን ጎርፍ በዛሬው ውሸት ልትገድቡት?ሰዓት ቆጣሪ ዘግን በእጅ በመያዝ የጊዜን(ታሪክን)ግስጋሴ ማቆም ይቻላልን?
የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መበታተን ዓላማው ከሆነ ህብረት ጥምረት ከጓሮው እንዲበቅል ለምን ይፈቅዳል?ማነው የመበታተንን፤የመክፋፈልን እቅድ በመንግስት ደረጃ የሰራበት ወያኔ ወይስ በሙስና ያልታማው የኤርትራ መንግስት? የኤርትራ መንግስት የወያኔ ወዳጅ ነበር።ይህን እናውቃለን። ዛሬ ግን አይደለም።በወያኔና በኤርትራ መንግስት መካከል ያጥፊና ጠፊ ቅራኔ ነው ያለው።የጥምረት ውህደት ሀይሎች ይህን ሳይገነዘቡ የዓመታት ጥረት አላደረጉም።ጋዜጠኛ ነኝ ያለ እንደ ኢሳት መሄድ የሚከለክለው አለ ማለት አይቻልም።አይቶ ነው ማውራት።የተረፈው የሻይ ስኒ ውስጥ ማእበል ነው።
ወያኔ ህወሃት ከኤርትራ በኩል ከሚመጣበት ጥቃት ይልቅ የራሱ ጉድለት ቁልቁለት እያወረደው ነው::የጥንታዊ ገናናው የሮማውያን አገዛዝን ምን ምክንያቶች ጣሉት?ሞላ አስገዶም አንዳንዴ እንኳን እያነበበ፤ እየተማረ ቢሆን ኖሮ በኤርትራ የቆየው የሮማውያን አገዛዝ ከአምስት መቶ የገነነባቸው ዓመታት በኋላ የተንኮታኮተው በሙስና፤በኑሮ ውድነት፤ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና  ወታደራዊ ሽንፈቶች መሆኑን ይረዳ ነበር። የህወሃትም እጣ ይህ እንደሆነ ይረዳ ነበር።ጣሊያን በምን ምክኛት ሊቸነፍ በቃ? በሰራው ግፍ አልነበረም?
ሞላ ሲከዳ በኤርትራ የተመቸ ኑሮውን ነው ያስታወሰው።ጓዶቹ የተጋዳይ ኑሮ እሱ ተንደላቆ እንደነበረ ተናግሯል።ይችኑ ምቾት ፍለጋ ህሊናውን ሸጠ።የትግሉ የታሪክ ጉዞ ግን አይቆምም።የሞላ አስከዶም ተገቢው ጎራ መዘነቅ ወሬው ቶሎ ከሰመ::የወያኔ የጅል ፕሮፓጋ መሪ ተዋናይ በመሆን የአስራ አራት ዓመታትን ትግል በክዳት መደምድም ዝቅ ያለ የአእምሮ እሴት ውጤት ነው።ወያኔ አይለወጥም።አይታረምም።አያቸንፍም።ፕሮፓጋዳው ጅል ነው!
1)     https://en.wikiquote.org/wiki/Joseph_Goebbels

አነድነት ሀይል ነው!
ድል ለመብቱ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ!
ኢትዮጵያ  በህዝቦችዋ አንድነትና ፍቅር ለዘለዓለም በነጻነት ትኑር!

የተናገሩት ከሚጠፋ . . . በኤፍሬም ማዴቦ


ephrem-madebo
የተናገሩት ከሚጠፋ . . .
በኤፍሬም ማዴቦ                                                                      
ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት። ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ። ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ። ለራሱ የገባዉን ቃል የማያከብርና ቃሌ ቃል ነዉ ብሎ የገዛ ራሱን የእምነት ዕዳ ያልከፈለ ሰዉ ለህዝብና ለአገር ቃል መግባት አይችልም። ዛሬ ወያኔን እናጥፋ ብሎ ካራ ጨብጦ አብሮኝ የቆመ ሰዉ ነገ ከወያኔ ጋር ሆኖ ካራዉን እኔዉ ላይ አዙሮ ባየዉ እሱ ቀድሞዉንም ካራ የጨበጠዉ ወያኔን ለማጥፋት ሳይሆን ስጋ ሊቆርጥብት ነዉና ብዙ አይገርመኝም። እንዲህ አይነቱን ለቁም ነገር ሲፈልጉት አልሰማ ብሎ ሆዱ ሲሞላለት ግን ሳይጠሩት አቤት የሚል ስጋ ወዳድ ሆዳም ደግሞ ኢትዮጵያ በየዘመኑ አፍርታለችና ብዙ ሊገርመን አይገባም።  ከሰሞኑ ከምድረ ኤርትራ የነፈሰዉ ነፋስ ያስተማረን አንድ ትልቅ ቁም ነገር ቢኖር እንዲህ አይነቱን ሞላ ጎደለ የሚባል የካራና የስጋ ጨዋታ ነዉ። አዎ! የካራ ጨወታ – ወዲህ ማዶ ስጋ ሊቆርጡበት ወዲያ ማዶም ስጋ ሊቆርጡበት።
“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” . . . ገዢዎቻችን በተለይ የዛሬዎቹ ቃል አባዮች እንደቆሻሻ ዕቃ መሬት ላይ ጣሉት እንጂ ቃል የዕምነት ዕዳ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ዘመን አይሽሬ የአገራችን አባባል ነዉ። አባቶቻችን የተናገሩትን ወይም ቃል ገብተዉ የተማማሉትን ነገር ከሚያጥፉ የወለዱትን ማጣት ይቀላቸዋል። እኛ ልጆቻቸዉ ግን ከዬት የመጣን ጉዶች አንደሆንን አላዉቅም ቃል አባይነታችን እኛን፤ ልጆቻቸንና አገራችንን ሲያጠፋ በአይናችን እያየን ቅር እንኳን አይለንም። “እመጣለሁ ብሎ ሰዉ እንዴት ይዋሻል፤ ማበል እንኳን አንቺን ምድር ያበላሻል” መሬት ላይ ጠብ የማይል ትክክለኛ አባባል ነዉ። አገራችን ኢትዮጵያ ትናንት እንሞትልሻለን ብለዉ ዛሬ በሚገድሏት ቃል አባይ ልጆቿ እየተበላሸች ነዉ። እነዚህ ቃልአባዮች የኢትዮጵያን የምድር ላይና የምድር ዉስጥ ኋብቷን አንጂ የገረጣዉን ፊቷን ማየት አይፈልጉም- አዎ ወያኔ የሚያየዉ ኃብትሽን፤ የሳዑዲዉ ሰዉ ወርቅሽን፤ ባዕድ ከበርቴዉ ለምለም መሬትሽን . . . ወይኔ ኢትዮጵያ ማን ይሆን የሚያየዉ የጠቆረዉ ፊትሽን፤ ማን ይሆን የሚያብሰዉ እምባሽን፤ እኮ ማን ይሆን የሚያቆመዉ መከራሺን . . .  ማን ይሆን?. . . ማን ይሆን?
የዛሬዋ ኢትዮጵያ አንድ ትዉልድ ዉሸት ብቻ እየሰማ ያደገባት የዉሸት መዲና ሆናለች። ጳጳሱ፤ ቄሱና ፓስተሩ “እኔ መንገድ፤ አዉነትና ህይወትና ነኝ” ያለዉን የሰማዩን አምላካቸዉን ረስተዉ ለምድር ዉሸታሞች አደሩ። ሂዱና ዋሹ ሲባሉ ሄደዉ ዋሹ፤ እዉነትን በዉሸት አስተባብሉ ሲባሉ አስተባበሉ፤ በሀሰት መስክሩ ሲባሉ አፋቸዉን ሞልተዉ በሀሰት መሰከሩ።  “ታላቁ መሪ” እየዋሸን ኖሮ እየዋሸን ሞተ። መታወቂያዉ ዉሸት ነዉና ሞቶም አልሞተም ተብሎ ተዋሸለት። ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ምን ለምዳ ትመጣለች እንዲሉ ሌላ ሁሉ ቢቀር ዉሸትን ይፀየፋል ተብሎ የተነገረለት የዛሬዉ ጠ/ሚኒስቴር ጭራሽ “ታላቁን መሪ” እንደዋቢ እየጠቀሰ ስራዉ ሁሉ ዉሸት፤ ዉሸት፤ ዉሸት ብቻ ሆኖ ቀረ። የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲከፈት ዉሸት ይናገራል፤ ሲዘጋ ደግሞ ነገ ስለሚዋሸዉ ዉሸት ያስባል። ጋዜጦች በስህተት አንኳን እዉነት አይጻፍባቸዉም። የኢቲቪ ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ ግማሽ ሰዐት የዋሸዉን ዉሸት ለማካካስ ዜናዉን አንብቦ ሲጨርስ ለ15 ደቂቃ ጎንበስ ብሎ ይሰግዳል።
ለረጂም ግዜ ተማምነን ጀርባችንን የሰጠነዉ ሰዉ ለጠላት እጁን ሰጥቶ ጦርነት ሲያዉጅብን አንዳንዴ በትግሉ ዉስጥ ማንን አምነን ጀርባችንን እንደምንሰጠዉ ግራ ሊገባን ይችላል። ከሰሞኑ የሰማነዉ ዜና እንዲህ ግራ የሚያጋባ ዜና ነዉ። ሆኖም ሳንተማመን ትግል ብሎ ነገር የለምና የትግል ጓዶቻችንን ማመን ብርታት እንጂ ደካሞች እንደሚሉት ሞኝነት ወይም የዋህነት አይደለም። በጓዶቻችን ላይ ክህደት ፈጽመን ከምናሰቃያቸዉ እኛ ብንሰቃይ ይሻላል፤ ደግሞም ጓዶቻችንን ማመን አቅቶን በጥርጣሬ ተፋጥጠን ባለንበት ከምንረግጥ አንዳንዴ አዉቀንም ቢሆን ብንታለል ብዙ መንገድ መጓዝ እንችላለን። ትግል በተለይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ከሚያስተምረን ትምህርቶች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ሌሎች በኛ ላይ እምነት እንዲኖራቸዉ ከፈለግን እኛ አስቀድመን ልናምናቸዉ አንደሚገባን ነዉ። አለዚያ ሁለታችንም አንተማመንም። አለመተማመን ደግሞ ያጠፋፋናል እንጂ አንድ ቤት ዉስጥ አብሮ አያኖረንም። እንደኔ እንደኔ የወያኔን ስርዐት ደምስሰን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር የምናደርጋት እያንዳንዳችን ለትግል ጓዶቻችን የገባነዉን ቃል ሰብረን ረጂም ህይወት ከመኖር ቃላችንን አክብረን ዛሬዉኑ መሞትን ስንመርጥ ብቻ ነዉ። ወያኔ አንደ እሳት የሚፈራዉና በፍጹም የማያሸንፈዉ አንዲህ አይነቱን ከብረት የጠነከረ ጽኑ አቋማችንን ብቻ ነዉ። ለዚህ ነዉ እንዲህ አይነት ጽናት የሌላቸዉን ደካማ ግለሰቦች ፈልጎ እያማለለ ጽናታችንን የሚፈታተነዉ። ከሰሞኑ ለህዝብ ከመታገል ህዝብን መታገል መርጦ ከለየላቸዉ የህዝብ ጠላቶች ጋር የተቀላቀለዉ ሞላ አስገዶም ለዚህ ዉሳኔ የበቃዉ ህዝባዊዉ ትግል የሚፈልገዉ የአለማ ጽናት የሌለዉ ደካማ ግለሰብ ስለሆነ ብቻ ነዉ። ዉድ ኢትዮጵያዉያን ክህደት ትናንት ነበር፤ ዛሬ አለ፤ ነገም ይኖራል። ስለዚህ ክህደት ሊያስተምረን እንጂ በፍጹም ሊያስበረግገንና አንገታችንን ሊያሰደፋን አይገባም። ክህደትና ከሀዲዎችን እያሰላሰልን የምንኖር ከሆነ የበለጠ እንዲጎዱን ተጨማሪ ዕድል እንሰጣቸዋለን እንጂ ሌላ ምንም የምንፈይደዉ ፋይዳ የለም።
ሞላ አስገዶም እሱን የመሰሉ ደካማ ጓደኞቹን ከተቀላቀለ በኋላ መቀሌ፤ አዲስ አበባና አዳማ ዉስጥ ክህደቱን አስመልክቶ እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ሦስት ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ሰጥቷል። እርግጠኛ ነኝ ይህ ቁርስ ላይ የተናገረዉን ምሳ ላይ የማያስታዉስ ግለሰብ በተያዘለት የጉብኝት ሰሌዳ መሠረት ዘጠኙን ክልሎች የሚዞር ከሆነ ዘጠኝ የተለያዩና እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ምክንያቶችን መደርደሩ አይቀርም። የወያኔ የመረጃና የደህንነት መ/ቤት ተብዬዉም ቢሆን ምን ያህል የዉሸትና የጉራ ቤት ለመሆኑ መረጃ ብሎ የለቀቃቸዉን ዉሸቶችና ቱልቱላዎች መጥቀሱ ይበቃል። ለምሳሌ የመረጃና ስለላ ድርጅቱ ከአንድ አመት በላይ ከሞላ አስገዶም ጋር በሚስጢር ይሰራ እንደነበር ተናግሯል። ይህ እዉነት ከሆነ የደምህት ታጋዮች በዚህ አንድ አመት ግዜ ዉስጥ በወያኔ ታጣቂዎችና ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ለወሰዷቸዉ እርምጃዎች በተለይ እግር ኳስ ጨዋታ በመከታተል ላይ እንዳሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር እንዳለ ለተደመሰሱት የኢትዮጵያ ወታደሮች ተጠያቂዉ ከሞላ አስገዶም ጋር ይሰራ የነበረዉ የወያኔ የመረጃና የስለላ ድርጅት ነዉ ማለት ነዉ።

ሞላ አስገዶም ትናንት ከኛ ጋር ሆኖ እኛ ሲል ነበር፤ ዛሬ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጠለቶች ጋር ሆኖ እኛ ይላል። ይህ ሰዉ  “እኛ” ሲል የሱ እኛ እነማንን እንደሚያጠቃልል አይታወቅም፤ እሱ እራሱም የሚያዉቀዉ አይመስለኝም። ሞላ አስገዶም ወያኔን እንደተቀላቀለ አፉን ሞልቶ ጥምረቱን የፈጠርነዉ “እኛ” ነን ብሎ ሲናገር በተደጋጋሚ ተደምጧል። ጥምረቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ህዝባዊ ትግሉ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ዉጤት ነዉ እንጂ ሞላ አስገዶም ስለፈለገዉ የሚፈጠር አለዚያ የሚቀር የሞላ አስገዶም የቤት ዉስጥ ዕቃ አይደለም። ደግሞም እንደ ሞላ አስገዶም ፍላጎት ቢሆን ኖሮ የደምህት ጥምረቱ ዉስጥ መግባት ለግዜዉም ቢሆን ሊዘገይ ይችል ነበር። ደምህት ጥምረቱ ዉስጥ ገብቶ አገር አድን የጋራ ንቅናቄዉ የተፈጠረዉ የደምህት ሠራዊትና ከሞላ አስገዶም ዉጭ ሁሉም የደምህት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሌሎች ኢትዮጳያዉያን ወገኖቻቸዉ ጋር ሆነዉ በጋራ ለመታገል በመወሰናቸዉ ነዉ። የሞላ አስገዶም ፈርጥጦ ወያኔ ጉያ ዉስጥ የመሸጎጡ ዋነኛዉ ምክንያትም የዚህ ዉሳኔ ዉጤት ነዉ እንጂ የወያኔ መረጃና ስለላ ድርጀት ሚስጥራዊ ግንኙነት ዉጤት አይደለም። ሌላዉ እርስ በርሱ የሚጋጭ የወያኔ ዉሸት –  በአንድ በኩል ሞላ አስገዶምና የደምህት ሠራዊት ሙሉ ትጥቃቸዉን እንደታጠቁ ጠቅልለዉ ወደ አገራቸዉ ተመለሱ የሚለዉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቁጥሩ ወደ 700 የሚጠጋ የደምህት ሠራዊት ወደ አገሩ ተመለሰ የሚለዉ የተምታታ ዘገባ ነዉ። እዚህ ላይ የደምህትን ሠራዊት ብዛት መናገሩ አስፈላጊ ባይሆንም ግንዛቤ ማግኘት የፈለገ ሰዉ ግን ተመድ ያወጣቸዉን ሪፖርቶች መመልከቱ የሚበቃ ይመስለኛል። ደግሞም ሞላ አስገዶም አታልሎ መንገድ ካስጀመረዉ ሠራዊት ዉስጥ ገሚሱ ወደ ትግሉ ሜዳ ተመልሷል፤ የተቀረዉ ደግሞ ወደ ትግሉ ሜዳ ካልተመለስኩ እያለ ከሱዳን ባልስልጣኖች ጋር እየተደራደረ ነዉ። በነገራችን ላይ የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ሞላ አስገዶም አታልሎ ሀምዳይት ከወሰዳቸዉ በኋላ ትግል ወይም ሞት ብለዉ ተመልሰዉ ከትግል ጓዶቻቸዉ ጋር ከተቀላቀሉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን ጋር አብሮ ቡና ጠጥቷል።

ጓዜን ጠቅልዬ ትግሎ ሜዳ ከመግባቴ በፊትም ሆነ ከገባሁ በኋላ የደምህት ስም በተነሳ ቁጥር አብረዉ የሚነሱ ሁለት መላምቶች አሉ። አንደኛዉ መላምት ደምህት የኤርትራ መንግስት ሆን ብሎ የፈጠረዉና ጭራሽ ኤርትራ ዉስጥ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ተክቶ በመንግስታዊ ተቋሞች ጥበቃና ደህንነት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነዉ የሚል መላምት ሲሆን ሁለተኛዉ መላምት ደግሞ ሞላ አስገዶም በኤርትራ መንግስት ድጋፍ ሁለተኛዉ መለስ ዜናዊ ሆኖ ህወሃትን ተክቶ አትዮጵያን ይመራል የሚለዉ መላምት ነዉ። ደግነቱ የነዚህ መላምቶች የማዕዝን ራስ የሆነዉ ሞላ አስገዶም ኮብልሎ ወያኔን መቀላቀሉና ከተቀላቀለ በኋላ የሰጣቸዉ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ሁለቱንም መላምቶች እንዳልነበሩ አድርጓቸዋል። እኔን አልገባ ያለኝና በጣም የሚገርመኝ ግን በአንድ በኩል የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ትብብር እንዲፈጥሩ አይፈልግም ይባላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጥምረቱ የተፈጠረዉ በሻዕቢያ ግፊት ነዉ ይባላል። መቼም ገና በልጅነቴ ካልጃጀሁ በቀር ሻዕቢያና የኤርትራ መንግስት መሃል ልዩነት ያለ አይመስለኝም። ሌላዉ የሰሞኑ አስቂኝ ድራማ ደግሞ ሞላ አስገዶም ጥምረቱን የፈጠርነዉ እኛ ነን ሲል የሱን መኮብለል አስመልክቶ የሚሰጠዉ አስተያያት ደግሞ ሞላ አስገዶም ጨርቁን ጠቅልሎ ወያኔን የተቀላቀለዉ ብርሀኑ ነጋ በኤርትራ መንግስት ግፊት የጥምረቱ ሊ/መንበር መሆኑ አልዋጥ ብሎት ነዉ ይባላል።

ሌላዉ አሁን በቅርቡ ወይም ከሞላ አስገዶም መኮብለል በኋላ የተጠነሰሰዉ መላምት ደግሞ ደምህቶች እራሳቸዉ ኤርትራ ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ድርጅቶች በወያኔ ስርዐት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መዉሰድ እንዳይችሉ ሆን ተብለዉ በወያኔ የተፈጠሩ እንቅፋቶች ናቸዉ የሚለዉ መላምት ነዉ። በኔ ግምት ይህኛዉ መላምት ከሁሉም መላምቶች የከፋና እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ጽንፈኛ መላምት ነዉ። እንደዚህ መላምት ፈጣሪዎች አባባል የትግራይ ህዝብ በህወሃት አመራር በደል አይደርስበትም ወይም የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ሆኖ የህወሃትን ግፈኛ ስርዐት አይታገልም ማለት ነዉ። እንዲህ አይነቱ ጭፍንነትና ጠባብነት የሚመነጨዉ ደግሞ ሞላ አስገዶምንና ደምህትን ወይም ህወሃትንና የትግራይን ህዝብ ለያይቶ ማየት ካለመቻል አባዜ ነዉ። በደርግ ስርዐት ዉስጥ ጭቆናዉና በደሉ በዛብኝ ብሎ ጠመንጃ ያነሳዉ ጀግናዉ የትግራይ ህዝብ ህወሃት ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ተነጥሎ እንዲታይ ለማድርግ የሚሸርብበትን ሤራና የሚያደርስበትን ግፍና መከራ አፉን ዘግቶ የሚቀበልበት ምንም ምክንያት የለም። ስለዚህ ደምህት የትግራይ ህዝብ ብሶትና ምሬት አምጦ የወለደዉ ፀረ ህወሃት ንቅናቄ ነዉ እንጂ ወያኔ የፈጠረዉ ድርጅት አይደለም፤ሊሆንም አይችልም። ሞላ አስገዶምም ቢሆን የራሱ የተጠረቃቀመ ድክመት ከንቅናቄዉ ሊ/መንበርነቱ እንደሚያስነሳዉ ሲያዉቅ የፈረጠጠ ፈርጣጭ እንጂ እሱና ወያኔ እንደሚሉት የአንድ አመት ቀርቶ የአንድ ወርም ተከታታይ ግንኙነት አልነበራቸዉም።

ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረከ ብቅ ብለዉ የጠፉትንም ሆነ ዛሬም ድረስ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ባህልና ድርጅታዊ አሰራር ስንመለከት የድርጅቶች ህልዉና መመዘኛና የማንነታቸዉ መለኪያ ቆምንለት የሚሉት አላማ ሳይሆን የመሪዎቻቸዉ በተለይ የዋናዉ መሪ ተክለሰዉነት ነበር። የድርጅት ወይም የፓርቲ ሊ/መንበር ከድርጅቱ ባለይ ነዉ፤ እሱ ይሁን ያለዉ ይሆናል፤አይሁን ያለዉ አይሆንም። ብዙ ግዜ የድርጅት/ፓርቲ ሊ/መንበር ድርጅቱን የማፍረስ አቅም ጭምር አለዉ። ይህንን ደግሞ በቅርብ ግዜ ታሪካችን በተደጋጋሚ አይተናል። አንድን ድርጅት ወይም ፓርቲ አባላት ሲቀላቀሉ የሚመለከቱት የፓርቲዉን ሊ/መንበር እንጂ የፓርቲዉን የፖለቲካና የኤኮኖሚ ፕሮግራም አይደለም። የፓርቲ ሊ/መንበርም ቢሆን የኔ የሚላቸዉን ሰዎች ነበር እየመረጠ የሚያሰባስበዉ። እንደዚህ አይነቱ የፓርቲ አደረጃጀትና አሰራር አሁን እየተቀየረ የመጣ ቢሆንም ለረጂም ግዜ የፖለቲካ ትግላችን ችግር ሆኖ ቆይቷል። ሞላ አስገዶም በቅርቡ የደምህትን ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ይዤ ኢትዮጵያ ገባሁ ብሎ በድፍረት የተናገረዉ ንግግር ይሄዉ የድርጅት ሊ/መንበር ያሰኘዉን ሁሉ ማድረግ ይችላል የሚለዉ የቆየ የፖለቲካ ባህላችን በሽታ ተጠናዉቶት ነዉ። “ዝንጀሮዉን ከጫካ ያዉጡታል እንጂ ጫካዉን ከዝንጀሮዉ ዉስጥ አያወጡትም” የሚል ብህል አለ፤ ትክክለኛ ብህል ነዉ። ሞላ አስገዶም ህወሃት/ወያኔ የኢትዮጵን ህዝብ በአጥር እየለያየ በትናናንሽ ጎጆዎች ዉስጥ ማኖሩ አልዋጥ ብሎት ሁሉንም የሚያቅፍ ሰፊ ቤት ሰርተን ኢትዮጵያን የዲሞክራሲ አገር እናደርጋለን ብሎ ለብዙ አመታት የታገለ ሰዉ ነዉ። ችግሩ ሞላ አስገዶም ነዉ ከነዚያ ትናንሽ የወያኔ ጎጆዎች የወጣዉ እንጂ ትናንሽ ጎጆዎቹ ከሞላ አስገዶም ዉስጥ ስላልወጡ እንደ ማግኔት እየሳቡት ወደነበረበት ቦታ መልሰዉታል። ለሁሉም የሞላ አስገዶም ታሪክ ሲጻፍ – መጣና ሄደ ከሚሉ አምስት ሆሄያት የዘለለ ምንም ቁም ነገር የለዉም። እየመጡ መሄድና እየሄዱ መምጣት ደግሞ ትናንሽ ቤት የሚናፍቃቸዉ ትናንሽ ሰዎች እስካሉ ድረስ ይቀጥላል።

ሁለት ሺ ሰባት ሊጠናቀቅ ሦስት ቀን ሲቀረዉ አንድ የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ጆሮ የሳበ ዜና ቴሌቪዥኑን፤ ሬድዮኑን፤ ጋዜጣዉንና ድረገጹን ተቆጣጠረዉ። ዜናዉ የወያኔ/ህወሃትን ስርዐት በመሳሪያ ኃይል የሚታገሉ አራት ድርጅቶች አገር አድን የጋራ ንቅናቄ ፈጠሩ የሚል የአዲስ አመት የምስራች ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጂም ዘመን የናፈቀዉ የምስራች ነበር። ግን ምን ያደርጋል – በጥባጭ እያለ ንጹህ ዉኃ አይጠጣምና ይሀንን የአዲስ አመት የምስራች ሰምተን ሳናጣጥም ነበር የሞላ አስገዶምን ዜና ክህደት የሰማነዉ። አስደንጋጭ ዜና ነበር። በእርግጥም የአራት ድርጅቶች ጥምረት ተፈጠረ የሚል ዜና በተሰማ ማግስት የጥምረቱ ምክትል ሊ/መንበር ሠራዊት እየመራ ሄዶ ወያኔን ተቀላቀለ የሚል ዜና መስማት የሚያስደነግጥና በመጀመሪያዉ ዜና ላይ ቀዝቃዛ ዉኃ የቸለሰ ልብ ሰባሪ ዜና ነዉ። ደግነቱ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ። የሞላ አስገዶም መክዳት ተራ ዜና ነዉ ማለቴ አይደለም። ግን ሞላ አስገዶምና የወያኔ መረጃ ድርጅት በትብብር ሠራነዉ ያሉት አዲስ ድራማ ተዉኔቱ ሳይጻፍ አየር በአየር የተከወነ ምናቡ ያልተባ ድራማ በመሆኑ ድራማዉ ከያኒዉን ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብና ለአንድነቱና ለነጻነቱ የሚታገሉ ልጆቹን በከፍተኛ ደረጃ የጠቀመ መሆኑን ማሳዉቁ አስፈላጊ ይመስለኛል።

ደምህት በዚህ የወያኔ ድራማ ዉስጥ በእሳት ተፈትኖ ወርቅነቱን አረጋግጧል። ሞላ አስገዶም የደምህትን ሠራዊት ለወያኔ አስረከብኩ ብሎ በተናገረ ማግስት የደምህት መሪዎች የሰጡት አርቆ አስተዋይነት የታየበት አመራርና ያሳዩት ቆራጥነት የፖለቲካ ድርጅቶቻችን የደረሱበትን የዕድገት ደረጃ በግልጽ አሳይቷል። ደምህት እራሱም እንደ አንድ የትግል ድርጅት የተደቀነበትን አደጋና ፈተና በጣጥሶ በመዉጣት በትናንሾችና በደካሞች ሴራ በፍጹም የማይናጋ ጠንካራ ድርጅት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። የዛሬዉ ደምህት ዉስጡን ከአድርባዮች ያፀዳ ሁለትና ሦስት እርምጃዎች ወደፊት የተራመደ ጠንካራ ድርጅት ነዉ። እርግጠኛ ነኝ ይህ የደምህት መሪዎች ያሳዩት አስተዋይነት፤ ጽናትና ቆራጥነት እኔ የምፈልገዉ ነገር ካልሆነ ድርጅቱን በአፍጢሙ እደፋዋለሁ ብለዉ ለሚያስቡ ዕብሪተኛ መሪዎች ጥሩ ትምህርት ነዉ። ሌላዉ የሞላ አስገዶም ክህደት በግልጽ ያሳየን ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ የሀዝብ መብትና ነጻነት ይከበር በሚሉ የነጻነት ሀይሎችና ህዝብን ረግጠን እንገዛለን በሚሉ ፀረ ህዘብ ሀይሎች ለሁለት መከፈሉን ነዉ። ወደድንም ጣላን ካሁን በኋላ ያለን አማራጭ ሁለት ብቻ ነዉ፤ ወይ ወያኔ ሆኖ ከህዝብ ጋራ መዋጋት ወይም ከህዘብ ጋር ሆኖ ወያኔንና ስርዐቱን መዋጋት። ሞላ አስገዶም ጎራዉን ለይቷል፤ እኛም ጎራችንን እንለይ። መኃል ቆሞ መመልከት አብቅቷል።

ጠላቴን አግዝፌ መመልከት አልወድም፤ ትንሽ ነዉ ብዬም ጠላቴን በፍጹም አልንቅም። በቅርቡ የወያኔ የመረጃና ደህንነት መ/ቤትና ሞላ አስገዶም ከአንድ አመት በላይ አብረን ሠራን ያሉትን የጀማሪዎች ስራ ስምለከት ግን ወያኔ/ህወሃት “የምትሰሩትን ብቻ ሳይሆን የምታስቡትን ጭምር የሚያይ አይን አለኝ” እያለ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማስፈራራት ዉጭ የረቀቀ የመረጃ ስራ መስራት ቀርቶ አረፍተነገሮችን አገጣጥሞ ለጆሮ የሚጥም ንግግር ማድረግ የሚችል አዋቂ የሌለበት የባዶዎች ድርጅት መሆኑን ነዉ የተረዳሁት። ሞላ አስገዶምም በወዶገባነት ሄዶ የተቀላቀለዉ ይህንኑ አዋቂ የሌለበትን እሱን የመሰለ ድርጅት ነዉ። ይህንን ደግሞ እስከዛሬ በሰጣቸዉ ቃለመጠይቆች በግልጽ አይተናል። ህወሃት/ወያኔን እስከዛሬ በሥልጣን ላይ ያቆዩት ሁለት ነገሮች ቢኖሩ አንዱ ጠመንጃ ሁለተኛዉ የኛ የነጻነት ኃይሎች መበታተን ብቻ ነዉ።

ነገ የምንፈልጋት ኢትዮጵያ እንደ መኪና ተገጣጥማ አትጠብቀንም – የዛሬዉ ጥረታችንና ድካማችን ዉጤት ናት። ኢትዮጵያና ህዝቧ ከወያኔ ሲፀዱ የሚነፍሰዉ የነጻነት አየር ሁላችንንም ቢያስደስትም ደስታዉ የሚገለጸዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ። ዛሬ ከጠላት ጋር ተፋልመን የተቀማነዉን ነፃነት ማስመለስና እንደገና እንዳንቀማ ነቅቶ መጠበቅ ግን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት ነዉ። እንግዲህ ወገን ወገባችንን ጠበቅ የምናደርግበት ግዜ አሁን ነዉና ሁላችንም በየተሰለፍንበት መስክ እንበርታ። ጠላታችን ጠንካራ መስሎ የሚታየዉና ያለ የሌለ ጡንቻዉን የሚያሳርፍብን የማይቀረዉን ድል ማሽተት ስንጀምር ነዉ። የድል መአዛችንን የምናሸትበት ግዜ ደግሞ ሩቅ እንዳይመስለን ነገና ከነገ ወዲያ ነዉ። ከወላዋይና እዚህም እዚያም እየዘለለ ከሚያዘናጋን አጉል ጓደኛ አንዱኑ የለየለት ጠላት ይሻላልና የሞላ አስገዶም ክህደት ትግላችንን ሊያጠራዉና መንገዳችንንም ሊያሳጥረዉ ይገባል እንጂ በፍጹም ግራ ሊያጋባን አይገባም። አይዞን. . .  ሞኝ ከዘመዱ ከሚያገኝዉ ጥቅም አዋቂ ከጠላቱ የሚያገኘዉ ጥቅም ይበልጣልና ጠላቶቻችን የፈጠሩልንን አጋጣሚዎች ሁሉ በሚገባ እንጠቀምባቸዉ እንጂ ለጠላት አንመቻች። ጠላታችን እየተሳሳተልን ነዉ፤ ጠላት ሲሳሳት ማቋረጥ ነዉር ነዉ። ቸር ይግጠመን!!!

Friday, September 18, 2015

The sun is shining over Ethiopia

 

by Yilma Bekele
Ethiopia has been in darkness. We had light before most but that is history. We can recite our ancient history; write beautiful poetry extolling our virtues and fill a library with our traditional lore unfortunately it is not something we can take to the bank. It is not all lost. Ethiopia and her wellness has been woven into our soul. Thus today where ever we go we survive and thrive. Don’t take the fact you walk with your head high for granted my friend, that pride in you is cultivated and nurtured.
The Ottoman Turks, the Egyptians, the British, the French, the Italians have all tried to force their ways on us. It just did not work. Outsiders have learnt their lesson and have stopped trying force to make us serve their interest. It is the homegrown variety that has become a challenge. It could be a (seyawkush yinkush ሲያውቁሽ ይንቁሽ) situation where naturally one disarms in the presence of family and friends. Sooner or later one member goes rogue. It never fails. Throughout our history we have encountered such situations where kings, warlords or madmen have fought for power and glory. TPLF is our child gone rogue.
TPLF is the worst internal enemy faced by our county. There isn’t any aspect of our culture and history they have not tried to contaminate with negativity and hate. For over thirty years they have systematically worked on destroying the unity and strength that has taken hundreds of years to build. It is due to the solid foundation that our dear country has been built on that they are unable to even cause a little crack let alone a fissure. We are grateful to all those that sacrificed and painstakingly built this formidable home we call Ethiopia.
The current struggle being waged by TPLF on one side and Democratic forces on the other is about the kind of Ethiopia we want to build on the foundations already laid by our ancestors. Instead of building on that and adding value we have been busy subtracting, dividing and undermining our precious asset.
On this side we have the current Ethiopian government led by Tigrai Peoples Liberation Front (TPLF) that has been in power for the last twenty two years uninterrupted. The TPLF Party with its clueless and unwritten guiding dogma it calls ‘Revolutionary Democracy is based on the following principles:
• The Ethiopian people are not ready for Democracy.
• The vanguard TPLF will oversee the development of Democracy.
Despite what the regime and its international supporters claim this arrangement has not worked well for the average Ethiopian. There is no need to try to convince an Ethiopian how bad the Tigrai People’s party has been to our country. All one has to do is look around one’s own family and ask ‘how are you doing?’ If you do not know of a family member in distress you my friend is an exceptional Ethiopian. We all salute you but that unfortunately is not the norm.
That is why there are many that have decided to sacrifice life and family and stood against the tyranny of the Tigrai Peoples Liberation Front. We Ethiopians are such a lucky people to have been able to produce such dynamic and selfless leaders that would rather suffer than accept injustice.
Kinijit is the grandfather of all independent movements in Woyane era politics. Kinijit beyond a shadow of doubt showed how hollow and wild Woyane’s are. Before Kinijit we used to view Woyane as being benign with no harmful effect. Thanks to Kinijit Woyane was forced to show what a malignant tumor it is.
Ever since then many have tried to work within the system Woyane created. We are finding out even that is not possible. The brave leaders and members of Semayawi Party are a living testimonial that conversation with Woyane is not possible.
That in a nutshell is Ethiopian history the last twenty two years. We produce selfless individuals that have entered the fray knowing full well what savage Woyanes are capable of. Common sense shows that carrot (staying quiet) alone has not worked in Ethiopia. A stick is an absolute requirement to balance the equation. Do you follow me? After twenty three years of abuse we Ethiopians should be the last to be bewildered by this situation.
Patriotic Ginbot7 is our stick. There have been others, what makes this one any different is a good question. That is the reason I raised our recent history earlier. Woyane has held five or more election the last twenty two years, which one is memorable? May 2005 is when we divorced Woyane. The 2005 was led by Kinijit with Berhanu Nega as a central figure. Dr. Berhanu and friends whipped Woyane. Dr. Berhanu is the first popularly elected leader to a high office in our entire history. His election to be Lord Mayor of Addis Abeba was a landslide. The people of Addis Abeba loved him. No need to say more.
The formation of Ginbot7 Movement for Unity and Democracy was the result of lessons learnt from the 2005 attempt to seize power through peaceful and legal means. By all scale of measurement G7 has exceeded all expectations. It has shown what it means to be an organization focused on one thing and one thing alone. To leave no stone unturned to find a way to grow Freedom and Democracy in Ethiopia.
To this end the last five years the Organization has painstakingly built the network necessary to do the work. What is there not to admire more than the fact despite the mighty power of a Nation State’s attempt to kill, undermine, destroy, wreck from inside, jail exile so many times in the name of fighting terrorism but to protect single ethnic rule, G7 has managed to blossom to an organization that in the eyes of many Ethiopians managed to bring that old feeling of pride that has quietly been sitting inside all of us. Elel Belu!
How do you fight one of your own has been our dilemma. Believe me if Woyane was an outsider no matter what; we all would fight back and there would not be discussion like what we are having now. Unfortunately it is not so. At the moment Patriotic G7 is in the forefront of the struggle to get rid of this disease that is infecting our homeland.
It is said ‘leadership is the capacity to translate vision into reality’ that is what we have in Dr. Berhanu Nega. In every turn of our movement he has been there crafting winning strategy to get us closer to our goal of building a better Ethiopia where her children invest time and energy in making it a place we are proud to call home. His simple manners, generous smile and focus His style has been pay any price, walk the extra mile so we Ethiopians can drink from the fountain of freedom.
The TPLF regime has done all it could to discourage our leader. A mere mortal would have thrown his hands in the air and walked away. Dr. Berhanu stayed the course and showed little Woyane there are some Ethiopians that are determined and resolute. Such character is not a trait Woyane understands.
In Arbegnoch G7 we Ethiopians at last have achieved a winning formula to bring national salvation to our homeland. In Berhanu Nega and his team we have found leaders with a record and a winning formula. Kinijit paved the way and Arbegnoch G7 is poised to finish the job. We say it with confidence because the experience the last ten years have shown us that an organization built on democratic principles, staffed by able leaders and carrying the torch of freedom and equality cannot fail. Especially when the enemy is a group led by gangsters and shameless characters that have not achieved much in life using legal and transparent means it does not need much for the house of cards they built to come crashing down.
All patriotic Ethiopians are fighters in this war of salvation. The question we should ask ourselves is what can I contribute to hasten the day of freedom. Today this joke of I am not into politics, I am neutral has no place. It is like standing back and watching while your house is on fire. Ethiopia is burning and her children are dying in droves. This is not the time to be a spectator or a shameless supporter of the ethnic regime. It is past time for verbal condenations. We have done that, we have been there.
The current activity to support and celebrate our Freedom fighters is a breath of fresh air. It is nice to stand up rather than always be a victim. We used to cry for Ethiopia. Today we cry for Woyane that is already feeling the wrath of the people. All over the world Ethiopians are giving what they could without being compelled. Five dollars or a thousand, five minutes or a lifetime, whatever is offered, it is sure to bring satisfaction to the heart, pride to the family and debt paid top our mother. Here in Oakland, California we are preparing to give the mother of all fundraising events since Kinijit. The enthusiasm of the members, the reception of our people and the smile painted on our face is an indication the sun is shining on our motherland. Find out where Arbegnoch G7 activity is held in a location near you and be part of this tsunami of support for our liberators. Tell everybody that the Sun is shining brighter than ever over Ethiopia.