Monday, September 18, 2017

ፋሽስት ሆይ! ጠገዴ አንድ ቤተሰብ፣ ድንበሩም ተከዜ ነው! (ልሳነ ግፉዓንና የጠለምት አማራ ማንነት ጥምረት ኮሚቴ)

Welkait Tsegede

ፋሽስቱ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባርና ተላላኪው ብአዴን በአዲሱ አመት ዋዜማ ለመላው የጎንደር ህዝብ የሰጡት ስጦታ ቢኖር ሰላምና አንድነትን ሳይሆን አካሉ የሆነውን የጠገዴን ማህበረሰብ ለሁለት እንደ ቅርጫ መቀራምትን ነው።
ታላቋን ኢትዮጵያ የማፍረስና ህዝቧን የማተራመስ ተልዕኮ እንደ ቀደምት ባንዳ አባቶቹ ከጠላቶቻችን የተሰጠው የትግራዩ ወራሪ ቡድን የአማራን ህዝብና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀዳሚ ኢላማው አድርጎ በውድ ሃገራችንና በኩሩው ህዝባችን ላይ መርዙን መዝራት ከጀመረ እነሆ 26 የፅልመት አመታት ተቆጠሩ።
ከሽፍትነት ዘመኑ ጀምሮ ታሪካዊና ለም የሆኑትን የጎንደር መሬቶች በተቀዳሚነት ኢላማው ያደረገው ወራሪው ተ.ሃ.ት የተከዜን ወንዝ በመሻገር የወልቃይትን መሬት ከረገጠበት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በወገናችን ላይ ያደርስ የነበረው ዝርፊያ፣ እስራት፣ ድብደባና፣ ግድያ እስከ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ሲሆን በተለይም ከአንድ አመት በፊት የወልቃይትን ህዝብ ሙሉ ውክልና ይዘውና የህዝብን ጥያቄ አነግበው በሰላማዊ መንገድ ፍትህን የጠየቁ የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ መሪዎችና አባላት በሽብርተኝነት ተወንጅለው በዋና ዋና የህወሃት የማሰቃያ ካምፖች ውስጥ መከራን እየተቀበሉ የሚገኙ ሲሆን፤ወረራውንና መስፋፋቱን በፍፁም ጭካኔና ማንአለብኝነት የቀጠለው ይህ እኩይ ቡድን ወደ ጠገዴና ጠለምት ያደረገውን ወረራ የተቃወሙትን ታሪክ ነጋሪ የሃገር ሽማግሌዎችን፣ ትውልድና ሃገር ጠባቂ ጎልማሳዎችን፣ እንዲሁም ሃገርና ታሪክ ተረካቢ የሆነውን ወጣት ትውልድ በግልፅና በስውር በመጨፍጨፍ ካጠፋ በኋላ ዕርስታችንን በሃይል ወደ ትግራይ በመጠቅለል በይፋ የምትገነጠለው ትግራይ አካል ከተደረገ እነሆ ሃያ ስድስት የሰቆቃ አመታት አሳለፍን።
ምንም እንኳ ህዝባችን በፋሽስቱ ህወሃት የጭቆና አገዛዝ ስር ሆኖ ቃላት ሊገልፁት በማይቻላቸው መከራና ስቃይ ውስጥ ቢገኝም ጭቆናንና ባርነትን አሜን ብሎ መቀበል ከአባቶቹ አልወረሰምና በሚቻለውና ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ተጠቅሞ የጠላቱን እኩይ ሴራ በማክሸፍ ላይ ይገኛል። ይሁንና ይህ ህዝባዊ ተጋድሎ እረፍት የነሳውና ኢትዮጵያን የማፈራረስና ትግራይን የመገንጠል ሰይጣናዊ ተልዕኮ እያኮላሸበት የሚገኘውን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ለማዳከምና ከፋፍሎ ለማጥቃት በማለም አንድን ቤተሰብ የሆነውን የጠገዴ ማህበረሰብ ለሁለት በመክፈል ግማሹን ጠገዴ ሌላኛውን ግማሽ ፀገዴ በማለት ለያይተው የሚቻላቸውን ክፉ ተግባር ሁሉ ሲፈፅሙብን ኖረዋል።
ይሁን እንጂ ምንግዜም ቢሆን ጀግና መውለድ የማታቆመው የጎንደር እናት ዛሬም እንደ ትላንቱ አንድ ጠገዴ!!! ብለው በተነሱ ልጆቿ አማካኝነት ህዝባዊ ትግሉን በማፋፋም የፋሽስቱን ጎራ እያንቀጠቀጡት ይገኛሉ። “ወላድ በድባብ ትሂድ” እንዲሉ በጠገዴ የቁርጥ ቀን ልጆች የማያወላዳ ጥያቄ የተሸበረውና የዘመናት ሴራው በዜሮ የተባዛበት የተገንጣዩ ጎራ ከጳጉሜ 1, 2009 ዓ.ም ጀምሮ አንዳች የአማራ ህዝብ ድጋፍ በሌለውና እርሱ ህወሃት በአምሳሉ ጠፍጥፎ ከሰራው ብአዴን ተብዬ የአሻንጉሊቶች ስብስብ ጋር በመሆን አንዱን የጠገዴ ቤተሰብና ዕርስቱን ለሁለት በመከፈል መቀራመታቸውን በየፊናቸው እያወጁ ይገኛሉ።
የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ጥያቄ ግልፅና አንድ ነው። ይሃውም ህዝቡ ጎንደሬ/አማራ፣ መሬቱ የጎንደር፣ ድንበራችን ተከዜ ነው! የሚል ነው። ከዚህ ታሪክና ማንነትን መሰረት ካደረገ ህዝባዊ ጥያቄ አንዳች ጎደሎና እንከን የታከለበት ሽርፍራፊ ምላሽ ህዝባችን እንደማይቀበል የአለፉትን ሃያ ስድስት የፅልመትና የጭቆና ዘመናትን በፅናት በማለፍ ዛሬ እንደ አዲስ አይነቱንም ሆነ ይዘቱን ቅንጣት ሳይቀር ዳግም በወጣቱ ትውልድ መነሳቱ አብይ ማረጋገጫ ነው።
ታዲያ ይህን ታሪካዊ እውነታ አንዴ “በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ” ኮሚቴ አማካኝነት፣ ሌላ ጊዜ “ጠገዴ አንድ ነው” በሚለው የጠገዴ ህዝብ ጥያቄ ሳይወድ በግዱ እንዲጋፈጠው የተደረገው ፍሽስቱና ተስፋፊው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር “የማይተማመን ጓደኛ በየወንዙ ይማማላል” እንዲሉ ለሃያ ስድስት አመታት በሃይል ከልሎ ሲበዘብዛቸው የኖሩትን የጠገዴ ወገኖችን በተለይም ዕርስታችን የሆኑትን የግጨውና የጎቤ ጎንደሬ/አማራ መንደሮችን ትግሬ ያደረገ የትግራይን ድንበር ከአማራ ጋር ተካልያለሁ በማለት ሎሌዎቹን ሰብስቦ ከበሮ እየደለቀና ሻምፓኝ እየተራጨ ይገኛል።
እኛ በመላው ዓለም የምንገኝ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ተወላጆች ዛሬም እንደትላንቱ በአንድነት ከህዝባችን ጐን በፅናት በመቆም የትግል አጋርነታችንና አንድነታችን እየገለፅን ከጳጉሜ 1, 2009 ዓ.ም ጀምሮ በህወሃትና በብአዴን መሪዎች አማካኝነት የታወጀው ጠገዴን ከሁለት በመክፈል በተለይም የጎንደር/አማራ ለምና ታሪካዊ የሆኑትን የግጨውና የጎቤ መንደሮችን ወደ ትግራይ መከለል ፍጹም ሰብአዊነት የጎደለውና አንድን ቤተሰብ ለሁለት የሚከፍልና የሚለያይ ጭራቃዊ ተግባር በመሆኑ የምንፀየፈው አጥብቀን የምናወግዘው መሆኑን እየገለፅን፤ ትላንት ከቀጣሪዎቹ በተሰጠው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ባንዳዊ ተልዕኮ አንዱ የሆነውን ኤርትራን የማስገንጠልና የህጋዊና ዓለም አቀፋዊ ድንበር ባለቤት የማድረግ ሴራና ድራማ በቅጡ መከወን ያልተቻለው ፍሽስቱ ሟች መለስ ዜናዊ  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊያስፈፅም አልጀርስ ላይ ከኤርትራ ጋር የተስማማበትንና በአንፃሩ ደግሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ከጅምሩ አጥብቆ የተቃወመውን መሰሪ ውል ሲያፈርስ እንደ ዋነኛ ምክንያት ሲቀላምድ የነበረው “አንድ ቤተሰብ ለሁለት የሚከፍል” ፍርድና የድንበር ማካለል አልቀበልም በማለት ነበር።
ዛሬ የሙት መሪያቸው ራዕይ ወራሾች ነን በሚል በየመድረኩ ሲምሉና ህዝብን ሲያደነቁሩ የሚውሉ ውልደ ፋሽስቶች ህዝባችን በወኪሎቹ አማካኝነት “እኛ አንድ ቤተሰብ ነን!” “ጠገዴ አንድ ነው!” በሚል ያቀረበው ህዝባዊ ጥያቄ ለአልጀርሱ በተባው የክህደት ምላስና ህሊናቸው “አንድ ቤተሰብ ለሁለት የሚከፍል” ፍርድና የድንበር ማካለል አንቀበልም ማለትን እረስተው ህዝባችንን ዛሬም ድረስ ዘመን መለወጫን እየጠበቁ ያስለቅሱታል። ዕርስታችንም ታላቋን ትግራይ ለመመሥረት በሚል ቅዥት ወደ ትግራይ በማካለል ለሕዝባቸው የአዲስ ዓመት ስጦታነት ያውሉታል።
ይሁን እንጂ ዛሬም ህዝባችን በፍፁም ጨዋነት ያቀረበው ሰላማዊና ህጋዊ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረት በተገንጣዮች የእብሪት እርምጃ አሁንም እንዲለያይ በግፍ የተፈረደበት ቤተሰባችን ዳግም አንድ ሆኖ በሃገሩ ላይ በነፃነትና በእኩልነት መኖር እስኪችልና ሰላሙና አንድነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ትግላችን ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ለፍሽስቱ ህወሃትና ለተንበርካኪው ብአዴን አመራሮች፣ አባላትና፣ ደጋፊዎች እያሳወቅን፤ በዚህም ምክንያት ለሚደርሱት ማንኛቸውም ሃገራዊና አካባቢያዊ ችግር ብቸኛ ተጠያቂው ፋሽስቱ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባርና ተላላኪው የብአዴን አመራር አካላት መሆናቸውን ከጥብቅ ማሳሰቢያ ጋር እንገልፃለን።
ጠገዴ አንድ ቤተሰብ፣ ድንበሩም ተከዜ ነው!
ልሳነ ግፉዓንና የጠለምት አማራ ማንነት ጥምረት ኮሚቴ
መስከረም 1, 2010 ዓ.ም
ሰሜን አሜሪካ

ኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት የሚያብራሩ አምስት ነጥቦች

by maleda times

BBC AMHARICካርታ

አሁኑ ወቅት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች በምክንያት የሰዎች ህይወት ጠፍቷል፤ ከሃምሳ አምስት ሺ በላይ የሚቆጠሩ ዜጎችም ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ ተገደዋል።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፤ የሶማሌ ልዩ ፖሊስን እንዲሁም ሚሊሻዎች ወደ ኦሮሚያ ዘልቀው በመግባት ጥቃት አድርሰዋል ሲል የሚከስ ሲሆን፤ የሶማሌ ክልል በበኩሉ አጥቂዎቹን በኦሮሚያ ክልል የሚደገፉ ናቸው ሲል በኮሚኒኬሽን ቢሮው በኩል አሳውቋል። መወነጃጀሉና የቃላት ምልልሱ መካረር የክልሎቹ መንግስታት ግንኙነት ያለበትን ደረጃ ከማሳበቁም ባለፈ የግጭቶቹን መረር ማለትም አመላካች ነው። ይሁንና በሁለቱ ክልሎች መካከል ውዝግብ፣ ግጭት፣ ሲያልፍም ደም መፋሰስ ሲያጋጥም የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም።
1.አጨቃጫቂ ወሰን
በቆዳ ስፋቱ ከአገሪቱ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የኦሮሚያ ክልል፤ ከሁለተኛው ሰፊ የሶማሌ ክልል ጋር የሚያዋስነው 1410 ኪሜ ድንበር አለው። ይህ ድንበር ግን ክልሎቹ አሁን ያሉበትን ቅርጽ ይዘው ከተመሰረቱበት ጊዜ አንስቶ ውዝግብ አያጣውም። ውዝግቡን ፈትቶ ወሰኖቹን መልክ ለማስያዝ ታስቦም ሕዝበ ውሳኔ ከ400 በሚበልጡ ቀበሌዎች በጥቅምት ወር 1997 ዓ.ም ተደርጓል።
በሕዝበ ውሳኔው መሰረት ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑ ቀበሌዎች በኦሮሚያ አስተዳደር ሥር እንዲጠቃለሉ የተወሰነ ቢሆንም የወሰን ማካለል ሥራው ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቷል። ይህም በየጊዜው ለሚነሱ ግጭቶች አባባሽ ምክንያት መሆኑ አልቀረም።
ባለፈው ሚያዝያ ግን የሁለቱም ክልሎች ፕሬዚዳንቶች ሕዝበ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል የተባለ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ "ትልቅ ድል" መገኘቱን ሲገልፁ፥ የሶማሌ ክልል አቻቸው አብዲ መሃመድ በበኩላቸው "በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ ግጭት አይኖርም።'' ብለው ነበረ።
የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋም የችግሩ ምንጭ ''የድንበር ጉዳይ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥልን፤ ድንበር በማንጋራባቸው አካባቢዎች ጭምር ጥቃት ሲፈፀም የነበረው። የድንበሩን ጉዳይ በ1997 ሕዝበ-ውሳኔ መሰረት ለመፍታት በተደረሰው ስምምነት መሰረት እየሰራን ነው።ሥራውም ሰባ በመቶ በላይ ተጠናቋል።'' ሲሉ ሌላ ምክንያት ሊኖር እንደሚችል ይጠቁማሉ።
2.የተፈጥሮ ሃብት ፉክክር
በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር የሚገኙ የኦሮሞ እና የሶማሌ ክልል አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አድር ሕዝቦችን ግንኙነት ያጠኑት የማኅበረሰባዊ ሥነ-ሰብ ተመራማሪው ፈቃዱ አዱኛ እንደሚሉት ፉክክርና ግጭት በተለይ የቦረና ኦሮሞዎችና የአካባቢው ሶማሌ ጎሳዎች መገለጫዎች ሆነው ቆይተዋል ይላሉ።
ፉክክርና ግጭቶቹ በብዛት ውሃ እና የግጦሽ መሬትን በመሳሰሉ የተፈጥሮ ሃብቶች ተጠቃሚነት ዙርያ የሚያጠነጥኑ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ አንስቶ የብሔር መልክ እየያዙ መምጣታቸው ይወሳል።
በአገሪቱ ፖለቲካዊ አወቃቀር የብሄር ድንበሮች የፖለቲካ ድንበሮች ጭምርም በመሆናቸው፤ በማኅበረሰቦቹ ዘንድ ያለውን የፉክክር መንፈስ ክልላዊ ገፅታ አላብሶታል ሲሉ ይከራከራሉ አቶ ፈቃዱ። ለዚህም በማሳያነት የሚጠቅሱት ከዚህ ቀደም በአንፃራዊነት ሰላማዊ ግንኙነት የነበራቸው የአርሲ ኦሮሞና አጎራባች የሶማሌ ጎሳዎች ደም ወዳፋሰሰ ግጭት መግባታቸውን ነው።
አካባቢዎቹ ለድርቅ ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ መሆኑ በተፈጥሮ ሃብት ፍላጎቶች ላይ ለሚነሱ ቅራኔዎች ተጨማሪ ነዳጅ የሆኑ ይመስላል።

ተፈናቃዮችን የሚያሳይ ምስል

3.የሕዝበ-ውሳኔ ራስ ምታት
ለተመራማሪው ፈቃዱ አዱኛ፤ መንግሥት ለአካባቢዎቹ ወሰን ተኮር ግጭቶች ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ባደረገው እንቅስቃሴ ሕዝበ-ውሳኔ ማከናወኑ የአካባቢዎቹን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። የአካባቢው ኗሪዎች በአብዛኛው አርብቶ አደሮች እንደመሆናቸው ከሥፍራ ሥፍራ ይንቀሳቀሳሉ። ይህም ወሰኑን ቁርጥ ባለ ሁኔታ ማስቀመጥን አዳጋች ያደርገዋል።
የህዝበ-ውሳኔው ውጤት በሁለቱ ክልሎች መካከል የተነሳውን ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል ቢባልም የተካሄደበትን ወቅት መሰረት ያደረገ ሌላ ጉዳይ አሁን እንደተነሳ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር "ከሶማሌ ክልል በኩል የሚነሳው ጥያቄ ሕዝበ-ውሳኔው የተካሄደበት ወቅት የሶማሌ ክልል የራሱን ግዛት ሊያስጠብቅ በማይችልበት አቅም ላይ በነበረበት ጊዜ በመሆኑ ብዙ ግዛት ተወስዶብኛል የሚሉ ጥያቄዎች እያነሳ ነው።" ይላሉ።
4.ሞትና መፈናቀል
ባለፈው ነሐሴ የተካረሩ ግጭቶችን ያስተናገደው የሚኤሶ አካባቢ ለወትሮውም ለዚህ መሰል ፍጭቶች ባይታወር አይደለም። ሕዝበ ውሳኔን ባስተናገደው የ1997 ዓ.ም በመኢሶና በቦርደዴ አካባቢዎች በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዲፈናቀሉ ያስገደዱ ግጭቶች ተከስተዋል ይላል የአይ ዲ ፒ ፕሮጄክት ሪፖርት።
በ2005 ዓ.ም ደግሞ በሞያሌ አካባቢ በተቀሰቀሰ የሁለቱ ብሔር አባላት ግጭት ከ20ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ሸሽተው ኬንያ መግባታቸውን የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር በዚሁ ወቅት አስታውቆ ነበር። በወቅቱ ለግጭቱ መቀስቀስ ምክንያት ተደርጎ የተጠቀሰው በግጦሽ መሬት ይገባኛል ቢሆንም ግጭቶቹ ብሄር ተኮር ይዘት እንዳላቸውም አብሮ ተዘግቧል።
ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር የሚከሰቱት ግጭቶች መንስዔ የብሄር ይዘት አለው ባይሉም፤ በግጦሽ መሬትና በውሃ የተቀሰቀሰ ነውም አላሉም። ከዚያ ይልቅ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ያሏቸውን የአካባቢውን አስተዳዳሪዎችን ወቅሰዋል።
5.ማኅበረ-ባህላዊ ልዩነቶችና አንድነቶች
የኦሮሞና ሶማሌ ሕዝቦች ከምስራቅ ኩሽ የቋንቋ የዘር ግንድ የሚመዘዙ ሲሆን በኢትዮጵያ ሶማሌዎችና በተለይም እስልምና በገነነባቸው የኦሮሞ አካባቢዎች መካከል መልካም የሚባል ግንኙነት ተመስርቶ መቆየቱን የሚያነሱት አቶ ፈቃዱ፤ ባሌ ውስጥ የሚገኘው የሼክ ሁሴን መስጊድ በሁለቱም ሕዝቦች እንደ ቅዱስ ቦታ መቆጠሩን ያስታውሳሉ።
የሶማሌና የኦሮሞ ሕዝብ አብሮ ከመኖሩ አንፃር በርካታ አንድ የሚያደርጓቸው ነገሮች እንደሉ የሚጠቅሱት የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ፤ ምንም እንኳን እነዚህ ግዛቶች በወሰን ቢከፋፈሉም አሁንም የሁለቱ ህዝቦች የሚንቀሳቀሱባቸው ከተሞች አሉ፤ በማለት የሁለቱ ሕዝቦች አብሮነት እንደማይቋረጥ ይናገራሉ።

Sunday, July 17, 2016

Ethiopian government cadres vow to kill Prof. Dr. Birhanu Nega.

 The Ethiopian current government (TPLF juntas) has sent its cadres and spies to the heart of Europe (Germany) to threaten those who fight against its 25 years dictatorial rule. The successful Patriotic Ginbot 7 fund-raising programs which have been held in the month of June 2016 in three different European countries (Norway, Switzerland, and Germany) have shocked these undemocratic Ethiopians leaders. , prof. Dr. Birhanu Nega’s speeches ( the chairperson of Patriotic Ginbot 7) on the fundraising session in Oslo and Switzerland, has boiled these dictators’ blood and made them come out on the street of Frankfurt on 11.06.2016. On their demonstration, they have exposed their cruelty, crime and killing habits to the world.
(“ኢትዮጵያ አትገባትም እዚሁ ነው የምትቀበረው”) “You will never get into Ethiopia. You will be buried here.” (https://www.youtube.com/watch?v=ywugKQfWVn4 (1:29-1:42)) One of the TPLF’s cadres, who is seen on the video wearing blue suits having an eyeglass and taking photos with his cell phone, was threatening the supporters and members of Patriotic Ginbot 7 in Frankfurt on 11.06.2016. This cadre did not even have a clue that he was in the land of democracy where freedom of speech and association are respected. If he openly threatens supporters and members of Patriotic Ginbot 7 standing in the heart of Europe, it will not be difficult to imagine what the savage dictators in Ethiopia, who send him and his likes, could do to anyone who dares to oppose them inside Ethiopia.
(“ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያን አይወክልም መቀጣት አለበት”) “Birhanu Nega does not represent Ethiopia. He must be punished. He will be imprisoned just like Andargachew Tsige.” (https://www.youtube.com/watch?v=ywugKQfWVn4) (1:50-2:20) .These were additional threats, which are the translated form, that these cadres were shouting using a microscope on the street of Frankfurt to all supporters and members of Patriotic Ginbot 7. These TPLF’s cadres were also heard shouting loudly in German language saying (“ግንቦት 7 ቴሬሪስቶች ናቸው“ “Birhanu Nega ist ein Terrorist.” (Birhanu Nega is a terrorist. Ginbot 7s are terrorists) https://www.youtube.com/watch?v=ywugKQfWVn4 (2:38-2:59). They still do not understand the meaning of terrorism and terrorist. If Prof. Dr. Birhanu Nega, chairperson of Patriotic Ginbot 7, is a terrorist, what in the world is he doing in Europe and North America? If he is a danger to civilians, do not the Europeans and the Americans worry for the safety of their nation as he travels and holds speeches on their soil? This clearly shows how the 25 years Ethiopian dictatorial government labels anyone who opposes him as a terrorist. In fact, these dictators label anyone who sits and drinks a cup of tea with member or supporter of Patriotic Ginbot 7 as a terrorist. Isn’t that crazy?
Hailemariam led corrupted and dictatorial Ethiopian government should understand the fact that the struggle against tyranny and dictatorship will go on until we see a free and democratic Ethiopia. It is my duty, as an exile Ethiopian and supporter of Patriotic Ginbot 7, to do everything in my power to remove the current dictatorial Ethiopian government from power. The struggle for freedom will go on either peacefully or in an armed means till we hit our goal of disposing the TPLF’s leaders and cadres from their thorn.
Source https://www.youtube.com/watch?v=ywugKQfWVn4
By Abenezer Ahmed
Germany

Wednesday, December 30, 2015

ኢትዮጵያ የማን ናት? ከአንተነህ መርዕድ

"ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው" ( ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ)

"ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም" (ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ)

ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት የብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የልብ ህመም ሆኖ የቆየው የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ዛሬም በኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ጥያቄ ቢኖር የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሆነ በጨለማ ለመግዛት የተነሱት ጣልያንም ሆነ ወያኔ ለአላማቸው ማስፈፀምያ የዚህን ታላቅ ህዝብ ጥያቄ ነበር ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚጠቀሙበት። ከላይ በጥቅስ ያስቀመጥኋቸውን ሃሳቦች የተናገሩት በኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ ትፅዕኖ ፈጣሪና ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከአስራ አራት ዓመት በፊት በሞት የተለዩን ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳን ንግድ ማተምያ ቤት አጠገብ ባለው መኖርያ ቤታቸው ለጦቢያ መጽሄት ቃለ መጠይቅ ልናደርግላቸው አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ጋር ሄደን ነበር። ሜጫና ቱሉማን በመመስረትና ለኦሮሞ መብት በመታገል ኢትዮጵያዊ መፍትሄ እንዲያግኝ በመልፋት የሚታወቁት እኒህ አንጋፋ አባት አመሻሽ እድሜአቸው ላይ ሆነው ያዩት ሁሉ አላስደሰታቸውም።

አክራሪ ፅንፍ የያዙ የኦሮሞ ኤሊቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን መለየትን እንደመፍትሄ በግልፅ በሚሰብኩበትና ለተግባራዊነቱ በሚገፉበት፤ ወያኔም ይህንኑ አጀንዳ አስጨብጦ በሚያራግብበት ፈታኝ ወቅት ነበር የሄድንባቸው። አምቦ አካባቢ ግንደበረት ተወልዶ ከማደጉም በላይ የኦሮሞን ህብረተሰብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጋሽ ሙሉጌታ ከኮሎኔሉ ጋር ያላቸውን መግባባትና መከባበር ስመለከት ተገርሜያለሁ። በርካታ አገራዊና የግል ጥያቄዎችን ያቀረብንላቸው ቢሆንም በቁጣ ስሜት የመለሱት ለኦሮሞ ችግር ከኢትዮጵያ መገንጠል መፍትሄ ይሆናልን? የሚለውን ጥያቄአችንን ነበር። "ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው?" በማለት ነበር ጥያቄአችንን በጥያቄ የመለሱት።

ኦሮሞ የኢትዮጵያ እምብርት ብቻ ሳይሆን ከሰሜን ጫፍ እስከ ትግራይ፣ በደቡብ እስከ ኬንያ፤ በምስራቅ ኦጋዴንን ነክቶ በምዕራብ ሱዳን ድረስ ሲያጣቅስ በመሃል ከአብዣኛው ኢትዮጵያውያን ተዛንቆ፣ ተዋልዶ፣ ተዋህዶ በመኖሩ እድሉ የኢትዮጵያ ባለቤት መሆን እንጅ ጊዜው እንደወለዳቸው ፖለቲከኞች ቁራሽ መሬት ይዞ መወሰን አይደለም የህዝቡ ፍላጎት። ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳም የገለፁት ይህንኑ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት ነበር። ቃለ መጠይቁን ለህትመት አብቅተን ኮሎኔል ዓለሙን ደግመን ስናገኛቸው ያየሁትና የሰማሁት ለብዙ ጊዜ አሳዝኖኛል። የጊዜው የፖለቲካ አራጋቢዎች ትልቅ የመንፈስ ስብራት ፈጥረውባቸው ነበር። "ዛሬ በሽምግልናዬ ቤት ውስጥ ተወስኜ ሞቴን በጸጋ በምጠብቅበት ሰዓት የአገር ጉዳይ ጠልቆ ያልገባቸው ወንድሞቼ በእኔና በቤተሰቤ ያሳደሩብኝ ጫና ቀላል አይደለም። ቀሪ ጊዜዬን በሃዘን እንዳልቋጨው ታገሱኝ" አሉን። እኛም ታገስናቸው።

ዛሬ ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳና አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት የሉም። ጋሽ ሙሉጌታ ሊለየን ትንሽ ሰዓታት ሲቀረው "ለዘመናት ወጣቱ ላይ የነበረኝን ወቀሳ አንስቻለሁ፤ አገሩን የሚታደግ ወጣት በማየቴ ኮርቻለሁ። በሉ ተነሱ ሰልፍ የጀግና ነው፣ ድል የእግዜብሄር ነው" ሲል ተስፋውንና ጥሪውን ገልፆ አልፏል። የኦሮሞ ህዝብና ቀሪው ኢትዮጵያዊ ባንድ ቁሞ ታላቋን ኢትዮጵያን የመገንባቱ ተስፋ እየለመለመ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ባለቤት ለመሆን አገራዊ አጀንዳ ይዞ እየተነሳ ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች (ኤሊቶች) እንደ ኦሮሞ ህዝብ ሰፊ ልቦናና ኢትዮጵያዊ ባለቤትነትን ካላቀፉ ለጠባቡና ለጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ ራሳቸውን ወስነው መነሳት እንደማያዋጣቸው የተረዱ ይመስላል። ከአንጋፋ ፖለቲከኞች ሌንጮ ለታና ጓዶቻቸው፣ ከወጣቶቹም ጁአር ሞሃመድና ሌሎችም ሰሞኑን ያሳዩት ሁሉን አቃፊ (አኮሞዳቲቭ) አቋም ያየ፤ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የኦሮሞን ህብረተሰብ በሚመጥን ደረጃ ለመገኘት መንቀሳቀሳቸውን ወይንም መፈለጋቸውን ይገነዘባል። ያድርግልን። ከሰሞኑ የህዝብ አመፅ በኋላ የአማራውና የኦሮሞው አንድነት ጥሪ በሰፊው ተሰብኳል። አመፁን ተከትሎ የመጣ በረከት ይመስላል (ፈረንጆች ኤ ብሌሲንግ ኢን ዲስጋይዝ እንደሚሉት)። አመፁን ወደ እውነተኛ አንድነት እንዲያድግ ከተፈለገ አጀንዳው ከክልላዊነት ወጥቶ ወደ አገራዊነት መለወጥ አለበት።

ለኢትዮጵያ ህልውናና እድገት የህዝቦቿ መተባበር፤ በተለይም የኦሮሞውና የአማራው በአንድነት መቆም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጠው ለመግዛት የሚያልሙ የውጭ ሆነ የውስጥ ጠላቶች እነዚህን ጉልህ የህዝብ

ክፍሎችን የጥቃታቸው ኢላማ የሚያደርጉት። አድዋ ላይ አባቶቻችን ያንበረከኳትና በዓለም ፊት ያዋረዷት ጣልያን የሽንፈቷ ምክንያት የኢትዮጵያውያን ህብረት መሆኑን ከውድቀቷ ተምራለች። ከአርባ ዓመት በኋላ ቂም ቋጥራ ዳግም ስትመጣ፤ መጀመርያ የተሰማራችው ተባብረው የደቆሷትን አማራና ኦሮሞን በመለያየት ላይ ነው። ብዙ ክፍተት ለጊዜው ብትፈጥርም እንዳልተሳካላት ሌላውን የኦሮሞ የጀግንነት ምሳሌ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ታሪክእንቃኝ። የበጋው መብረቅ የሚባሉት የጀግናው የጄኔራል ጀጋማ ኬሎ አጎት ናቸው። ፊታውራሪ አባዶዮ ዋሚ ገሮ ይባላሉ። አባ ዶዮ የፈረስ ስማቸው ነው። ጣልያን አማራንና ኦሮሞን ለመከፋፈል በሰፊው ሠርቶ ስለነበር፤ ይህ ሰበካ እውነት የመሰላቸው ታላላቅ ሰዎች የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮን ምክርና ይሁንታ ለመሻት ቤታቸው ሄዱ። "አማራ የሚበድለን ስለሆነ ከአካባቢያችን ልናስወጣ አስበናል ምን ይመክሩናል?" የሚል ሃሳብ አቀረቡላቸው። እንግዶቻቸውን አብልተው አጠጥተው፣ በነገሩም አሰላስለው ቆዩና ለእያንዳንዳቸው እፍኝ እፍኝ ሙሉ ሰርገኛ ጤፍ እንዲሰጣቸው አዘዙ። ጤፉም ለእንግዶቹ ተሰጠ። "በሉ ቀዩን ከነጩ ጤፍ ለዩልኝ" አሏቸው። ግራ የተጋቡት እንግዶች "አባ ዶዮ ይሄማ እንዴት ይቻላል?" በማለት እንደማይሆን ነገሯቸው። "ያቀረባችሁልኝ እኮ እንዲህ ያለ ጥያቄ ነው። ከአማራ ያልተጋባ፣ ያልወለደ፣ ያልተዛመደ ማን አለ? እንዝመት ካላችሁ በራሳችን፣ በቤታችን እንጀምር። ይህንን ደግሳ ያበላቻችሁ የልጆቼ እናት አማራ ናት። ልጆቼንና ልጆቿንም፣ እሷንም ጭምር ግደሉ፤ እናንተም በየቤታችሁም ሂዱና የአማራ ደም ያለበትን አጥፉ። ይህ እንዲሆን አይደል የምትጠይቁኝ" አሏቸው። በርግጥም ከአማራ ያልተዛነቀ ኦሮሞ፤ ከኦሮሞ ያልተዋለደ አማራ ጥቂት ነው። ጥፋታቸውን የተረዱት መልዕክተኞች የጣልያንን ተልዕኮ አከሸፉ። በነገራችን ላይ ዶክተር መረራ ጉዲናም አንዳንድ ፅንፈኛ የሆኑትን ፀረ አማራ የሆኑ የኦሮሞ ልሂቃንን "ማታ ቤታቸው አማራ ሚስቶቻቸውን ታቅፈው እያደሩ ቀን ስለእነዚህ ትልልቅ ህዝቦች መለያየት ይሰብካሉ" ሲሉ ከሃያ ዓመት በፊት መተቸታቸውን አስታውሳልሁ።

ታሪኩ በዚህ አያበቃም። የፊታውራሪ አባ ዶዮ ዋሚ ገሮ ወንድም የአባ ኬሎ ገሮ ልጅ ጀጋማ ኪሎ ጣልያንን ገና በአስራ አራት አመታቸው ጀምሮ ነው በጥይት እየቆሉ መውጫ መግቢያ አሳጥተው ነፃነታችንን ያጎናጸፉን። የጣልያንን ሴራ ብቻ ሳይሆን ሰላቶን ከነባንዳው አይቀጡ ቅጣት የቀጡት ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ ከአምሳ አምስት ዓመት በኋላ የባንዳ ልጆች የሆኑ የወያኔ መሪዎች በአማራውና በኦሮሞው ልዩነት ፈጥረው ለማፋጀት ሲነሱ አጎታቸው ዘንድ ለምክር እንደሄዱ መልዕክተኞች የህወሃትን መርዝ ይዘው ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ሲያቀነቅኑ ልባቸው በሃዘን ተነክቷል። አዛውንቱ ፖለቲከኛ ቡልቻ ደመቅሳ "ለኦሮሞ መገንጠል ይበጀዋል ወይ?" ብለው ለጠየቋቸው "ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም" ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይገነጠልም ብለው እንደመለሱላቸው ሰምቻለሁ። ዛሬ ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ የ95 ዓመት አዛውንት ናቸው። የኦሮሞ አድባር፣ የኦሮሞ ዋርካ፣ የአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ዋርካ በህይወት እያሉ ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ስንት ጊዜ ተጠቃች? ስንት ጊዜ አፈር ልሳ ተነሳች?

አብዛኞቹ የህወሃት መሪዎች ለጣልያን ያደሩ የባንዳ ልጆች መሆናቸውን ከገብረመድህን አርዓያ የበለጠ ምስክር አንሻም። Rኡቅ ሳንሄድ የህወሃት ሴራ ባለቤት የመለስ ዜናዊ አያት የጣልያኑ ደጃዝማች አስረስ በርካታ ህዝብ ያስፈጁ አገር የሸጡ ባንዳ መሆናቸውን ሁሉም ያውቀዋል። ታድያ እነመለስና ጓደኞቻቸው ከአባቶቻቸው የተማሩት አገርን መታደግ ሳይሆን ማፍረስ ነው። ጀግናው አፄ ዮሃንስ ከበርካታ የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋር(የትግራይን ጨምሮ) አንግታቸውን የተሰውበትን መሬት ሳይቀር ለሱዳን ሲሰጡ ሃፍረት የማያውቁ ከሃዲ ወንጀለኞች ናቸው። በመሆናቸውም ነው መሃል ኢትዮጵያን አፍኖ ለመግዛት አማራና ኦሮሞን ለመለያየት የባንዳ አባቶቻቸውን ጌቶች ፖሊሲ የተከተሉት። ይህ ተንኮል ከጣልያን የበለጠ ለእነሱ ሰርቷል። ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ከሁለቱ ህዝብ ፅንፈኛ የሆኑና ለፍርፋሪ የሚያድሩትን በማግኘታቸው ዙፋናቸው ላይ እስከአሁን ተደላድለዋል።

አማራው በየሄደበት እንደ አውሬ ታድኗል። ዐይኑ እያየ ገደል ላይ ተጥሏል። ይህንን ደግሞ ሃውዜን ላይ በትግራይ ህዝብ ሲፈፅሙት የተካኑ በመሆናቸው በፊልም እየቀረፁ "ኦሮሞው አማራውን እንዲህ አድርጎ ነው የገደለው" ብለው በአደባባይ በማሳየት እስከዛሬ የሠራላቸውን የመከፋፈል ሴራ ውጤታማ አድርጎታል። ተንኮላቸው በሁለት በኩል ስለት እንዳለው ቢላዋ ባንድ በኩል ኦሮሞውን ከአማራ ለመለያየት ሲያገለግላቸው፤ ሌላኛው ስለት ኦነግን የፖለቲካ ሞት እንዲሞትላቸው ማድረጋቸውን የዚህ ተንኮል መሃንዲስ ከሆነው መለስ ዜናዊ ጋር በቅርብ የሠሩትና አጥርተው የሚያውቁት ሊንጮ ለታ ዛሬ በአዛውንት እድሜአቸውና በሰከነ አእምሮአቸው ቢመሰክሩ ደስ ይለናል። ለትናንት የፖለቲካ ዓላማ ባይጠቅምም፤ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ ትምህርት ይሆነዋል።

ኦሮሞው በየቦታው ሲሰደድ፣ ሲገደልና የአገሪቱን እስር ቤቶች ሲያጨናንቅ፤ አድር ባይ ልጆቹ ወያኔ የሰጣቸውን የመቶ ዓመት ታሪክ ሲቆፍሩና ተጠያቂ ሲፈልጉ፣ ዛሬ የሚፈጸመውን ዐይን ያወጣ በደልና ግፍ እነሱም ዐይተው እንዳላዩ፣ ህዝቡም እንዳያይ ብዙ የከፋ ወንጀል ሠርተዋል። ቢዘርፉ የማይጠረቁ የወያኔ መኳንንት አዲስ አበባን ጨርሰው የአካባቢውን ገበሬ ሲያፈናቅሉ "የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ" በሚል ጅል ተመክሮአቸው ህዝቡን አጥንቱ እስኪቀር ትንሽ ፍርፋሪ እያገኙ አስግጠውታል። ዛሬ ፅዋው ሞልቶ ሲፈስና ህዝቡ ከዳር ዳር ሲነሳ በድንገት ባነኑና የህዝብ ደጋፊ ነን ለማለት በአዳራሽ ተሰብስበው ወያኔ ላይ መፎከራቸውን ከኢሳት ሰምተናል። ልጃገረዷ አረገዘች የሚል ሃሜት ሲናፈስ "እስቲ ታገሱ፤ እህል ከሆነ ይጠፋል፣ ሽል ከሆነም ይገፋል" እንዳሉት ኦህዴዶቹ ከልባቸው ከሆነ የምናየው ነው። ጌታቸው ወያኔ ሳይቀድሙት በመቅደም አባዜ የተካነ ነውና ቀበቶአቸውን ጠበቅ ሊያደርጉ ይገባል። የስምንት ዓመት ልጅ በጥይት ከሚደፋ፣ አስከሬን ለወላጅ በሺህ ብር ከሚሸጥ፣ አገርን ቆርሶ ከሚቸበችብ አምባገነን ጋር ከመስራት የከፋ ወንጀል አለ? ርህራሄ የሌለው ህወሃት ለዚህ ድፍረታቸው በመቶ ሺዎች አሳልፈው ከሰጧቸው፣ እስር ቤት ከሚገኙ ወንድሞቻቸው ጋር ለማጎር አይሳሳም። ደርግ መኢሶንን ተጠቅሞበት ደመኛ ጠላቶቹ ከሆኑት ኢህአፓዎች ጋር በአንድ እስርቤትና በአንድ ጉድጓድ እንዳገናኛቸው ሁሉ ወያኔም ይህንኑ እንደሚያደርግ ግልፅ ነው። ኦህዴድ ሆይ! በአገሪቱ በተለይ በኦሮሞው ላይ ለተሠራው ሁሉ ወንጀል ሃላፊነቱን በግልፅ በመውሰድና ከህዝብ ጎን በመቆም ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት ካልታገላችሁ ይህ ሙት ስርዓት ይዟችሁ ይሞታል።

የኦሮሞ ህዝብ ልበ ሰፊ ነው። አስተዋይና አዋቂም ነው። ይህንን ትልቅነቱን ሰሞኑን በሚገባ አሳይቷል። በውስጡ ያሉትን አማሮችና ሌሎችንም እንዲተነኩስ ዘረኞች ቢሰብኩትም በልበ ሰፊነት ሰላማዊ ትግል እያደረጉ ልጆቹ ለሰላምና ለፍቅር ሲሉ ወድቀዋል። አምናም ዘንድሮም የወደቁ ጀግኖች የኢትዮጵያ ሰማዕታት ናቸው። ለጠባብ አላማ አልወደቁም። ይልቅስ ገዳዮቻቸው ወራዳ ታሪክ ፈፅመዋል። የኦሮሞ ህዝብ በትልቅነቱ ልክ አባቶቹ በደማቸው የአቆዩአትን አገር ባለቤት ሆኖ ነፃ ሊያወጣት ከወንድሞቹ ጋር ይሰለፋል እንጂ ፖለቲከኞች በሰፉለት አርቲፊሻልና ጠባብ ዓላማ ራሱን ወደ ትንሽነት አይቀይርም። ለዚያውም የትግራይን ህዝብ የካዱ የባንዳ ልጆች መጠቀምያ አይሆንም። ለኦሮሞ ህዝብ እንኳን ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካ ትጠበዋለች። "ኢትዮጵያ የማን ሁና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው" ያሉት ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ ዛሬ በህይወት ቢኖሩ ምንኛ ተስፋቸው በለመለመ። "ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም" ያሉት ጀግናው ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ እንደልብ መስማት ባዳገታቸው በዚህ የሽምግልና ወቅት አሁን በምልክትም ቢሆን የኦሮሞን ህዝብ እንቅስቃሴ መረዳታቸው አይቀርምና የመጨረሻ ዘመናቸው በሃዘን እንዳይቋጭ መትጋት ያስፈልገናል።

የእኛ ያልሆነን ሶሻሊዝም ለማፅደቅ የብዙ ኢትዮጵያውያን ደም ፈስሶ ስር ሳይሰድ ቀርቷል። የልዩነትና የጎሳ ፖለቲካም አፍላው ያለፈበትና የመሸበት አስተሳሰብ መሆኑን እንደሶሻሊዝሙ ብዙ ከፍለንበት ተምረናል። ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ካለንበት ጨለማ ለመውጣት በጋራ ካልተነሳን ተስፋ የለንም። በተለይም ከአማራውና ከኦሮሞው የወጡ ጽንፈኞች በህዝቡ ስም በመነገድ አምባገነኑና ዘረኛው የውያኔ አገዛዝ እድሜ እንዲኖርው ከማገዝ እንዲቆጠቡ በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል። በዘውግ ፖለቲካ ተጨፍነን እያለ፣ ለከተማ መሬት ስናዝን፣ የአግሪቱ ለም መሬት ለሱዳን እየተሰጠ ነው። በጉርሻ ስንጣላ የህልውናችን መሰረቱ ራትና ምሳችን ሊሄድ ነው። መተማ ላይ የአፄ ዮሃንስን አንገት የቀላ ሰይፍ ድንበሯን አናስነካም ያሉትን ንፁሃን በመቁረጥ ላይ ነው። ሰይፉ ከሁለት አቅጣጫ ተደቅኖብናል። ከሱዳንና ከህወሃት። ሰሞኑን የሱዳኑ መሪ አልበሽር ሰራዊታቸው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲንቀሳቀስ አዝዘዋል። በኢትዮጵያ ምንግስት በኩል ደግሞ ኃይለማርያም ደሳልኝ ኢትዮጵያውያንን ሱዳንን የሚያጠቁ ሽፍቶች ሲሉ በፓርላማው ፊት ወንጅለዋል። ይህም ይህወሃት ሰራዊት ከሱዳን ጋር ተባብሮ ዜጎቹን ለመውጋት መዘጋጀቱን ያመለክታል። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደዚህ ያለ ለህልውናዋ ጠላት የሆነ መንግሥት አጋጥሟት አያውቅም።

ይህን ጽሁፍ በማጠቃለል ላይ እያለሁ ወያኔዎች በቀለ ገርባንና ሌሎችንም እያደኑ ማሰራቸውን ሰማሁ። ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ እጣ መሆኑን ያላወቀ ካለ አንድም የዋህ ነው፣ ያለዚያም የስርዓቱ አገልጋይ ነው። በቀለ ገርባን የመሰለ የተረጋጋ፣ ሰላም ፈላጊና ትልቅ የዓላማ ሰው አገሪቷ እንዳይኖራት ወያኔ ተግቶ መሥራት የጀመረው አሁን አይደለም። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ አሰፋ ማሩን፣ ተስፋዬ ታደሰን….ገድሏል፤ የቅንጅት መሪዎችን፣ አንዱዓለም አራጌንና ሺህ የኢትዮጵያ ተስፋዎችን አስሯል። በአራቱም ማዕዘናት ወጣትና ሽማግሌ ኢትዮጵያውያንን ገድሏል። አገርንና ህዝብን እንደጠላት ኢላማ አድርጎ ከተነሳ ስርዓት በጎ ነገር የመጠበቅ የዋህነት አብሮ የመግደልን ያህል ወንጀል ከሆነበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያውያን ሌት ተቀን መስራት ያለብን በቀለ ገርባንና ተመስገን ደስአለኝን ከመሰሉ ጀግኖች ጎን መቆምና

እነሱን የመሰሉ ሺዎችን ከመካከላችን ማፍራትና መንከባከብ መሆን አለበት። ዳር ቆሞ ሌሎችን በመተቸት የተጠመደው ልሂቃን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ተገቢ ዋጋ እየከፈሉ ባለበት ሰዓት የጥርጣሬና ያለመተማመን ዲስኩሩን ያቁምና የትግሉ አካል ይሁን።

ኢትዮጵያ የቅን ልጆቿ ሁሉ የጋራ ናት!

በሁሉም አቅጣጫ መስዋዕት በሚከፍሉ ልጆቿም በቅርቡ ጨለማው ይገፍላታል!!

በአንድነት የተነሱ ታጋዮቿ ይታደጓታል!!

Amerid2000@gmail.com

Wednesday, October 21, 2015

Report of the Conference on the Future of Eritrea and Ethiopia

October 21, 2015
EROn Sunday October 18, 2015 a successful one-day long conference was held at Georgetown Marriott Hotel, 1221 22nd St NW, Washington, DC 20037. The theme of the conference was on the present and future relationship between Eritrea and Ethiopia and had conflict prevention and resolution threads. The panelists range from former United States diplomats and State Department officials to former government officials of Ethiopia, senior academics, authors, professionals and social and political activists. The conference was organized by Vision Ethiopia, a network of Ethiopian academics and professionals residing in the United States and Japan, in collaboration with the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT).  The number of people who attended the conference was at full hall capacity.   The audience had ample opportunities to ask and express diverse view points on a variety of current and sensitive issues affecting Ethiopia and Eritrea.  The full conference audio and video is available and will be transmitted to the people of Eritrea and Ethiopia very soon.  Although there were four panel sessions scheduled only three sessions were delivered because of lack of time. They all focused on historical, social, cultural and professional dimensions of building and rebuilding trust between the two related people, the role of super powers and regional powers in the Ethio-Eritrea relationship, and the risks and opportunities of establishing fraternal relationship between the Government of Eritrea and the Ethiopian political organizations.

The Master of Ceremonies, W/t. Birtawit Girmay, Manager of  ESAT Washington DC studio, opened the conference at 10:15. She outlined the objectives of the conference and laid out the conduct and procedure of the conference. After clarifying on important issues of housekeeping, W/t Birtawit invited Ato Gizaw Legesse of Vision Ethiopia and ESAT producer to make the formal opening remarks about the purpose, importance and timeously nature of the conference.
The first of the three panel sessions was moderated by Professor Getachew Begashaw. The four panelists were Mr. Tariku Debretsion, Mr. Gashaw Gebre, Dr. Assegid Habtewold, and W/t Lulit Mesfin. They all presented their well researched and documented papers that were well received by the audience. As a prelude to the ensuing two sessions, drawing on their vast experiences of engagements and studies, these four panelists talked on the roles of Ethiopian and Eritrean Community leaders in building people-to-people relationship at different levels, how much the basic principles of peaceful co-existence of nations can be foundations for peace between the two countries and the region as a whole, and how social and professional organizations, including but not limited to churches, mosques, professionals and men and women of the Arts can create useful links and elevate  the relationship to an even higher level.
The second session was moderated by Professor Minga Negash.  The theme of the session was on the roles and interests of foreign powers in the regional peace, security and stability. On the panel were former senior diplomats of the United States, Ambassador Herman Cohen, Former Assistant Secretary of State and Ambassador David Shinn. Their tenure at the State Department coincided with the collapse of central government of Ethiopia and the takeover of Addis Ababa and Asmara by the TPLF/EPRDF and EPLF in 1991, and the 1998-2000 war between Ethiopia and Eritrea. They were joined by the veteran critical scholar of Ethiopia, Professor Emeritus Mesfin Wolde Mariam.  There was a candid discussion about the United States’ policy failure towards Ethiopia and Eritrea. Ambassador Cohen revealed that Eritrea’s relation with the United States is unlikely to change during the term of office of President Obama.
He was also open about what transpired in 1991. He revealed that the crisis in Somalia is a threat to the United States and its policy appears to be driven by a singular concern for security. For Ambassador Cohen Ethiopia must accept the boundary commission’s ruling and start engaging Eritrea on all other matters. He underscored that both governments do not trust one another.  As regards to the lifting of the UN sanctions against Eritrea he informed that it was only the the United States that used its veto power to block the lifting. He also revealed his efforts to engage in second tier diplomacy and organizing expert level discussion between the two countries.
Drawing from his experience as an Ambassador, Dr. Shinn went on straight to the identification of the powers that have interest in the region. He classified them into a two tier countries and acknowledged the United States’ influence must be examined in light of other countries’ interests. For Ambassador Shinn accepting the boundary commission’s ruling was evident and did not spend time on that. He was more cautious about the prospect of peace and urged that more work needs to be done to prevent another cycle of conflict. The European Union, China, and regional powers are also important and noted that much of what happens in Ethiopia is influenced by regional powers.
repo Er

Professor Mesfin was unforgiving in letting his audience know that successive Ethiopia governments, including the current regime, were clients of super powers, and Eritrea is being punished for resisting dominance by the United States. The old Ethiopian ethos of not bending to foreign powers and pride exists only in Eritrea, as manifested by the behavior of the Eritrean government and in contrast to the behavior of the regime in Addis Ababa in relation to foreign powers, Professor Mesfin Woldemariam asserted.
As a peace activist he regretted that the peace proposal he initiated before the collapse of central government in 1991 was not supported by the United States. He highlighted the double standards of the United States, and compared Ethiopia and South Africa’s reconciliation.  He also urged that Ethiopians must take ownership of their own destiny and start building and rebuilding the relationship with Eritrea.  In general, there was a consensus about the successes and failures of U.S diplomacy in the area. And all the three panelists explained the economic incentives that are available from reconciliation and cooperation between the two countries.
Nine participants from the audience presented varieties of questions. Most of them were directed to Ambassador Cohen and Ambassador Shinn. There was no unanswered question that was important. The questions to Professor Mesfin were more focused on seeking his guidance. The session closed with vote of thanks and a call for the continuation this type of productive panel discussion. The session took more time than was originally planned because of the interest shown by the audience. The panel closed with a sense of satisfaction.
The third session started after a brief lunch break. The session was moderated by Professor Messay Kebede and the theme of the discussion was on relations between the Eritrean Government and the Ethiopian opposition forces.  Ambassador Dr. Kassa Kebede, former minister and diplomat of the Ethiopian Government under Dergue, Mr. Erimias Legesse, former deputy Minister of government communication under TPLF/EPRDF, Dr. Mesfin Abdi of the recently formed Oromo Democratic Front and Mr. Neamin Zeleke of the recently merged Patriotic Ginbot 7 were on the panel.
Dr Mesfin Abdi presented a carefully thought out document and indicated that the view expressed in the document is also being adopted as the official position of his party. He outlined a carefully thought out proposal and invited discussion. He emphasized the need to recognize the sovereignty and independence of Eritrea in order to have peace, stability and prosperity in the sub-region.  He further announced that his organization is planning to host a conference shortly, and called upon for participation.
Dr Mesfin was followed by former Ambassador Dr. Kassa Kebede.  Dr.  Kassa started his presentation by making few remarks on Ambassador Cohen’s presentation.  Citing early historical inscriptions he outlined the history of state formation in Ethiopia.  Ethiopians and Eritreans lived together for thousands of years and shared language, culture, religion, and geography until recently. Dr. Kassa Kebede stated that the two countries had defended the region from enemy forces and colonialists in unison. “Of course, Eritrea was under Italian colonialism for fifty years and British Military Administration (BMA) for ten years before the Federation which was abrogated during Emperor Haile Selassie’s regime, “he recalled.
He then moved to answering the questions about the feasibility of good relationships between the government of Eritrea and Ethiopian political parties. He recognized the rights of the Ethiopian opposition forces to do so by declaring that the choice must be left to the organizations themselves.  Throughout his presentation Ambassador Kassa detoured from time to time and intimated a number of important information which surprised/excited the audience. For instance, he confirmed that the relation between Eritrea and the United States might be simply explained by personality clashes between Ambassador Suzan Rice, who is now the Chief National Security Advisor of President Obama and President Isayas Afeworki, and noted that this relation is unlikely to change while President Obama is in office.  The implications of this for Eritrea is that lifting the UN sanction against Eritrea may not be possible.
Dr. Kassa Kebede cited closed door negotiations and backdoor meetings held with leaders of the Eritrean People’s Liberation Front (EPLF) during his time as a top official and Ambassador in under the PDRE/WPE regime. He told the audience that President Isaias Afeworqi has an unbending belief in the existence of a united Ethiopia and that he is a living witness to this belief held by the Eritrean President.
Mr. Ermias Legesse presented the TPLF/EPRDF’s policy towards Eritrea. He explained the differences between what are discussed in EPRDF internal documents and what are published in its ideological magazine, using pennames.  Ethiopia’s policy and party official statements, including Prime Minister Haile Mariam public pronouncements are exact extracts from the party’s ideological magazine which were written by the late Prime Minister Meles Zenawi and Minister Bereket Simon.  According to Ermias, the policy of containment, isolation and undermining the Eritrean government and eventual regime change is the strategy of the government of Ethiopia.
The fourth panelist was Mr. Neamin Zeleke. Although he did not prepare a formal presentation, he made few general remarks about the nature of the government in Ethiopia and provided the rationale for his organization’s   actions. He told the audience that there are thousands of political refugees in Eritrea. He emphasized that Eritrea is the only safe place in the Horn of Africa where Ethiopian refugees can go.  He reported that Patriotic Ginbot 7’s relationship with the government of Eritrea has passed the initial tests of building trust and Eritrea does not interfere in his organization’s internal affairs.
There were a total of eight questions and views from the audience; and some from both sides of the Eritrean political divide. There were some views coming from different angles from the Ethiopian side as well. Some of the views regarding Eritrea include call for democracy in Eritrea and how Ethiopia can be helpful. This view was not well received by Ethiopians in that Ethiopians acknowledge the fact that this must be left for Eritreans. The comments from the Ethiopian side include the reliability of the government of Eritrea in committing itself to the unity of Ethiopia, what Ethiopian political organizations may have to give in order to get Eritrea’s support, and Ethiopia’s right to own the port of Assab.
Mr. Neamin stated unequivocally that his party has no mandate to negotiate on the future of Ethiopia with any government or international body and only an elected and properly constituted future government of Ethiopia would take the matter forward. He, however, said that they see the current relationship, not as a tactical one, but as a groundwork for building confidence, trust, and a springboard to chart a new era of peace, stability prosperity within a framework of a comprehensive and strategic partnership with the state of Eritrea that should include economic, security, and other vital interests such as the question of ports and access to the sea.
The panelists agreed that at present the focus must only be on building trust between The Eritrean government and the Ethiopian opposition forces.
Vote of thanks and concluding remarks were delivered by Dr Assegid Habtewold and the conference was closed at 6:30 pm.
Note: the moderators’ session, scheduled to be the last one, “Quo Vadis? Where are we going to? The un-answered Questions”, was to be presented by Professors Messay Kebede, Minga Negash, and Getachew Begashaw.

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጀርባ

አርበኞች ግንቦት 7
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጀርባ  ከሁለት አመት በፊት በቂ ህዝባዊ ምክርና ውይይት ያልተካሄደበት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባር ላይ ለማዋል የተደረገው ሙከራ በበርካታ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ እንደገጠመውና በየኮሌጁ በተነሱ ተቃውሞዎች ሳቢያ በርካታ ወጣቶች በወያኔ እንደተገደሉ ብዙዎች በእስር እየማቀቁ እንዳሉ ይታወቃል። ግጭቱ የፈጠረው ቀስል ገና ባላገመ ማግስት በአሁኑ ወቅት የህወሃቱ አባይ ጻሀይ በውድም በግድም ፕላኑ “ይተገበራል” ብሎ በዛተው መሰረት ተግባር ላይ ለማዋል ሰሞኑን ሽር ጉድ ተይዟል። 
ከዚህ ማስተር ፕላን በስተጀርባ የተደበቀው የህወሃትና ጀሌዎቹ አላማ በአግባቡ አለመተንተኑ የፕላኑ ተቃዋሚዎች ኦሮሞዎች ብቻ በመሆናቸው ጥያቄው የግዛት ስፋትና ጥበት ወይም ባለቤትነት ጉዳይ መስሎ ይታይ እንጂ ነገሩ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስቆጪና ተቃውሞ ሊያስነሳ የሚገባው ደባ ነው። ከህወሃት/ ወያኔ ማስተር ፕላኑ ጀርባ የመሬት ዝርፊያ እቅድ እንዳለው አርበኞች ግንቦት 7 ከእስከ አሁኑ ተመክሮና ባህሪያቸው በግልጽ ማየት ይቻላል ብሎ ያምናል።
     እስከዛሬ ባለን ተመክሮ ከተማውን በማስፋፋት ስምና መሬት የመንግስት ነው የሚለውን ሰበብ በመጠቀም ድሃ ገበሬዎችን በማፈናቀል የተዘረፈውን መሬት ልብ ማለትና ማስታዎስን ያሻል።
     በሀገራችን ቅጽበታዊ ሚሊየነር የሆኑት የወያኔ ሹማምንት፣ ዘመዶቻቸውና ባለሟሎቻቸው ዋናው የሃብታቸው ምንጪ ድሆችን በማፈናቀል በገፍ እየዘረፉ የሸጡትና የተቆራመጡት መሬት ነው። የአዲስ አበባ መሬት የወያኔ የወርቅ ማእድን ጉድጓድ ከሆነ ቆይቶል። በየከተማው ዙሪያ ያሉ ምስኪን ገበሬዎች የረባ ካሳ እንኮን ስላላገኙ ከግብርና ወጥተው ወደኩሊነትና የቀን ሰራተኝነት ተበታትነው ቤታቸው ፈርሶ ይገኛል።
     የወያኔ መንግስት ይህን ማስተር ፕላን ስራ ላይ ለማዋል የሚስገበገብበት ዋናው ምክንያት የሀገርና ከተማ ልማት ጉዳይ አይደለም። የከተማው መሬት ተዘርፎ በማለቁ ሌላ በገፍ የሚዘረፍ መሬት ለማመቻችት ብቻ ነው። ችግሩ ለምን ፕላን ኖረ፣ አዲስ አበባ በአግባቡ ማደግና መልማት የለባትም የሚል አይደለም። ቁምነገሩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በቅጽበት እያፈናቀለና እየደኸዩና ቤተሰብ እየፈረሰ፤ በጥቂት ህገ ወጥ ባለስልጣናት የሚደረገው ሀፍረት የለሽ ዝርፊያ ነው ችግሩ። በመሆኑም ይህን የዝርፊያ ተግባር ብሄረሰብ ሳንለይ ሁላችንም ልንቃወም ይገባል። ይህ ማስተር ፕላን የህግ የበላይነትና ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ ስራ ላይ በአግባቡ ስራ ላይ መዋል አይችልም። በፕላኑ የተጠቃለለውን ህዝብና አካባቢ ሊጠቅም የማይችል ፕላን ሊሆን የሚችለው የዝርፊያ ፕላን ብቻ ነው።
      የወያኔ መንግስት በሰፈራ ሁኔታ ባካሄደው የከተማ ቦታ ዝርፊያ ነው ዛሬ በየመሸታ ቤቱና በየከተማው ዋና ዋና መዝናኛ ቦታዎች ብር እንዳሻቸው የሚነዙ የወያኔ ቱባ ባለሟሎች  የተፈጠሩት። ወያኔ ሌላው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ዘረኝነት በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን።
     መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን በማር የተላወሰ መርዛማ ፕሮጀክት አጥብቆ እንዲታገል አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
በሀገራችን ጥቂቶች እያረፉ የሚከብሩበት ድሃ ወገኖቻችን ይበልጥ እየደኸዩ የሚሄዱበት ዘመንና ስርአት አለንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወገድ ወጣቱ አርበኞች ግንቦት 7ን ባለበት ይቀላቀል። ትግላችን እስከመጨረሻው ድል ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
አርበኞች ግንቦት 7

Report of the Conference on the Future of Eritrea and Ethiopia

by Vision Ethiopia and ESAT

Conference on the Future of Eritrea and EthiopiaOn Sunday October 18, 2015 a successful one-day long conference was held at Georgetown Marriott Hotel, 1221 22nd St NW, Washington, DC 20037. The theme of the conference was on the present and future relationship between Eritrea and Ethiopia and had conflict prevention and resolution threads. The panelists range from former United States diplomats and State Department officials to former government officials of Ethiopia, senior academics, authors, professionals and social and political activists. The conference was organized by Vision Ethiopia, a network of Ethiopian academics and professionals residing in the United States and Japan, in collaboration with the Ethiopian Satellite Television and Radio (ESAT). The number of people who attended the conference was at full hall capacity. The audience had ample opportunities to ask and express diverse view points on a variety of current and sensitive issues affecting Ethiopia and Eritrea. The full conference audio and video is available and will be transmitted to the people of Eritrea and Ethiopia very soon. Although there were four panel sessions scheduled only three sessions were delivered because of lack of time. They all focused on historical, social, cultural and professional dimensions of building and rebuilding trust between the two related people, the role of super powers and regional powers in the Ethio-Eritrea relationship, and the risks and opportunities of establishing fraternal relationship between the Government of Eritrea and the Ethiopian political organizations.