Monday, October 30, 2017

ህወሃት ጣእረሞት ባጭሩ ሲዳሰስ (መስቀሉ አየለ ,October 24, 2017)


Meles Zenawi on fireለዘር ፖለቲካ የበላይነት በመስጠት ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከም የቋንቋ ባቢሎን ገንብቶ ክልላዊ አድረጃጀትን ሲገነባ የኖረው ወያኔ የዘራው ዘር ፍሬ አፍርቶ ዛሬ የሱን ልሳን የሚናገሩ ሚሊዮኖች በየአቅጣጫው እንደ እንጉዳይ መፍላት ጀምረዋል። በዚህም የተነሳ ማእከላዊ መንግስቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ግባተ መሬቱ ተፈጽሟል ማለት ይቻላል።
በመሆኑም ከታሰበላቸው አቅም እጅግ አልፈው በመሄድ ለራሱ ለህወሃት የማይበጁበት ብቻ ሳይሆን የህልውናው ስጋት ወደ መሆን ደረጃ የደረሱትን ክልሎች እንደገና በማዳከም ብሎም ማእከላዊ መንግስቱን በተወሰነ ደረጃ በማጠናከር የህወሃትን የበላይነት መልሶ ለማስጠበቅ ምን ማድረግ እንዳለበት መቀሌ ከትሞ የከረመው የትግራዩ ገዥ ጉጅሌ አንድ እስትራቴጅ ይዞ ወጥቷል።
ይኸውም በለማ መገርሳ፣ ዶር አቢይና አዲሱ አረጋ በኩል የታየው መቀናጀት፣ በተሾሙ በአጭር ግዜ ውስጥ ያገኙት የህዝብ ተቀባይነት እንዲሁም ከብአዴን ጋር የጀመሩት የጎንዮሽ ግንኙነት ቀጣዩን አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳየው በመሆኑ በእድገት ሽፋን ወደ ፌደራል መንግስቱ አምጥቶ ከህዝብ በመነጠልና ሽባ በማድረግ እነሱን የተሻለ ሎሌ ሆነው ሊተኩ በሚችሉ አዳዲስ አሽከሮች ለመተካት ከስር ሰዎች አዘጋጅቶ የጨረሰ ሲሆን ሂደቱም ሃይለማርያም ደሳለኝን በራሱ በለማ መገርሳ እስከመተካት ድረስ ዘልቆ ሊሄድ እንደሚችል ፍንጮች መታየት ጀምረዋል።
ነገር ግን ይህ አካሄድ የማያዋጣ እና ህዝባዊ ተቃውሞውም የሚቀጥል ከሆነ “ማእከላዊ መንግስቱ ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ የአገሪቱን ህልውና ሊያስጠብቅ ስላልቻለ በህዝቡ ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለመቀልበስ መከላከያው ላልተወሰነ ግዜ አገሪቱን የመምራት ሚናውን እንዲወጣና ጸጥታ እንዲያስከብር ሃላፊነቱን ወስዷል” በሚል አጭር የማርሻል አዋጅ ቤተመንግስቱን በታንክ በመክበብ የሃይለ ማርያምን ካቢኔ ጠራርጎ በማውረድ በኩዴታ ስልጣኑን ለሳሞራ የኑስ ወደማስረከቡ ይሄዳል ማለት ነው።
የመጀመሪያው አማራጭ የማይሰራ ከሆነና ወደ መፈንቅለ መንግስቱ መሄድ የግድ ከሆነበት ደግሞ ለዚሁ እርምጃ እንደዋና ግብአት ይሆነው ዘንድ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ዘር ተኮር የሆኑ ግድያዎችና ዘረፋዎች በስፋትና በተቀናጀ መልኩ በተጏዳኝ እንዲካሄዱ ህወሃት ያለውን አቅም ሁሉ አሟጦ እየተጠቀመ ነው። እዚህ ላይ ወያኔ አሁን ባለው የዘር ክፍፍልና ውሱን አቅም እንደ ግብጹ ሴሴ መፈንቅለ መንግስት አደርጋለሁ ቢል ይሳካለታል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ይልቁንም ለህወሃት እንደዳይኖስረስ እራሱን በራሱ በልቶ ለመጨረስ የመጨረሻው ደወል መሆኑ አይቀርም።
በመሆኑም በተለያዩ የኦሮሞያ ግዛቶች ሰሞኑን በከፋ መልኩ ሲፈጸም እያየነው ያለው ከኢንተርሃሞይ የማይተናነስ የዘር ማጽዳት ከጌታቸ አሰፋ እየተቀበለ የሚያስፈጽመው ሰው ረዳት ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/መስቀል ይባላል። ይኽ ሰው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ነው።የትውልድ ስፍራው ምእራብ ሸዋ ዞን፣ የትምህርት ዝግጅት፦ በፖሊስ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በአመራር ሳይንስ እና በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን ሁለተኛ ዲግሪ ሲኖረው የስራ ልምዱ በኦሮሚያ ክልል ከወረዳ አንስቶ እስከ ክልል የፖሊስ አመራር፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዳይሬክተር በመሆን አገልግሏል።እዚህ ድረስ የደረሰው ለህውሓት ታማኝ በመሆኑ እና በጣም ጨካኝ እንደሆነ ይነገራል።

No comments:

Post a Comment