በሳውዝ አፍሪካ የተዘጋጀው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ በደመቅ ሁኔታ እየተከናወነ እንዳለ ከስፍራው ለማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ሪፖርት ለማድረግ የሄደው ባለደረባችን ገልጾአል ። እንደ ባልደረባችን አገላለጽ ከሆነ የቴዲ አፍሮ ፕሮግራም በከፍተኛ ድምቀት ከመጀመሩ በፊት ሙሉ ባንዱ የብሄራዊ ቡድኑን መለያ ለብሶ እንዲጫወት መደረጉን ገልጾአል ይህ ደግሞ ደጋፊውን ህብረተሰብ እና የሙዚቃ ወዳጆቹን ይበልጥ ሊያስደስት እንደሚችል እና የብሄራዊ ቡድኑን ይበልጥ ድጋፋቸው ሊያጠናክረው እንደሚችል አክሎ ተቁሞአል ። ከቴዲ አፍሮ ጀምሮ አጃቢ ሩት ገብረመስቀል ኪቦርድ ቴዲ አሃዱ አሁንም፣ ኪቦርድ ያሬድ አብርሃም፣ ጊታር ኤርሚያስ ከበደ ፣ ቤዝ ጊታር አበራ አለሙ ፣እና ሩፋኤል ወልደማርያም ድራም በመጫወት ከነ ሙሉ መለያቸው ደምቀው መታየታቸውን እና በስፍራው ከተጠበቀው ህዝብ በላይ መታደማቸውን ረዳት ሪፖርተራችን ተወልደ ከስፍራው ዘግቦአል ።
Comment |
No comments:
Post a Comment