ባለፈው ሐሙስ በተደረገው የኢህአዴግ/ወያኔ የካቢኔ ሹም-ሽር ላይ በርካታ አስተያየቶች በመደመጥ ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም የበርካቶቹ አስተያየትና ትንተና እዚህ ግባ የማይባልና፣ በወያኔዎች አማርኛም “ውኃ የማይቋጥር” ሆኖ ስላገኘሁት፣ የኔን አስተውህሎት ላቀርብ ወደድኩ፡፡ በቅድሚያ ግን፣ በሀገር ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ ፖለቲካ ማኅበሮች/ፓርቲዎች መሪዎች እየተቀባበሉ የሚደጋግሙት ነገር ያው የተለመደውን ነው፤ “ሹመቱ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ አይደለም!” ምናምን የሚል ወቀሳ አይሉት ትችት፣ እንዲያው የንፉግና የፈሪ ጩኸት ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹን መሪዎች ወያኔ ደጋግሞ አጥጋቢ አማራጭ የላችሁም የሚላቸው ለምን እንደሆነ፣ ብዙዎቹ አሁንም አልተገለጠላቸውም፡፡ መቼ “ተገለጠ/ቡድሀ!” ብለው እንደሚጮሁ አላውቅም፤ በተስፋ ግን እንጠባበቃለን፡፡
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEgCSRBgxNU1-g84rlIdgBQh9nh5bS4wBzlCnQZVbb-tmKWLczCcf_Bs1dWP98maw9HmpPDLcCR4m6IPm08WTLUrBSGtqK2MZUapQawX8i5SEsUw1pwwP_qlcIXJeymH5766uAQTqXv-ae0b/s200/images1.jpg)
የፓርላማውን ስርጭት ለተመለከተው ሰው ሁለት የሚደንቁ አልቦ-ቋንቋ እንቅስቃሳችን ጠቅላይ ሚኒስትሩና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን አሳይተዋል፡፡ የተሹዋሚዎቹን ስም ዝርዝር ሲያነብ የነበረው ኃይለ ማርያም ደሳለኝ (The Mimic Man)፣ መለሰ ዜናዊኛ ማስኩ/ጭንብሉ ጠፍቶበት ሲኮለታተፍ ነበር፡፡ ምናልባትም በሥራ ብዛት ሰበብ ይህንን የሚያህል ድርጅታዊ ውሳኔ ሲወሰን በስብሰባ ላይ አልተገኘም ነበር ይሆናል፡፡ ጎበዞቹ የወያኔ አርክቴክቶች ውሳኔያቸውን እንዲያነብ አዳራሹ ውስጥ ከገባ በኋላ ነው የሰጡት፡፡ የተሹዋሚዎቹን ስም ዝርዝር ሲያነብ ከፍተኛ የሆነ ቃና-ቢስነት ይታይበት ነበር፡፡
ተሹዋሚዎቹ ቃለ መኻላቸውን ከፈፀሙ በኋላ ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን ፊቱን አቀጭሞ ለማጨብጨብ እንኳን ሲጠየፍ ላየው፣ በሥራ ብዛት የተነሳ፣ እርሱም ይህንን ከፍተኛ ድርጅታዊ ውሳኔ ሳይሰማ እንደቀረ ያጋፍጣል፡፡ ያም ሆኖ፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በእኩልነት ላይ ያልቆመው የኢሕአዴግ/ወያኔ ካቢኔ በስመ ክላስተር፣ ቀደም ብሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ለገሰ አስይዞት የነበረውን የግብርናና ገጠር ልማት ኃላፊነት ሸርሽሮ ልፍስፍስ ክላስተር አደረገው፡፡ በአቅም ግንባታው ሚ/ር ተፈራ ዋልዋ ተይዞ የነበረውን ሸርሽሮ ለአቶ ሙክታር ሰጠው፡፡ በዶ/ር ካሱ ኢላላም ተይዞ የነበረውን የመሠረተ ልማት ሚኒስትርነት ሥልጣን አዘምኖና ደራርቦ፣ በዚያም ላይ የቴሌኮሙን ደሕንነት ከነማዕከላዊው ደሕንነት ተያያዥ ኃላፊነቶች ለዶ/ር ደብረ ፂዮን ሰጠው፡፡ እንደተለመደው፣ ከፈረንጆቹ ጋር የመሞዳሞዱን ጉዳይ ለይስሙላ ለኃይለ ማርያም ሰጥተው ሲያመነቱ ከቆዩ በኋላ፣ መልሰው “በስዩም መስፍን ርስት፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኀኖም ሆይ-ግባበት!” አሉት፡፡
የሹምሽሩ ፖለቲካዊ አንደምታዎች ምንድናቸው?
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEgxttMBmyKsLFLTNSxNC07pRSEIu3RZStX0x01-kO-JZxCe1iY-1NvMA98G555wxDt6MCutbCGftPNeruW5BC93G8W2TiTQ0m8HtkFYR80Bf-NptPxfO51m9FG0qzCRu3LIDw7RLmSrryTQ/s1600/images2.jpg)
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEhsXs1UgwWYypP0X2Mci5PBC2ptteJiOpcxieISHqfxOrh4AE9OCf4XsqfWAjDDlX1GXx3ctUE_OqkWz1DBG79goc-__NgHvV3AURssk4B3dfGFvayZ4Rud7ehyC9nqlWrsn4QT1ItuFv-f/s1600/images3.jpg)
ስለሆነም የሹም ሽሩ ዋነኛው አንደምታም፤ ምናልባት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በርትቶ ኃላፊነቱን ከተወጣ እሰየው፤ ካልተወጣ ግን በነሐሴ 2004 እና በመስከረም 2005 ዓ.ም፣ በድሕረ-መለሠ ዜናዊ ወቅት የተፈጠረውን የሕወሀት-ወያኔ የተተኪ መሪዎች ችግር ለመፍታት ነው፡፡ በመሆኑም፣ ሦስቱ የወያኔ እህት ድርጅቶች አንድ አንድ እጩዎችን ሲያዘጋጁ (ለዚያውም የፖለቲካ ውሳኔዎቻቸውና የሥልጣን ምሕዳራቸው ልፍስፍስ በመሆኑ የተነሳ አፈጻጸማቸው ደካማ እንዲሆን ሆን ተብሎ ተዘይዷል)፣ ሕወሀት-ወያኔ ግን ሁለት እጩዎችን አዘጋጅታለች፡፡ ለዚያውም በጉልሕ ሙሉ ሥልጣናቸውና አፈጻጸማቸው ሳይቀር እንዳይስተጓጎል ተብሎ የፋይናንስና የኤኮኖሚውን ክላስተር ከነደሕንነቱ፣ ከነውጭ ጉዳይ ጽ/ቤቱ፣ ብሎም ከነመከላከያ ሠራዊቱ ይዘው እንዴት አፈጻጸማቸውና ሥልጣናቸው ሊቀጥል አይችልም?
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEiamnoAxf9Mmt8Ixio6EcGStYQtT8voV2eOlEcc9IrW0jJ2KTq6qMhhP1ZjUKleqwjPrHDM1t_ToXRvea-Y-h4snL6JRAT7eY6t4giDJBn1jwhKa67R2qvfgIz-oRcJ9it8sz1y_BlpiK2H/s1600/images6.jpg)
No comments:
Post a Comment