Monday, May 18, 2015

የቀን ጨለማ የወረሳቸው የመርካቶ ልጆች



ህልማቸው በሜዲትራንያን ባህር የተዋጠው 7ቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከኤልሳቤት እቁባይና አለማየሁ አንበሴ በቅርቡ በሜዲትራኒያን ባህር ከዘጠኝ መቶ በላይ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ ሰጥማ 28 ተጓዦች ብቻ በህይወት በተረፉባት ጀልባ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት መካከል በአደጋው የሞቱት የሰባት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አሳዛኝ መርዶ የተሰማው ከትላንት በስቲያ ነበር፡፡ የሰባቱም ሟቾች የትውልድ ሰፈር ደግሞ በአዲስ አበባ መርካቶ በሚገኘው የአባኮራን ሰፈር ውስጥ ነው፡፡
በትላንትናው ዕለት የሟቾች ቤተሰቦችን ለማነጋገር ወደ አካባቢው ስንሄድ ሰባት ድንኳኖች ተርታውን ተተክለው ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድና ጓደኞች ለቅሶ ተቀምጠው ነበር፡፡ ከሊቢያ ባህር ዳርቻ ተነስታ ጣሊያን ልትደርስ ስትል በሰጠመችው ጀልባ ውስጥ ተሳፍረው ከነበሩት የአባኮራን ሰፈር ልጆች መካከል ዘመን ኢብራሂም የተባለው ወጣት በአስገራሚ ሁኔታ ህይወቱ ሊተርፍ ችሏል፡፡ የጀልባዋን መስጠም አስመልክቶ በአልጀዚራ በተሰራጨ ዘገባ፣ ልጁ ከአደጋው ተርፎ በእርዳታ ሰራተኞች ድጋፍ ሲደረግለት ታይቶ ነበር። ይሄኔ ነው አብረውት የሄዱት የሰፈሩ ልጆች የት ገቡ የሚለው ጥያቄ በቤተሰብና በጓደኞች ዘንድ የተነሳው፡፡
ቀደም ሲል በተመሳሳይ መንገድ በባህር ተጉዘው ጣሊያን የገቡ የሰፈር ልጆች ባደረጉት ማጣራት ግን ከዘመን ኢብራሂም በስተቀር ሁሉም ባህር ውስጥ ሰጥመው እንደሞቱ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡ ወጣቱ ዘመን ኢብራሂም ተዓምራዊ በሚመስል ሁኔታ ነው ህይወቱ የተረፈው፡፡ ወደ ባህሩ ሲወድቅ በአጋጣሚ ውሃው ላይ ስትንሳፈፍ ያገኛትን አንዲት ጀሪካን ይዞ ለ2 ሰዓታት ያህል ራሱን ለማዳን ጥረት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ነው የነፍስ አድን ሰራተኞች የደረሱለት፡፡ እስከዚያው ግን ብዙ በመሰቃየቱ አሁንም በሙሉ ጤንነት ላይ እንደማይገኝ ጓደኞቹ ነግረውናል፡፡ ዘመን ኢብራሂም አሁን የሚገኘው በጣሊያን ነው ተብሏል፡፡
መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ.ም የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለማሻሻል አውሮፓን አልመው ከሰፈራቸው የወጡት 9 ወጣቶች ሲሆኑ ስምንቱ በአደጋው እንደሞቱ ቢነገርም የአንደኛው ወጣት ወላጆች ግን “ልጃችንን በቲቪ አይተነዋል፤ አልሞተም” በማለት መርዶውን አልተቀበሉትም፡፡ አብዱል ጅላል ወጉ ወይም በሰፈር ስሙ ሙራድ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን በቀን ስራና በሱቅ በደረቴ ይተዳደር ነበር፡፡ ኑሩ መሀመድ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ የትምህርት ክፍል አንድ አመት ተምሮ ቤተሰብ ለመርዳት ትምህርቱን አቋርጦ ነው የተሰደደው፡፡
አብዱልከሪም ዘይኒ ደግሞ የ20 ዓመት ወጣት ሲሆን በቀለመወርቅ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነበረ፡፡ ሰይድ ይመር የ22 ዓመት ወጣት ሲሆን በተለያዩ የጉልበት ስራዎች ራሱንና ቤተሰቦቹን ያስተዳድር ነበር ተብሏል፡፡ አሊ መሀመድ የ26 ዓመት ወጣት ነበር፡፡ የሚሰራበት ሱቁ እንዲፈርስ በመወሰኑ ነው እቃዎቹን ሸጦና ገንዘብ ተበድሮ ለስደት የወጣው፡፡ ነጃ ሳቢር አወል የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን የተለያዩ ተባራሪ አነስተኛ የንግድ ስራዎችን በመስራት ይተዳደር ነበር፡፡ እንድሪስ አደም ደግሞ የ18 ዓመት ወጣት ሲሆን ከኢንፎኔት ኮሌጅ በቴክኒክና ሙያ ተመርቆ ስራ አጥ እንደነበር ከአካባቢው ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል፡፡ የእነዚህ ወጣቶች መርዶ ሰሞኑን ቢነገርም ወላጆች፣ ቤተሰቦችና ጓደኞች መሸበር የጀመሩት ግን በሊቢያ በአይኤስ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መርዶ ከተሰማ ጊዜ አንስቶ ነው፡፡ በየጊዜው ወጣቶቹ በአይኤስ እጅ ወድቀዋል የሚል መረጃን ጨምሮ ብዙ ያልተጣሩ ወሬዎች ይመጡ ስለነበር፣ ቤተሰብና ጓደኞች በስጋት ውስጥ ነው የከረሙት። አብዱ ሀሰን አሊ የተባለው የሟቾቹ አብሮ አደግ መርዶውን እንዲያረዳ ከጣሊያን ሲደወልለት ሊሸከመው የማይችል ዱብ እዳ እንደወረደበት ነበር የቆጠረው፡፡ “ ማን ማንን ሊያፅናና ነው?” የሚል ከፍተኛ ጭንቀትና ፍርሀት ውስጥ ገብቶ እንደነበር ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡
ሆኖም መርዶው በድንገት ደርሶ ቤተሰብ ከሚጎዳ በሚል የአካባቢውን ሽማግሌዎች ሰብስቦ መርዶው ከትላንት በስቲያ እንዲነገር ማድረጉን ገልጿል፡፡ በመርካቶ አባኮራን ሰፈር መርዶው ለቤተሰብ ከተነገረበት ሰአት ጀምሮ በከፍተኛ ሀዘን የተዋጠ ሲሆን ሰባቱም ሟቾች ጎረቤታሞች በመሆናቸው በመደዳ በተጣለው ሰባት ድንኳን ሰዎች ሀዘን እየደረሱ ነው፡፡ ይሄ አሳዛኝ ክስተት ለመላው ኢትዮጵያውያን መሪር ነው – በተለይ ደግሞ ለወላጆችና ቤተሰቦች፡፡ ህልማቸው በሜዲትራኒያን ባህር የተዋጠው ወጣቶች ወላጆች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን ብዙዎቹ ልጆቻቸው የሚጦሯቸው ናቸው፡፡
መተዳደሪያ ያላቸው ደግሞ ከእጅ ወደ አፍ የሚባል ዓይነት ነው፡፡ በጥበቃ፣ በፅዳት፣ ልብስ በማጠብ፣ ጉሊት በመቸርቸርና እንጀራ በመጋገር ነው የሚተዳደሩት፡፡ ልጆቻቸው ሊቢያ፣ ቤንጋዚ ሲደርሱ ወደ አውሮፓ ለመሻገር በመቃረባቸው ገንዘብ እንዲልኩላቸው ጠይቀው፣ ከሰፈር ሰዎች ተዋጥቶና አንዳንድ ወላጆች በዋስ ተበድረው እንደላኩላቸው ለማወቅ ችለናል፡፡ ወጣቶቹ ሊቢያ ለመድረስ እያንዳንዳቸው ወደ 80ሺ ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደፈጀባቸው ታውቋል፡፡ በህይወት የተረፈው የዘመን ኢብራሂምን ወላጆች ለማግኘት ብንሞክርም ልጁ ወላጆቹን ያጣው በለጋ እድሜው እንደነበርና ጎረቤቶች እንዳሳደጉት ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ በጓደኞቻቸው ላይ ያጋጠመው አደጋ ያስደነገጣቸው አብሮ አደጎቻቸው በግራ መጋባት መንፈስና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ያሉ ሲሆን አሁንም ጣሊያን መግባት የቻሉ ሁለት የሰፈሩ ልጆች ወደ ሌላ ከተማ ለመሻገር ሁሉም የቻለውን አዋጥቶ እንዲልክላቸው በመማፀናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚችሉትን እያደረጉ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡ ምንጭ – በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ

Wednesday, May 13, 2015

ይድረስ ለሳኡዲው ባለሃብት ሼክ መሃመድ ሁሴን አላሙዲ “ዝምታን” ለምን መረጡ?


alamoudi-dmeke

ከዘላለም ገብሬ (ጋዜጠኛ)

የተከበሩ ሼክ መሃመድ ሁሤን አላህሙዲ ክብረቴ ይድረስዎት እያልኩኝ በአሁን ወቅት ባለው አንገብጋቢ እና አሰቃቂ በሆነው ጉዳይ ላይ ምላሽዎን ቢሰጡኝ ብዬ ይህችን አጭር ደብዳቤ ለእርስዎ እና እንዲሁም ለወኪሎችዎ እንዲደርስዎ በማለት ከልቤ ያለውን ሃሳብ ልጠይቅዎት ወደድኩኝ ፣ እኔን በውል የሚያውቁኝ ሰው አይደለሁም ተራ ሰው እና ሳገኝ የውስጤን የምሞነጫጭር የእስኪርቢቶ ጓደኛ ስሆን እርስዎን የማግኘት እድል ከአንድም ሁለት ጊዜ ቢገጥመኝም የእጅ ሰላምታ ሰጥቶ የእግዜር ሰላምታ ከመስጠት ያለፈ ሂደት አላከናወንኩም ፣ ይሄ ማለት ደግሞ ትልቅ ነገር ሆኖ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም ግን ማነው ብለው የሚሉ ከሆነ አንድ
ተራ ብእርተኛ ብለው እንዲያስቡን እሻለሁ፣ እንዲህ ስልዎት ደግሞ ከሳቅዎ ጋር እየገነፈለ የሚወጣው ቁጣዎ መጥቶ እንዴት እኔን ይደፍረኛል ብለው እንዲሉ ሳይሆን እንዲያው ሃሳብን በሃሳብ ይረዱልኝ ዘንድ ቤዬ ችግሬን ላካፍልዎት ብዬ ወደድኩ ፤ ይሄውም በጣም በሚወዷቸው እና ዜግነትዎን ሁሉ ተናግረውለት በማይጠግቡት ሳኡዲዎች ፣በሌላ ወገንዎት (በትውልደ ኢትዮጵያውነትዎን በሚናገሩበት ዜጋዎት ላይ ፣)ደግሞ ከምንም በማይቆጥሩት እና ከመንግስት ጋር ባለዎት መልካም እና ጥብቅ ግንኙነት የሚጠቀሙበትን ህዝብ ፣ መንግስት እና እንዲሁም ሃገር ላይ ያለዎትን አስተያየት እና እንዲሁም አመለካከት እንዲነግሩኝ ሲሆን በአሁን ሰአት በዜጎችዎ የኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንዴት እንዳዩት ልብ ሊሉልኝ ይገባል ።

በአሁን ሰአት ባሉበት ስውዲን ሆነው ይህችን ብጣሽ ደብዳቤዬን ሊያነቡልኝ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ እርስዎ ማንበብ ባይችሉ እና ጊዜ ቢያጡም አማካሪዎችዎ ከመናገር ወደ ኋላ አይሉምና ሊያገኝውት እደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ ። እንደ ኢትዮጵያውያን የኑሮ ሁኔታ 85 በመቶ የሚኖረው ህዝብ ከገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል፣ከፍተኛው አርሶ አደር ነው ጥቂቱ ደግሞ አርብቶ አደር ፣የአርሶ አደሩ እና የአርብቶ አደሩን የገቢ ምንጭ ቁጥር ስናነጻጽረው የአርሶ አደሩ የተሻለ ህይወት አለው ሆኖም ግን 75 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ በድህነት አለም ላይ ያለ ህብረተሰብ በመሆኑም የብዙ ቤተሰብ ጫንቃ በአንድ ሰው ትከሻ ላይ የሚጫንበት አገር እንደሆነች ብጠቅስልዎት ለእርስዎ ተረት ተረት ሊመስልዎት ይችላል ግን አይደለም ግልጽ ነው ።
ይህንን ስናገር እርስዎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩ እረጅም ጊዜ እንዳስቆጠሩ በአንድ ወቅት ላይ በተናገሩት በራስዎት አንደበት ለመረዳት ችያለሁ ታዲያ በደሃ አገር በደሃ ህዝብ ላይ ሃብታም የሆነ አንድ ባለሃብት የደሃውን ጉሮሮ ለመድፈን ሳይሆን የራስን ጥቅም ለማሽከርከር ሲል ከአለው መንግስት ጋር ተጣብቶ የግል ፍላጎትን ለማሟላት የሚደረገው ጥረት ከእርስዎ ብቻ የመጣ ሳይሆን ታላላቅ ሃገሮች የሚባሉት አውሮጳ እና አሜሪካውያኖች በአፍሪካ ሪሶርስ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን እጃቸውን አስገብተው እንደፈለጋቸው ለማሽከርከር በሚያመቹበት መልኩ እራሳቸውን አደላድለው ተቀምጠዋል ። ታዲያ እርስዎም በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና የንግድ ተቋም ላይ ለምን ገቡ ብዬ ልጠይቅዎት አልፈልግም በአንድ በኩል ትልቅ አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን ይገባኛል ይሄውም የዜግነት ግዴታዎን እየተወጡ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የደሃ ቤተሰቦችን ጉሮሮ እየደፈኑ እንደሆነ የሚታወቅ ስለሆነ ፣እንደዚያም ቢሆንም ከኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ይልቅ እርስዎ የሚያገኙት ጥቅም 90% በላይ ሲሆን ሃገሪቱንም ጎድተው አንጡራ ሃብቶቿንም ተጠቅመው ሃብትዎንም አካብተው ዛሬ ላይ ደርሰዋል ፣ይሄን ሁሉ ለሆነልዎት ባለውለታ ለከፈለልዎት ህዝብ እና አገር ምላሽዎ ዝምታ ሆኖአል ።
ለምን ዝምታን መረጡ ? እንደዜግነትዎ የሁለት አገር ዜግነት እንዳለዎት እየተናገሩ ባለበት ወቅት ፣በሃገራችን ላይ የመጀመሪያውን ዘርዎን ለማስጠራት ሲሉ ሳኡዲ ስታር የሚለውን ኩባንያ ተክለው ፣ምርቶቹን ወደ ሳኡዲ እንዲሄድ እያደረጉ የሳኡዲ ዜግነት ያላቸውን ወገኖችዎን እየረዱ ባለበት በዚህ ሁኔታ ለምንስ ይሄን ያህል ዋጋ ለከፈለልዎት ህዝብ ደግሞ የውለታው ምላሽ አልሆኑለትም ? ከላይ እንደጠቀስኩልዎት ሃሳብ መሰረት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የገጠሩ ህዝብ እንደሆነ እና የገጠሩ ህብረተሰብ ደግሞ በድህነት አረንቋ የሚኖር እነመሆኑ መጠን እራሱን ለማሻሻል ቤተሰቡን ለመርዳት ብሎም ሃገሩንም ከችግር ለማውጣት ሲል በሌላ ዜግነት ባለዎት የሳኡዲ ምድር ላይ ስራ ሰርቶ እንዲኖር ያስችለው ዘንድ አገሩን ፣ ወገኑን ፣የትውልድ ቀዬውን እንዲሁም የልጅነት ናፍቆቱን ያሳለፈባቸው ጓደኛ ዘመድ አዝማዶቹን በእዝነ ህሊናው እየዳሰሰ በረሃን አቋርጦ ኑሮው ሲያሸንፈው ኑሮን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ሲል “የሰው አገር ሰው ቢረግጡት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ “ሆኖበት መከራ እና ስቃዩን ማየት ከጀመረ ከራርሞአል።
bereket alamudi demeke
ታዲያ አገር እየገዛሁ ነው ያለው መንግስትም ምንም እርዳታውን በተገቢው መልኩ ሊያደርግ አልቻለም ፣የሳኡዲ ዜግነት እያለዎት በሳኡዲ መንግስት ላይ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ ሳይቻልዎ ቢቀር በደሃ አገሮች ላይ ክርንዎን ለማሳየት የሞከሩበት ዋነና ሁኔታ በማንቂያ ገንዘብ እያሳዩ በአካፋ መዛቅ የለመዱበት አገር ላይ ህዝቡ ዝምታን ስለመረጠልዎ ይመስለኛል ታዲያ እርስዎ ለዚያ ደሃ ገበሬ ፣ያፈራውን ምርት ነጥቀው ለሳኡዲዎች የሚሰጡበት ገበሬ ያ ደሃው ህዝብ ዛሬ የድረሱልኝ ጥሪ ሲያሰማ እርስዎስ የት ገቡ ።
ንጉስ አብደላንስ ለምን ለማማከር አልሞከሩም ። ነው ወይስ እንደ አቶ አይለማርያም ደሳለኝ ቅጥፈትዎን በአደባባይ ሊያሳዩን ፈለጉ?
በኢትዮጵያ ምድር እና ህዝብ ላይ ከ20 በላይ ትላልቅ የሆኑ ኩባንያዎችን መመስረትዎ የሚታወቅ ነው ጥቂቶቹን ብናነሳ ኤልፎራ ፣ኒያላ ኢንሱራንስ ፣ኒያላ ባንክ፣ሸራተን አዲስ፣ሳኡዲ ስታር ፣ሰን ላይት የኤሌትሪክ ኩባንያ ፥እንዲሁም የወርቅ ማእድን ቁፋሮ የሚያመርተው ትልቁ ኩባንያዎት
Managed under the parent MIDROC Group is MIDROC Ethiopia Technology Group with several further
companies under its management:
– MIDROC Gold Mine
– ELFORA Agro-Industries
– Huda Real Estate
– Kombolcha Steel Products Industry
– Modern Building Industries
– Trust Protection and Personnel Services
– Addis Home Depot
– Trans Nation Airways
– Addis Gas & Plastics Factory
– Wanza Furnishings Industry
– Daylight Applied Technologies
– Blue Nile P.P & Craft Paper Bags Manufacturing
– United Auto Maintenance Services
– Unity University
– Rainbow Exclusive Car Rental and Tour Services
– Summit Engineered Plastics
alamudiየሃገሪቱን አመታዊ በጀት በአንድ ቀን የሚያገኙበት ዋነኛው የንግድዎ ምንጭ እና እንዲሁም ሌሎች የአበባ ፣ሰሊጥ ፣እህል እና ትራጥሬ ምርት የሚሰበስቡበት ኩባንያዎት ትልቁን የሃገሬን ገበሬ ጉሮሮ እየነጠቀ ምንም የሚበላ ነገር ለማያመርቱት እና በግብርናው አለም ህይወታቸው አልፎ የማያወቀው ፣ በነዳጅ ምርት ብቻ እምሮአቸው ለተደፈነው ጥጋበኛ ባለ ሃብቶች ዝርያዎችዎ ምርታችንን በማከፋፈል ስራዎ መጠመድዎን አውቃለሁ ፣ታዲያ ለምንስ በእናትዎ ወገን ያሉትንስ ለማዳን አይጥሩም ?ሴት እህቶቻችን ሲደፈሩ ሲገደሉ ፣ወንዶችም ሲደፈሩ ፣ሲገደሉ ፣በርሃብ እና ውሃ ትም ሲሰቃዩ እናት ከእንጭጭ ልጆችዋ ጋር በሜዳ ላይ ያለ መጠለያ ስትወድቅ ሰው ያለ ሃገሩ በደል እና ስቃይ ሲደርስበት አስትዋሽ ሲያጣ መንግስትም ጉዳየ አይደለም ብሎ ህዝቡን በንቀት ሲመለከት እርስዎስ እንዴት አዩት ? ከ63 % በላይ መሬቱን ነጥቀው ምርት የሚያመርቱት የእርስዎ ዝርያ ያላቸው የሳኡዲ አረቦች መሆናቸውን ዘንግተውታልን ? በሃገራችን ገብተው እንደሚሰሩት ሁሉ ለምን የሌሎቹንም ዜጎች ክብር ሊጠብቁ እንዳልቻሉ ለምን አንደበትዎን ከፍተው አልተናገሩልንም ? ኢትዮጵያን እወዳለሁ እያሉ የሚደነፉት የግላዊ ጥቅምዎ እስኪከናወን ብቻ እንደሆነ ያየንበት እና የታዘብንበት ወቅት ዛሬ መሆኑን ገብቶናል እንጂ የንብ ቲሸርት ለብሰው እኔ ወያኔ ነኝ ባሉበት ወቅት አልነበረም ምክንያቱም ለኢትዮጵያ ህዝብ
ፖለቲካ ሳይሆን የቸገረው ዳቦ ፣ሰላም እና መልካም አስተዳደራዊ መንግስት ብቻ ነው ስለዚህ ያንን ሰላሙን በሃገሩ የነጠቀው መንግስት በሰው አገር እንዲሰደድ አደረገው በሰው አገርም ስደቱ አልበቃ ሲለው ስቃዩ እና መከራው በዛበት እንደርስዎ በገንዘብ የጠገበ ዲታ ሰው ማንንስ ደሃ ያስታውሳል ብቻ ድከም ብሎኝ እና የደሃ እህት እና ወንድሞቼ ደም ቢከሰኝ ጥያቄዬን ልጠይቅ ብዬ እንጂ መልስዎን ሊመልሱ እንደማይችሉ አውቃለሁ ፣ስለዚህ ምላሽ ካለዎት ምላሹን በዝግጅት ክፍላችን ልናስተናግድ ዝግጁዎች ነን ስለዚህ በኢሜል አድራሻችን ቢያቀርቡልን ለህዝብ ከማድረስ ወደ ኋላ አንልም ።ለዚህ ደግሞ ውድ ጊዜዎን ተሻምቼ ይህችን ስላነበቡልኝ ሳላመሰግን አላልፍም ፣ታዲያ እንዲህ ስልዎት ስም ያለውን ሰው እየፈለጉ ወይን ባለስልጣን እያሰሱ ብርዎን ከሚረጩ የድረሱልኝ ጩኸታቸውን እያሰሙ ያሉትን ዜጎቻችንን መፍትሄ ቢሰጡልኝ ደስታዬ እጅግ የላቀ ነው ።ከዚያም አልፎ ከስደት መልሳቸው በሃገራቸው ኮርተው ይኖሩ ዘንድ ስራንም ፈጥረው የስራ አጡን ቁጥር ቢቀንሱት የስደተኛው ቁጥር ሊቀንስ ይችላል እናልብ ሊሉት ይገባል በማለት የዛሬውን ሃሳቤን እቋጭልዎታልሁ ላደረጉት ነገሮች ሁሉ በድጋሚ እያመሰገንኩ በኢሜል አድራሻችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ቢልኩልን እንወዳለን እናስተናግዳለን zelalem@maledatimes.com ወይንም
editor@maledatimes.com አሁንም ለጊዜዎ ክብረትን ይስጥልኝ !

Monday, May 11, 2015

አላሙዲ በኦሮሚያ ክልል የተገኘው ከፍተኛ ክምችት ያለው የወርቅ ማዕድንን ሊያወጡ ነው።

ምንጭ  ሪፖርተር ጋዜጣ
ብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ዳዋ ዲጋቲ ቀበሌ በሚገኘውና በልዩ መጠሪያው ኦኮቴ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ያገኘው ከፍተኛ ክምችት ያለው የወርቅ ማዕድን ላይ ሥራ ሊጀምር መሆኑን፣ የኮርፖሬሽኑ ባለቤትና ባለሀብት ሼክ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ ሚያዝያ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ገለጹ፡፡

ሼክ አል አሙዲ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት መገኘቱን የገለጹት፣ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በማዕድንና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ የስምንት ቢሊዮን ብር ማስፋፊያ ፕሮጀክት መጀመሩን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ነው፡፡
ብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ላለፉት 15 ዓመታት ባደረገው ጥናት የወርቅ ክምችቱ መገኘቱን የተናገሩት ባለሀብቱ፣ ‹‹የማዕድን ሥራችን እየሰፋ ነው፡፡ ቦታው ትልቅ የወርቅ ልማት ያለበት ነው፡፡ ትልቅ የወርቅ ክምችትም አግኝተናል፡፡ ለሚድሮክ ጎልድ ትልቅ ፕሮጀክት ከመሆኑም በተጨማሪ ኢትዮጵያን የሚያስጠራ ፕሮጀክት ነው፤›› ብለዋል፡፡
የተገኘው የወርቅ ክምችት ለሚቀጥሉት 15 ዓመታት ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለአገሪቱ ገቢ የሚያስገኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ሁሉም ዝርዝር ጥናት እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባም ሼክ አል አሙዲ ገልጸዋል፡፡ ሌላው በትግራይ ክልል ስለተገኘው የማዕድን ክምችት ገልጸው፣ ብዙ ወርቅ ባይኖርበትም የዚንክ፣ የሊድና የብር ክምችት መገኘቱንና ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሶዳ አሽ ፕሮጀክት እንዳላቸውና ማምረት መጀመራቸውንም አክለዋል፡፡
በሌላ በኩል በዶ/ር አረጋ ይርዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚነት የሚመራው ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ወደ ላቀ ስኬት የሚያሸጋግረውን አዲስ ፕላን መንደፉን ገልጾ፣ የወርቅ ማዕድንና አግሮ ፕሮሰሲንግ ማስፋፊያ የስምንት ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር አረጋ እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ ቴክኖሎጂ ግሩፑ ተግባራዊ ማድረግ የሚጀምረው ዕቅድ ከ15 እስከ 20 ዓመታት የሚያገለግል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በስምንት ቢሊዮን ብር ወጪ የሚስፋፉት ፕሮጀክቶች የወርቅ ማዕድን ልማት፣ የተቀናጀ ዘመናዊ የዶሮ ዕርባታ፣ በመስኖ የተደገፈ ዘመናዊ የከብት መኖ (አልፋ አልፋ) ልማትና የተቀናጀ የወተትና የሥጋ ልማትን እንደሚያካትቱ አስረድተዋል፡፡
የማስፋፊያ ፕሮጀክቶቹ በሦስት ክልሎች እንደሚከናወኑ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ 4.2 ቢሊዮን ብር (55 በመቶ የሚሆነው) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ሥራ፣ ቀሪው በአማራ ክልል ለሚካሄደው አግሮ ፕሮስሲንግ (የዶሮ እርባታ) እና በኦሮሚያ ክልል ለሚካሄደው አግሮ ፕሮሰሲንግ (የመኖ፣ የወተትና የሥጋ) ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች የሚውል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ከሦስት እስከ አምስት ዓመታት የሚወስድ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በማዕድንና በአግሮ ፕሮሰሲንግ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ሥራው ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራው ሲገባ፣ በየዓመቱ ከምርት ሽያጭ 3.5 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚገኝና በልማቱ ዕቅድ ዘመን 61. 90 ቢሊዮን ብር የሽያጭ ገቢ ሊገኝ እንደሚችል ዕምነታቸው መሆኑን ዶ/ር አረጋ ተናግረዋል፡፡ ከልማቱ በታክስ፣ በሮያሊቲና በሌሎች ክፍያዎች በየዓመቱ 880 ሚሊዮን ብር ለመንግሥት ገቢ እንደሚደረግ ገልጸው፣ በተወጠነው የኦፕሬሽን የዕቅድ ዘመን (ከ15 እስከ 20 ዓመታት) በጠቅላላው 14.85 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ገቢ ሊሰበሰብ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡ ቴክኖሎጂ ግሩፑ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የልማት ዘርፎች የወርቅ ማዕድንና አግሮ ፕሮስሲንግ መሆናቸውን የጠቆሙት ዶ/ር አረጋ፣ ማዕድንን በሚመለከት ዋናው ተዋናይ ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ መሆኑንና አግሮ ፕሮስሲንጉን በሚመለከት ደግሞ ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሚድሮክ ወርቅ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አሥር ዓመታት በመተከል አካባቢ ሰፊ የማዕድን ፍለጋ ሲያካሂድ ቆይቶ፣ በቂ የወርቅ ክምችት መኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ባህር ዶልቢር ሚኒራልስ ኢንዱስትሪ አድቫይዘርስ በተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ የአዋጭነት ጥናቱን ማስጠናቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡ አሥር ዓመታት የፈጀውን የማዕድን ፍለጋ ግን ኢትዮጵያውያን የኩባንያው ሠራተኞች ማከናወናቸውን አክለዋል፡፡ ኩባንያው በለገደንቢ፣ በሳካሮ፣ በሻኪሶና በረጂ ከተሞች አካባቢ የወርቅ ማምረቻ እንዳሉት ይታወቃል፡፡ ለአሥር ዓመታት ባደረገው የማዕድን ፍለጋ 310 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንም ዶ/ር አረጋ አክለዋል፡፡ ሚድሮክ ጎልድ በመተከል አካባቢ ያገኘውን የወርቅ ማዕድን ልማት በ200 

Saturday, May 9, 2015

US admits supporting Dictators.


US admits supporting Dictators.

Wendy Sherman US Under Secretary of State for Political Affairs has openly admitted the desire to help dictators and mass killers in the horn of Africa. On April 16,2015 in Addis Ababa , the capital of Ethiopia, has the Secretary given a press briefing praising the Ethiopian ruthless dictatorial regime EPDRF (the ruling party since 1993). It is really a wonder how the secretary failed to see the reality of the deep political , social and economical problem the current stubborn undemocratic ruling party brought on the Ethiopian people. Should this government be praised or condemned? It might have been that she was not properly informed by her staff the following facts about the Ethiopian current government.
The prison cells of, Kality , Makelawi and Zewye Prisons, ( the main prison compounds in and on the skirt of Addis Ababa) are filled with political prisoners , journalists and civil societies at the very time as she was giving this press briefing. Winner of the 2013 UNESCO Guillermo Cano world press Freedom prize journalist Reeyot Alemu , winner of the 2012 Pen America journalist Esknder Nega , Journalist Temesegen Desalegn , nine Ethiopian bloggers known as Zone 9 are charged of terrorism and many others are still being thrown to jail by the Ethiopian government. The very truth is that these journalists were doing only what was expected from a professional , respected and responsible journalist according to the principles and essence of journalism. “At least 60 journalists have fled their country since 2010 while at least another 19 languish in prison. The government has shut down dozens of publications and controls most television and most radio outlets.”(Human Rights Watch wrote in a January report.)The government allocated and invested excessive amount of money to block almost all diaspora-based Ethiopian websites, by purchasing and using a very sophisticated and modern European and Chinese spyware to target critical journalists including those in the United States. The secretary seemed to deliberately ignored all these vivid facts but acknowledge the Ethiopian government as democratic . Is locking journalists behind bars for their profession and freedom of speech one of the democratic criteria in USA? The Secretary of state John Kerry forwarded this statement right at the heart of Addis Ababa on his visit to five African countries on may 2014 ‘’ We should not use the anti terrorism proclamation as mechanism to be able to curve the free exchange of ideas.’’ It seemed that Wendy Sherman has failed to take the time to inform herself about the visit and comments made by her boss.
Wendy Sherman's comment on the coming fake parliamentary election ,which is planned to be held on the coming may 24 2015, showed either the secretary has not done her assignment of assessing the present political situation in Ethiopia or her government's desire to protect and support dictatorial , corrupted , undemocratic and ruthless regime such as the Ethiopian government . It is so surprising how she praised the Ethiopian government regarding an open and inclusive electoral process. Actually she had only talked with the delegates of the dictatorial ruling party . Moreover she was giving this press briefing standing along side with one of the minster of the ruling party. She never had the chance or probably not the desire to have at least a short discussion with the very finger counted opposition parties which are battling the 23 years dictatorial regime on a very narrow and uncomfortable political field. Had she given some of her valuable times at least to hear what these opposition parties( whose top leaders and large numbers of members are thrown in prison or forced to flee the country) have to say, she might have praised the opposition parties for their struggle for freedom , equality, peace and democracy. Rather she chose to spend her time being lectured and filled with the propaganda of the ruling party and consequently gave this painful speech that bled the hearts of almost all Ethiopians in and abroad except of course the very small percent supporters and members of this savage government EPDRF. On her speech she dared to call Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy ( presently being merged with Ethiopian People’s Patriotic Front (EPPF) and carry on the struggle for peace and democracy by the name “Arbegnoch-Ginbot7 for Unity and Democracy Movement”) as a terrorist group trying to overthrow an elected government. There are two things the Secretary had missed here. In the first place the government did not come through a peaceful election process. She could have traced back to the past two decades and found out the fact that the present ruling party TPLF ( EPDRF) has taken power after a 17 years bloody civil war. Is this how President Obama came in to office back in 2008? The second point that she missed was the very truth that the chairperson , top leaders and members of the Ginbot 7 front reside in her own country, USA, because they are sentenced to death in absence by the Ethiopian injustice government. To her surprise the chairperson of Ginbot 7 Dr Birhanu Nega lectures in one of USA's university. I am sure she knows how the American government is determined to fight terrorist not alone in the land of USA but on other counties also. So in her speech she termed Ginbot 7 as a terrorist group as the Al qaeda. IS, and so on. How come her government allow Dr Birhanu and many of his colleagues to teach , to work or to live inside the US soil if they are terrorist or running a terrorist organization? Does it make sense or has she failed to read between the lines but focused only on what the dictatorial but smart Ethiopian government showed her?
At the presidential election in 2012 Barack Obama (Democrat) was re-elected president beating his opponent Governor Mitt Romney (Republican). The Governor and his party ( The Republicans ) had opposed the president on his plans and strategies. They even openly criticized the Obama administration in their election campaigns. In addition these two candidates (Governor Mitt Romney and President Barack Obama) had gone through a series of public debate one on one which were aired live to the world. In those public debates they argued not only regarding their different strategies and ideologies but also to the extent of criticizing or even insulting one another. However the Republicans , their members , their supports or Governor Mitt Romney were not arrested and thrown in jail for openly criticizing the ruling party and the president. They were not tortured or forced to live in exile because of initiating the American people not to vote for the president. Wendy Sherman did not pay due attention to the fact that those who oppose or criticize the dictatorial and undemocratic rule or system of the Ethiopian current government are destined to rot in prison , live in exile or sadly being killed. The various opposition parties inside Ethiopia have been deliberately targeted by the democracy allergic TPLF regime. Prominent opposition party leaders are still being harassed , imprisoned or forced to leave the county. For example , Ato Andualem Arage from UDJ party, Ato Andargachew Tsege ,chair person of Ginbot 7 for democracy movement,Ato Natnael Mekonnen , Ato Abrha Desta from Arena Party,Ato Habtamu Ayalew head of publlic relation for UDJ party, Ato Daniel Shibesi from UDJ, Ato Yeshiwas Asefa from Blue Party,Ato Bekele Gerba and many hundreds are rotting in prison. In addition supporters and members of opposition parities are being given very difficult times in their jobs especially those in the public service sectors. It is a common seen to find large numbers of opposition party members and supporters dragged in to prison only for having and expressing their views and ideas which are not the kinds that make dictators or mass murders to sit peacefully and suck the blood of the citizens. But shockingly Wendy Sherman bothered not a little bit about these realities in Ethiopia rather she totally absorbed what the current Ethiopian ruling party fed her. She could have double checked all the data before she could jump in to this shameful conclusions and opinions regarding the Ethiopian election process or democratic process in general.
Any one who opposes the current Ethiopian ruling party is termed terrorist by the government. It is quite natural for dictators to accuse any one who is a threat to their power. In fact the great Nelson Mandela and his party ( the ANC) were labeled terrorists and a terrorist organization by the Apartheid government. Was that not the same Mandela (who was sentenced for 27 years of imprisonment as a terrorist by the Apartheid leaders) ,the whole world now depicts him even after his death as the father of peace and equality? May be Wendy Sherman has to listen and watch the press briefing given by her president ( Barak Obama) right after the announcement of the death Mandela. It is very disturbing to hear Wendy Sherman grouping Ginbot 7 in line with Al qaeda and other terrorist organizations. Probably the secretary does not even know what exactly is going on in her own country. Surely she did not have any idea the different times when the former Secretary of State Hilary Clinton giving an interview to Fox News and publicly on CNN admitting that the USA has created and funded the terrorists including Al qaeda which they are fighting today. In fact these were Hilary’s word for word speech as she was interviewed by Fox News , “When the Soviet Union invaded Afghanistan we had this brilliant idea that we are going to come Pakistan and create a force of Mujiadin equip them with stingers Missiles and every thing else to go after the Soviets inside Afghanistan. And we were successful the Soviets left Afghanistan and we said great good bye leaving these trained people who were fanatical in Afghanistan and Pakistan leaving them well armed creating a mess frankly that the time we didn't really recognize we were just happy to see the Soviet Union fall we thought ok,fine we're ok now every thing is going to be so much better . Now you look back the people who we are fighting today we were supporting in the fight against the Soviet.”( Hilary Clinton for Fox News) In case the above quote was not enough for Wendy Sherman ,it is also possible to click on CNN website and watch and listen Hilary Clinton accepting the reality that the US created these terrorist organizations . Here is a part of her speech “ We also have a history kind of moving in and out of Pakistan. Lets remember here the people we are fighting today we funded twenty years ago and we did it because we were locked in the struggle with the Soviet Union…..”( Hilary Clinton for CNN). The people of Ethiopian have never voted for EPDRF. Actually the people from the very beginning were fighting these cruel leaders from taking the power. Moreover the Ethiopians in and abroad have and never given their vote to these dictators. The 2005 Ethiopian general election consequences and the 2010 general election result are the evidence how the people had enough with these butchers and blood suckers. Wendy Sherman should have examined the worsening of both the political and economical issues in Ethiopia years after years before standing in front of cameras and humiliate herself of her lack of knowledge and failure to do research about the overall political , social and economical situations in Ethiopia. After all that was her job and what she was paid to do. In fact that was the least she could have done.
The speech given by the Wendy Sherman showed how she failed in digging out the truth which was not difficult to find. In fact the truth was right in front of her nose but she ignored it and chose to be misinformed and to mislead others. According to the 2015 report and research by Freedom of House “Ethiopia ranked 32 out of 52 countries surveyed in the Ibrahim Index of African Governance, below the continental average and among the bottom in East Africa. The country’s modest gains in the index are due to its improvement in human development indicators, but its ranking is held back by low scores in the “Participation and Human Rights” category. Political Rights and Civil Liberties”( Source://freedomhouse .org/report/) In this undemocratic parliamentary election in Ethiopian on may 2015, foreign countries showed no interest in sending election observers to Ethiopia. “ The EU notes that the previous reports of EOMs have not been accepted by Ethiopian , which is an essential precondition for such a mission. In any case , no invitation has been received by the EU to send an EOM to Ethiopia , .”( Source: https://www.gov.uk/government/news/eu-statement-on-the-absence-of-an-eu-election-observation-mission-for-the-may-2015-national-elections--2)
As it was described on the above source European countries have decided not to send a group of observers because the coming election will not be free and fair just as the other previous ones. Wendy Sherman on the behalf of the oppressed Ethiopians (including me) I urge you to do your assignment and research before giving such unprofessional and dishonest press briefing again.

http://ethsat.com/video/esat-egna-manen-by-serkaddis-fear-09-may-2015/

information to Norwegian citizens in Ethiopia

Options in Ethiopia - information to Norwegian citizens
Last updated: 05/08/2015 .The Norwegian Embassy in Addis Ababa encourage Norwegian citizens to exercise caution when traveling to or stay in Ethiopia before , during and after the Ethiopian elections on 24 May 2015 .

We advise everyone to avoid demonstrations and other large gatherings of people . Norwegian citizens should also stay away from the polling stations on election day , and be aware of specific bans , for example . foto ban , at polling stations or other places of political importance. The embassy recommends Norwegian citizens to remain continuously updated via local media and the internet. Please also be aware that telephone and internet services can occasionally come to be blocked , as this has occurred during previous elections in Ethiopia .

The embassy recommends all Norwegian visitors to register on the State Department's portal for study abroad

Friday, May 8, 2015

የጨርቆስ ወጣቶች እግዚአብሄር ከቁም ነገር ያብቃቸው


(ከፊልም ባለሙያው ያሬድ ሹመቴ ማስታወሻ) 

በትላንቱ ምሽት የሀዘን ቤት ቆይታዬ የሟቾቹ ቤተሰቦች ሲያጽናናቸው የሰነበተውን መላ ህዝብ እጅጉን ስሜት በሚነካ ሁኔታ አመስግነው አሰናብተዋል።

ከሰማዕታቱ መሀል የአንዱ እናት (የብሩክ) የሆኑትም እንዲህ አሉ " እኔ (ሀገሬ) ኢትዮጵያን በጣም አመሰግናታለው። ልጄ እንደሞተም አልቆጥረውም።..... በህይወት እንዳለ ነው የምቆጥረው። በጣም ደስ ብሎኛል። በናንተ ፊት መቆም የሚገባኝም አይደለሁም። (በልጄ ምክንያት) እዚህ በመቆሜም እግዚአብሄርን አመሰግነዋለው። በጣም ደስ ብሎኛል። ብድር ይግባቹ እግዚአብሄር ይስጣቹ።"

"...የጨርቆስ ወጣቶች... መግለጽም ያቅተኛል። በጣም ነው ያስደሰቱኝ። እግዚአብሄር ከቁም ነገር ያብቃቸው። ልጄ አልሞተም በህይወት ነው ያለው።" በማለት በጉባኤው ላይ ለተሰበሰበው ህዝብ ከሌሎቹ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች ጋር በጋራ በመሆን መጽናናታቸውን በመግለጽ ከዛሬ ጀምሮ ህዝቡ ወደዕለት ኑሮው እንዲመለስ አሰናብተዋል።

በምሽቱ ተጋባዥ አስተማሪ የነበሩትን የመምህር መጋቤ አዲስ እሸቱን ከመንፈሳዊነቱ ተጨማሪ ዘና የሚያደርገውን ትምህርት በጥቂቱ ላካፍላቹ።

"ሰው ብቻ አትሁኑ .....ሰው ብቻ ማለት ምንድን ማለት ነው? ብዬ ሳስብ፤ የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ በሚለብሰው ልብስ፣ በሚነዳው መኪና የኑሮን ስኬት የሚለካ ማለት ነው። እስከ ሞት የሚኖር ማለት ነው፦ እንደ እንስሳ።

"...ታላቁ ሊቅ ዮሀንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል 'ሰው እግዚአብሄር ሲለየው' ይላል። ሰው ፈጣሪ ከሌላው ሲለየው፤ ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሄር ሆኖ ይቀራል። በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲም ካርዱ የወጣ ሞባይል ማለት ነው። ጥሪ የማይቀበል። ለጉትቻ ማንጠልጠያ ብቻ የተሰራም ጆሮ አለ።"

"...እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ አይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት የሰዉ አስተሳሰብ ነው።... የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል። ጃፓንና ቻይና አገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው። አስተሳሰቡ ያልለማ ህዝብ የለማውን ያወድማል።"

"...ምንድነው አሁን ያሳየሁዋቹ? (ትንሽ ጣታቸውን አውጥተው ወደላይ እያሳዮ) ይህች ጣት ብትታምም ሀኪም ቤት ብቻዋን ነው የምትሄው?... የማይመለከታቸው እነ ጉበት፣ እናፍንጫ፣ እነ እግር፣ አብረው ነው የሚሄዱት።"

"...ከረባት የሚታሰረው የት ላይ ነው?... አንገት ላይ የታሰረ ከረባት አካሄድን ይቀይራል። አሁን እግር ምን አገባው እውነት ለመናገር? (ከፍተኛ ሳቅ) ውድ መነጽር አይናቸው ላይ ያደረጉ ሰዋች አካሄዳቸውን ሁሉ ነው የሚቀየረው። አይን መነጽር ያደረገው መላ የሰውነት አካላትን ተክቶ ነው። ሰው እጁ ተቆርጦ ይኖራል፤ አይኑ ጠፍቶ ትኖራል። እራሱ ተቆርጦ ግን አይኖርም። 

"ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው። እነዛ... (ምንትስ) የምንላቸው ክርስቲያኖችን አርደዋል ይባላል ... ምዕራባውያኑ ደግሞ ክርስትናን እራሱን አርደውታል።....ወንድ ለወንድ፣ ሴት ለሴት፣ በቤተክርስቲያናቸው እያጋቡ፤ ክርስትናን አጋድመው ያረዱ ምዕራባውያን ናቸው። (ይህን ሁሉ ያመጣውም) የምዕራባውያን ልክ ያጣ ነጻነትና ገደብ ያለፈ ዝርክርክነት ነው።"

"...አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ። እማይረባ እማይረባ ነገር ስናይ (ዓይናችንን) የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር... መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር እላለሁ...።

"አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሀሜት እንሰማ ነበር?(ከፍተኛ ሳቅ)... የምንፈልገውን (ብቻ) አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር። ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ።

"ጀርመን ሀገር ሄጄ ሲነግሩኝ፤ ባለ አምስት ኮከብ የውሻ ሆቴል አለ ተባለ። እኛ ሀገር አምስት ኮከብ ሆቴል ገብተው የበሉ ትንሽ ዝና (ሀብት) እና ትንሽ ስልጣን ያላቸው ናቸው። ማን ይገባል ከነሱ ውጪ። ግን ሰዋች ነን። የጀርመን ውሻ ዛሬም ውሻ ነው ለዘላለምም ውሻ ነው። እኛ ግን ሰው ነን። እንደ ሰው አስቡ (ምዕመናን) በማርያም።"

" እስኪ እንደው ትዳራችሁን ገምግሙት ደስተኛ ናችሁ? እንደሰው እየኖራችሁ ነው? ሚስቶቻችሁን ታከብራላችሁ? ፖለቲከኞቹ የኪነጥበብ ሰዎቹ (እዚህ) አላቹ ሲባል ሰምቻለሁ። ቆም ብላችሁ ልታስቡ ይገባል።"

" እኛም የሀይማኖት ሰዎች ሰበክን ሰበክን፤ ስብከቱ የህዝቡን አመለካከት መቀየር ትቶ የኛን ኑሮ ቀየረ።(ከፍተኛ ሳቅ)... የሰበክነው ሳይታወቅ እኛ እንታወቃለን። ማስታወቂያ ሰርተው ዝነኛ የሆኑ ሰዎች አሉ። ምርቱ ተሽጠ? ወይስ አልተሸጠም?" ማነው የሚያውቀው? (ከፍተኛ ሳቅ)

" ተርቦ ያበላን፣ በክራይ ቤት እየኖረ እኛን በቪላ ቤት ያኖረን፣ እሱ በግሩ እየሄደ ለኛ መኪና የገዛልንን፤ ዝነኛ ያደረገንን ህዝብ እኛ አመለካከቱን ልንቀይረው ይገባል። አለባበስን መቀየር ቀላል ነው አስተሳሰብን መቀየር ግን ዋጋ ያጠይቃል።"

"የግሪክ ፈላስፎች እነ ሶቅራጥስ የህዝቡን አመለካከር ለመቀየር ደከሙ። ዛሬ በኢኮኖሚ ውድቀት የምትንገላታ ግሪክ ናት፦ የነ ሶቅራጥስ ሀገር። 'ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል' ይባላል። እኛ እንክዋን ይክበር ይመስገን ኢትዮጵያውያን ነን። .... "አሁንም ደግሜ እናገራለው። ይሄን ችግር ያደረሱብን ኢትዮጵያውያን አይደሉም። አብረውን የኖሩት ጎረቤቶቻችንን እነ መሀመድ እነ ከድጃ... ስጋዎቻችን፣ ደሞቻችን፣ አካሎቻችን ናቸው።"

"...ወቀሳ አበዛሁ?(የተሰበሰበው ህዝብ ከሳቅ ጋር አላበዙም አለ) ማርያምን?... ኮሶ የሚጠጣው ስለሚጣፍጥ አይደለም ስለሚያሽር(ስለሚያድን) ነው። ለመጣፈጥማ ስኩዋር ይሻል ነበር ግን ወስፋት ነው ትርፉ።" (ሳቅ)

አመሰግናለሁ።

የሀዘን ቤቱ ድባብ በደስታና በመጽናናት ተሞልቶ ሁሉም ወደ ህይወቱ ሊመለስ፤ መጽናናት የሚነበብባቸውን ቤተሰቦች ተሰናብተን ወጣን።
(ተዘገበ - ከጨርቆስ አዲስ አበባ)