Thursday, April 24, 2014

ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት? ክፍል አንድና ሁለት ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም


freedom

አንድ

በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ።
አንድ መጽሐፍን በመጥቀስ ወይዘሮ መስከረም የሚከተለውን ጽፋለች፡–
ፈጣሪ የሠራውን  ውጫዊ  ገጽታን ማሽሞንሞን በቂ እንደሆነ ሲነገራት የኖረች ሴት፣ በምን ተነሳሺነት አእምሮዋን የሚመግብ  እውቀት ልትሻ ትችላለች? … በልጅነት እውቀትን  ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት በጉብዝና ወራት አላዋቂ በመሆን ቢወቀስ ትርጉም አይኖረውም፤ … ››
ወይዘሮ መስከረም ሔዋን ሲነገራት የማትሰማ የመጀመሪያዋ ሰው (ልብ በሉ ሴት አላልሁም፤) መሆንዋን እንዴት እስከዛሬ ሳታውቅ ቀረች? ባለመጽሐፉም ይሁን መስከረም የሔዋንን ታሪክ ሳያነሡ መቅረታቸው መሠረታዊ ስሕተት ነው፤ በተጠቀሱት ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አንድም እውነትን የሚመስል ነገር የለም፤ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› ከማለት በፊት የሔዋንን ሥራ ቆም ብላ ብታስታውስ የጠቀሰችውን መጽሐፍ እኔ እንደምነቅፈው ትነቅፈው ነበር፤ የሔዋን ታሪክ የሚነግረን የሚከተለውን ነው፡ ‹‹ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም  መልካም እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ፤ የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፤›› ዘፍ. 3
የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ ማለት ‹‹እንደእግዚአብሔር መልካምንና ክፉን የሚያውቁ›› ሆኑ ማለት ነው፤ አሁንም ሔዋን መስከረምና ባለመጽሐፉ እንዳቀለሏት አለመሆንዋን መረዳት ይቻል ነበር፤ እንዲያውም ከዚህ በፊት እንደጻፍሁት ሔዋን የመጀመሪያዋ አብዮተኛና የነጻነት እናት ነች ለማለት ይቻላል! በአንጻሩ አዳም የፍርሃት አባት ነው፤ ‹‹ራቁቴን ስለሆንሁ ፈራሁ፤›› ያለው እሱ ነው! ስለዚህ ወይዘሮ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› የምትለውን በድላለችና ይቅርታ መጠየቅ ሳያስፈልጋት አይቀርም!
ሔዋን የተጠቀመችው ውጫዊ ገጽታን የሚያሽሞነሙን ሳይሆን የውስጥን የመንፈስ ኃይል ቆፍሮ በማውጣት ነበር፤ በዚህ የውስጥ ኃይል ለሚጠቀም ከውጭ ግፊት አይጠብቅም።
‹‹እውቀትን ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት›› አይወቀስም፤ ትላለች ወይዘሮ መስከረም፤ እየተገፉ የሚገኘው ባርነት ነው፤ እውቀት የሚገኘው በነጻነት ነው፤ መገፋት ከእውቀት ያርቃል እንጂ ወደእውቀት አያስቀርብም፤ የመስከረም ዋናው መልእክት ሰላቢውን እንጂ ሰለባውን አትውቀስ የሚል ነው፣ ወይም የኔ ሀሳብ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ዓይነት ሆኖባታል፤ ለመሆኑ ሰለባ የሚሆን ከሌለ ሰላቢ ይኖራል ወይ? ሰለባ ከመሆን በፊት ሰለባ ላለመሆን መጣር አንዱ የኑሮ ዓላማ አይሆንም ወይ? ከዚህ በፊት ስለጨቋኝና ተጨቋኝ ደጋግሜ ጽፌ ነበር፤ ጭቆና የጨቋኙ ባሕርይ የሚሆነውን ያህል የተጨቋኙም ባሕርይ ይሆናል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የሚጠቅመውን ያህል ለተጨቋኙም ጭቆና ይጠቅመዋል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የኑሮው መሠረት የሆነውን ያህል ለሚርመሰመሱት የጨቋኝ ሎሌዎች ጭቆና የኑሮ መሠረታቸው ነው፤ እንዲህ እያለ ወርዶ ወርዶ የጭቆና ጠቃሚነት ለሎሌው ሎሌ፣ ለሎሌው ሎሌ ሎሌ … በኢትዮጵያ ምናልባትም የመጨረሻዋ የጭቆና ሰለባ ሚስት ትሆናለች፤ ወይም ልጆች ይሆናሉ! ጨቋኝና ተጨቋኝ የባሕርይ ቁርኝት አላቸው፤ አንዱ ያላንዱ አይኖርም፤ ወይዘሮ መስከረም ይህ እውነት ያልሆነበት ሁኔታ ወይም አጋጣሚ የምታውቀው ካለ ብታጋራን ደስ ይለኛል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤›› የሚለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱትንና በቁማቸው የሞቱትን ሲያመሳስላቸው ነው! ለእኔ የሚታየኝ እንዲህ ነው።
መስከረም ብዙ ታላላቅ ሴቶችን ጠቅሳለች፤ በእስዋ ግምት ሁሉም በአባታቸው ወይም በባላቸው እየተገፉ ወደትልቅነት መድረኩ የወጡ ናቸው፤ አዙራ ብታየው የጠቀሰቻቸውን ሴቶች ገፉ የምትላቸው ወንዶች መጀመሪያውኑ በሴቶቹ ተገፍተው እንደነበረስ ሊታሰብ አይገባም? ምናልባት ከጠቀሰቻቸው ሴቶች ይልቅ መስከረም የሄለን ኬለርን ታሪክ ብታስታውስ ኖሮ መገፋትን አታነሣም ነበር፤ ሄለን ኬለር በሕጻንነትዋ ዓይኖችዋም ጆሮዎችዋም ሥራቸውን አቆሙ፤ የሄለን ኬለር የመንፈስ ጥንካሬ ከውስጥዋ አዲስና የተሻሉ ዓይኖችንና ጆሮዎችን እንድታበቅልና እንድትማር፣ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲም የመጀመሪያዋ ሴት ምሩቅ ለመሆን እንድትበቃ አድርጓታል፤ ይህች አስደናቂ ሴት ከመቶ ሠላሳ ዓመታት ግድም በፊት ማኅበረሰቡ በሴቶች ላይ የነበረውን አጥር ሰብራ፣ ዓይኖችዋ ባለማየታቸውና ጆሮዎችዋ ባለመስማታቸው የገጠማትን እክል አሸንፋ ራስዋን ከወንዶች በላይ ለማድረግ በቅታለች።
መገፋትን የሚፈልግ ሁሉ፣ ካልገፉት የማይነቃነቅ ሁሉ፣ ሬትን ሲግቱት ይጣፍጣል እያለ የተቀበለ ሁሉ፣ ዶሮ ማታ፣ ዶሮ ማታ፣ እያሉ አታልለው እንኳን ዶሮ የለም ሹሮ ሲሉት የማይናደድ ሁሉ፣ ምኞቱ ልደግ ልመንደግ እያለ ሲነዘንዘው በአፈና ጭጭ የሚል ሁሉ ለወቀሳ ብቻ አይደለም ለውርደትም ክፍት ነው፤ ስለዚህም ተወቅሶ ከውርደት ከዳነ ወቀሳው ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ማለት ነው፤ ዞሮ ዞሮ የሰው ልጆች ሁሉ — ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት ሽማግሌ-አሮጊት፣ ባለሥልጣን ተራ፣ ገበሬ ነጋዴ፣ ወታደር ፖሊስ፣ አስተማሪ አስተዳዳሪ፣ ዳኛ ጠበቃ፣ ሀኪም መሀንዲስ፣ … — የፈለገውን ቢሆን ላለበት ሁኔታ ኃላፊነቱ የራሱና የግሉ ነው፤ ራሱን የሚገነባው ወይም ራሱን የሚንደው ራሱ ነው፤ ሰበብ እየፈለጉ ከዚህ ኃላፊነት መውጣት ቀላል ቢመስልም ተመልሶ እምቦጭ ነው፤ ዳገቱን ለመውጣት የሚመረውን እውነት መቀበል ያሻል።
በመጨረሻም በማናቸውም መንገድ፣ በማናቸውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ወደቁልቁለት የሚገፉትን ወይም የሚነዱትን ‹‹እምቢ!›› ብሎ ድምጹን ያላሰማ ገደል ገብቶ ሲንፈራፈር ከራሱ በቀር የሚወቅሰው የለም፤ አቅመ-ቢስነት ከውጭ አይመጣም።

ሁለት

አንድ በሀርቫርድ የኒቨርሲቲ ያጋጠመኝን ነገር መግቢያ ላድርገውና ልቀጥል፤ በአንድ ሴሚናር (የጥናት ውይይት) ላይ አንድ ጥቁር አሜሪካን ፕሮፌሰር ወደአሜሪካ በባርነት በመጡት አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ በመዘርዘር አስረድቶ አሁን ለእነሱ ልጆችና የልጅ ልጆች ካሣ መከፈል አለበት የሚል ክርክር አነሣ፤ ካሣውን የመክፈል ግዴታ የሚጣለው ማን ላይ ነው? ካሣውንስ የመቀበል መብት የሚሰጠው ለማን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ሳናነሣ ብዙ ሌሎች ጥያቄዎች ይኖራሉ፤ — እነዚያ ከአፍሪካ በባርነት ተይዘውና ተሸጠው የመጡት ሰዎች ዛሬ የሉም፤ እነሱ በባርነት ሞተዋል፤ ዛሬ በሕይወት የሚገኙት ጥቁር አሜሪካውያን ነጻነታቸውን አግኝተው ባለሙሉ መብት ዜጎች ሆነዋል፤ በአንጻሩ ደግሞ ለባሪያዎች ነጻነት የተጋደሉ ነጮች አሉ የእነዚህ ልጆች ከባሪያዎቹ ወይንስ ከጌቶቹ ወገን ይመደባሉ? ዛሬ ለልጆቻቸው ካሣ ይከፈል ማለት ልጆቹ የራሳቸውን ነጻነት ችላ ብለው ከአባቶቻቸው ባርነት ጋር እንዲቆራኙ ማድረግ አይሆንም ወይ? የባርነት ምልክቶችን ሁሉ ደምስሰው ነጻ ሰዎች ለመሆን የመጀመሪያው ግዴታ ራስን ችሎ በሁለት እግሮች መቆም ነው፤ ካሣ ክፈሉን ማለት አንደኛ ዋጋ ለማይሰጠው ነጻነት ዋጋን በማውጣት ማርከስ ነው፤ ከሰውነት ወደቤት እንስሳነት መውረድ ነው፤ ሁለተኛ በጌታና በባርያ መሀከል ያለው ግንኙነት መልኩን ለውጦ እንዲቀጥል መድረግ ነው፤ የውይይቱ ባለቤት እኔ ያቀረብሁትን ሀተታ እንዳላሰበበት ቢናገርም የእኔ ጥያቄ የተወደደ አልመሰለኝም፤ ካሣ ተቀባዮች ባርነታቸውን ካሣ ከፋዮች የባሪያዎች ባለቤትነታቸውን ጠብቀው እንደተቆራኙ መቀጠላቸው ባርነትን አያጠፋም፤ ለእኔ ጤናማ አልመሰለኝም።
ባሪያና ኃላፊነት አይተዋወቁም፤ ባሪያ ለገዛ ራሱ ኑሮም ቢሆን ኃላፊነት የለውም፤ ለምግቡም ሆነ ለልብሱ፣ ለመጠለያውም ሆነ ለቀብሩ ኃላፊነት የለበትም፤ ለሁሉም ነገር ኃላፊነቱ የጌታው ነው፤ ከባርነት መውጣት ማለት፣ ከባርነት መላቀቅ ማለት ነው፤ ለገዛ ራስ ሕይወት፣ ለገዛ ራስ ኑሮ ሙሉ ኃላፊነትን መሸከም ነው፤ ስለዚህም ከባርነት ወደነጻነት መሻገር ከግድዴለሽነት ወደኃላፊነት መሻገር ነው፤ ስለዚህም ከግዴለሽነት ወደኃላፊነት ሳይሻገሩ ከባርነት ወደነጻነት መሻገር አይቻልም! ኤልሪድጅ ክሊቨር የሚባል ጥቁር አሜሪካዊ በእስር ቤት ሆኖ የጻፈው (Soul on Ice) የሚል መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ አፍአዊ ምልክቶችን ዘልቆ የሚገባ የነጻነትንና የባርነትን ባሕርያት ያሳያል፤ በአንድ በኩል በሴት ባርያና በወንድ ጌታ መሀከል ያለውን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በወንድ ባርያና በሴት እመቤት በኩል ያለውን ግንኙነት በግላጭ ያወጣዋል፤ ባርነትን የባሕርዩ ያደረገ መገለጫው ለምንም ነገር ኃላፊነት የማይሰማው መሆኑ ነው፤ ለምንም ነገር ሳያስብ፣ በትእዛዝ ብቻ መመራት የተመቸው ባርያ ነው።
ደግ ጌታ በራሱ ተነሣሺነትና በራሱ ፈቃድ ባሪያውን ነጻ ቢያወጣው ባሪያው ሙሉ በሙሉ ነጻ የሚሆን አይመስለኝም፤ በሕግ ነጻ ይሆናል፤ በውስጡ ግን ገና ከባርነት አልተላቀቀም፤ ከጌታው ጥገኛነት ለመውጣት ባለመዘጋጀቱ በኑሮውም ቢሆን ከጌታው አልተላቀቀም፤ ሳይለቀለቅ ከነእድፉ እንደተሰጣ ልብስ ነው፤ ተፈቅዶለት ከባርነት የወጣ ገና ነጻነትን አላገኘም፤ ከባርነት ለመላቀቅ በፍላጎቱና በፈቃዱ ወስኖ ነጻነቱን ከጌታው በግድ ፈልቅቆ ማውጣት አለበት፤ ለምን? የነጻነቱንና የሰውነቱን ቁርኝት ተገንዝቦ፣ የዜግነት እኩልነቱን ተረድቶ፣ በሰውነትም በዜግነትም ጌታህ-ነኝ ከሚለው የማያንስ መሆኑን አምኖ በቆራጥነት ሲነሣ ነው፤ የሰውነቱንና የዜግነቱን ልክ፣ የነጻነትን ትርጉምና ጣዕም አውቆ በትግል ነጻነቱን ሲያገኝ ያለጥርጥር ከባርነት ወጣ ማለት ይቻላል፤ አለዚያ ነጻነቱን በስጦታ፣ በጌታው መልካም ፈቃድ የሚያገኘው የነጻነት ሙሉ ባሕርይ አይኖረውም።
የአፍሪካን አገሮች ብንመለከት የመረረ የነጻነት ትግል የተካሄደባቸው ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ አልጂርያ፣ ዚምባብዌ ናቸው፤ እንደሚታወቀው እነዚህ አራቱም አገሮች ለአውሮፓውያን ሰፈራ የታጩ ነበሩ፤ ምናልባት በእነዚህ ዘገሮች ለነጻነት የተደረገውን ትግል መራራ ያድረገው ዋናው ምክንያት አፍሪካውያኑ አገር-አልባ ሆነው እንዳይቀሩ የነበረው ስጋት ሊሆን ይችላል፤ በአንጻሩ ሱዳን የነጻነት ትግል አልነበረም፤ የኢትዮጵያ ጎረቤት ስለሆነ ቶሎ ነጻነትን በመስጠትና ወዳጅ በመፍጠር፤ በሶማልያም በኩል እንዲሁ ቶሎ ነጻነትን በማሸከም ምዕራባውያን ወደፊት ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት እየቀረጹ ነበር ለማለት ይቻላል፤ ግብጾች ከስንት ሺህ ዓመታት በኋላ ነው አሁን በዘመናችን ወንዶችና ሴቶች በአደባባይ ወጥተው እምቢ! በማለት ሙባረክን ያስወረዱት! ለነጻነት የመታገሉ ልምድ ስለሌላቸው፣ በዚያም ላይ ባህልና ሃይማኖት ተጨምሮበት ሙባረክን አስወርደው ነጻነትን አላገኙም፤ እንደዚሁም የኢትዮጵያ ሕዝብም አጼ ኃይለ ሥላሴን አስወርዶ ነጻነቱን አላገኘም::
እያንዳንዱ ሰው የተፈጠረው ከነፍላጎቱና ፍላጎቱን ለማሟላት ካለው አዛዥነት ጋር ነው፤ ባርያ ፍላጎቶቹን ለማሟላት አዛዥነቱ የለውም፤ አዛዡ የራሱ ፈቃድ ነው፤ የራሱ ፈቃድ የሌለው ሰው ወና ሰው ነው፤ ዋናውን የሰውነት ባሕርዩን ያጣ ባዶ ዕቃ ነው፤ ከባዶ ዕቃ ውስጥ የሚወጣ ነገር የለም፤ ለዚህ ነው ለነጻነቱ መታገልና በራሱ ጥረት ድልን ለመጎናጸፍ የማይችለው።

Tuesday, April 1, 2014

የማሕበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት ከተመስገን ደሳለኝ


“ማሕበረ-ወያኔ” ... mahbere-kidusan-300x168 በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል፡፡ የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ አካባቢ የሚንቀሳቀሱት የወያኔ መሪዎች ምሽጋቸው እንደ ሳህል ምቹ ባለመሆኑ፤ በርካታ ክፉ ቀናትን ያሳለፉት በተራራማ አካባቢዎች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ገዳማት ውስጥ ተደብቀው እንደሆነና ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሲፈልጉም የመነኮሳቱን አልባሳት ይጠቀሙ እንደነበረ በትግሉ ዙሪያ የተዘጋጁ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ በተለይም ታጋይ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ ስዩም መስፍን፣ ስብሐት ነጋን…. የመሳሰሉ የአመራር አባላት የገዳማቱ ቤተኛ ነበሩ፡፡ ከዚሁ ጋ ተያይዞ የሚነገርም አንድ ታሪክ አለ፤ የመንግስት ፀጥታ ሰራተኞች ሁለት የ‹‹ወንበዴ›› መሪዎች በትግራይ በሚገኝ አንድ ገዳም ውስጥ ከመነኮሳቱ ጋር ተመሳስለው መሸሸጋቸው መረጃ ይደርሳቸውና በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ወታደሮችን በመላክ ዙሪያ ከበባ ያደርጋሉ፡፡ ይሁንና መደበቂያ በመስጠት የረዷቸው መነኮሳት ሁለቱን ታጋዮች ‹‹ወይባ›› በመባል የሚታወቀውን ረጅሙን ቀሚሳቸውን አልብሰው እና ቆብ አስደፍተው ከአካባቢው በማሸሽ ይታደጉዋቸዋል፡፡ የታሪኩ ባለቤት መለስ ዜናዊ እና አባይ ፀሀዬ ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ የ‹‹ወንበዴ›› መሪዎች ‹በእንዲህ አይነቱ ከመርፌ አይን እጅግ በጠበበ ዕድል ህይወታችን ከሞት መንጋጋ ተርፎ ኮለኔል መንግሥቱን በጓሮ በር ወደ ዜምባብዌ ሸኝተን በትረ-መንግሥቱን ለመጨበጥና ለሃያ ምናምን ዓመታት ኢትዮጵያን ታህል ታላቅ ሀገር አንቀጥቅጠን ለመግዛት እንበቃለን› የሚል ጠንካራ እምነትና የእርግጠኝነት ስሜት በወቅቱ ነበራቸው ብሎ ማሰብ ለእነርሱም ቢሆን እጅግ አዳጋች ይመስለኛል፤ የሆነው ግን ይህ ነበር፡፡
‹‹ማሕበረ-ቅዱሳን››
መለስ ዜናዊና ጓዶቹ በለስ ቀንቷቸው ባልጠበቁት ፍጥነት የመንግሥት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር እየተቆጣጠሩ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉትን ግስጋሴ ሲያፋጥኑ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥቱ ኃይለማርያም ሰብሳቢበት፣ በደህንነት ሠራተኞች እና የኢሠፓ ካድሬዎች ገፋፊነት ትምህርታቸውን አቋርጠው ለወታደራዊ ስልጠና ደቡብ ኢትዮጵያ ወደሚገኘው ብላቴና የጦር ማሰልጠኛ ከተቱ፤ ዩኒቨርሲቲውም ተዘጋ፡፡
…ከመላው ዘማቾቹ አስራ ሁለት የሚሆኑ ተማሪዎች ተሰባስበው ሲያበቁ፣ በየቀኑ ካምፓቸው አቅራቢያ ወደሚገኘው ‹ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን› በመሄድ፣ ከመዓቱ ይታደጋቸው ዘንድ ፈጣሪያቸውን በፀሎት መማፀን የህይወታቸው አካል አደረጉት፤ ከቀናት በኋላም በአንዱ ዕለት አንድም ለመታሰቢያና ለበረከት፣ ሁለትም ስብስቡ ሳይበተን ወደፊት እንዲቀጥል በሚል ዕሳቤ ‹ማህበረ ሚካኤል› ብለው የሰየሙትን የፅዋ ማህበር መሠረቱ፡፡ …ይሁንና ከመካከላቸው አንዳቸውም እንኳ በ1977 ዓ.ም በ‹ፓዊ መተከል› ዞን የተደረገውን ‹የመልሶ ማቋቋም› ፕሮግራም እንዲያመቻቹ በዘመቱ ተማሪዎች ከተመሠረተውና ከተለያዩ የፅዋ ማህበራት ጋር በመዋሀድ የዛሬውን ‹ማህበረ-ቅዱሳን› እንደሚፈጥሩ መገመት የሚችሉበት የነብይነት ፀጋ አልነበራቸውም፤ የሆነው ግን እንዲያ ነበር፡፡
ኃይማኖትን ጠቅልሎ የመያዝ ዕቅድ
በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሓት አመራር ገዳማትን ለመሸሸጊያነት ብቻ ሳይሆን ለእርካብ መወጣጫነትም ጭምር ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ከድርጅቱ መስራቾች አንዱ የነበረው አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ‹‹A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopi›› በሚል ርዕስ ጽፎት፤ ኋላም ወደ መጽሐፍ በቀየረው የጥናት ጽሁፉ ላይ፣ ‹‹የቤተ-ክርስቲያኗን ሥልጣን (በትግራይ የነበረውን) ለማድቀቅ ሲባል በስብሀት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ተቋቋመ፡፡ ይህ ቡድንም ደብረ-ዳሞን ጨምሮ በትግራይ ውስጥ ባሉ ገዳማት አባላቱን መነኮሳት በማስመሰል፣ የገዳማቱን እንቅስቃሴ በህወሓት ፍላጎት ስር የማስገዛት ስራ ሰርቷል›› ሲል በገፅ 317 ላይ ገልጿል፡፡ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሐይማኖትን ጠቅልሎ ለመያዝ የተነሳበትን ገፊ-ምክንያትም እንዲህ በማለት አብራርቶታል፡-
‹‹ቤተ-ክርስቲያኗ ተከታዮቿን፣ ለነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እንዲገዙ ከማስተማር በዘለለ የብሔራዊ ንቃት (ማንነት) ማስተማሪያም ነበረች፡፡ …ለህወሓት እንቅስቃሴ እንቅፋት እንደነበረች ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህም ቤተ-ክርስቲያኒቱን በህወሓት ዓላማ ስር ለማሳደር ፍላጎት ነበር፤ በዚህ የተነሳም የእርሷን ተፅእኖ ለማግለል ጥልቅ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡›› (ገፅ 315-316)   ዶ/ር አረጋዊ ‹‹ጥልቅ እርምጃዎች›› ብሎ ከጠቀሳቸው መካከል አንደኛው ‹‹ለአጥቢያ ቀሳውስቱ ኮንፍረንስ በማዘጋጀት፣ በትግራይ ውስጥ ያሉትን ቤተ-ክርስቲያናት ለብቻ ነጥሎ ህወሓት በሚያራምደው የትግራይ ብሔርተኝነት ስር ማካተት›› እንደነበረ በዚሁ መጽሐፍ ጠቅሷል፡፡ ይሁንና አስገምጋሚ መብረቅ የወረደብን ያህል የምንደነግጠው፣ ዶ/ሩ ከዚሁ ጋ አያይዞ ‹‹የተጨቆነው የትግራይ ብሔርተኝነት የተነሳሳውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን ተፅእኖ ለመገዳደር ነው›› በማለት መመስከሩን ስናነብ ነው፡፡ የአረጋዊ መረጃ የሰሚ-ሰሚ ወይም በቢሆን ሃሳብ የተቀኘ አይደለም፤ ይልቁንም ራሱም በመሪነትና ሃሳብ በማዋጣት ከተሳተፈበት ከድርጅቱ የፖለቲካ ፕሮግራም የተቀዳ እንጂ፡፡
የሆነው ሆኖ ህወሓት ከ1970-72 ዓ.ም ድረስ ባሰለጠናቸው ካድሬ ‹‹ካህናት›› አማካኝነት ‹‹ነፃ በወጡ›› መሬቶች ላይ ራሱን የቻለ የቤተ-ክህነት አስተዳደር (ከሲኖዶሱ የተገነጠለ) መመስረቱ ይታወሳል፡፡ ድርጅቱ ለእነዚህ ቤተ-ክርስቲያናት መተዳደሪያ ደንብ ከመቅረፅ አልፎ ዓላማውንም እንደ አስርቱ ትዕዛዛት በፍፁም ልባቸው የተቀበሉ ‹‹መንፈሳዊ ክንፍ›› አድርጓቸው እንደነበረ፣ አረጋዊ በርሄ ተንትኖ አስረድቷል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰርጎ ገብነት በእስልምናም ላይ መተግበሩ አይዘነጋም፡፡ በተለይም የእምነቱ ተከታዮች በሚበዙበት አካባቢዎች ወላጆቻቸው ሙስሊም የሆኑ ታጋዮችን እየመረጠ እና ከክርስቲያን ቤተሰብ የወጡ ካድሬዎችንም ሀሰተኛ የሙስሊም ስም እየሰጠ ‹የትግሉ ዓላማ እስልምናን ማስፋፋት› እንደሆነ በመግለፅ የፕሮፓጋንዳ ስራ ይሰራ ነበር፡፡ በዚህ ስልቱ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የአንዳንድ ዓረብ ሀገራትን ቀልብ ማግኘት ችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ከዓረቦች በገፍ ዕርዳታ ያጎረፈለት ሲሆን፣ ወደ መሀል ሀገር የሚያደርገውን ጉዞም አፋጥኖለታል፡፡
ከመንግስት ለውጥ በኋላም ሁለቱን ሐይማኖቶች የተቆጣጠረው በታጋይ ‹‹ካህናት›› እና ‹‹ሼሆች›› ለመሆኑ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ዛሬም በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት የበላይ በሆነው ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ውስጥ ከሚገኙት አስራ ስምንት መምሪያዎች፣ አስራ ስድስቱ በህወሓት ሰዎች የመያዛቸው ኩነት ስልቱ በተሳካ ሁኔታ መተግበሩን ያስረግጣል፡፡ በተለይ ዋነኛው ሰው አቡነ ማቲያስ ሲኖዶሱን ብቻ በሚመለከት ጉዳይ ላይ ጭምር ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ‹‹የመንግስት ባለሥልጣናትን ላማክር›› ሲሉ በተደጋጋሚ መደመጣቸው እና አንዳንድ ጳጳሳት ተቃውሞ በሰነዘሩባቸው ቁጥር በአፃፋው ‹‹መንግስት ያግዘኛል ብዬ ነው እዚህ መንበር ላይ የተቀመጥኩት፤ ባያግዘኝ ሥልጣኑን አልቀበልም ነበር›› በማለት በግላጭ ሲመልሱ መስተዋላቸው ለስርዓቱ ጣልቃ-ገብነት እንደማሳያ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ከዚህ ቀደም ለሶስት ወር የቋሚ ሲኖዶሱ አባል ሆነው የሰሩ አንድ ጳጳስም ‹‹ሁልጊዜም ቋሚ ሲኖዶሱ ሲሰበሰብ እርሳቸው (ፓትርያርኩ) ‹መንግስት እንዲህ አለ›፣ ‹መንግስት ሳይፈቅድ›… የሚል ንግግር ይጠቀማሉ›› በማለት ለፋክት አስተያየት ሰጥተዋል (በነገራችን ላይ ፓትርያርኩ የመዘንጋት፣ ለውሳኔ የመቸገር፣ እንቅልፍ የማብዛትና መሰል ችግሮች ስራቸውን እያስተጓጎሉባቸው እንደሆነ ይነገራል፤ ራሳቸውም ‹‹ሲጨንቀኝ እተኛለሁ፤ ስተኛ ደግሞ እረሰዋለሁ›› በማለት ችግሩን አምነው ተቀብለዋል)
በእስልምና እምነት ውስጥም የመንግስት ጣልቃ-ገብነት ከቀድሞውም መጅሊስ የባሰ እንደሆነ በርካታ መዕምናን የሚያውቁት እውነታ ነው፡፡ ይህ መጅሊስ የሚዘወረው እንደተለመደው በምክትል ፕሬዚዳንቶች ሲሆን፤ ይች አይነቷ ጨዋታ ደግሞ ህወሓት ጥርሱን የነቀለበት ስለመሆኑ ነጋሪ አያሻም፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሼህ ከድር ለ17 ዓመታት የትግራይ ክልል መጅሊስና የሸሪአ ፍ/ቤቱን ደርበው በመያዝ መእምናኑን ቀጥቅጠው ሲገዙ ከመቆየታቸውም በላይ ታጋይ እንደነበሩ በኩራት ለመናገር የሚደፍሩ እንደሆነ የቅርብ ሰዎቻቸው ይመሰክራሉ፡፡ በአናቱም ከታማኝ የመረጃ ምንጭ ባይረጋገጥም የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት ሼህ ኪያር መሀመድ ከእኚሁ ‹‹ታጋይ›› ምክትላቸው ጋር በአንዳንድ ጉዳዮች መስማማት ባለመቻላቸው እና ‹‹መንግስት የሚያዘውን ሁሉ ለመስራት ለምን እንገደዳለን?›› የሚል ተቃውሞ እስከማሰማት በመድረሳቸው በቅርቡ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ እንደሚችሉ ተወርቷል፡፡
ኢህአዴግ እና ‹‹መንፈሳዊ›› ገበያው
ግንባሩ የእምነት ተቋማትን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ጠርንፎ መያዝን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የመንቀሳቀሱ መግፍኤን ከሶስት ጉዳዮች አንፃር በአዲስ መስመር ለመተንተን እሞክራለሁ፡- የመጀመሪያው ቤተ-ክህነት በነገስታቶቹ ዘመን የነበራትን ፖለቲካዊ ተሰሚነት (ምንም እንኳን ራሱ ኢህአዴግም በአፋዊነት ከማውገዝ ቸል ባይልም) ለቅቡልነት መጠቀሚያ የማድረግ ፍላጎቱ ነው፡፡ በገቢር እንደታየውም በኃይል በተቆጣጠራቸውም ሆነ ካድሬዎቹ ሊደርሱባቸው በማይችሉ የገጠር ቀበሌዎች ተቀባይነት ለማግኘት ማህበራዊ አክብሮት ባላቸው ሼሆች፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት… ሲቀሰቅስ ተደጋጋሚ ጊዜ ተስተውሏል፡፡ እንዲሁም የእስልምና እምነት በታሪክ ያሳለፈውን አገዛዛዊ ጭቆናንም ሆነ የደርጉን ሁሉንም ሐይማኖት ማግለልን በማጎን ለፕሮፓጋንዳ ተጠቅሞበታል (በወቅቱ የድርጅቱ አመራር አባል የነበረው አቶ ገብሩ አስራት፣ እንደ ሼሆች በመልበስና በመጠምጠም ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከቱን ብዙሀኑ ታጋዮች አይዘነጉትም) በዚህ ዘመንም በቤተ-እምነቶች ካድሬ-ጳጳሳትንና ካድሬ-n ሼሆችን አሰርጎ የማስገባቱ ምስጢር ይኸው ነው፡፡
በሁለተኛነት እንደምክንያት ሊጠቀስ የሚችለው የታገለለትን ዘውግ ተኮር ፖለቲካ ያለአንዳች ተግዳሮት ማሳለጥን ታሳቢ ማድረጉ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሐይማኖቶች ‹‹የሰው ልጅ በሙሉ የአንድ አምላክ ፍጡሮች ናቸው›› በሚል አስተምህሮ የሚመሩ ከመሆናቸው አኳያ፣ በዘውግ ከፋፍሎ ማስተዳደርን ቀላል አያደርገውምና ነው፡፡ ስለዚህም መፍትሔው አክራሪ ብሔርተኛ ‹‹መንፈሳውያን›› በየእምነት ተቋማቱ እንዲፈለፈሉ እና ከፍተኛውን የሥልጣን እርከን መቆጣጠር እንዲችሉ በማብቃት ላይ የተመሰረተ ብቻ መሆኑን የህወሓት መሪዎች ያውቃሉ፡፡ ይህ ‹‹እውቀታቸው››ም ይመስለኛል ሀገራዊ ስሜት የሌላቸው፣ በችሎታ ማነስ እና በስነ-ምግባር ጉድለት የሚታወቁ፤ እንዲሁም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅቡል ያልሆኑ ሰዎች ቦታውን እንዲይዙ እስከማድረግ ያደረሳቸው፡፡
የራሳቸው የስለላ መዋቅርም በጥቅምት 2 ቀን 1995 ዓ.ም ‹‹ለዋናው መ/ቤት፣ አዲስ አበባ፤ ከ-ል.ዮ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ጉዳይ ይመለከታል›› በሚል ርዕስ ለደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት በላከው ጥናታዊ ዘገባ ላይ እውነታውን እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- ‹‹…ለፓትርያርኩ ወዳጅነት አላቸው የሚባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ከሦስትና አራት ብዙም ያልበለጡ ናቸው፡፡ ፓትርያርኩ ምንም ዓይነት ተቀባይነትና ከበሬታ ያጡ በመሆናቸው ህልውናቸውን የአንዳንድ መሪዎችን ስም በመጥራትና እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ላይ የተንጠላጠለ ሆኗል››፡፡ ከዚህ ሪፖርት በኋላም እንኳ ለማስተካከል አለመሞከሩ መከራከሪያውን አምነን እንድንቀበል ያስገድደናል፡፡
አገዛዙ መንፈሳዊ ተቋማትን ጠቅልሎ ለመያዝ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ በሶስተኛነት ሊጠቀስ የሚችለው ምክንያት፣ ምንም እንኳ ‹‹ተሳክቷል›› ሊባል ባይቻልም፤ በስነ-ምግባር መታነፅ፣ በሀገር አንድነት ማመን፣ ለሕዝብ ጥቅም መቆም፣ የትኛውንም ህገ-ወጥነት ‹ለምን› ብሎ መጠየቅና መሰል መንፈሳዊ አስተምህሮዎችን መርሁ አድርጎ የሚነሳ ትውልድ እንዳይፈጠር መከላከልን ታሳቢ በማድረግ እየሰራ ያለውን ሴራ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም የስርዓቱ ሰዎች በዚህ መልኩ የሚቀረፅ ትውልድን ዛሬ ባነበሩት አይነት የጭቆና ቀንበር ለተራዘሙ ዓመታት መግዛት ከባድ እንደሆነ ለመረዳት አይሳናቸውምና ነው፡፡ ከዚሁ ጋር አንስተን ማለፍ ያለብን ጭብጥ፤ መቃብር ከሚቆፈርለት የኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ጋር የሚያያዝ ነው፤ የሐይማኖቱና የማዕከላዊ መንግስቱ የቅድመ-አብዮቱ ጋብቻ (በምንም አይነት መከራከሪያ ትክክለኛነቱን ልንሟገትለት ባንችልም)፣ ቤተ-ክርስቲያኗ ለኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነቱ የታሪክ ብያኔ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጓን አያስክደንም፡፡ ይህም ‹የሐይማኖቱን ተቋም የብሔርተኝነቱ ወካይ ሆኖ እንዲታሰብ ይገፋዋል› ብሎ ለሚያምነው ህወሓት፣ ሐይማኖቱ ተቋማዊ ነፃነት እንዳይኖረው የሚቻለውን ሁሉ ሲያደርግ፤ ሐይማኖቱን በማዳከም የብሔርተኝነት መንፈሱንም ማላላት ይቻላል ከሚል መነሾ ነው ብሎ መደምደም ተምኔታዊ አያስብልም፡፡
ገደል አፋፍ የቆመው ማሕበረ ቅዱሳን…
ስርዓቱ የሐይማኖት ተቋማትንና መንፈሳዊ መሪዎቹን ለመቆጣጠር ገፊ-ምክንያቶች ሆነውታል ብዬ ከላይ ለማብራራት የሞከርኳቸውን ሶስት ምክንያቶች ሙሉ ለሙሉ መተግበርን አስቸጋሪ ያደረገበት፣ ቀጥታ በምዕምናኑ የተመሰረቱ ማሕበራት መሆናቸውን መገመት ይቻላል፡፡ ለማስረጃም ያህል ከኦርቶዶክስ ክርስትና-ማሕበረ ቅዱሳን፤ ከእስልምና ያለፉትን ሁለት ዓመታት የእምነቱ ተከታዮች ወካይ ሆኖ የተመረጠው ኮሚቴ አባላት መንግስትንም ሆነ መጅሊሱን በመገዳደር ያደረጉትን አበርክቶ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይሁንና የሙስሊሙን ተወካዮች በገፍ ሰብስቦ እስር ቤት ካጎረ በኋላ፣ ከሲኖዶሱም ሆነ መሰል ማሕበራት ጠንካራ እንደሆነ የሚነገርለትን ማሕበረ ቅዱሳንን ዋነኛ ኢላማው አድርጎ ለመደፍጠጥ የቆረጠ ይመስላል፡፡ የማሕበሩ አባላት በዓለማዊ እውቀት የተራቀቁ፣ በሀገር አንድነት በፍፁም የማይደራደሩ፣ በጥቅመኝነት የማይደለሉ… የመሆናቸው ጉዳይ አገዛዙ ከኃይል አማራጭ የቀለለ መፍትሔ የለም ብሎ እንዲያምን አድርጎታል ብዬ እገምታለሁ፡፡
በርግጥ በአቶ መለስ ዜናዊ ይዘጋጅ እንደነበረ ከህልፈቱ በኋላ በተነገረለት የኢህአዴግ የንድፈ ሃሳብ መጽሔት ‹‹አዲስ ራዕይ›› ከተወሰኑ ዓመታት በፊት አብዛኛውን ጊዜ ‹‹የከሰሩ ፖለቲከኞች ‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት፣ አንድ ሐይማኖት አንድ ሀገር› እና ‹ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ቀደም ሲል ሲደርስበት የነበረውን በደል በማራገብና በመቀስቀስ፤ ከዚህም አልፎ ተገቢነት የሌላቸው አዳዲስ ጥያቄዎችን በማቅረብ ለማነሳሳትና ለማተረማመስ ሲሰሩ ማየት የተለመደ ሆኗል›› በማለት ከሚያቀርበው የሾላ-በድፍን ፍረጃ ዘልሎ ብዙም መንፈሳዊ ማሕበራትን በስም ጠቅሶ ሲያወግዝ አይሰማም ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ማንኛውንም ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄን ‹‹ወሃቢያም ይሁን ማሕበረ ቅዱሳን…›› በማለት ማውገዙ የተለመደ ሆኗል፡፡ ከውግዘትም ተሻግሮ ጥያቄያቸውን በሕጋዊ መንገድ ወደ አደባባይ ያወጡትን የሙስሊሙን ተወካዮች ሰብስቦ አስሯል፤ በተለያየ ጊዜ የተደረጉ ሰላማዊ ተቃውሞዎችንም በማስታከክ በበርካታ የእምነቱ ተከታዮች ላይ ግድያና ስቀየትን ጨምሮ ብዙ ግፍ በመፈፀም ጉዳዩን በጠብ-መንጃ ብቻ የሚፈታ አድርጎ ካወሳሰበው ሰነባብቷል፡፡
‹‹ቀጣዩ የኢህአዴግ ኢላማ ማሕበረ ቅዱሳን ይሆን?›› በሚል ርዕስ ከስድስት ወር በፊት በዚሁ መጽሔት ላይ ለማተት እንደሞከርኩት ሁሉ፤ ከላይ በተዘረዘሩ የፖለቲካ አጀንዳዎች እና በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ በለመደው የማጭበርበር መንገድ አሸንፎ ያለኮሽታ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም ዓለማዊም ሆነ መንፈሳዊ ነፃ ተቋማት እንዳይኖሩ በይፋ ኢ-ሕገ መንግስታዊ ድርጊቶችን እየፈፀመ ያለው የእነ አባይ-በረከት መንግስት፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ትኩረቱን ማሕበረ ቅዱሳን ላይ ማድረጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይህንን አፈና ለማሳካትም ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በፍፁም ልባቸው ከመተባበር ለአፍታም እንደማያመነቱ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህልም አንዱን በአዲስ መስመር ላቅርብ፡-
ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት አስተዳደርን ወደ ዘመናዊነት ለማሻገር ሲኖዶሱ ጥናት ተደርጎ እንዲቀርብለት ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ እናም ጥናቱ ተጠናቆ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ከአንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎች ብርቱ ተቃውሞ ስለገጠመው፣ በሀገረ-ስብከቱ ሥራ-አስኪያጅ አቡነ እስጢፋኖስ አማካኝነት በጠቅላይ ቤተ-ክህነት አዳራሽ ከሁሉም አድባራትና ገዳማት የተወጣጡ 2700 ሰዎች የሚሳተፉበትና አስራ አራት ቀን የሚፈጅ የውይይት ፕሮግራም ይዘጋጃል፡፡ ይሁንና ውይይቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ጠዋት ፓትርያርኩ፣ ከአቡነ እስጢፋኖስ ጋር በስልክ ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው መወዛገባቸውን ሰምቻለሁ፡-
‹‹ጥናቱን የሚሰሩት ባለሙያዎች ናቸው ብለውኝ አልነበረም ወይ?›› ‹‹አዎ! ታዲያስ ባለሙያዎች ናቸው የሰሩት፡፡›› ‹‹አይደለም! የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው፤ እርስዎ አታለውኛል!›› ‹‹የጥናት ኮሚቴው አባላት በቤተ-ክርስቲያን ልጅነታቸውና በየአጥቢያው ባላቸው ተሳትፎ ተጠርተው የመጡ ሙያቸውን ‹አስራት› ያደረጉ ናቸው፡፡›› ‹‹በፍፁም! ጥናቱ የማሕበረ ቅዱሳን ነው!›› ‹‹ቅዱስ አባታችን ቢሆንስ? ከጠቀመን ችግሩ ምንድን ነው?›› ‹‹በቃ! ውይይቱ ከመንግስት ይቋረጥ ተብሏል፡፡›› ‹‹ለምን ይቋረጣል?›› ‹‹የጥናቱ ተቃዋሚዎች ረብሻ ያስነሳሉና የፀጥታ ስጋት አለ፡፡›› ‹‹ለምንድን ነው ረብሻ የሚያስነሱት? ከፈለጉ መጥተው መሳተፍ ይችላሉ፤ እኛ እየተወያየን አይደለም እንዴ! ተቃውሞ ያለው መጥቶ ሃሳቡን ይግለፅ እንጂ ማቋረጥ እንዴት መፍትሄ ይሆናል? ደግሞስ ሲኖዶሱ አይደለም ወይ ‹ሰነዱ ወደታች ወርዶ ይተችበት› ብሎ የወሰነው?›› ‹‹የለም! ይቁም ተብሏል፤ ይቁም!›› ‹‹እንግዲያውስ የከለከለው አካል ራሱ መጥቶ ይንገረን፡፡››
…የስልክ ምልልሱ ከተጠናቀቀ ከሰዓታት በኋላ አንድ ባለሥልጣን አቡነ እስጢፋኖስ ቢሮ ድረስ መጥቶ ትእዛዙን ያስተላለፈው እርሱ እንደሆነ ገልፆ ውይይቱ እንዲቋረጥ አሳሰባቸው፤ እርሳቸውም ‹‹እናቋርጣለን፤ ነገር ግን እናንተ ‹የፀጥታ ስጋት አለ› ብላችሁ በደብዳቤ ኃላፊነቱን ውሰዱ፡፡ እኛም ለካህናቱም ሆነ ለመዕምናኑ ሁኔታውን ዘርዝረን እንገልፃለን›› የሚል ምላሽ ሰጥተው ይሸኙታል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ለጊዜው ግልፅ ባልሆነ አንድ ምክንያት መንግስት ‹‹ይቋረጥ›› የሚለውን ማስፈራሪያ ሊያነሳ የቻለው፡፡ ኩነቱ ግን ፓትርያርኩ ማሕበሩን በጥርጣሬ ማየታቸውንና አገዛዙ ለሚወስድበት ማንኛውም አይነት እርምጃ ተባባሪ መሆናቸውን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡
ሌላው መንግስትና ፓትርያርኩ፣ ማሕበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ በሰምና ወርቅነት እየሰሩ መሆናቸውን የሚያመላክተው የዛሬ ሳምንት በጠቅላይ ቤተ-ክህነት የማሕበሩ ተቃዋሚዎች ያደረጉትን ውይይትና የአቋም መግለጫ ስናስተውል ነው፡፡ ለመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል የደረሰው በድምፅ የተቀረፀ የውይይቱ ሙሉ ክፍል እንደሚያስረዳው፣ ተሰብሳቢዎቹ ማሕበሩን በተመለከተ ባወጡት የአቋም መግለጫ የሚከተሉትን ነጥቦች ዘርዝረዋል፡- ‹‹የዋነኛ አመራሮቹ የባንክ አካውንት ይመርመር፣ የማሕበሩ ሒሳብ መንግስት በሚመድበው የውጪ ኦዲተር ይመርመር፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቹ (ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸው ቀላልና ከባድ መኪናዎቹ ሳይቀሩ) ወደ ቤተ-ክህነት ይግቡ፣ የንግድ ተቋማቱ (ትምህርት ቤት፣ ሬስቶራንቶቹን፣ ንዋየ ቅድሳት ማምረቻና ማከፋፈያውን) ያስረክብ፣ ከምዕምናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚቀበለው አስራት እየፈረጠመበት ስለሆነ እንዳይቀበል ይከልከል፣ የግቢ ጉባኤ (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው እንዳይወሰዱ መስራት፣ ተጠሪነቱ ከዋና ሥራ-አስኪያጁ ተነስቶ፣ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ስር አንዱ ንዑስ ክፍል ይሁን…›› የሚሉና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ከዚህ ሴራ ጀርባ ፓትርያርኩና መንግስት በትብብር መቆማቸውን የሚያሳየው በተቀረፀው ድምፅ ላይ፣ የውይይቱ መሪ አዳራሹን መጠቀም የቻሉት በአቡኑ መልካም ፍቃድ እንደሆነና እርሳቸው በዛሬው ውይይት ያልተገኙት የሕዳሴው ግድብ ምክር ቤት አባል በመሆናቸው ግዮን ሆቴል ስብሰባ ስላለባቸው መሆኑን ከመግለፅም በዘለለ፤ ‹‹ቅዱስ አባታችን በዚህ የተቃውሞ ምክንያት ከሥራ የሚባረር የለም አይዟችሁ አትፍሩ ብለውናል›› በማለት ሲናገሩ መደመጣቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹ከዚህ ግቢ አቅም ኖሮት የሚያስወጣን የለም፤ ካስወጡን ግን መንግስታችን ስለሚተባበረን (ቸር ስለሆነ) ከእርሱ ሌላ መሬት ተቀብለን የራሳችንን ቤተ-ክርስቲያን እናቋቁማለን›› እና ‹‹የኦርቶዶክስ እምነት አገልጋዮች የሚል ማሕበር እንመሰርታለን›› እስከማለት መድረሳቸው ከአገዛዙ ጋር ያላቸውን የጠበቀ ቁርኝት ያመላክታል፡፡ በነገራችን ላይ በስብሰባው እንዲሳተፉ ከተጠሩት ከመቶ ስልሳ ዘጠኙ አድባራትና ገዳማት፣ እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ ሠራተኞቻቸው መካከል የተገኙት የስምንት አድባራት አስተዳዳሪዎችና 150 ሠራተኞች ብቻ እንደነበሩ ከመረጃ ምንጮቼ አረጋግጫለሁ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በተለይም በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ምኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም አዝማችነት ማሕበሩ ላይ የደቦ ዘመቻ ከተከፈተ ሰነባብቷል፡፡ በተከታታይ በ‹‹ጥናት›› ስም የሚወጡ ወረቀቶች ማሕበሩን ከአክራሪነትም አሻግረው ‹‹የግንቦት ሰባት መንፈሳዊ ክንፍ›› ሲሉ ይወነጅሉታል፡፡ በጥቅሉ የእነዚህ ‹‹ጥናት›› ተብዬዎች መደምደሚያ ‹‹ማሕበሩ የትምክተኞች ምሽግ ነው፣ አክራሪነት አለበት፣ አመራሩና የሕትመት ውጤቶቹ የፖለቲካ አዝማሚያ ይታይባቸዋል፣ በቤተ-ክርስቲያን አስተዳደር ጣልቃ ይገባል፣ ሕዝቡ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው ይሰራል፣ በውጭ ፅንፈኛ የፖለቲካ ኃይሎች ይዘወራል›› የሚሉ ናቸው፡፡ የማሕበሩ የአመራር አባላት እንዲህ አይነቱን ውንጀላ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ከአቶ በረከት ስምኦን እስከ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም፤ ከአዲስ አበባ የፀጥታ ኃላፊዎች እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ የደህንነት አማካሪ ፀጋዬ በርሄ ድረስ ያሉ ባለሥልጣናትን በቢሮአቸው ተገኝተው ውንጀላው ማስረጃ የማይቀርበበት የሀሰት እንደሆነ ቢያስረዱም መፍትሄ እንዳላገኙ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በግልባጩ በመንግስት ተቋማት ያሉ የፋክት መረጃ አቀባዮች፣ በግንቦት ወር ከሚካሄደው የሲኖዶሱ መደበኛ ጉባኤ በፊት፣ ከሃያ የሚበልጡ የማህበሩ አመራርን ከሽብርተኝነት ጋር በማያያዝ ለመክሰስ እና ማሕበሩንም እንደተለመደው በዶክመንተሪ ፊልም ለመወንጀል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በአቡነ ገብርኤል ሰብሳቢነት የሚመራው የሐይማኖቶች ምክር ቤት ስብሰባውን ካጠናቀቀ በኋላ ዶ/ር ሽፈራው አቡኑን ቃል-በቃል የጠየቃቸው ጥያቄም ይህንን መረጃ የሚያጠናክር ነው፡-
‹‹በማሕበረ ቅዱሳን አመራር ውስጥ ከሃያ በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አሉ›› ‹‹ለዚህ ምንድን ነው ማስረጃህ? አቅርበውና እስቲ እንየው?›› ‹‹ሀገር ውስጥ ካሉ ፅንፈኛ ጋዜጠኞች በተጨማሪ በስደት የሚገኙና በሽብር ተግባር የተሰማሩ ጋዜጠኞች በአመራርነት አሉበት (የሁለት ሰዎችን ስም ጠቅሷል)›› ‹‹እኛ እስከምናውቀው ማሕበሩ ከእንዲህ አይነት ተግባር የራቀ ነው፤ እናንተ ማስረጃ አለን ካላችሁ ደግሞ አቅርቡልንና እንየው፤ ከዚህ ውጪ ይህንን አይነት ክስ አንቀበልም፡፡››
በአናቱም ከወራት በፊት የስርዓቱ የንድፈ ሃሳብ መጽሔት የማሕበሩን ስም ሳይጠቅስ በደፈናው የወነጀለበትን እና ‹‹ለምን?›› ብለው የሚጠይቁ ጳጳሳትን በሚከተለው አገላለፅ ማሸማቀቁን ስናስታውስ የማሕበሩ ዕጣ-ፈንታ በመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ መቆሙን ያስረግጥልናል፡፡
‹‹በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ትርምስና ብጥብጥ ለመፍጠር፤ በኦርቶዶክሶችና ሌሎች ሐይማኖቶች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሞክሩት የደርግና የተለያዩ ትምክህተኛ ኃይሎች ቅሪቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የትምክህት ኃይሎችና አንዳንድ የእምነቱ አባቶች በጋራ ሐይማኖትን በፖለቲካ ዓላማ ዙሪያ መጠቀሚያ አድርገው እየሰሩ ለመሆናቸው ከ97 ምርጫ በኋላ እንዳንድ በአሜሪካ የሚገኙ ጳጳሳት ቅንጅት በጠራው ሰልፍ ላይ የሐይማኖት አባትነት ካባቸውን እንደለበሱ ከመሰለፍ አልፈው አስተባባሪ ሆነው መታየታቸው በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡›› (አዲስ ራዕይ ሐምሌ-ነሐሴ 2005)
የሆነው ሆኖ ከፍረጃውና ከእስራቱ በተጨማሪ ማሕበሩን ለማዳከም በዋናነት በአገዛዙ የተነደፉት እቅዶች ማሕበሩ መሰረቱን የጣለበት የግቢ ጉባኤን ከመከልከልና ንብረቶቹን ከመውረስ ጋር የሚያያዙ ናቸው (ከላይ የተጠቀሰው የአቋም መግለጫም ለማሕበሩ የደም-ስር የሆኑትን እነዚህን ሁለት ጉዳዮች ትኩረት እንደሰጣቸው ልብ ይሏል)
ስቅለትን-ለተቃውሞ
ኢህአዴግ ወደ ስልጣነ-መንበሩ ከመጣ ሦስተኛ ዓመት ላይ ‹‹የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ግቦችና ቀጣይ እርምጃዎች›› በሚል ርዕስ ለካድሬዎቹ በበተነው ድርሳን (በሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የተዘጋጀ ነው ተብሎ ይገመታል)፤ ይህን አሁን የተነጋገርንበትን ሐይማኖታዊ ተቋማትን በሚያቅዳቸው የስልጣን ማራዘሚያ አማራጮች ስለመጠቀም ካወሳ በኋላ ተቋማቱን ለስርዓቱ ፖሊሲዎች እንዲታመኑ ማድረጉ ዋነኛ እንደሆነ ያሰምርበታል፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ ደግሞ፣ እስከ ከፍተኞቹ መንፈሳዊያን መምህራን ድረስ ዘልቆ በመግባት ሐይማኖቶቹን መምራት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ግብ መሆን እንዳለበት ያው ሰነድ በግልፅ ቋንቋ ይናገራል፡፡ እንግዲህ ከመጅሊሱ እስከ ማሕበረ ቅዱሳን ያየነው መንግስታዊ አፈና የዚህን ሃያ ዓመት የሞላው የተፃፈ ሀሳብ መተግበርን ነው፡፡
ግና፣ ከዚህ ቀደም በተፃፈ ነውረኛ ሀሳብ ትግበራ ፊት ከሁለት አስርት በላይ ህልውናውን ለማቆየት የተጋው ማሕበረ ቅዱሳን፣ ከላይ በሚገባ በጠቀስኳቸው አሳማኝ መረጃዎች እና ተጨባጭ ሁነቶች በተከታታይ መከሰት መጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ ተመልክተናል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ደግሞ፤ መነሳት የሚኖርበት መሰረታዊ ጥያቄ፣ እንዴት ይህን ማሕበር ወደ ቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ይቻላል? የሚለው ሲሆን፤ ምላሾቹም ሁለት ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የማሕበሩ አመራሮችና አባላት እስከዚህች ቀን እያደረጉ ያለው የውስጥ ለውስጥ የእርምት እንቅስቃሴን ይመለከታል፡፡ በሐይማኖቱ ተቋማት በኩል ለዓመታት ሲሞከር የቆየው ይኸኛው አማራጭ፣ እንደ አስተዋልነው ማሕበሩን ሞት አፋፍ ላይ ከመድረስ ሊታደገው አልቻለም፡፡ ስለዚህም፣ ወደ ሁለተኛውና ዋነኛ የመፍትሔ አማራጭ መሻገር ግድ የሚል ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ስፅፍ ለማስረዳት እንደሞከርኩት፤ የማሕበሩ አመራሮች፣  አባላት እና ደጋፊዎች ወደ አደባባይ በመውጣት፤ ማሕበራቸውን ብቻ ሳይሆን ህልውናቸውንና ህያውነታቸውን የመሰረቱበትን ሐይማኖት ለማውደም የሚተጋውን ስርዓት በሰላማዊ አመፅ መናድ ብቸኛው የዚህ አስቸጋሪ ጊዜ መሻገሪያ መንገድ ነው፡፡ በዋናነት የተማሩ ከተሜ ወጣቶችን፣ በአለማዊም ሆነ በትምህርተ-ሐይማኖቱ የማይታሙ ዜጎችን የያዘው ይህ ማሕበር፤ ከህዝበ ሙስሊሙ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የአደባባይ ተቃውሞ ስኬቶችና ሂደቶች በመማር፤ ፊቱ በተገተረው ኢህአዴግ ላይ በሕጋዊና ሰላማዊ እምቢተኝነት ከማመጽ የተሻለ አማራጭ እንደማይኖረው የሚረዳ ይመስለኛል፡፡
‹‹ችግሮች ሁሉ የየራሳቸው በጎ ገፆች አሏቸው›› እንዲሉ፤ ማሕበሩ የደረሰበት ይህ ፈታኝ ጊዜን ተከትለው የሚመጡ ሁለት ወቅቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው፣ በቀጣዩ ወር የሚካሄደው የስቅለት በዓል ነው፡፡ የሐይማኖቱ ተከታዮች በሙሉ በየቤተ-ክርስቲያናቱ የሚውሉበት ይህ በዓል፣ አገዛዙ እጁን ከማህበሩ ላይ እንዲያነሳ ለመጠየቅ የተመቸ ቀን ስለመሆኑ ማስታወስ አባላቱን አሳንሶ መገመት እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሁለተኛውና በእጅጉ የተሻለ ነው ብዬ የማስበው ጊዜ ደግሞ ቀጣዩ የ2007 ምርጫን ነው፡፡ ለየትኞቹም የህገ-መንግስቱ ሀሳቦች አልያም የሞራል ዕሴቶች የማይገዛው ኢህአዴግ፣ በሐይማኖቱ ላይም ሆነ በማሕበሩ ላይ የዘረጋውን የረከሰ እጅ እንዲያነሳ ያለው ብቸኛ አማራጭ ሕዝባዊ አመፅ መሆኑ ላይ እስከተማመንን ድረስ፣ ከዓመታዊ የንግስ በዓላት ጀምሮ ያሉ መድረኮችን በዕቅድ ለመጠቀም የዝግጅቱ ጊዜ ዛሬ ነው፡፡ ይህ አይነቱ የተቃውሞ እንቅስቃሴም፣ ካነሳነው ርዕሰ-ጉዳይ አኳያ የማሕበሩን መኖር የሚሹ ሁሉ ቀጣዩን የምርጫ ወቅት ለማስገደጃነት የመጠቀም ተሞክሮዎቻቸውን ተፈላጊው ብቃት ላይ እንደሚያደርሰው አምናለሁ፡፡ ጥቂት ሊባሉ የማይችሉ አባላቱ፣ የምርጫውን ተጨባጭ ዕድል መንግስታዊ ተቋማት በማሽመድመድ ጭምር እንዴት ስርዓቱን ወደመቃብሩ ማሻገር እንደሚያውቁ ስንገነዘብ፤ ቀሪው ጉዳይ ‹‹ሐይማኖታችሁን ተከላከሉ›› ብለው ላስተማሩት ቅዱሳን መጻሕፍትና ለሰማያዊው መንግስት የመታመን ብቻ እንደሚሆን እንረዳለን፡፡ ምንጭ፡ ፋክት መጽሔት
maleda times | March 31, 2014 at 9:02 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-4j9
Comment   See all comments

Sunday, March 30, 2014

የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፈኑ “ወያኔ እጅ ገብተዋል” ጎልጉል by ምንሊክ ሳልሳዊ

የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።
በመለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ከማምራታቸው በፊት ኬንያ እንደነበሩ፣ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን ለምን እንደተጓዙ የዜናው ምንጮች በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲደበቅላቸው የጠየቁ የጋምቤላ አስተዳደር ባልደረባ ለጎልጉል የአካባቢው ዘጋቢ እንደተናገሩት አቶ ኦኬሎ ደቡብ ሱዳን ሆቴል በተቀመጡበት መታፈናቸውን አረጋግጠዋል።
“ወያኔ እጅ ገብቷል” ሲሉ ያከሉት እኚሁ ሰው “አቶ ኦኬሎ ብረት በማንሳት ወያኔን ለመታገል ከተነሱ ጋር ተቀላቅለዋል በሚል ስማቸው መመዝገቡንና ወደ ደቡብ ሱዳን ማቅናታቸው በመታወቁ ህወሃቶች እጅ ሊወድቁ ችለዋል” ብለዋል። ምንጩ ይህንን ይበሉ እንጂ አቶ ኦኬሎ አክዋይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑበትን ምክንያት በርግጠኛነት ሃላፊነት ወስዶ የገለጸ ወገን አልተደመጠም። ኢህአዴግም ቢሆን የቀድሞውን ሹመኛ ስለመያዙ ይፋ ያደረገው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ የኑዌር ተወላጅ ከሆኑት ሬክ ማቻር ጦር ጋር በመሰለፍ የሳልቫ ኪርን ሃይል ሲወጉ ከተገደሉ ወታደሮች መካከል የኢህአዴግን ሰራዊት መለያ የለበሱ ኑዌሮች መገኘታቸው ውዝግብ አስነስቶ እንደነበር ያመለከቱት ምንጭ “ደቡብ ሱዳን እየወጋት ካለው ኢህአዴግ ጋር አብራ የቀድሞውን የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳደር ከምድሯ ላይ እንዲታፈኑ መፍቀዷ ቅሬታ ያስነሳል” ብለዋል።
ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዛ ማቅናታቸውን ባሥልጣኑ “ታላቅ ጥፋት” ብለውታል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በቅርቡ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
ምንሊክ ሳልሳዊ | March 28, 2014 at 10:45 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-4fp



Comment   See all comments

Sunday, March 23, 2014

20 ዓመት ሙሉ ውህደትና ጥምረት ያልሰመረለት የተቃዋሚ ጎራ (ኤልሳቤጥ እቁባይ እና አለማየሁ አንበሴ)


20 ዓመት ሙሉ ውህደትና ጥምረት ያልሰመረለት የተቃዋሚ ጎራየሐሙሱ የመኢአድና አንድነት ውህደት ሳይጀመረ ፈረሰ
ምርጫን ብቻ ግብ ያደረጉ ጥምረቶች ዋጋ አይኖራቸውም
የፓርቲዎች ውህደት ባይሳካም የተገኘው ልምድ ቀላል አይደለም
ለተቃዋሚዎች አለመጠናከር ኢህአዴግ ተጠያቂ ነው
“በሀገራችን የፓርቲ ፖለቲካ ብዙ ዘመን አስቆጥሯል ማለት
ባይቻልም በአሁኑ ጊዜ ፓርቲዎች ማደግ ሲገባቸው እየቀጨጩ ነው፣ በሜዳው ላይ መኖር የማይገባቸው ፓርቲዎችም አሉ፡፡ ፕሮግራማቸው አንድ ሆኖ እንኳ ተከፍለው መንቀሳቀሳቸው ትክክለኛ አካሄድ ካለመሆኑ በተጨማሪ ለገዥው ፓርቲም የስልጣን እድሜን እየሰጠ ነው ያሉት ከዚህ ቀደም በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራረርነት ቆይተው አሁን ላይ ከፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸው ያገለሉት ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም ናቸው፡፡
አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) እና የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ውህደት ይፈፅማሉ ተብሎ ሲጠበቅ መኢአድ ለአንድነት በፃፈው ደብዳቤ፣ ውህደቱ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን አስታውቋል፡፡ በመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መኃሪ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ፣ የፕሮግራምና የደንብ ጉዳይ፣ የስያሜ፣ የኃላፊነት፣ አንድነት ከመድረክ ጋር ስላለው ግንኙነት እንዲሁም የንብረት ጉዳዮችን በተመለከተ ተጨማሪ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይጠቁማል፡፡
ረቡዕ እለት ደብዳቤው እንደደረሳቸው የገለፁት የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ፤ እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2006 ዓ.ም የሁለቱም ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በመኢአድ ፅ/ቤት ተገናኝተው ባካሄዱት የጋራ ውይይት ላይ ድርድሩ ማለቁን በማመልከት፣ ውህደቱ ከመጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም እንዳያልፍ አሳስበው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
“አባላቱ በጥቃቅን ምክንያት ውህደቱን እንዳታሰናክሉ የሚል ማሳሰቢያ ሠጥተውን ነበር” ያሉት አቶ ስዩም፤በዚህ መሰረት አንድነት አስፈላጊ ዝግጅቶችን አጠናቆና  የሆቴል አዳራሽ ተከራይቶ ካጠናቀቀ በኋላ ደብዳቤው እንደደረሰው ተናግረዋል፡፡ “አሁን ኳሱ በመኢአድ እጅ ነው ያለው” ያሉት አቶ ስዩም፤ በአንድነት በኩል እንደ ምክንያት የተጠቀሱት ጉዳዮች በድርድሩ እልባት አግኝተዋል የሚል እምነት አለ ብለዋል፡፡
የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መኃሪ በበኩላቸው፤ ሰሞኑን በወጣ አንድ ጋዜጣ ላይ በአንድነት በኩል “ከመድረክ ጋር እንቀጥላለን” የሚል መግለጫ በመሰጠቱ ውህደቱን ልናዘገየው ተገድደናል ብለዋል።    “ድርድሩ ቆሟል ማለት አይደለም፤ይቀጥላል ነገር ግን መኢአድ በደብዳቤው የጠየቃቸው ካልተሟሉ ውህደቱ ላይፈፀም ይችላል” ብለዋል-ፕሬዚዳንቱ፡፡
ውህደት፣ቅንጅት፣ጥምረት…
ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ከተቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የመላ አማራ ህዝብ ድርጅት (መአኅድ) ሲሆን ነሐሴ 5 ቀን 1994 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ ወደ አገር አቀፍ ፓርቲነት በመለወጥ መኢአድ በሚል ስያሜ እንደሚንቀሳቀስ ይፋ አደረገ፡፡ ይሄኔ በአባላቱ መካከል ክፍፍል ተፈጠረ፡፡ መኢአድ ሆኖ ከተዋቀረ በኋላ በልዩነት ከፓርቲው የወጡ ሰዎችም ኢዴአፓን አቋቋሙ፡፡  ኢዴአፓ፤ከኢዲዩ፣ ከኢዳግ እና ከመድህን ጋር ውህደት ፈፅሟል፡፡ መስከረም 20 ቀን 1997 ዓ.ም ኢዴአፓ (ከመኢአድ የወጣ) እና መድህን መዋሀዳቸውንና  በግንቦት ወር የሚከናወነው ምርጫ፤ ነፃና ሚዛናዊ እንዲሆን  በመንግስት በኩል መሟላት ያለባቸው ጥያቄዎች ቢኖሩም በምርጫው እንደሚሳተፉ ገለፁ፡፡
ውህደታቸውን ተከትሎም ዶክተር አድማሱ ገበየሁ ፕሬዚደንት፣ ዶክተር ኃይሉ አርአያና ዶክተር ጎሹ ወልዴ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም አቶ ልደቱ አያሌው ዋና ፀሀፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በዛው ሰሞን ኢዴአፓ፣መድህንና መኢአድ ለመዋሃድ ያደረጉት ሙከራ ጫፍ ላይ ከደረሰ በኋላ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ጥቅምት 1997 ዓ.ም ኢዴአፓ መድህን፣ መኢአድ ኢድሊ እና ቀስተ ደመና ቅንጅትን መስርተው ኢህአዴግን በግንቦቱ ምርጫ በብርቱ ለመፎካከር መዘጋጀታቸውን አስታወቁ፡፡ ህዳር 9 ቀን 1997 ዓ.ም አራቱ ፓርቲዎች በምርጫው ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በሚል ስያሜ ለመወዳደር መወሰናቸውን በፊርማቸው አረጋገጡ፡፡ በምርጫው ቢሸነፉ እንኳን ተዋህደው አንድ ፓርቲ የመሆን የረጅም ጊዜ እቅድ እንዳላቸውም አስታወቁ፡፡ ቅንጅቱ አልፎ አልፎ ከሚሰሙ ልዩነቶች ውጪ ብዙዎችን ከጎኑ በማሰለፍ እና  ደጋፊዎችን በማሰባሰብ፣ ኢህአዴግን የሚገዳደር ጠንካራ ፓርቲ ሆነ፡፡ ምርጫው ግንቦት ተካሂዶ ሰኔ ላይ የልዩነት ወሬዎች በስፋት መውጣት ጀመሩ፡፡ በዚያው ወር መኢአድ በውስጣዊ ችግር መተብተቡ የተነገረ ሲሆን ድርጅቱን ከመፍረስ ለመታደግ ኮሚቴ አቋቁሞ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ የቅንጅቱ ክፍፍል እየተብላላ ቆይቶ ጥቅምት ላይ ከኢዴአፓ መድህን አቶ ልደቱ አያሌውንና አቶ ሙሼ ሰሙን አገደ፡፡
የቅንጅት አመራሮች ከታሰሩ በኋላ የተወሰኑ  ፓርላማውን የተቀላቀሉ የቅንጅቱ ተመራጮች  ኢዴፓ፣ የፓርላማ ቡድን፣ መኢአድ  እና ቅንጅት በሚል ተከፋፍለው መቀመጫቸውን ያዙ፡፡ ምርጫ 2002 ዓ.ም ሲቃረብም ምርጫን ዓላማ ያደረጉ የትብብር ስምምነቶች፣ ግንባር እና መድረክ መፍጠር እንዲሁም መቀናጀት ይፋ ተደረጉ፡፡ ህዳር 25 ቀን 2002 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት በግንባር ደረጃ ተቀናጅተው እንደሚንቀሳቀሱ ገለፁ፡፡ የካቲት 21 ቀን 2002 ዓ.ም በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ አምስት የኦሮሞ ድርጅቶች- የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር፣ የኦሮሞ አንድነት ነፃነት ግንባር፣ የገዳ ስርአት አራማጅ ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ነፃነት ብሄራዊ ፓርቲ እና የመላው ኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ለቀጣዩ ምርጫ በቅንጅት ለመንቀሳቀስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ፡፡
አንድነት ከተቋቋመ በኋላም በታህሳስ 2001 ዓ.ም “መርህ ይከበር” የሚል መሪ ቃል ያነገቡ ወገኖች ከፓርቲው ወጥተው ሰማያዊ ፓርቲን አቋቋሙ፡፡ በሰኔ 2000 ዓ.ም መድረክን ለማቋቋም መምከር ተጀመረ፡፡ የካቲት 2001 ዓ.ም ደግሞ የስድስት ፓርቲዎች ጥምረት ተመሰረተ፡፡ መስከረም 24 ቀን 2003 ወደ ግንባር ተሸጋገረ፡፡ በያዝነው ዓመት አንድነት ከመድረክ የታገደ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ  ከመኢአድ ጋር ውህደት ለመፈፀም በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡
“ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ፓርቲዎች የተጓዙበት መንገድ ሲገመገም፣ ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ ተጨባጭ ውጤት አላመጣም፡፡ ንቅናቄያቸውም በየጊዜው እየቀጨጨ የሚሄድ ሲሆን  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ አብሮ ለመስራት ያላቸው ተነሣሽነትና ፍላጐት የተዳከመ ብሎም ተስፋ የሚያስቆርጥ ደረጃ ላይ የደረሰ ነው” ይላሉ - የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መኃሪ፡፡
ባለፉት 23 አመታት በሀገሪቱ ያሉ ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሲቀናጁ፣ ሲጣመሩ፣ ሲዋሃዱ  ሲፈርሱ ነው የኖሩት፡፡ አቶ አበባው እንደሚሉት፤ለዚህ ምክንያቱ ከሃገራዊነት ስሜት ይልቅ የግለሰቦች ስሜትና ፍላጐት አይሎ መውጣቱ ነው፡፡ “የተሞከሩት ቅንጅቶች እና ጥምረቶች በሙሉ ሴራ ያልተለያቸው፤ የግለሰቦችን ፍላጐት ብቻ ጠብቀው የተፈጠሩ በመሆኑ በትንሽ ተንኮል ይፈርሳሉ፡፡ ዛሬ  ይህ ተንኮል ይበልጥ መልኩን ቀይሮ ተባብሮ ለመስራት ሳይሆን አንዱ ሌላውን ፓርቲ ለመውረስ ነው የሚጥረው” ብለዋል - አቶ አበባው። በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ከፍተኛ የፖለቲካ መነቃቃት የፈጠረው ቅንጅት፤ የፈረሰበት ምክንያትም በዚህ መሰሉ ሴራ ነው ይላሉ - ቅንጅቱ ፓርቲዎች ሠምና ወርቅ ሣይሆን ውሃና ዘይት ሆነው የተቀናጁበት መሆኑን በመጠቆም፡፡
በፕሬዚዳንትነት የሚመሩት መኢአድ የስበት ማዕከል ሆኖ መቆየቱን የጠቀሱት አቶ አበባው፤ፓርቲው ከሌሎች ጋር ለመጣመርና ለመዋሃድ ያደረጋቸው ሙከራዎች ያልሰመሩት ፓርቲዎች ወደ መኢአድ ሲመጡ በቅንነት ሳይሆን ህልውናውን በሚፈታተን መልኩ ስለሆነ ነው ይላሉ፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ሠላማዊ ትግሉ በእነዚህ ምክንያቶች ውጤት አልባ ሆኖ ቆይቷል የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ለውጤት አልባነቱ ኢህአዴግም የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል ሲሉ ይወቅሣሉ፡፡ “የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆነ ገበሬ፣ መሬት እና የግብርና ግብአቶች እንዳያገኝ፣ የመንግስት ሠራተኛ ከሆነ ከስራው እንዲፈናቀል፣ እርዳታ ፈላጊ እርዳታ እንዳያገኝ እየተደረገ፣ ሰዎች በነፃነት መብታቸውን እንዳያስከብሩና በፈለጉት የፖለቲካ ፓርቲ ጥላ ስር እንዳይሰባሰቡ ከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና ፈጥሯል” ሲሉ ይኮንናሉ፡፡ ኢህአዴግ  ባለፉት 23 አመታት በትጋት ተቃዋሚዎችን ለማቀጨጭና ከተቻለውም ለማጥፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሲሠራ፤ ህብረቶችንና ቅንጅቶችን በሴራ ሲያፈርስ ነው የኖረው ሲሉም አምርረው ይወቅሳሉ፡፡
“ለዲሞክራሲ ምቹ የሆንን ሰዎች አይደለንም” የሚሉት አቶ አበባው፤ ከጥቂት አመታት በፊት በጦርነት ሲታመሱ የነበሩ እንደ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን የመሳሰሉ ሃገሮች እንኳ ከኢትዮጵያ በተሻለ ሁኔታ ዲሞክራሲን እየተገበሩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ ተቃዋሚ ሆኖ ለዲሞክራሲ የሚደረግ ትግል ውስጥ ውጤት ለማምጣት ብዙ ሂደቶችን ማለፍ እንደሚጠበቅ ገልፀው፤ በዚህ ረገድ የሚፈለገውን ያህል ተስፋ የሚሠጥ ባይሆንም ህዝቡን በማነቃቃት ረገድ ተቃዋሚዎች የነበራቸው ሚና የሚዘነጋ አለመሆኑን አቶ አበባው አመልክተዋል፡፡
ቀደም ሲል የመኢአድ አባል በመሆን በፓርቲው ውስጥ ሲሠሩ ከቆዩ በኋላ በተፈጠሩ አለመግባባቶች አዲስ ፓርቲ ወደማቋቋም ከተሸጋገሩት አቶ ልደቱ አያሌውና ሌሎች ግለሰቦች ጋር በመሆን የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን (ኢዴፓ) የመሠረቱት አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው፤ ባለፉት 23 አመታት በመቀናጀት፣ ግንባርና ጥምረት በመፍጠር ረገድ ውጤት ያመጣና አላማውን ያሳካ ፓርቲ አላየሁም ሲሉ የአቶ አበባውን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ በትንሹ ሊጠቀስ የሚችለው 1997 ላይ የተፈጠረው ቅንጅት ብቻ ነው የሚሉት አቶ ሙሼ፤ እሱም ቢሆን ጠንካራ ስላልነበረ ሙሉ ለሙሉ ውጤታማ መሆን እንዳልቻለ ይገልፃሉ፡፡ በዋናነትም የፓርቲዎች ጋብቻ ውጤታማ የማይሆነው ጥምረታቸው ከፕሮግራም፣ ከአላማ እና ከግብ አንድነት በሚመነጭ ሳይሆን ኢህአዴግን ተሰባስቦ ለማሸነፍ ካለ ፍላጐት ወቅታዊ ጉዳይን ብቻ መነሻ አድርጐ የሚፈጠር በመሆኑ ነው የሚሉት አቶ ሙሼ፤ ምርጫ ሲደርስ ብቻ ፓርቲዎች ለመቀናጀትና ለመጣመር መሯሯጣቸውም ይህን ያመለከታል፣ ምርጫን ብቻ ግብ ያደረጉ ጥምረቶች  ደግሞ ከምርጫው በኋላ ዋጋ አይኖራቸውም ብለዋል፡፡
“የውህደት ጥምረት እና ቅንጅት ምስረታ ውጥኖች ከሚከሽፉባቸው ምክንያቶች መካከልም ፓርቲዎች አንድነቱን ከመፈለግ ባሻገር ማን አመራር ይሁን በሚለውና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ በቂ የስነ ልቦና ዝግጅት አለማድረጋቸው እና አርቆ አለማሰባቸው ዋናው ነው” ይላሉ አቶ ሙሼ፡፡
ፓርቲያቸው ኢዴፓ ከተመሰረተ ጀምሮ ከሶስት ፓርቲዎች ጋር ስኬታማ ውህደት መፍጠሩን አቶ ሙሼ ይጠቅሳሉ፡፡ ከኢዳግ፣ ኢዲዩ እና ከመድህን ጋር ጥሩ ምሳሌ ሊሆን የሚችል ውጤታማ ውህደት መፈጠሩን ያስታወሱት አቶ ሙሼ፤ ከመኢአድ ጋርም በ1996 መጨረሻ አካባቢ ለመዋኃድ የተደረገው የድርድር ሂደት 90 በመቶ ከደረሰ በኋላ መክሸፉን ከፓርቲያቸው ያልተሳኩ ተሞክሮዎች አንዱ ነበር ይላሉ፡፡ በወቅቱ መኢአድ እና ኢዴፓ በበርካታ ጉዳዮች ላይ የተስማሙ ቢሆንም በስራ አስፈፃሚ ውስጥ ትልቁ ድርሻ የማን ነው? የሚለውን መሰረታዊ ጉዳይ ጨምሮ ምን አይነት የመንግስት አወቃቀር ሊኖር ይገባል፣በመሬትና በቋንቋ ጉዳይ ላይ እንዲሁም በፓርቲው ስያሜ ልዩነት ተፈጥሮ እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ መኢአድ በወቅቱ የመንግስት ስርአቱ ፕሬዚዳንታዊ ይሁን ሲል ኢዴፓ የለም ፓርላሜንታዊ ይሁን በማለቱ የተፈጠሩ የፕሮግራም ልዩነቶችን መነሻ አድርጎ እስከ መዘላለፍና መወነጃጀል የደረሱ አለመግባባቶች መፈጠራቸውንም አቶ ሙሼ ያስታውሳሉ፡፡ ፓርቲያቸው ከቅንጅት ጋር የፈጠረው ጥምረትም በአላማ እና በአካሄድ ልዩነት መክሸፉን አመልክተው፣ ፓርቲው ካደረጋቸው ውጤታማ ውህደቶች መካከልም ከኢዲዩ ጋር የነበረውን ይጠቅሳሉ። በአንዳንድ ግለሰቦች ምክንያት እክል አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም  መፍትሄ አግኝቶ አብሮ መጓዝ እንደተቻለ ያስታውሳሉ፡፡
የእስከ ዛሬው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉዞ ጠቅለል ብሎ ሲገመገም፣ ህዝብን ተስፋ ያስቆረጠ ነበር ያሉት አቶ ሙሼ፤ ከዚህ በኋላም ቢሆን አንድ ላይ ለመስራት ከፍላጎት ባሻገር የስነልቦና ዝግጅት ሳይደረግ የሚፈጠሩ ውህደቶች እና ጥምረቶች ከሚፈለገው ውጤት ላይ መድረስ አይችሉም ይላሉ፡፡ “የተጠናቀረ ፓርቲ መፍጠር ቀላል አይደለም” የሚሉት አቶ ሙሼ፤ 23 ዓመት ኢህአዴግን የሚገዳደር ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር የሚያስችል በቂ ጊዜ ነበር ለማለት አያስደፍርም ብለዋል፡፡ “ማህበረሰቡ ምርጫ ያስፈልጋል ብሎ እንዲያስብ፣ ገዥው ፓርቲ ልጓም አልባ እንዳይሆን በማድረግ በኩል ተቃዋሚዎች የማይናቅ ድርሻ ነበራቸው” ይላሉ አቶ ሙሼ፡፡
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በሃገሪቱ ለተስተዋለው ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ቀውስ በስልጣን ላይ ካለው ኢህአዴግ በበለጠ ተቃዋሚዎች ተጠያቂዎች ናቸው የሚሉት ደግሞ የአንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ናቸው፡፡ ህብረት፣ ቅንጅት፣ አማራጭ ኃይሎች፣ መድረክ እየተባለ እስከዛሬ ቢዘለቅም ያስገኘው ውጤት ሲገመገም በዜሮ የሚጣፋ ነው የሚሉት ሊቀመንበሩ፤የፓርቲ አመራሮች ከአመት አመት ከስህተታችን ሳንማር የኢትዮጵያን ህዝብ በድለነዋል፤ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ጉጉቱንም አጨልመንበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለኢህአዴግ ጠንካራ መሆን የተቃዋሚዎች ድክመት አስተዋፅኦ ማበርከቱን በአፅንኦት የሚገልፁት ኢ/ሩ፤ ውጤት አልባው ሂደት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቁ አሳዛኝ ታሪክ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“በሀገራችን የፓርቲ ፖለቲካ ብዙ ዘመን አስቆጥሯል ማለት ባይቻልም በአሁኑ ጊዜ ፓርቲዎች ማደግ ሲገባቸው እየቀጨጩ ነው፣ በሜዳው ላይ መኖር የማይገባቸው ፓርቲዎችም አሉ፡፡ ፕሮግራማቸው አንድ ሆኖ እንኳ ተከፍለው መንቀሳቀሳቸው ትክክለኛ አካሄድ ካለመሆኑ በተጨማሪ ለገዥው ፓርቲም የስልጣን እድሜን እየሰጠ ነው ያሉት ከዚህ ቀደም በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራረርነት ቆይተው አሁን ላይ ከፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸው ያገለሉት ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም ናቸው፡፡
እንደ አስተያየት ሰጪው ከሆነ የፓርቲዎች ስኬትና ውድቀት የሚያጋጥም ከመሆኑም በላይ በሀገራችን ጠንካራና አስተማማኝ ተቀናቃኝ ፓርቲ ለመፍጠር ጊዜው አልረፈደም፡፡ ከዚህ በፊት የተደረጉ የጥምረት፣ ህብረት፣ ቅንጅት--- ሙከራዎች ፍፃሜ አልሠምር ካለባቸው ምክንያቶች አንዱ የፓርቲ ስልጣን ጥመኝት ነው ያሉት ዶ/ር ያዕቆብ፤“ጥመኝነቱ ምናልባትም ብሔራዊ ፀባያችን ሳይሆን አይቀርም” ብለዋል፡፡ እንደተቀሩት አስተያየት ሠጪዎችም ባለፉት 23 አመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላለመጠናከራቸው ኢህአዴግን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ጠንካራ ከነበረው ቅንጅት መፍረስ ጀምሮ አሁን ድረስ የሚደረጉ ተመሳሳይ ሙከራዎች ስኬት አልባ ለመሆናቸውም የገዥው ፓርቲ ረጅም እጅ አለበት ሲሉ ዶ/ር ያዕቆብ ይወቅሳሉ የፓርቲ አመራሮችን በቅንጅት ጊዜም ሆነ ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዜያት ለእስራት መዳረጉን በዋቢነት በመጥቀስ፡፡
ከኦነግ ታጋይነት እስከ ኢህአዴግ ከዚያም የአገሪቱ ፕሬዚዳንትነት በመጨረሻም የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው፤የፓርቲዎቹ የውህደት እና ጥምረት ስኬታማ ባይሆኑም የተገኘው ልምድ የማይናቅ ነው ይላሉ፡፡ ለፓርቲዎች ጥምረት ውጤት አልባነት ዶ/ር ነጋሶ በምክንያትነት ከጠቀሷቸው መካከል በፓርቲዎች መካከል የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ፉክክሮች፣ የስልጣን ጥመኝነት፣ የአላማ እና የአደረጃጀት ግልጽ አለመሆን፣ ህዝቡ ከዳር ሆኖ ከመተቸት ባለፈ በየአደረጃጀቱ ገብቶ ተጽዕኖ ለመፍጠር አለመቻሉ እንዲሁም በፓርቲዎች ላይ ተጽእኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ ህዝባዊ አደረጃጀቶች አለመኖራቸው ይገኙበታል፡፡
የእስከዛሬ የፓርቲዎች የቅንጅት፣ ጥምረት እና ውህደት ውጤት አልባ ናቸው የሚለውን ሃሳብ የሚጋሩት ዶ/ር ነጋሶ፤በግንባር ደረጃ ከተሄደ ግን እስከ ዛሬ ሁለት የግንባር አደረጃጀቶች መኖራቸውን ያስቀምጣሉ። አንደኛው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሲሆን ሌላኛው “መድረክ” ነው፡፡ የመድረክን ውጤታማነት በተመለከተ በሂደት የምናየው ይሆናል ብለዋል ፤ዶ/ር ነጋሶ፡፡
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳንና የቀድሞውን የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስየ አብርሀን  በማካተት የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከተፈቱ በኋላ የተወሰኑት አመራሮች አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚል ፓርቲ አቋቋሙ። ምርጫ 2002 መቃረቡን ተከትሎ አንድነት ፣ ኦፌዴን ፣ ኦብኮ፣ አረና ተሰባስበው መድረክን አቋቋሙ፡፡
maleda times | March 22, 2014 at 9:27 am | URL: http://wp.me/p2gxmh-498
Comment   See all comments

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ከአውሮፓ ህብረት የ13ሚ. ብር ድጋፍ አገኙ


ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ  ከአውሮፓ ህብረት የ13ሚ. ብር ድጋፍ አገኙ
ያሬድ ዘለቀ Lamb ለሚለው ፊልሙ 12ሚ. ብር አግኝቷል
የኃይሌ ገሪማ “የጡት ልጅ” ቀረፃ  በሰኔ ወር ይጀመራል
የሁለቱም ፊልሞች ቀረፃ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው 
ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የፊልም ፕሮዱዩሰርና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ፤ “የጡት ልጅ” በሚል ርዕስ ለሚሰሩት አዲሱ ፊልማቸው የሚውል የ500 ሺህ ዩሮ (13ሚ. ብር ገደማ)  ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት አፍሪካን ካረቢያን ፓሲፊክ ፈንድ ያገኙ ሲሆን በፈረንሳይ የሚኖረው የፊልም ባለሙያ ያሬድ ዘለቀም Lamb ለሚለው ፊልሙ  መሥሪያ የ495 ዩሮ (12ሚ. ብር ገደማ) ድጋፍ አግኝቷል፡፡
ሳንኮፋ፣ አድዋ እና ጤዛ በተሰኙት ፊልሞቻቸው በአለማቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደናቂነትን የተጎናፀፉትና በርካታ ሽልማቶችን የወሰዱት ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ፤ በቀደምት ኢትዮጵያውያን አኗኗር ላይ የሚያተኩረውን “የጡት ልጅ” የተሰኘ አዲስ ፊቸር ፊልማቸውን ለመስራት የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ ድጋፍ የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓስፊክ ሀገራትን የፊልም ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ከምደባው ገንዘብ ማግኘታቸውን የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ደልጌሽን የፕሬስና ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር አቶ ሰለሞን ከበደ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡
በለጋ ዕድሜዋ በፊውዳል ባላባቶች ቤት በባርነት ማገልገል በጀመረች አንዲት ልጃገረድ ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥነውና ቀረጻው በመጪው ሰኔ ወር  በባህር ዳር እና በጎንደር ከተሞች የሚጀመረውን ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ፣አንድ ዓመት ከስምንት ወር  እንደሚፈጅ ታውቋል፡፡
ተቀማጭነቱን በጀርመን ያደረገውና “ፊልም ፎርም ኮሎኝ ጂኤምቢኤች” የተባለው የፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ የፊልም ኩባንያ፤ ከአውሮፓ ህብረት ያገኘውን የ500 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ከሚገኘው “ነጎድጓድ” የተሰኘ የፊልም ድርጅትና ከሃይቲው ቬልቬት ፊልም ግሩፕ ጋር በአጋርነት ለሚሰራው ለዚህ የፊልም ፕሮጀክት እንደሚያውለው ተጠቁሟል፡፡
ከአቶ ሰለሞን ከበደ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው፤ ይሄን ፊልም  በማዘጋጀት፣ በመቅረጽና በማከፋፈል ሥራ ላይ  ለሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና የፊልም ባለሙያዎች ስልጠና የሚያገኙበት አውደጥናቶች ይዘጋጃሉ፡፡
በፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ከሚሰራው “የጡት ልጅ” በተጨማሪ፣ የዘንድሮውን የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ያገኘው ሌላው ኢትዮጵያዊ የፊልም ዳይሬክተር ነዋሪነቱን በፈረንሳይ ያደረገው ያሬድ ዘለቀ ሲሆን “ላምብ” በሚል ርዕስ ለሚሰራው ፊቸር ፊልሙ የ495 ሺህ ዩሮ (12ሚ. ብር ገደማ) ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡
ተቀማጭነቱን በፈረንሳይ ያደረገው የያሬድ “ግሎሪያ ፊልምስ ፕሮዳክሽን”፤ ከኢትዮጵያው “ስለም ኪድ ፊልምስ” እና ከአይቮሪ ኮስቱ “ዋሳካራ ፕሮዳክሽንስ” ጋር በአጋርነት የሚሰራ ሲሆን  ለዚህ የፊቸር ፊልም ፕሮጀክት፣ የ495 ሺህ ዩሮ ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡
እናቱን በልጅነቱ በሞት ከተነጠቀ በኋላ፣ ከአንዲት የበግ ግልገል ጋር ጥብቅ ወዳጅነት በፈጠረ አንድ ኢትዮጵያዊ ብላቴና ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥነው “ላምብ” ፊልም፤በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ ሲሆን  ቀረጻው ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡
አጠቃላይ ስራው ከኢትዮጵያና ከአይቬሪኮስት በተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን በሚመራው በዚህ ፊልም ላይ የሚሳተፉት ኢትዮጵያውያን ተዋንያን ሲሆኑ የገንዘብ ድጋፉ የተደረገውም የኢትዮጵያን የፊልም ኢንዱስትሪ ለማጠናከርና በዘርፉ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ክህሎት ለማሳደግ በሚል እሳቤ መሆኑን ከአውሮፓ ህብረት የኤትዮጵያ ደልጌሽነ የፕሬስና ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ከተለያዩ የአፍሪካ የካሪቢያንና የፓስፊክ አገራት ከሚገኙ አመልካቾች የሚቀርብለትን ፊልምና የተለያዩ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል በመገምገም፣ ለተመረጡ ፕሮጀክቶች በየአመቱ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርገው የአውሮፓ ህብረት፤ ዘንድሮም በተለያዩ ምድቦችና ዘርፎች ለመረጣቸው 37 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በመጀመሪያው ምድብ “የጡት ልጅ” እና “ላምብ’ን ጨምሮ ለዘጠኝ የተለያዩ የአፍሪካና የካረቢያን አገራት ፊቸር ፊልሞች እንዲሁም በሞዛምቢክ ለሚሰራ “ፍሮም ዎር ኤንድ ፒስ” የተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪዥን ዶክመንታሪ ፊልም የገንዘብ ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡
በዚሁ ምድብ ውስጥ ለተካተቱ ስምንት የተለያዩ አገራት የሲኒማና ኦዲዮ ቪዥዋል፣ የኔትወርኪንግና የፌስቲቫል ዘርፍ ፕሮጀክቶች፤ የማከፋፈልና የፕሮሞሽን ስራ ለማከናወን የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ተበርክቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በባለሙያዎች ስልጠናና በሙያ ክህሎት ግንባታ መስክ ከቤልጂየም፣ ከኡጋንዳ፣ ከጣሊያን፣ ከታንዛኒያና ከፈረንሳይ ለቀረቡ አምስት የሲኒማና ኦዲዮ ቪዥዋል ዘርፍ ፕሮጀክቶች ጠቀም ያለ ገንዘብ ተሰጥቷል፡፡
በሁለተኛው ምድብ በክዋኔ ጥበባት፣ በፌስቲቫል ዝግጅት፣ በኔትወርኪንግ፣ በባህል አስተዳደርና በቅርስ ጥበቃ ዘርፎች ለቀረቡ ስድስት ፕሮጀክቶች የማከፋፈልና የፕሮሞሽን ወጪ የሚውል ገንዘብ የተሰጠ ሲሆን፣ በክዋኔ ጥበባት፣ በባህል ልማት፣ በሙዚቃ ኢንዱስትሪና በቅርስ ጥበቃ ዘርፎች ለቀረቡ ሰባት ፕሮጀክቶችም የስልጠናና የሙያ ክህሎት ግንባታ ገንዘብ ተለግሷቸዋል፡፡ በፓሲፊክ አገራት የባህል እድገት ለመፍጠር ለተቀረፀ አንድ ፕሮጀክትም የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
maleda times | March 20, 2014 at 7:01 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-47y
Comment   See all comments

Friday, March 21, 2014

መኢአድ የቅድመ ውህደት ፊርማውን አደናቀፈ



                          አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)                                                     
  UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የሕዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ  ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
 
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የሕዝብ ፍላጎትና  አንገብጋቢ የሆነውን ተቃዋሚዎች ‹‹ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ›› ጥያቄ   ለመመለስ በስትራቴጂና አምስት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የውህደት ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሰሞን ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂክ ግብ ነው፡፡ የዚሁ አካል የሆነ እንቅስቃሴ በመኢአድና አንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም  ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባላት በእጅጉ እያሳዘነ ነው፡፡

በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)    መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓም የተፃፈልንን  ደብዳቤ መሠረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀውን ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ  ተቀብለነዋል፡፡ በዚሁ መሠረት      መጋቢት 4 ቀን 2ዐዐ6 ዓም  በሰጠነው የደብዳቤ መልስ ላይ እንደገለጽነው  በአንድነት ፓርቲ እይታ አመራሩ  የፊት ለፊት ውይይት የምንፈልገውና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ  መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተጠራውና የሁለቱ ፓርቲዎች የብ/ም/ቤት አባላትና የላዕላይ ም/ቤት አባላት በተገኙበት ለታሪክ በተቀረፀ ወሳኝ ስብሰባ ሠፊ የኃሳብ ልውውጦች ተካሂደው የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉትን አስገዳጅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡
በዚሁም መሠረት፡-
  1. የሁለቱም ፓርቲዎች አባላት አላስፈላጊ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት ውህደቱን አታጓቱ ውህደት የማትፈፅሙ ከሆነ እኛ አባላት በራሳችን ውህደት እንፈፅማለን የሚል ጥብቅ ተማፅኖና ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡
  2. በአጠቃላይ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዚደንቶችና አደራዳሪ ሽማግሌዎች በገቡት ቃል መሠረት ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቅድመ ውህደት የመግባቢያ ሰነድ እንዲፈረም ከስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡
  3. የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የውህደት አስፈፃሚውን ጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑትን የስም ዝርዝር፣ የፊርማው ስነ ሥርዓት በሚከናወንበት እለት እንዲያመጡ ተስማምተን ነበር፡፡
በከፍተኛ አመራሮችና በሁለቱ ሥራ አስፈፃሚዎች ውሳኔ መሠረት የሁለቱ ፓርቲ ፕሬዝደንቶች ተስማምተው፣ የቅድመ ውህደት መግባቢያ ሰነድ በሁለቱ ፓርቲዎች የድርድር ኮሚቴ አባላት መካከል ተፈራርመን፤ ሆቴል ተከራይተንና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል  የዕውቅና  ሠነድ አግኝተን  የመጨረሻ የስነ-ስርዓቱን መርሃ-ግብር በመጠባበቅ ላይ እያለን  በድንገት በመኢአድ ፕሬዝደንት  በኩል  በቁጥር መ/ኢ/አ/ድ 278/06 መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም በእለቱ የቅድመ ውህደት ፊርማውን መፈረም እንዳማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓርቲያችን  መድረሱ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡  ከደብዳቤው እንደተረዳነው  መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲዎቹ ከፍተኛ  አመራሮች ከበርካታ የሃሳብ ልውውጥ በኋላ የደረሱበትን ውሳኔ  የሚቀለብስ፣ የሁለቱ ፓርቲዎች ተደራዳሪዎች እየተስማሙ በቃለ ጉባኤ ያፀደቁትንና ከሁሉም በላይ የሁለቱ ፓርቲ  ተደራዳሪዎች ለቅድመ ውህደት ባዘጋጁትና ባፀደቁት የመግባቢያ ሰነዶች ላይ የሰፈሩ ነጥቦችን እንደ አዲስ  በማንሳትና በጥቃቅን ጉዳዮች በመጠመድ የቅድመ ውህደቱ እንዳይፈረም ተደርጓል፡፡ ለዚህ ታሪካዊና የሕዝብ ጥያቄ መደናቀፍ  ምክንያቱ የመኢአድ ፕሬዚንት ሲሆኑ  ይህን ሁኔታ   በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ  ለሁለቱ ፓርቲዎች አባላት፣  ደጋፊዎች፣ በግል ተነሳሽነትና በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ሁለቱን ፓርቲዎች ለማደራደር ሲደክሙ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ለሕዝቡ ጥሩ ዜና ባይሆንም ላለመፈረሙ   ኃላፊነቱን የሚወስዱት የመኢአድ አመራሮች በተለይም ፕሬዝደቱ  መሆናቸውን  ማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ  ለውህደቱ መሳካት የመኢአድ አባላትና ከፊል አመራሩ  እያሳዩ ለሚገኘው ፍላጎትና ጥረት ፓርቲያችን መልካም አክብሮቱን መግለፅ ይወዳል፡፡

መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

maleda times | March 20, 2014 at 3:47 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-47o
Comment   See all comments

Sunday, March 16, 2014

በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን የጦር መኮንኖች መካከል ውጥረት ነግሷል::


ጄኔራል አበባውን ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት የመቀየር እቅድ ተይዟል::

ምንሊክ ሳልሳዊ :- ህገመንግስታዊ ጥያቄ ባነሱ ከጄኔራልነት እስከ ሻምበልነት ማእረግ ባላቸው የቀድሞው የኢሕዴን ታጋዮች እና የአሁን የብኣዴን የጦር መኮንኖች እና በሕወሃት ጄኔራሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥያቄዎችን ያማከለ እና ህገመንግስታዊ ስርኣትን ተከትሏል የተባለለት ጥያቄዎችን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት መከሰቱን የመከላከያ ምንጮቻችን ጠቁመዋል::
ባለፉት ሰሞናት የተደረጉት ስብሰባዎች በከፍተኛ አለመግባባት የተበተኑ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በስፋት የፓርቲ ስራዎች እንጂ ሃገራዊ ስራዎች እየተሰሩ አይደለም የሚሉ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱ ለህገመንግስቱ መከበር ተገኢ መሆን አለበት በአሁን ወቅት ለአንድ የፓርቲ አመራር እና ለፕሮፓጋንዳ ተገኢ ሆነናል የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን የእድገት የትምህርት እና የደምወዝ መብትን በተመለከተም ከፍተኛ ክርከር ቢደረግም ካለመግባባት መኮንኖቹ ጥርስ እንደተነካከሱ ወደየመጡበት ተበታትነዋል::
የሰራዊት አባላትን ለመቀነስ በተደረገው ጥናት መሰረት ለምን ሁለት ብሄር ላይ አተኮረ የሚሉ ጥያቄ እንዲሁም የስኮላርሺፕ አድሏዊነት በተመለከተ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአንድ ብሄር ለትምህርት ተመርጠው የሚላኩ መኮንኖች በዛው ሳይመለሱ ይቀሩና ነገሩ ይድበሰበሳል የሚሉ አስጨናቂ ጥያቄዎች ተከታትለው ቢነሱም ከመድረኩ መልስ ሳይሰጥባቸው ተድበስብሰው አልፈዋል::ከአንድ ብሄር ብቻ ተመርጠው ለትምሕርት አውሮፓና አሜሪካ ከሄዱት መኮንኖች 80 ከመቶ ያልተመለሱ ሲሆን ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ ሌላው ብሄር ስኮላሺፕ እንዳያገኝ ምክንያት እየተፈጠር በዚያው ስለምትከዱ ሃገር ውስጥ በቂ አካዳሚ ስላለ እዚህ እንድንማር ይደረጋል::ስኮላሺፕ የሚሰጣቸው ለማይመለሱ መኮንኖች ነው የሚሉ አቤቱታዎች ተሰምተዋል::
በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል የተነሳውን ፍጥጫ ተከትሎ ጄኔራል አበባውን ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ለማዘዋወር የታቀደ መሆኑን የገለጹት ምንጮሽች በአሁን ሰአት ጄኔራሉ እንደ ቁም እስረኛ አብዛኛው ጊዜያቸውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚያሳልፉ እና ወደ ቢሯቸው አልፎ አልፎ እንደሚገቡ ታውቋል::
የሳሞራ የኑስን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቀው ጄኔራል አበባው ጄኔራል ዮሃንስን ወደ ሳሞራ ሕወሓት በሹመት አቅርቦ ካመጣቸው በኋላ ይተለያየ ተጽእኖ እየተደረገባቸው ቢሆንም የብኣዴን ፓርቲ አመራሮች ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ ነው ቢባልም ምንም አይፈጥሩም የአሽከርነት ሚና ካልሆነ በስተቀር ሲሉ ምንጮሹ ገልጸዋል::የጄኔራል አበባው ስልጣን ማቆም እና ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት መቀየር በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንዳይኖር ሁኔታዎች እየተገመገሙ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት ወደ ውጪ ለእረፍት ለመሄድ ጥያቄ ያቀረቡት ጄኔራል አበባው በተለያየ ምክንያት ሲሰናከልባቸው የቆየ ሲሆን እሳቸውን እና መሰላቸውን ከሰራዊቱ በዘዴ እና በብልሃት ገፍቶ ለማስወጣት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ካሁን ቀደም ሜጄር ጄኔራል የነበሩት አባዱላ ገመዳ አቶ ተብለው ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ሲዘዋወሩ ሁለት ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች ደግሞ ወደ እስር ቤት መወርወራቸው አይዘነጋም::
maleda times | March 16, 2014 at 9:08 am | URL: http://wp.me/p2gxmh-41U
Comment   See all comments

Thursday, March 13, 2014

የኛዎቹ አንቲገኖች

የሠላማዊ ትግልን ምንነት እና ሁነት በጥልቀት ያጠኑ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ወደ ጥንታዊ ግሪክ ኪናዊ- ትውፊት እስከማመላከት ይዘልቃሉ፡፡ የአንቲገንን ተግባር በምሳሌነት በማጣቀስ፡፡ በዚያ ዘመን ግሪክ በእርስ በርስ ጦርነት ትታመስ ነበር፡፡ እንዲያም ሆኖ በወቅቱ ሀገረ-ግሪክን ይገዛ የነበረው ኤዲፐስ ንጉስ፣ በእርስ በርስ ጦርነቱ የሞተ ማንኛውም ሰው አስከሬን እንዳይቀበር የሚል ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ የንጉሡ ከውሃ የቀጠነ ሕግ ያልተዋጠላት አንቲገን ግን የመጣው ይምጣ ብላ ትዕዛዙን ጣሰች፡፡ በጦርነቱ ሕይታቸው ካለፈ ሁለት ወንድሞቿ የአንዱን (የፖሊንሰስን) አስከሬን ቀበረች፡፡ በዚህም የተነሳ ተጠያቂ ሆና ንጉሡ መንበር ፊት እንድትቀርብ ተደረገ፡፡ ንጉሡም ለወጉ ያህል ቃሉን (ሕጉን) የተላለፈችበትን ምክንያት እንድታስረዳና ለቀረበባትም ክስ መከላከያ ካላት እንድታቀርብ ጠየቃት፡፡ እናም የሚከተለውን መልስ ሰጠች፡- “… ታማኝነት ለእግዚአብሔር ሕግ እንጂ ለምድራዊው ንጉስ ለአንተ ሕግ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ሕግ ደግሞ የሞቱትን ወገኖች አስከሬን እንድንቀብር ያዛል፡፡ ስለዚህ መጠየቅ ያለብህ አንተ እንጂ እኔ አይደለሁም፤ የእግዚአብሔር ቃል የሚፃረር ሕግ ያወጣኸው አንተ ነህና፡፡…” አንቲገን ከላይ የሰጠችውን ምላሽ ብቻ ተናግራ አላበቃችም፡፡ እውነትን ተመርኩዛ ንጉሱን ባለማወላወል ተጋፈጠችው፡፡ “… ይልቅስ ከተማው በሙታን ክርፋት ተጥለቅልቆ ወረርሽኝ እንዳይከሰትና እንዳይስፋፋ ሙታኖች እንዲቀበሩ ትዕዛዝ ስጥ፡፡…” አለችው፡፡ በዚህ ቁርጠኛ ምላሿ በንዴት የጦፈው ኤዲፐስ ንጉስ ከቅጣት ሁሉ እጅግ የከፋውን የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈባት፡፡ ሳትሞት ከነሕይወቷ እንድትቀበር ወሰነ፡፡ “በማይሻር ንጉሣዊ ቃሉ” መሰረት አንቲገን በቁም ተቀበረች፡፡ እኛስ? አሁን፤ እኛም በኤዲፐስ ንጉስ ዘመን በጥንታዊቷ ግሪክ ውስጥ ያለን ይመስለኝ ይዟል፡፡ በግልፅ “ምንም ዓይነት የመብት ጥያቄ አትጠይቁ” የሚል አዋጅ አልወጣም እንጂ፤መንግስት ምንም ነገር ላለመስማት የወሰነበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ አሁን አሁን ሳስበው መንገድ ላይ እየሄድን ጨጓራችንን ቢያመን እና ብናቃስት፣ (ለነገሩ ምን ጨጓራ አለን? ተቃጥሎ አልቋል) “የማይፈለግ ድምፅ ማሰማት” በሚል በፖሊስ ተይዘን ዘብጥያ የምንወርድ ይመስለኝ ይዟል፡፡ ለዚህ አባባሌ ምክንያት አለኝ፡፡ ከቀናት በፊት በተደረገው የሴቶች ታላቁ ሩጫ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት “አላስፈላጊ ድምፅ በማሰማት” ወይም እየሮጡ የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው በፖሊስ ተይዘው እስርቤት መጣላቸውን ሰማሁ፡፡ አዘንኩ፡፡ እነዚህ ወጣት ሴቶች ለእኔ “አንቲገንን” ማለት ናቸው፡፡ የሚገርመው በዚህ ዘመን በግንባር ቀደምትነት የመብት ጥያቄን ከሚያነሱ ግንባር ቀደም ታጋዮች መሃል የሚበዙት እና ጎልተው የሚንቀሳቀሱት ሴቶች መሆናቸው ነው፡፡ ከእኛ ወንዶቹ በላይ ሴቶቹ “እምቢ ለመብቴ” ለማለት ቁርጠኞች መሆናቸውን ስንቶቻችን ልብ ብለን ይሆን?....(ይህንን ጉዳይ ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ) ሌላው ቀርቶ እዚህ ማህበራዊ ድረገፅ ላይ በሰከነ መንገድ በመወያየት ረገድ፤ በተለያየ መድረኮች ላይ በግንባር ቀደምትነና በቁርጠኝነት በመሳተፍ ሴቶች እህቶታቻችን ዓይነተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አለመናገር ንፉግነት ነው፡፡ …. የሆነ ሆኖ እየሮጡ መናገር፣ እየሮጡ መብትን መጠየቅ ሊያሳስር አይገባም ባይ ነኝ፡፡ ስለዚህ የ“እኛዎቹ አንቲገኖች” (ሴት ታጋዮች) ይፈቱ፡፡ የመብትን ጥያቄ ዜጎችን በተለይም ሴት እህቶችን እና እናቶችን በማሰር ማዳፈን አይቻልም፡፡ ክብር ለሴት ታጋዮች!! .
maleda times | March 12, 2014 at 7:41 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-3Y2

Sunday, February 23, 2014

ለ አብራሪው ( በ ይግዛው እያሱ)



ቢመረው ቢከፋው ግፍ አላይም ብሎ 
ጨርቄን ማቄን ሳይል ካገር ወጣ ጥሎ።
ለሙያው ሊታመን ምሎ ቢቀጠርም
ስራን በነጻነት ሊያገኘው አልቻለም።
የህዝብ ብሶት መከራ በሱ ተመስሎ
ላይመለስ ሸኘው ድምጽ አሰማ ብሎ።
ይህ የህዝብ ድምጽ ነው የአንድ አገር ዜጋ
በግፍ የሚገረፍ በወያኔ አለንጋ።
22 ዓመት ህዝብ ከህዝብ ከፋፍለው
አንዱን ባንዱ አዝምቶ አንገት የሚያስደፋው
የወያኔን መንግስት የግፍ አገዛዙን
ለዓለም ሊያሳውቅ ነው በመጥላት እራሱን።
በጣም በተሻለ መኖር እየቻለ
ለሆዱ ሳያድር ነጻነቴን ያለ
የቁርጥ ቀን ጀግና እንደ ሀይሌም የለ። (ሀይለመድህን)
የዓለም መንግስታት ይህን ይወቁልን
ለሀይለመድህን አበራ ጥሩ ፍርድ ይስጡልን።
ወያኔ እንደሚለው አሸባሪ አይደለም
ወያኔ እንደሚለው አገሩን አልከዳም
ወያኔን ግን ከድቷል ህዝብን አስቀድሞ
ራሱን ሻማ አርጎ የወገን ድምጽ ሆኖ።
ቢሞትም አይቆጭም ቢያስሩትም ይፈታል
ያጎነበሰን ህዝብ አንገት ቀና አድርጓል።
ለተበደለው ህዝብ ድምጹን አሰምቷል።
ሞት አዲስ አይደለም በኢትዮጵያ ምድር
ሁሉ ሚከፍለው ነው ለወያኔ ግብር።
የሱም ተራ ደርሶ ለእርድ ሳይዘጋጅ
በሰማይ እያለ እግዚአብሔር እረድቶት
እራሱ አመቻችቶ ዘዴ ፈጠረለት
ህዝብን አድን አለው ሂድና ጩህለት።
ቃሉን ተቀብሎ ለራስ ሳያዳላ
ጄኔቭ ገባ ሀይሌ ለመፈለግ መላ።
መላ ባንተ ይገኛል ድካምህ አይቀርም
የዓለም መንግስታት ይህን ዝም አይልም።
በቅርብ ታየዋለህ ካንተ ፍርድ ጀምሮ
የኢትዮጵያ አምላክ አይጥልህም ጥሎ።

maleda times | February 21, 2014 at 8:16 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-3DX

Monday, February 3, 2014

9.34 kilos of cocaine in stomach; tummy-ache leads police to 5


Nigerians caught with 441 cocaine capsules in transit lounge of Abu Dhabi AirportBy Mohammed El Sadafy
maleda times | February 3, 2014 at 9:10 am | URL: http://wp.me/p2gxmh-3kH


The give people arrested at Abu Dhabi Airport for drug trafficking and the capsules of cocaine found in the stomachs and intestines.
Five Nigerians have been arrested at Abu Dhabi International Airport during the past 12 days for trying to smuggle 441 capsules weighing a total of 9.34kg of cocaine in their stomachs.
Police said the five men were seen very tired and confused in the transit lounge of the airport.  One of them was suffering from stomach pain.
Colonel Dr Rashid Mohammad Bu Rasheed, Director of Criminal Investigation, said the arrested people had arrived in Abu Dhabi from Sao Paulo in Brazil and Lagos, Kano and Abuja in Nigeria. They tried to change their flight to mislead the police, he added.
He also said the drug traffickers intended to leave the pills in their stomach for more than 24 hours. Their lives could have been at risk even if just of the capsules burst inside their bodies, he added.
Comment   See all comments

በሀገራችን የሉዓላዊነት ጉዳይ እንኳን እሥራት ሞትም ይምጣ(ጌታቸው ዘብ-ጎ )


አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል እንደሚባለው አበዋዊ የአነጋገር ዘይቤ ሰሞኑን የሰላማዊ ፓርቲ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ያለው ሥርዓት ገዥ ኃይል(ህወሃት) የኢትዮጵያ ሀብት የሆነውን ለሙንና ውሃ ገቡን በአጭር ጊዜ ምርት አምርቶ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ችግር ሊቀርፍ የሚችለውን በርካታ የማሽላ አይነቶች፤ሰሊጥና ኑግ፤ጥጥና የሙጫ ዛፍ በብዛት የሚገኝበትን ለሀገር ውስጥ ፍጆታም ምሰሶ የሆነውን ሕዝብ እንደ መተንፈሻ ሳንባው የሚተማመነውንና እንደ ዐይኑ ብሌን የሚመለከተውን ሰፊውን የምዕራብ ኢትዮጵያ ክቡር ግዛት ለሱዳን ለመስጠት ከሕዝቡ በስተጀርባ በድብቅ ድንበር ማካለል ፊርማ በመፈራረሙ ምሥጢሩን ለህዝብ እናጋልጣለን በማለት የሰላማዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደናቀፍ በመስጋት ስከታተል ነበር። ትዕይንተ ሕዝቡን ለማካሄድ የሚደረገውን ቅስቀሳ በማዎክ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ላይ ይህ ነው የማይባል ወከባ እሥራት ተፈጸመ። ሕዝብ በዚህማ አትምጡብን አይቀሬ ነው ብሎ ከወጣ በኋላ መንገዶችን ከመስቀል አደባባይ ወደ አራዳ ፤ከመስቀል አደባባይ ወደ ብልኮ ፤ ከመስቀል አደባባይ ወደ ቼቸላ በትራፊክ በመዝጋት ሕዝብ ታግቶ እንደዋለ ከዘ-ሐበሻ ዘገባ ለመረዳት ችያለሁ። ዘ- ሐበሻ ትልቅ ታሪክ ሰርታለች ሁላችንም እናመስግናት። እናም ሰሞኑን ርቄ የምገኝ ብሆንም ከዚህ የተፈረደበት ሕዝብ አብራክ የተፈጠርኩ በመሆኔ ወላጆቼ ጥሬ ቆርጥመው አስከብረው ያቆዩዋትን ሀገሬን የበሉበትን መሶብ የሚደፉ ሰብአዊነትና ርህራሄ የበማይሰማቸው እምብርት የለሽ ሆዳሞች የተፈጸመው ተግባር እጅግ አሳዝኖኛል። በመሠረቱ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ የተደረገው በደሙና በጥንቱ አስከብሮት የኖረው መሬቱ ታሪካዊ ጠላት ለሆነችው ሱዳን በድብቅ ሊሰጥ በመሆኑ እንጅ ድንጋይ ለመወርወርና ጥይት ለመተኮስ ቢሆንማ መንገዱ ይህ አልነበረም። ያን ህወሃቶች ከዚህ አሳፋሪ ተግባራቸው የማይመለሱ ከሆነ ወደፊት የምናየው ይሆናል።
በህዝብ ላይ ለተፈጸመው ድርጊት ኃላፊነቱን የሚወስዱት እነማን እንደሆኑ ጠንቅቄ ስለማውቃቸው ጊዜውን ይጠብቅ በማለት የቀድሞ የደርግ ፖሊስ የነበሩ ደርግ ከወደቀ በኋላ አዲሶቹ ገዥዎቻችን ቦታውን ሲሸፍኑ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ ሆኖ ነበር። የኦሊሶችና የቤተሰቦቻቸው ሁኔታ ታይቶ በሕዝብ ላይ ግፍ ያልፈጸሙትን እየተገመገሙ እንዲመለሱ ሲደረግ ከክልል አንድ ሰው ጋር በመሆን የደርግ ፖሊስ የነበሩትን በጎንደር ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲመለሱና የድሮ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ካደረጉት አንዱ ስለነበርኩ ፖሊሶች ሕዝቡን መተባበር ሲገባቸው አግቶ ማዋልና የህዝቡ ስሜት እንዲታፈን ማድረግ ከትናንትናው አለመማር ይሆናል። እንኳን ይህ ውስጡ የነቀዘ ምስጥ እንደበላው አገዳ ባዶውን የቀረ ቅጥረኛ ገዥ ቡድን ማንም ቢሆን የህዝቡን ስሜት በኃይል አፍኖ በመያዝ የሥልጣን ዘመኑን ማራዘም አይችልም።!! «ለዚያውም ህወሃት ህወሃት እኮ እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም የተባለ ነው።»ከዚህ ላይ አንድ የሚያሳዝነኝ ነገር ቢኖር የጎንደር ሕዝብ ሩህሩ ፤ትዕግስተኛ ፤ አርቆ አሳቢ ፤ለጋስና ተካፍሎ የሚያድር ሕዝብ ነው። ለምሳሌ ዛሬ ተመልሰው መጥተው ሊሰፍሩ ኤርትራውያን ውጡ በተባለበት ወቅት ሁሉም ኤርትራዊ ታፍሶ ፖሊስ መምሪያ ግቢ ውስጥ ነበር። ጎንደሬዎች ኤርትራዊ ወገኖቻቸውን ወደ አዲሲቱ አገር ለመሸኘት የመጡት ድንጋይ ይዘው አልነበረም። እንጀራ በመሶብ፤ወጥ በትልቅ መገፈጅ፤ ጠላ በመንቀልና በገንቦ ተሸክመውና አሸክመው እያለቀሱ ነበር ኤርትራዊ ወገኖቻቸውንና አብሮ አደጎቻቸውን የሸኙዋቸው። ታሪክ ለመተረክ ፈልጌ ሳይሆን በአይኔ ያየሁትና በቦታውም ስለነበርኩ ነው። በአጋጣሚ አንድ የአክስቴ ልጅ የተባበሩት መንግሥታት ውስጥ የሚሰራ ሌረፍት መጥቶ እዛው ፖሊስ መምሪያ ፊት ለፊት አብረን ቆመን የተመለከትነው ሁኔታ ነበር።
አለመታደል ሆኖ የትኛውም ገዥ ኃይል ሲመጣ ለዚህች ታሪካዊ ክ/ሀገር የሚሾሙ ባለሥልጣናት ቀዳሚ ተግባራቸው ዘረፋ ነው። ክፍሌ ዳዲ ይጠቀሳል።መላኩ ተፈራ የጎንደር ተወላጅ ሆኖ የፈጀው የጎንደርን ወጣት ነው። የዛሬዎቹ የህወሃት ነጭ ለባሾችና እንባ ጠባቂዎችም ይህን ሕዝብ የሚመለከቱት በጠላትነት ፈርጀው ነው። በረከት ስሞኦን ( መበርኻቱ ገበረእግዚአብሔር) ወላጆቹ እነማን እንደሆኑ ቢታወቅም ተወልዶ ያደገው ጎንደር ነው። በረከት ግን «ጎንደሬዎች ወሬ እንጅ ሥራ አያውቁም » ብሎ መተቸቱን ከአንድ ለገዥው ቡድን ቅርብ የሆነ ሰው አጫውቶኛል። አቶ በረከት የትኛውን የሥራ እድል ፈጥሮ ነው ጎንደሬዎች ሥራ እንደማናውቅ የከሰሰን? ሥራ ለመያዝ የድርጅት አባል መሆን መመዘኛ ሆኖ በሚሰራበት እንዴት ብሎ?ለማን ሲባል ምን ለማትረፍ? ሰሞኑን የአማራ ክልል ካድሬዎችን ሰብስቦ ስለ አማራው ሥነ-አእምሮና አመለካከት ገለፃ ያደረገው አለምነው መኮንን የተናገረውን በኢሳት ቀርቦ ተደምጧል። ለማረጋገጥ እንደቻልኩት ሁሉም ሰምቶታል። ይህ አሳዛኝ ፍጡር የሰደበው ራሱን ሲሆን የሚገርመው ደግሞ የዚህ የሚንቀው ሕዝብ ክልል ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ ነው። አይ ! ነገን መርሳት ሆዳም! ይሏል ይህ ነው። የታደሰ ካሳ(ታደስ ጥንቅሹ)እና የሕላዊ ዮሴፍ፤ የተፈራ ዋልዋ ኮፒ እነሱ አዘውትረው የሚናገሩት ይህን ነበር። ታደስ አንድ ቀን እኔን ለማናደድ የአማራ ደም ቢመረመር ውጤቱ ትምክህትን እናገኛለን ነበር ያለው። እንግዲህ የአማራው ክልል እንደዚህ በመሰሉ ገፈፎች ነው የሚተዳደረው። በቅርቡ አንድ ከዚህ ጋር የሚያያዝ ሰፋ ያለ ጹሑፍ ለማቅረብ እየሰራሁ ስለሆነ ዛሬ የጎንደሩ ሰላማዊ ሰልፉ እንደ 1969ኙና በአባአምሃ ኢዮሱስ ወቅት የፈሰሰው ደም አይነት አለመፍሰሱ ተመስገን ለማለትና ስለተሰማኝ ሁኔታ ለመግለጽ ነው አመሰግናለሁ።
በቀጣይ እስከምንገናኝ በደህና ያሰንብተን።
የኢትዮጵያ ዳርድንበር ላለማስደፈር አንድ እንሁን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም በክብር ትኑር!!
maleda times | February 2, 2014 at 8:57 pm | URL: http://wp.me/p2gxmh-3kb
Comment   See all comments

Tuesday, January 28, 2014

ጌዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው? ቁጥር ሁለት


ማሳሰቢያ፦የእጅ  ጹህፍን  ይንን ሊንክ በመ ጫን  ያንብቡት:http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12324

ተስፋዬ ገብረአብ
ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን
አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ
ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመጀመሪያው ጽሁፍ ተከታይ
ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ።
ለዛሬ የማቀርበው መረጃ ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ሸፋን ከሚጠቀምበት የደራሲነት እና
የጋዜጠኘነት ስራ ባሻገር ለማመን በሚያዳግት ይሰራ የነበረውን የወንጀል ድርጊት ፍንትው አድርጎ
ያሳያል።
ከዚህ በታች አባሪ ተደርጎ የተያያዘው በእጅ የተጻፈ መረጃ፣በእጄ ላይ ካሉ መረጃዎች መሃከል
ትኩረቴን የሳበው ነው።እንደምትመለከቱት በራሱ በተስፋዬ ገብረአብ እጅ የተጻፈ ነው።ከሌሎች
መረጃዎች ለየት የሚያደርገው ደግሞ፣እንደሌሎች መረጃዎች በፎቶኮፒ እጄ ላይ የቀረ ሳይሆን፣
ዋናው (ኦርጅናል)መሆኑ ነው። ምክንያቱም በቀጥታ ወንጀል የተጻፈበት ሆኖ ስለታየኝ ነው።ከእጅ
ጽሁፉ ላይ እንደምትመለከቱት፣መኩሪያ መካሻ ከተባለ ግለሰብ ጋር ድብቅ(ህቡእ) ስራ ለመስራት
ጀምረው ነበር።እንደኔ ግምት የኤርትራ መንግስትን ጥቅም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስፈጽማል
ብለው ያሰቡትን ተልእኮ ለመፈጸም አሲረው ነበር፡፡እንደ መረጃው ከሆነ መኩሪያ መካሻ የተባለው
ግለሰብ ከፒያሳው ቦንብ ፍንዳታ በኋላ ፈርቶ ይሁን ሌላ ባይታወቅም፣ከተስፋዬ ጋር ያለውን
ግንኙነት አቋርጧል።የፒያሳው የቦንብ ፋንዳታ ብሎ የተገለጸው ደግሞ ሌላ ሳይሆን በ2002 እኤአ
በትግራይ ሆቴል ላይ የደረሰው ፍንዳታ ነው።
የእጅ ጽሁፉን ሙሉ ይዘትና ለአንባቢ ይመች ዘንድ የተየብኩትን ይመሳከር ዘንድ እንደሚከተለው
አቅርቤዋለሁ።
አሰሪ መሆንና በቀጥታ ከእሳቱ ጋር መጋፈጥ ልዩነት አላቸው መኩሪያ መካሻ የተባለው ሰው ጥሩ ጀምሮ
ነበረ።ፒያሳ ላይ ቦምብ ሲፈነዳ ከእኔ ጋራ ያለንን ግንኙነት አቁዋረጠ።በጣም ጉዋደኛየ ነበር ለስራው
ስል ሰዋሁት። ጉዋደኛን መሰዋቴ ትልቅ ነገር አይደለም።ህይወታቸውን የሰዉ፣ክቡር ዜጎች ያሉበት ሃገር
ሰው ነኘና። እዚህ ላይ በትክክል ማሰብ እችላለሁ።አስቃቂውን ስሜቴን ግን ለመግለጽ ያህል ነው።
ያሸማቅቁሃል ሲሳካልኝ በደስታ መጠጣት፣ሲከሽፍብኝ በንዴት መጠጣት፣ልምድ አደረግኩት።ደረጀ
ደስታ እራሱ ከገፋፋኝ በሁዋላ መልሶ በኢትኦጵያ የማምን ኢትዬጵያዊ ነኝ ሲለኝ ምን እንደሚሰማ ገምቱት።
ሚኒስትር የነበረው ደስታ ወልደማርያም ጋር ለዘላለሙ ተለያይቻለሁ።እነዚህ ሰዎች ለወያኔ ነግረው ምን
ያስፈጽሙብኝ ይሆን የሚል ስጋት አለብኝ።ያድዋን ወረዳ ያበላሸው ………… የደረሰበትን ታሪክ
እያሰብኩ መሰቃየቴን አልተውኩም።



ከብብቱ ፈልቅቄ ካስቀረዋቸው መረጃዎች ከዚህ በታች እንደምታዩት በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ላይ
የኢትዬ-ኤርትራ ጦርነት በሁዋላ እሱም እንዳለቆቹ እንዳቄመ ነው የምናየው።እስከጦርነቱ መጀመሪያ ድረስ
ግን፣የህወሃት አባልነቱን ግዴታ ለመወጣት በአለቆቹ ታዞ ይሁን በራሱ ተነሳሽነት የአማራንና የኦሮሞን
ህዝብ ለማጋጨት ነበር ስራዬ ብሎ የተያያዘው።አሁን ደግሞ በኤርትራ የመረጃና ደህንነት መስሪያቤት
ፕሮጀክት ተቀርጾለት የትግራይ ህዝብንም የትኩረታቸው መነሻና መድረሻ አካተው በተቀረው የኢትዬጵያ
ህዝብ ለማስጠላትና ለማሸማቀቅ፣የተስፋዬ ገብረአብን ብእር እንደዋነኛ መሳሪያ እየተጠሙበት እንደሆነ
በግልጽ ማየት ይቻላል። ከላይ እንደገለጽኩት መስሪያ ቤቱ በሃገራችን ህዝቦች መሃል ያለውን መተማመን እና አንድነት ለማትፋት
ፕሮጀክት ተቀርጽለት ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በዚህ ግለሰብ ኣማካኝነት እየተፈፀመ የከረመው እና
ሊፈፀም እየቴሰረ ያለው ሤራ እንደሚከተለው ይሆናል፥፥
አጠቃላይ የግቡ አላማ የኢትዮጵያን አንድነት ማዳከም ነው፥፥ ስልታዊ አካሄዳቸው ድግሞ አንዱን
ብሄረሰብ ከሌላኛው ጋር እርስ በእርስ እንዳይማመኑ በማድረግ በመሃላችን አንድ ሃገራዊ አጀንዳና እሴት
እንዳይኖረን ማድረግ ነው፥፥
ለዚህ ማጠናከሪያ የሚሆነው፣የአማራ፣የኦሮሞ እና የትግራይ ብሄረሰቦችን ለምሳሌ ያህል ብንወስድ
አንድ የኦሮሞ የዘር ሃረግ ያለው ግለሰብ፣አማራ ከሆነ ግለሰብ ጋር አብረው በጓደኝነት፣በጋብቻ
ሊኖሩ የሚችሉበት የግኑኝነታችው መሰረት አንድና አንድ ብቻ እንዲሆን ነው የሚፈለገው፡፡ ያም
የትግሬ ጥላቻ ነው።በተቀረው ሁለቱ ግለሰቦች የጋራ የሆነ ሃገራዊ አጀንዳ እና እሴት ቀርጸው
ስለዲሞክራሲ፣ፍትህ፣ልማትና የሰብአዊ መብት መከበር እንዲሁም ሌሎች ሃገራዊ አጀንዳዎች
እንዲያግባቧቸው ፈጽሞ አይፈለግም።የወዳጅነታቸው መሰረት አንድ ብቻ እንዲሆን ነው
የሚፈለገው፣እርሱም የትግሬ ጥላቻ ብቻ ነው። በሌላኛውም መአዘን የትግራይና ኦሮሞ ብሄር
ተወላጆች የወዳጅነታቸውና ያብሮነታቸው መሰረት መሆን ያለበት፣የአማራ ጥላቻ ብቻ እንዲሆን
ነው እቅድ ወጥቶለት ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦለት በተግባር ላይ እንዲውል እየተደረገ ያለው።
ይህንን ለምሳሌ አነሳን እንጂ ሁሉም የሃገራችን ብሄሮች በተገኘው አጋጣሚና እድል በዚህ መልክ
በጎሪጥ እንዲተያዩ በማድረግ እንደሰው ወይንም እንደ ኢትዬጵያዊ ማሰብ አቁመን ሳንፈልግ
በመረጥነው የብሄር ማንነታችን ላይ አትኩረን ስንኩላን እንድንሆን የተሸረበ ሴራ አካል ነው።
እዚህጋ በኤርትራ የደህንነትና መረጃ መስሪያቤት ሙሉ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በመታገዝ
የተስፋዬ ስነ-ጽሁፍ የበኩሉን የማናከስ ሚና በመጫወት ሃገራችንን ወደማያባራ ጦርነትና እልቂት
ለመክተት የራሱን ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ሁለት አመት ለሚቆጠር ጊዜ ቤቴ አስጠግቸው ሲኖር ከሚያደርጋቸው የስልክ ልውውጦች
እንደተረዳሁት ከሆነ በተስፋየ ገብረአብ ስም ይወጡ የነበሩ ጽሁፎች በአብዛኛው ማለት ይቻላል
ከኤርትራ የመረጃና ደህንነት መስሪያቤት የፕሮፓጋንዳ መልእክቶች እንደነበሩ ህያው ምስክር ነኝ።
ይህ ማለት ተስፋየ በጋዜጠኝነት ወይንም በደራሲነት ሽፋን የመረጃ መስሪያቤቱ የፕሮፓጋንዳ
ማስተላለፊያ መሳሪያ በመሆን ለኤርትራን ብሄራዊ ጥቅም የሚውል ስራ ይሰራ የነበረ መሆኑን
አስረጂ ነው።ለምሳሌ ከደህንነት መስሪያቤት የላኩለትን ምንም ለውጥ እንዲደረግበት ሃሳብ
ሲያቀርብ፣እነሱም ሃሳቡን ሳይቀበሉት ሲቀሩ በር ዘግቶ በስልክ ሲጨቃጨቅና ሃሳቡ ሲሸነፍ
በተደጋጋሚ መስማቴን አስታውሳለሁ።

እንደ እኔ እምነት ከሆነ ራሱ የኢትዬጵያ መንግስት እያራመደ ያለው የተንሸዋረረና የከረረ የዘር
ማንነትን ብቻ ማእከል ያደረግ የፖለቲካ ስርአት፣ከውጪ ሊመጣ ለሚችል እንዲህ አይነት
የማጋጫት ወይንም ሃገር የማፍረስ ጣልቃገብነት በር እንደሚከፍት ለመተንበይ አዳጋች አይሆንም።

ወደ ነጥቤ ልመለስና ከላይ በጠቀስኩት መሰረት፣አማራን ከተለያዩ የሃገሪቱ ብሄሮች ጋር እንዴት
ሲያላትም እንደነበረ፣ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር በክፍል አንድ ሪፖርታችን ላይ በሰፊው
ሄደንበታልና አሁን አልመለስበትም። ከዚህ በታች ደግሞ የትግራይ ብሄር አባል በሆኑ ግለሰቦች ላይ
ማህበራዊ ፤ የስነልቦና የአካል ጥቃት መፈጸሙ፤ የሱ መጽሃፍ ስኬት ውጤት እንደሆነ ለኤርትራ የመረጃና ደህንነት መስሪያቤት የቅርብ ተጠሪው ለሆኑት አቶ ዓለም እንዲህ በማለት በጽሁፍ
ያስተላልፍ እንደነበረ ከሚከተለው የፋክስ መልእክት ረቂቅ (ድራፍት ) መረዳት እንችላለን፡



የአምስተርዳም በአል ላይ አንዱ የመለስ ደጋፊ የመለስን ፎቶግራፍ ለብሶ ሲገባ፣እኔ እዚያው
በአሉ ላይ ነበርኩ እንደ እንደማርያም ጠላት እየተቀባበሉ ቀጠቀ።የአምስተርዳም በአል ላይ
የተፈጸመ ሌላ ታሪክ ልንገራችሁ።አንዱ ወጣት ትግርኛ ይዘፈን፣ትግርኛ ብሎ ይረብሻል።ቢራ
ጠጥተው ሞቅ ያላቸው ወጣቶች እየተንደረደሩ ያንቁታል፣ልጁ ክጃቸው ያመልጥና መሮጥ
ይሞክራል።ተከታትለው ሲይዙት ኤርትራዊ ነኝ ብሎ ይጮሃል።

ባለፈው እሁድ የልደት በዓሌን አከበርኩ።42ዓመት ሆነኝ።አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች፣አንዲት
የትግራይ ልጅ ጉዋደኛ አለችኝ።ደቡብ አፍሪካ ፕሮቶሪያ ዩኒቭርሲቲ ለትምህርት መጣታ ሳለ ነበር
የተዋወቅኩዋት። አሁን አዲስ አበባ ተመልሳለች።ሰንገናኘ የልብ የልባችንን እንጫወታለን፡፡እናም
ስንጨዋወት እንዲህ አለችኝ።እናቴ እንደቀድሞዋ የትግሬ ሹሩባ መሰራት ትታለች፣በወር አንድ
ግዜ በሹሩባዎቹዋና በወርቁዋ ማጌጥ ትወድ እንዳልነበረች፣አሁን ሰርግ ላይ እንኩዋን፣ሹሩባ
መሰራቱ አሳቁዋታል።ሰው ሁሉ የሚጠቁዋቆምብኝ ይመስለኛል ብላ ነገረችኝ ትላለች።

ከሰጠሁት ጥቆማ በላይ ግን በሁለቱ መጽሃፍት- እነዚያን ጥቆማዎች ለማድረግ በተደረገ
እንቅስቃሴም።…… እነዚህ ሁለት መጽሃፍት (የጋዜጠኛው ማስታወሻ እና የደራሲው ማስታወሻ )
ለመጻፍ ችያለሁ።እነዚህ ሁለት መጽሃፍት ያስገኙት የፖለቲካ ፋይዳ በአንድ ባለሙያ ማስጠናት
ብቻ በቂ ነው።
ያለፈውን ገድል በማንሳት ጉራ መንዛትም ብቻ ግን ዋጋ የለውም።ወደ ሚቀጥለው ተግባር
መሸጋገር ያስፈልጋል።

ከግማሽ ሚልዬን በላይ ህዝብ እነዚህን መጽሃፍት በማንበብ ከፍተኛ ግንዛቤ አግኝቶአል።


ተስፋዬ ገብረአብ ስነ ጽሁፍን እንዴት ለፖለቲካዊ አላማው እየተጠቀመ እንደነበረ በራሱ እጅ
ጽሁፍ እንደሚከተለው ያብራራል።

ለዓለም፣
አንዳንድ ማስታወሻዎች፣

የዚህ መጽሃፍ ፋይዳ ከቀዳሚዎቹ ሁሉ የላቀና ልዩ ትኩረት የሚያሻው ነው።የነዚህ ማስታዎሻዎች
ተከታታይ መጽሃፍትን ሃሳብ የጠነሰስከው እኔም ኢትዬጵያዊ ሆኜ ድራማ እንድሰራ ያዘዝክ (ሰርዞት)
ያግባባህኝ ራስህ (አበበ)በመሆንህ ይህ ፕሮጀክት የመስሪያ ቤታችን የስራ አካል ተደርጎ እንዲታይ
ምኞት አለኝ።ምክንያቱም የተጀመረ ፕሮጀክት እንደመሆኑ፣ልገፋበት የግድ ነው።ከኢትዬጵያ ህዝብም
ከፍተኛ ግፊት አለብኝ።ቢያንስ ከአራት መቶ ሺህ በላይ ኢትዬጵያውያን አንባቢዎች እንዳፈራሁ
ይገመታል።እነዚህም አንባቢያን የከተማ ሰዎችና ለፖለቲካው ቅርብ የሆኑ እንደሆነ ማረጋገጥ ይቻላል።

አሁን የሆላንድ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቻለሁ።ቀጣዩን መጽሃፍ እዚሁ ሆላንድ ሃገር ሆኜ ለመጻፍ
እየሞከርኩኘ ነበር።እየሰራሁትም ነው።ሆኖም እየተሳካልኝ ነው ማለት አልችልም።የተሳካ ስነ-ጽሁፍ
ለመስራት ያካባቢ ሁኔታ ወሳኝ ነው።የጋዜጠኛው ማስታወሻ እና የደራሲው ማስታወሻን የሰራሁት
አስመራ ሆኜ መሆኑን ታውቃላችሁ።የስደተኛን ማስታወሻ ሆላንድ ሆኜ መስራት አልቻልኩም።መስራት
ካለብኝ ኤርትራ መመለስ አለብኝ።ኤርትራ ከተመለስኩ ያገኘሁት የሆላንድ ዜግነት ሊቋረጥ ይችላል።
ምክንያቱም በሆላንድ ህግ መሰረት ከሆላንድ ውጭ መቆየት የሚፈቀድልኝ፣ለሶስት ወር ብቻ ነው።
ጥቅምና ጉዳቱን ስመዝነው ግን፣ሆላንድ ላይ ያገኘሁት ዜግነት ተሰርዞ ወደ ኤርትራ ብመለስ የተሻለ
ነው።ምክንያቱም እኔ ሆላንድ ላይ ከመቆየቴም በላይ የስደተኛው ማሰታወሻ መታተም፣ፖለቲካዊ
ፋይዳው የላቀ ነው።ይህን ሃሳብ ያቀረብኩት በርካታ ጥቅምና ጉዳቶችን ግራና ቀኝ ተመልክቼ ነው።

ከላይ ያቀረብኩት ሃሳብ፣ለማጠቃለል ያህል።መንግስት የሰጠኝን የመኖሪያ ፈቃድ ለአንድ ዓመት ያህል
ወደውጭ እንድቆይ የሚፈቅድልኝ ከሆነ እሞክራለሁ።ካልተቻለ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን መልሼላቸው
ጥቅምት 15፣2010 ዓም.ላይ የመመለሻ ትኬቴን በመጠቀም ወደ ኤርትራ እመለስ ዘንድ ሃሳብ
አቀርባለሁ።ለዚህም የናንተ ውሳኔ ያስፈልጋል።

ወደ ኤርትራ ከተመለስኩ በኋላ መስሪያቤታችን ገለል ያለ ቦታ ሆኜ 44 ምእራፍ 600 ገጾች ያሉትን
የስደተኛው ማስታወሻ ጽፌ፣መጨረስ እንድችል መስሪያቤታችን አንድንድ ሁኔታዎችን
እንደሚያመቻችልኝ እመኛለሁ።እነዚህ ነገሮችም፣ለአንድ ዓመት ጊዜያዊ መኖሪያ ቤትና የመጻፊያ ቢሮ
ናቸው።በ2011 የሚታተመው ይህ መጽሃፍ ከቀዳሚዎቹ ሁሉ የላቀ እንደሚሆን ቃሌን አምናችሁ
ይህን ታደርጉ ዘንድ እመኛለሁ።ሻቢያ በቀጣይ (መስሪያቤታችን)ከሚያስመዘግባቸው የስነልቦና
ጦርነቶች ሁሉ ይህ ቀዳሚ ስፍራ እንደሚኖረው ለማረጋገጥ እጥራለሁ።


የሆነው ሆኖ የሀገሬ አንድነትና የህዝቤን የፍቅር ሰንሰለት ለመበጠስ፣ የኢህአዴግ አስተዳደር ባነበረው
የዘውግ ፌድራሊዝም ሾልከው የሚገቡትን ሴራኞችን ማጋለጥ የኢትዮጵያዊነት ግዴታዬ ነውና በቀጣዩም ሌሎች
ያገኛኋቸውን መረጃዎች በተከታታይ አቀርባለሁ፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥበቃ ለዘላለም ትኖራለች!!!
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12324