Saturday, August 31, 2013

ወያኔ የ1997ን በማስታወስ አፋርታምነቱን ሲደግም ከአዲስ አበባ


 በ97 ምርጫ ወቅት ቅንጅት በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ጥሪ ሲያስተላልፍ አብል አልከፈለም፤ ቲሸርት አልሰጠም፤ ምሳ አላዘጋጀም፤ የላብ ማድረቂያና የፍልውሃ ብሎ በጀት አልተመነም፡፡ ኑ ውጡ እንውጣና ለዴሞክራሲ እንዝፈን፡፡ የፖለቲካ ዲስኩር ሳይደረግ፤ መፈክር ሳይሰማ፤ ሚያዝያ 30 በመስቀል አደባባይ ተገናኝተን አንዳችም ፖለቲካዊ ዲስኩር ሳይደረግ ዝም ብለን ለዴሞክራሲ፤ ለሰብአዊ መብት፤ ለፍትሕ መረጋገጥ፤ ለመጪው ምርጫ የሕዝብ ድምጽ መከበር እንዝፈን ተብሎ ሕዝቡ ሲጠራ ከሩቅም ከውጭም መልእክቱ ኑ ብቻ ነበር፡፡ ይህን የሰማው ወያኔ ልዋረድ ነው ብሎ ደንግጦና በርግጎ፤ ፈርቶና ተርበትብቶ፤ መግቢያ መውጫው ግራ ሆኖበት ለሚያዝያ 29 ጥሪ አስተላለፈ፡፡

የቀን ወጪ መደበ፤ ትራንስፖርት ከየአቅጣጫው መድቦ፤ ቲሸርት አድሎ ለቁርስ ሳንድዊች መግዣ በጥሬው ሰጥቶ፤ ከሰልፍ መልስ ለድካም ማካካሻ በነፍስ ወከፍ 50 ብር መድቦ፤ ለላብ ማጽጃ የፍልውሃ ሌላ ተጨማሪ ክፍያ ሰጥቶ በየቀበሌው፤ በየዞን አመራሮቹ፤ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡ መልእክቱ ለሁሉም ይድረስ፤ ፓርቲያችሁ ኢህአዴግ የተሰነዘረበትን የውርደት ጅራፍ አብረን እንድንከላከል፤ የተቃጣብንን የስልጣን ገፈፋ አብረን እንድንመክት፤ ቅንጅት የሚባል ጣውንታችንን አብረን እንድንዋጋው አስፈላጊውን ትራንስፖርትና ወጪ ለየአንዳንዳችሁ የመደበ ስለሆነ ለቁም ተዝካሬ እንድትደርሱልኝ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ ይህን ለማድረግ ትብብር የነፈገ ነጋዴው ከሱቁና ከንግድ ፈቃዱ ጋር ተማሪው ከትምህርት ቤቱ ጋር ጎዳና ተዳደሪም ተንደላቆ ከሚተኛባቸው የጎዳና አስፋልቶች ጋር የመንግስት ሰራተኛም ከደምወዝና ቅጥሩ ጋር ይሰናበት ለዚህ ኢህአዴግን አድን ሰልፍ ካልወጣ መገናኘት ህልም ነውና!፡፡ በማለት ተጣራ፡፡
     ነገ ከማልቀስ ጥሪውን በአዎንታዊ መልኩ መመለስ አለ ሁሉም 29ን ለወጪው፤ ለ50 ብሩ፤ ለቲሸርቱ፤ ለስራ፤ ለትምህርት፤ ለንግድ ፈቃዱ፤ ማዳኛና ማግኛ 30ን ለዴሞክራሲዬ ፤ ለሰብአዊ መብቴ፤ ለፍትሕ መረጋገጥ፤ ለነጻነቴ ለመቆም ብሎ አቀደ በ29 በተደረገው የትእዛዝና የዛቻ ሰልፍ፤ ዋ እቴ!፤ ነፍሳቸውን ይማረውና መለስ በተኩራራና በተረጋገጠ ሰሜት ይህን ጎርፍ ያየ ምርጫ ይሰረቃል ሊል አይችልም፡፡ ዛሬ ሕዝቡ አረጋገጠልን ፍላጎቱን፤ ምርጫዬ ኢህአዴግ ነው አለ ሲሉ፤ ሕላዊም በተሸከርካሪ ወንበሩ ላይ ሆኖ ቦታ አልበቃ አለው፤ ድል ታየኝ ብሎ ተኮፈሰ፡፡ በረከትም እንግዲህ ቅንጅት እርሙና ያውጣ አንድ ወንበር አይገኝም ብሎ ተወራረደ፤ እርግጥ እርታታው ሲታወቅ ግን ማፈር ቀለቡ ነውና ውርርዱን አልከፈለም፡፡ አፋርታም አይደል ድሮስ! ሚያዝያ 30 ያን ጎርፍ የተባለውን ሱናሚ ሲያደርገው፤ ሕዝቡ በራሱ ፍላጎትና በግል ትርንስፖርቱ፤ አደባባዩን ጠጠር መጣያ ሲያሳጣው እነ እንቶኔ የት ይግቡ፡፡
      እኛው ነፍሳቸውን ይማረውና እኛው ሰውዬ መላ ሲጠፋቸው ሰማይ ሲደፋባቸው ‹‹ያልኩት፤ ቃል የገባሁት ሁሉ ፉርሽ ሆኗል፤ ፎገርኳችሁ! ብለው ጣት እቆርጣለሁ፤ አስረለሁ ማለት ጀመሩ ብቻ ሁሉም ነገር ጨዋታ ፈረሰ…. ሆነ አሁን ደግሞ ተቃዋሚዎች ሕዝቡን ና እንነጋገርና ውሳኔህን አስተላልፍ ብለው ሲጠሩና፤ ወያኔ ኢህአዴግም፤ አዝማሚያውን በየቦታው በሰገሰጋቸው ሰላዮቹና አገልጋዮቹ ሲያጣራ ሕዝቡ ለተቃዋሚዎች ጥሪ ምላሹን ለመስጠት መዘጋጀቱን ሲያረጋግጥ፤ አርብ እለት ነሐሴ 24 ቀን፤ በየወረዳውና ቀበሌው ነዋሪውን ሰብስቦ፤ ካድሬዎቹን አሰልፎ መመርያ ሰጠ፡፡ መመርያውም እንዲህ ይላል---
1. ማንኛውም ነዋሪ በዚህ ሰልፍ መሳተፍ አለበት፤ ያን ካላደረገ የሽብርተኛ ተባባሪ ነው
2. ለመጓጓዣ ትራንስፖርት በየወረዳው ተመድቧልና በእግር ማንም ወደ መስቀል አደባባይ መግባት ስለማይችል በሚቀርበው ትራንስፖርት መጠቀም ግዴታ ነው
3. በአውቶቡሱና በመሰል ትራንስፖርት ላይ ያልተገኘና በስም መዝገቡ ላይ መገኘቱ ካልተረጋገጠ ስራ ያለው በስራው፤ ተማሪው በትምህርት እድሉ፤ ነጋዴው በንግድ ፈቃዱ እንደፈረደ እንዲያውቀው፡፡
4. በምንም መልኩ ከዚህ መቅረት ማለት ዘላቂ ቸግር ውስጥ መግባት ስለሆነ አስቡበት ተብሎ ስብሰባው ከምሽቱ 3 ሰአት ላይ ተጠናቋል፡፡ . ይህ ሁሉ ማስፈራሪያ፤ ይህ ሁሉ ዛቻ ያለበት የሰልፍ ጥሪ እንዴት ሆኖ ነው ሕዝቡ ሰልፍ ወጣ የሚያሰኘው፡፡ . መቼ ነው ወያኔ ከማስመሰል ተግባሩ የሚለያየው . አይ አቶ ሃይለማርያም ምነው ጃል የማይሆን ትምህርት ቀሰሙ ያውም በወረደና በተዋረደ መልኩ፡፡ ያሳዝናል፡፡ ልብ በሉ እንግዲህ ተቃዋሚው ባገኘው አጋጣሚና በኢንተርኔት ቀኑን አሳውቆ ጥሪ አስተላለፈ፡፡
ኑ አብረን ለኢህአዴግ ስህተቱን በመንገር እንዲያርም፤ ለሕዝብ ድምጽ እንዲገዛ፤ የግፍ እጁን እንዲሰበስብ፤ ማን አለብኝ ባይነቱን ትቶ ሕዝብን እንዲያከብር፤ ሕገመንግስቱን በሚጥመውና በሚጠቅመው ብቻ ሳይሆን ሳይሸራርፍ እንዲያከብረውና ለዚህም ከማንም ቀድሞ እንዲገኝ፤ ባሻው ማሰርና የፈጠራ ማስረጃ በማስደመጥ አሰልቺነቱን እንዲያቆም፤ ፍትሕን ፍትሃዊ በሆነው እውነታው፤ ሰብአዊ መብትን ከራሱ አሳልፎ ለመላው የሰው ልጅ እንዲጠቅም፤የአገልጋዮቹ አመልካች ጣት ወገን ላይ ጥይት ለማርከፍከፍ ሳይሆን ወንጀለኛንና ሕገወጥን ለመጠቆሚያ፤ በስልጣኑ አለአግባብ ከመባለግም አልፎ ለጋጠ ወጥ ድርጊት እንዳይሆን፤ ገዢው መንግስት ከመግዛት ወደ ማስተዳደር እንዲለወጥ፤ ወዘተ….. እንዲውሉ በአንድነት እንቁም ብሎ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ሕዝቡም ነሐሴ 26ን የነጻነቴ ቀን ብሎ በማስታወሻው፤ በሕሊናው፤ መዝግቦ ቀኑን ሲጠብቅ፤ ወያኔ በድንገት ከእንቅልፉ ነቃና በአዲስ አበባና በአካባቢው ያሉትን የወረዳ ነዋሪዎች በአስቀመጣቸው ጀሌ የወረዳ ሹማምንቶች፤ በሰገሰጋቸው ካድሬዎች፤ ባሕሪው በሆነው ማስፈራራት ለስብሰባ ጠራ፡፡ መመርያ ሰጠ፡፡ ዋ ብሎ ዛቻውን ደረደረ፡፡
       በገዢው ከሚቀርበው ትራንስፖርት ውጪ ማንም በእግሩም ሆነ በግል ትራንስፖርት ጨርሶ ወደ መስቀል አደባባይ መግባት ክልክል ነው አለ፡፡ ይህም ማለት ተቃዋሚ የጠራው ሰልፍ ላይ ለመካፈል ማንም ወደ መስቀል አደባባይ በእግር አይገባም ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ እንግባ አትገቡም በሚል በሚነሳ አተካሮ ወያኔ ኢህአዴግ የተቃዋሚ አባላትንና ደጋፊዎችን ሊደበድብ፤ ሊገል፤ ሰብስቦ ሊያስር፤ ማቀዱን አረጋገጠ፡፡ እዚህ ላይ ወያኔ ፈርቶ በማስፈራራት ባህሉ አሁንም ሕዝብ ዳግም ከተቃዋሚ ጋር እንዳይሰለፍ ማዘዣውን እያስተለካለፈና መንገዱንም እየዘጋ ነው፡፡ (ይሆን መስሎት) ያንንም እምቢ ለነጻነቴ ብሎ የተቃዋሚውን ሰልፍ፤ ሰልፌ ነው ብሎ ቢወጣ በከተማው የሚበትናቸው ‹‹ፖሊስ›› መሰል ጀሌና አገልጋዮቹ፤ በፖሊስ ልብስ ተጨንብለው ያን የግፍ እርምጃቸውን ሊወስዱ እንዲችሉ የተዘረጋ ዘዴ ነው፡፡ ሃገርን በጉልበቴ በመጠቀም እገዛለሁ፤ ያለ መንግስት ነኝ ባይ ቡድን፤ ለዚህ በምንም መመዘኛ መንግስት ሊያሰኘው በማይችል ተግባር ላይ መሰልፍን የመሰለ የወረደ፤ ያዘቀጠ፤ ምንም ነገር የለም፡፡ ያሳዝናል፡፡ ምን ቢደረግ፤ ምንም ቢዶለት ቀኑ መቆረጡ አይቀሬ ነውና የመጠየቂያ ወንጀላችሁን ባታበዙት ይሻላል፡፡ ያለው እኩይ ተግባራችሁ በቂ ነውና!
staff reporter | August 31, 2013 at 12:57 am | URL: http://wp.me/p2gxmh-2bM
Comment   See all comments

Friday, August 16, 2013

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ‹‹ጽንፈኞች›› ጋር እየተንቀሳቀሱ ነው ያሏቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስጠነቀቁ


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ‹‹ጽንፈኞች›› ጋር እየተንቀሳቀሱ ነው ያሏቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስጠነቀቁ-ኦፌኮ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሕጋዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀ

በኢድ አል ፈጥር በዓልና ከዚያ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሱትን ተቃውሞዎችና ግጭቶች ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ‹‹ጽንፈኞች›› ካሏቸው ጋር በመሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አገር ለማወክ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በመግለጽ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን የመንግሥትን ወቀሳና ማስጠንቀቂያ ውድቅ በማድረግ መላው ኢትዮጵያዊ ትግሉን እንዲያጠናከር ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በአገሪቱ እየተስተዋለ የሚገኘውን የእስልምና እምነት ተከታዮች ተቃውሞ አስመልክቶ ‹‹ጽንፈኞች በሃይማኖት ስም በመንግሥት ሥራ ጣልቃ እየገቡ ነው፤›› ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹ጽንፈኞች የሃይማኖት አባቶችን በመግደል፣ በማሸማቀቅ፣ ሕዝበ ሙስሊሙን መፈናፈኛ አሳጥተን የራሳችንን እምነት በኃይል እንጭናለን በሚል እሳቤ ሁከት እየፈጠሩ ነው፤›› ብለዋል፡፡
‹‹መንግሥትን መቆጣጠር ይገባል፡፡ የሸሪዓ ሕግን መንግሥት መተግበር አለበት፡፡ ከዚህ ውጭ ምንም ዓይነት እምነትም ሆነ ሃይማኖት አይኖርም፤›› በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ይህ ሁሉ ነገር እየሆነ በትዕግሥት ጉዳዩን ሲከታተል መቆየቱን የሚገልጹት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ‹‹መንግሥት ይህንን ያደረገበት ምክንያት ጽንፈኞቹን ከእስልምና እምነት ተከታዮች ለመለየት ነው፤›› ብለዋል፡፡
‹‹ጽንፈኞችን›› ለይቶ ለማውጣት መንግሥት የመረጠው ትዕግሥትና ያደረገው ጥረት ውጤታማ በመሆኑ፣ ሕጋዊ ዕርምጃ መውሰድ እንደተጀመረና ይህም ከዚህ በኋላ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
‹‹ከጽንፈኞች ጋር ጋብቻ ፈጥረው የአገሪቱን ሰላም ለማወክ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እየተሰጣቸው ያለውን ማስጠንቀቂያ የማይቀበሉ ከሆነ ሕጋዊ ዕርምጃ ይወስድባቸዋል፤›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የእስልምና እምነት ተከታዮች ተቃውሞ በተመለከተ በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ተመሳሳይ መግለጫና ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ እምብዛም ሲናገሩ አይስተዋሉም ነበር፡፡
የሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ግን መንግሥት ጠንከር ያለ ዕርምጃ ለመውሰድ አቋም የያዘ አስመስሎታል፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ‹‹መንግሥት የሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይግባ›› የሚል መሠረታዊ ጥያቄ ላይ በመንተራስ እያቀረቡ የሚገኙትን ተቃውሞና ጥያቄ በመደገፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖትና መንግሥት አንዱ በአንዱ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ በሕገ መንግሥቱ የሰፈረ መሆኑን በመግለጽ፣ መንግሥት ከሚነሳው ተቃውሞ ጀርባ ጽንፈኝነትና የአንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሌላ ዓላማ መኖሩን በመግለጽ እያስጠነቀቀ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመንግሥትን ውንጀላ ውድቅ በማድረግ የእስልምና እምነት ተከታዮች እያነሱ የሚገኙትን ተቃውሞ በመደገፍ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአገሪቱ ከሚገኙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ሰማያዊ ፓርቲ፣ መድረክና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ይገኙበታል፡፡
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ባለፈው ሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹መንግሥት በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መንገድ ብቻ የዜጐችን የእምነት ነፃነት በማክበር፣ ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሰላማዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ መስጠት አለበት፤›› ብሏል፡፡
መንግሥት የሙስሊሙ ኅብረተሰብን ጥያቄ በሕጋዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ጣልቃ ገብነቱን የሚቃወሙ የእምነቱን ተከታዮች በአሸባሪነት በመፈረጅ ማሰር፣ መደብደብና መግደልን መፍትሔ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ይህ የመንግሥት ተግባር ለአገር ሰላምና ደኅንነት አስጊ ሁኔታ ፈጥሯል በማለት መግለጫ አውጥቷል፡፡
መንግሥት የሙስሊሙ ኅብረተሰብን ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች በመደፍጠጥ ጭካኔና ሰብዓዊነት የጐደለው ተግባር እየፈጸመ ነው በማለት ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ አውግዟል፡፡
በማከልም፣ ‹‹ሙስሊሙም ሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢሕአዴግን ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ድርጊት በመገንዘብ ትግሉን በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ አጠናክሮ በመቀጠል አንድነቱንና ለሰላማዊ ትግል ትብብሩን ይግለጽ፤›› ሲል ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Comment   See all comments

Tuesday, August 13, 2013

Israel's Everyday Racism — and How American Jews Turn a Blind Eye to It

Jews were outraged when Jesse Jackson referred to New York as ‘Hymietown.’ Where’s the anger over Israeli public figures’ rampant racism? Refocus Anti-Semitism Outrage on Our Own Dirty Laundry


GETTY IMAGES
Jews were outraged when Jesse Jackson referred to New York as ‘Hymietown.’ Where’s the anger over Israeli public figures’ rampant racism?

By Larry Derfner

Published August 12, 2013.
The Anti-Defamation League and the rest of the American Jewish establishment owe Jesse Jackson a big apology. They put the man through the wringer, they made him apologize in every possible forum for his “Hymie” and “Hymietown” remarks back in 1984. Yet look at the kinds of things Israeli leaders — senior government ministers, chief rabbis — get away with without ever having to apologize, without ever being punished in the slightest.
Just last week, Naftali Bennett, the fresh new face of right-wing Orthodox Judaism, said in a cabinet meeting how he didn’t like these releases of Palestinian prisoners. “If you catch terrorists, you simply have to kill them,” he was quoted in Yedioth Ahronoth as saying. The head of the National Security Council, Yaakov Amidror, told Bennett, “Listen, that’s not legal.” Bennett replied: “I have killed lots of Arabs in my life – and there is no problem with that.”
The media, the left and the Arabs made a big deal out of it, nobody else. Bennett defended what he said, and so did countless talkbackers and Facebookers.
Two days later the newly-elected Ashkenazi chief rabbi of Israel, David Lau, was seen on a video telling an audience of yeshiva boys that they shouldn’t watch European basketball games in public.
“What difference does it make,” Lau said, “if the kushim who get paid in Tel Aviv beat the kushim who get paid in Greece?” Kushim, especially when used in a dismissive context like Lau did, is a well-understood derogatory term for blacks.
Again, the media, the left, some Ethiopian Jews and presumably some African refugees were outraged. But Lau defended his words, blaming the media, saying “they made a big deal out of a joke.”
Who else defended his remarks about “kushim”? Bennett: “The media are pouncing on him for a joking, insignificant remark.”
So really — what was so bad about “Hymies” and “Hymietown”? Or the thousand other anti-Semitic or even just possibly anti-Semitic remarks that the ADL and other American Jewish organizations have “pounced on” since then? Israeli public figures say the same kind of garbage, the difference is that they never, ever pay a price for it, in fact they usually manage to play the victim and get away with it, and at worst will be obliged to offer some backhanded apology.
Likud lawmaker Miri Regev is doing fine after having called Sudanese refugees “a cancer on our body” to a crowd of hopped-up south Tel Avivians in May of last year, shortly before the crowd went on a window-smashing mini-pogrom against the Africans in the neighborhood.
Legendary basketball coach Pini Gershon’s career and public stature didn’t suffer at all after he explained his racial theory about blacks to a class of amused army officers in 2000.
“The mocha-colored guys are smarter, but the dark colored ones are just guys off the street,” Gershon said. “They’re dumb like slaves, they do whatever you tell them.”
Nor was there any blowback whatsoever after Bibi Netanyahu bragged in 2007 that the cuts he’d made to child subsidies had brought a “positive” result, which he identified as “the demographic effect on the non-Jewish public, where there was a dramatic drop in the birth rate.”
Imagine the scandal if an American political leader boasted publicly that his cuts to child subsidies had reduced the “non-Christian” birth rate. Imagine the ADL’s reaction. But in Israel, in 2007, from the mouth of a once-and-future prime minister — nothing.
These are just a few of the more appalling examples of the kind of racist remarks that Israeli politicians, rabbis and celebrities feel free to make. I haven’t even mentioned Avigdor Lieberman and Rabbi Ovadia Yosef. As a rule the words are directed at Arabs, now and then against blacks: either Ethiopian Jews, African refugees or athletes.
I’ve lived roughly half my 61 years in the United States, the other half in Israel. There is absolutely no comparison between American tolerance for public displays of racism and Israeli tolerance for it.
I’ve stood in the middle of Israeli crowds chanting “Death to the Arabs.” I’ve sat in a Tel Aviv soccer stadium watching and listening to an entire section of fans erupt in monkey sounds – “Hoo, hoo, hoo!! Hoo, hoo, hoo!! – after a black player on the visiting team scored a goal.
A few liberals and a few do-gooders and a few journalists wring their hands. But the racists in the street, the synagogues, the Knesset and the government go on doing their thing.
Does this mean all Israelis, or even most of them, are racists? No. Does it mean Israeli society, by commission and omission, encourages racism? Oh, yes. To a degree that would be unthinkable in the United States.
And the leaders of the U.S. Jewish establishment, Israel’s most valued, devoted, determined friends, keep pouncing on every untoward or conceivably untoward remark about Jews or the Jewish state. Yes, the ADL will send out a press release about its “concern” over the “inappropriate” remarks made by some relatively minor Israeli figure.
But it never hits hard at the major figures. It said nothing last week about Bennett or Lau. The ADL goes after anti-Semitism with a fist, it goes after Israeli racism with a sigh.
As a matter of fact, the ADL and the entire American Jewish establishment should suspend their campaigns against anti-Semitism indefinitely and take a look at what’s going on in Israel.
When the Jewish state is this riddled with racism, its advocates abroad should be a little less outraged over the offenses of gentiles. They should be a little more humble — and a lot less hypocritical.


Read more: http://forward.com/articles/182171/israels-everyday-racism-and-how-american-jews-tu/#ixzz2bsVR7GSF

Monday, August 12, 2013

ስንቅና ውሸታም እያደር ይቀላል! ፈቃዱ ለሜሣ (ፕሮፌ


  የኮርስ ስም ፤ በኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ የሚሠነዘሩ የፈጠራ  ወሬዎችና ተጨባጩ ሃቅ
የኮርስ ቁጥጥር ፤ ‹hist101›  (ልቦለድና ፈጠራ በኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ላይ)
የኮርስ መምህር፤   ፕሮፌሰር ፈቃዱ ለሜሣ
ኮርሱ የተጀመረበት ወር፤ ሐምሌ 2005
ትርጉምና ቅንብር፤ ይነጋል በላቸው
 ማሳሰቢያ፡- አሁን እዚህ ያቀረብኩት የትርጉም ሥራ ከወቅቱ የፖለቲካ ንፋስ አኳያ በጣም ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑን አውቃለሁ፡፡    በቃላት የምንዛሬ ትርጉም ዜጎች እየተላለቁ በሚገኙባት ሆደባሻ ዓለም ውስጥ ይህን መሰሉን ጉዳይ በቀላሉ መተርጎም    እንደማይቻል እረዳለሁና ማንኛውም ዓይነት በዋናው  ጽሑፍ ላይ ያልተጠቀሰ ሃሳብ በዚህ ትርጉም ውስጥ በስህተት ቢገኝ      ኃላፊነቱ   ፕሮፌሰሩ ሣይሆን የኔ የተርጓሚው መሆኑን ለአንባቢያንና ለፕሮፌሰር ፈቃዱ ከታላቅ ይቅርታ ጋር በትህትና እገልጻለሁ፡፡ በተቻለኝ           መጠን የዋናው የእንግሊዝኛ ጽሑፍ ወዘና እንዳይጠፋ ጥረት አድርጌያለሁ - የኔ የራሴ ሥነ ልሣናዊ ‹የተፈጥሮ ለዛ›ም እንዳይከፋብኝ       ከሚል ቅን አስተሳሰብ በመነሣት የተጠጋጋ ግን ከዋናው እምብዝም የማያፈነግጥ ‹ኮዝሞቲክስ› እጅግ አልፎ አልፎ በጣም በስሱ ፈንጠቅ            ለማድረግ ሞክሬያለሁ - ለዚህ ደግሞ ፕሮፌሰርን በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ - እንዲህ የማደርገው እንግሊዝኛው ወዳማርኛ ሲመለስ        ድርቅ እንዳይልብኝና መሸጋገሪያ ድልድዩ ቢጠናከር ትርጉሙ ይበልጥ እንደሚያምር ሳምንበት ነው ፤ ለማንኛውም ግን ሰው       ነኝና ብሳሳት          በቀናነት እዩልኝ እንጂ ልፋቴን በሚያጣጥል የከፋ ደረጃ እንዳታብጠለጥሉኝ አደራ እላለሁ፡፡ ዛሬም መልካም ንባብ፡፡
 (ኦሮሞዎችንና የኢትዮጵያን ታሪክ በሚመለከት ዳሰሳ ለሚያደርጉ የውጭ ጋዜጠኞች የመነሻ ግንዛቤ መጨበጫ ይሆናቸው ዘንድ የተዘጋጀ) ኦሮሞና ኢትዮጵያ፤ ምሥጋና ለayyaantuu.com ድረ ገጽ)
 (ናዝሬት፣ ኢትዮጵያ) - መሠረቱን ኳታር ያደረገው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ኦሮሞዎችን በሚመለከት በርካታ ዝግጅቶችን በቅርቡ አየር ላይ ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡ የሕዝባችንን ገጽታ በመሰለው መልክ ለዓለም ማኅበረሰብ በስፋት በማስተዋወቅ ረገድ ይህ የሚዲያ ተቋም የመጀመሪያው በመሆኑና እያደረገ ያለውም አስተዋጽዖ ቀላል ባለመሆኑ  ሊወደስ ይገባዋል፡፡
ይህ ዓይነቱ ሕዝብን የማስተዋወቅ ሥራ ከሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ውስጥ አንደኛው፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በነሱና በተከታዮቻቸው አማካይነት በሕዝቡ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ግፍና በደል እንዲሁም የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የሚከታተል ገለልተኛ ወገን መኖሩን ተገንዝበው የሚያካሂዷቸውን የሰብኣዊ መብት ረገጣዎች በቀላሉ እንዳይመለከቱ ማስገደዱና በዚያም ሳቢያ እነኚሁ ባለሥልጣናት የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ የወቅት ሁኔታ የዓለም ሕዝብ በግልጽ እየተከታተለው መሆኑን እንዲያውቁት ማስቻሉ ነው፡፡  ኦሮሞዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው ለእኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው መከበር ላለፉት በርካታ አሠርት  ዓመታትና አሁንም ድረስ ሲታገሉ ቆይተዋል፡፡ ስለኦሮሞ ሕዝብ ጥንተ አመጣጥና ታሪካዊ  ዳራ የመዘገቡ አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ይህ ሲደረግ ግን በትክክል መዘገብ እንደሚኖርበት መረዳት ለማንኛውም ወገን ጠቀሜታ አለው፡፡ ትክክለኛ ያልሆነና የተጣመመ መረጃን ወይም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ አንድ ወገን የሚያጋድል ዘገባን ማቅረቡ ለዴሞክራሲ የምናደርገውን ሁለንተናዊ ትግል ይጎዳብናልና ከዚህ መሠረታዊ ነጥብ አንጻር ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል፡፡ ይህ የተንሻፈፈ አካሄድ ብሔራዊ መግባባትንና ሰላምን ከመፍጠር ይልቅ ቁጣንና አንዱ ባንዱ ላይ መንገፍገፍን እያስከተለ ቅራኔን ያባብሳል፡፡
በቅርቡ አልጀዚራ ትክክል ያልሆነ ወይም የተሳሳተ ዘገባ እንዲያርቀብ ከተገደደበት ምክንያቶች አንደኛው የመረጃ ምንጩ ግራና ቀኙን ያማከለ ሣይሆን በአንድ አቅጣጫ ብቻ ማለትም በአብዛኛው በዉጭ የሚንቀሳቀሱ ኦነግንና ኦ.ኤፍ.ዲ.ኤምን የመሳሰሉ የኦሮሞ ድርጅቶች መሆናቸው ነው፡፡ በዚህ ግን አልጀዚራ ብዙም ሊወቀስ አይገባውም፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ ትክክለኛውን መረጃ የሚያውቁ ሰዎች ወይም ድርጅቶች የሚያውቁትን እውነት ቢናገሩ የሚደርስባቸውን ያውቃሉና ለደኅንነታቸው ይሰጋሉ፡፡ ስለዚህም አልጀዚራን የመሳሰሉ የውጪ የመገናኛ ብዙኃን የተሻለ አማራጭ ሲያጡ በመረጃ ምንጭነት ለመጠቀም የሚገደዱት በውጭ ሀገራት በስደትና በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊም ይሁን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሠማርተው የሚገኙ ሰዎችን ወይም ቡድኖችን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን የመሳሰሉ የሦስተኛው ዓለም ሀገራትን ሁኔታ መዘገብ ለሚፈልጉ ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ የውጭ የመረጃ ተቋማት ትልቁ የራስ ምታት ነው፡፡ ምክንያቱም ከአንድ ወገን የሚያገኙትን መረጃ ሊያረጋግጡ የሚችሉባቸው የሀገር ውስጥ በሮችና መስኮቶች በሚዲያ አፋኝ አምባገነን መንግሥታት ስለሚዘጉባቸው በአብዛኛው ያልተረጋገጠና የአንድ ወገን መረጃ ለመዘገብ ይገደዳሉና፡፡
ለዛሬው ለመማማር ያህል እንዲጠቅመን ሰሞኑን አልጀዚራ በኦሮሞ ሕዝብ ታሪክና ለዴምከራሲያዊ መብቶቻችን መከበር በምናደርገው ትግል ዙሪያ ያስተላለፋቸውን ዘገባዎች በሚመለከት መታረም የሚገባቸው ዋና ዋና ህፀፆችና እውነትነት ጨርሶውን የሚጎድላቸው አሳሳች ጉዳዮች ስላሉ በነዚያ ላይ አንዳንድ የማስተካከያ ነጥቦችን ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡ የሚከተሉት የማስተካከያ ሃሳቦች ከፖለቲካዊ አስተሳሰብ በጸዱ ሃቀኛ ምሁራን የሚደገፉ ቢሆኑም በፖለቲካ ጠበል የተጠመቁ የማንኛውም ጎራ ‹ምሁራን› ግን ላይደገፏቸው ወይም ተቀባይነት ሊያሳጧቸው ይችላሉ፡፡ ይሁንና እነዚህን ሃቆች ማንም ይገፍትራቸው ወይም ይቀበላቸው ዋናው ጉዳይ እውነታዎቹ ስሜት ወለድ ሳይሆኑ የታሪክ መዛግብትን፣ የአውሮፓ ተመራማሪዎች የደከሙባቸው የታሪክ መጻሕፍትንና በዕውቅ ምሁራን የተዘገቡ የታሪክ ማስታወሻዎችን መሠረትና ዋቢ ያደረጉ በመሆናቸው የትኛውም ወገን ሊጠራጠራቸው አይገባም፡፡
ልቦለድ  ቁጥር  አንድ:-
“ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1868 እስከ 1900 ከጠቅላላው የኦሮሞ ሕዝብ መካከል ግማሹ የሚሆነውና ወደ አምስት ሚሊዮን አካባቢ የሚገመተው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ [በሀበሾች ንጉሥ በአጤ ምኒልክ ጦር]ተገደለ፡፡”
 ሃቅ ቁጥር አንድ፡-  
 ይህ መነሻና መድረሻ የሌለው ተራ አሉቧልታ እንጂ እውነት አይደለም፡፡ ይህንና ሌላም ይህን መሰል መሠረተቢስ ወሬ ተደጋግሞ የሚነገረውና እንደማለፊያ ዜማ ዘወትር የሚቀነቀነው በአብዛኛው የኦሮሞን መገንጠል በሚደግፉና ዓላማውንም በሚያራምዱ ‹ተምረናል› በሚሉ የተወሰኑ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትና ውጪ ባሉ አክራሪ የጎሣ ፖለቲካ አቀንቃኞች እንዲሁም ‹gadaa.com›ን በመሳሰሉ የኦነግ ደጋፊ ድረ ገፆች አማካይነት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን እነዚህ ወገኖች በዚያን ዘመን የተገደለው የኦሮሞ ቁጥር አምስት ሚሊዮን ማለታቸው የቁጥር ዕውቀታቸው ዜሮ መሆኑን ከማመልከቱ ባሻገር የሚያስተላልፈው መልእክት ሚዛን የሚያነሳ እንዳልሆነ ታሪክንና የሕዝብ ብዛት ዕድገትን የሚያውቅ ይረዳዋል፡፡ በዚያን የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ 90 የሚደርሰውን የኢትዮጵያን ዘውጎች ሁሉንም ሥሌት ውስጥ ባካተተ የሕዝብ ቆጠራ ጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከአምስት ሚሊዮንም በጣሙን የሚያንስ እንደነበር በታሪክ መጻሕፍት ሠፍሮ ይገኛል፡፡ እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ከዘጠናው ዘውግ ውስጥ የኦሮሞው ማኅበረሰብ ብቻ ተነጥሎ “10  ሚሊዮን ይደርስ ነበር፤ ከዚያም ውስጥ አምስቱ ሚሊዮኑ በ‹ጨካኝ ንጉሥ ተጨፍጭፎ› ተገደለ” ማለቱ በራሱ የጤናማነት ጉድለት እንጂ አንድም ተጠየቃዊ አመክንዮ የለውም፡፡ ለመዋሸት ደግሞ ይህን ያህል ረጂም ርቀት መሄድ ለምን እንዳስፈለገ ለማንም ግልጽ አይመስልም፡፡ ስለዚህ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞዎች በአፄ ምኒልክ ጦር ተገደሉ የሚለው የተሳሳተ መረጃ የማንንም ቀልብ የማይስብና የትኛውንም ዓላማ ለማራመድ የማያገለግል ተራ የፈጠራ ወሬ ነው፡፡ እውነቱ ግን በዚያን ዘመን በተቀሰቀሱ የገብር አልገብርም የርስ በርስ ግጭቶችና ጦርነቶች ሳቢያ በብዙ ሺዎች የሚገመቱ ኦሮሞዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውን - በሁለቱም ጎራዎች - ለሕልፈት መዳረጋቸው ነው፡፡ አንዳንድ ፖለቲከኞች ለራሳቸው ጠባብ አጀንዳ ሲሉ የዚያን ጊዜውን ዕልቂት ‹ጄኖሣይድ› እንደሆነ ቢፈርጁም እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ እውነቱ ታዲያ የጄኖሣይድ ሣይሆን በዘመኑ በአውሮፓ መሣሪያና በሰለጠነ የሰው ኃይል ተደራጅቶ የነበረው በንጉሠ ነገሥት ምኒልክ የሚታዘዘው የሸዋ ጦር በኋላቀር መሣሪያና ካለበቂ የጦር ልምድና ሥልጠና  ለጦርነት ከተሰለፈው የደቡቡ ኃይል ጋር በተፈጠረ የኃይል ሚዛን መበላለጥ ምክንያት በተከሰተው ግጭት በተለይ በደቡቡ በኩል ብዙ ወገን ማለቁ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ባልተመጣጠኑ ኃይሎች መካከል የተከሰተን ጦርነት ወይም ግጭት ያመለክታል እንጂ አንድ የታጠቀ ዘመናዊ ጦር ለልዩ ተልእኮ ወደ አንድ መንደር ወይም ቀየ ገብቶ ባዶ እጃቸውን በቤታቸው የተቀመጡ ንጹሓን ዜጎች እንደፈጀ በማስመሰል የዚያን ጊዜውን የርስር በርስ ውጊያ ወደ‹ጄኖሳይድ›ነት ለውጦ የተለዬ ስዕል መፍጠር ተገቢ አይደለም ብቻ ሣይሆን ጥፋት ነው፡፡ ታሪካዊ እውነቱ የዚያን ዓይነት መልክና ቅርጽ የነበረው አይደለም፡፡ እንዲያውም በነዚያ ያለፉ የመከራ ዓመታት ኦሮሞ ባልሆኑ ሰዎች ከተገደሉ ኦሮሞዎች ይልቅ በኦሮሞዎች የተገደሉ ኦሮሞዎች ቁጥር በጣም ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም በኦሮሞ የተለያዩ ነገዶች ውስጥ በሀብትም ይሁን በአስተዳደር የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክርና መቀናቀን ስለነበር ከጎረቤቶቻቸው ኦሮሞዎችና ከሲዳማዎችም የነበራቸውን ሽኩቻ በጠረጴዛ ዙሪያ የቃላት ድርድር ሳይሆን አንዱ አንዱን በኃይል በመጨፍለቅ የበላይነቱን ለማረጋገጥ ሲል በጦር መሣሪያ ይፋለሙ ስለነበር ነው፡፡የዚያ ዓይነቱ ወንድም በወንድሙ ላይ ‹የሚቀዳጀው› ግንጥል ጌጣዊ ድል ደግሞ በአፍሪካ የመጀመሪያው እንዳልሆነና የተፈጥሮ ሀብትንም ይሁን ሌላ ጥቅም የሚያስገኝን ነገር ለመቀራመት ሲባል በሚደረግ ፍልሚያ በሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎችና ነገዶች መካከልም የከረሩ ግጭቶች ይካሄዱ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል፤ ስለሆነም በደቡቡ ይበልጡን ኦሮምኛ ተናጋሪ በነበረው ማኅበረሰብና በሸዋው ባመዛኙ አማርኛ ይናገር በነበረው የአንዲት ሀገር ዜጎች መካከል የታዩ ግጭቶችን በሀገሪቱም ሆነ በሌላው ዓለም እንዳልታዩ ልዩ ተዓምሮች በመቁጠር ይህን ያህል ግዘፍ ነስተው መራገባቸው ማንንም ስለማይጠቅም እውነቱን ከእውነተኛ ምንጮች መረዳት አይከፋምና በተለይ በዚህ ቅንነት በሚጎድለውና የተንኮል ሤራ በተሸረበበት የጥፋት ጎዳና የሚራመዱ ወገኖች በአፋጣኝ ወደቀናው መንገድ በጊዜ እንዲመለሱ ይመከራሉ፡፡ ይህን ሃሳብ ጠቅለል ለማድረግ፣ የጂማ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ጳውሎስ መንግሥቱ የቀኝ ክንፍ የኦሮሞ ነጻነት ጎራን ፍልስፍና በሚመለከት ውብ በሆነ አገላለጽ በጽሑፍ ካስቀመጡት ሀተታ ውስጥ የሚከተለውን  ቀንጨብ አድርገን እንመለክት፡-

የኦሮሞን ማኅበረሰብ ታሪክ በሚመለከት ሆን ተብለው ተንሻፍፈው የተጻፉ ወይም የሚነገሩ በርካታ የፈጠራ ድርሰቶችና ልቦለዶች አሉ፡፡ እነዚህ በሬ ወለደ ዓይነት አሉታዊ ጥላ ያነገቡ የውሸት ታሪኮችን በጭፍን ተቀብለውና እውነት  እንደሆኑ አምነው በጭፍን የሚጓዙ ወገኖችም ሞልተዋል፡፡ የፖለቲካ ኪሣራ ያጋጠማቸውና ወደጎን የተተው እንደኦነጉ አሰፋ ጃለታን የመሰሉ አስመሳይ ‹የታሪክ ተመራማሪዎች›ና ‹ጸሐፊዎች› በቤተ ሙከራዎቻቸው የፈበረኳቸው እነዚህ የሀሰት ወሬዎች የየዋሃንን ቀልብ በመሳብና በማሳሳት ረገድ የተጫወቱትና እየተጫወቱ ያሉት አሉታዊ ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ይህ በስም የተጠቀሰ ግለሰብ በተለይ፣ አንድን ነገር ሆን ብሎ በማጣመም ለራሱ በሚያመቸው መልክ በመጥቀስና ቃላትን ወይም አባባሎችን ከቆሙለት ዐውዳዊ ፍቺ ሌላ ያልተፈለገ ትርጉም በማሸከም ሰውን የሚያወናብድ አሳሳች ሰው ነው፡፡ አንድ ምሳሌ ወስደን እንይ፤ አሌክሳንደር ቡላቶቪች የተባለ የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሩሲያዊ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ተከሰተ ባለው በሽታና ርሀብ እንዲሁም በኦሮሞ ጎሣዎች መካከል ተካሄደ የተባለን ግጭት ጨምሮ ኦሮሞዎች ከሌሎች የሀገሪቱ ጎሣዎች በተለይም ከአማራው ጋር አካሂደዋል በሚላቸው ጦርነቶች ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግማሽ በግማሽ እንዳለቀ ‹ምሁራዊ ግምቱ›ን ሰጥቶ ነበር፡፡ አጅሬ አሰፋ ጃለታ ይህን ዘገባ ካነበበ በኋላ ከአንድ ጤናማ ሰው በጭራሽ በማይጠበቅ ሁኔታ አጣምሞ በመተርጎም “ግማሹ የኦሮሞ ሕዝብ በ‹ክፉዎቹ› አማራዎች ተጨፍጭፎ ተገደለ፡፡” በማለት በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የግል ፈጠራ ድርሰቱን ሰንቅሯል፡፡ ይህ ተራ ነገር አይደለም፤ የአንዲት ሀገር ዜጎችን ጥርስ ለማናከስ በተንኮል የታቀደ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ በዚህ ደግሞ ማንም አይጠቀምም፡፡ ይህ የልቦለድ ታሪክ በአቶ ጃለታ የተፈለሰፈው ኦሮሞና አማራን በማጣላት ይገኛል ተብሎ የሚገመትን የሥልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ የጎሣ ፖለቲካ ውጤት ነው፡፡ ከመነሻው ሚስተር ቡላቶቪችም ቢሆን ያን በአኀዛዊ ግምት ያስቀመጠውን የኢትዮጵያውያን ዕልቂት ሊደርስበት የሚያስቸለው አንዳችም የሕግ ድጋፍም ሆነ በግሉ የሚታወቅባቸው አቅምና ችሎታ የነበሩት ሰው አልነበረም፡፡ በሁለተኛም ያ ሰው የኦሮሞው ማኅበረሰብ ይኖርባቸው በነበሩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ዝኆንና ሌሎች የዱር እንስሳትን እያደነ በዛ ቢባል ለሁለት ወራት ያህል ብቻ ተዘዋወረ እንጂ ያን ከፍተኛ ወጪና የተማረ የሰው ኃይል የሚፈልግ የሕዝብ ቆጠራና የዕልቂት መንስኤ ጥናት ለማካሄድ የሚያስቸለው መደላድል በነዚያን በ1990ዎቹ ዓመታት ውስጥ ፈጽሞውን ሊኖረው አይችልም፡፡
 ልቦለድ ቁጥር ሁለት፡-
 “… አብዛኛው ሙስሊም የኦሮሞ ሕዝብ”
 ሃቅ ቁጥር ሁለት፡-
 ይህ ሐረግ በጥቂት የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ዘወትር ባይሆንም ካለፍ ካገደም የሚስተዋል ነው፡፡ በመሠረቱ በኦሮሞ ሃይማኖታዊ ታሪክ ከጥንት እስከዛሬ መቼም ቢሆን ‹አብዛኛው ሕዝብ እስልምናን ተከታይ ነው› የሚባል ሕዝብ ሆኖ አያውቅም፡፡ እንደእውነቱ ክርስትናም ሆነ እስልምና ከጊዜ በኋላ የመጡ እንጂ የአያት የቅድመ አያት ጥንታዊ ሃይማኖቶቻችን አይደሉም፡፡ ለምዕተ ዓመታት ስንከተላቸው የነበሩና በትውልድ ሲወራረሱ የቆዩ ሀገር በቀል ባህላዊ እምነቶች ነበሩን፡፡ (አሁንም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡) ቀስ በቀስ ግን በተለይ የኦሮሞ መስፋፋት በተጋጋለባቸው ዓመታት እነዚህ ሁለቱ እምነቶች ወደኦሮሞው ሕዝብ ይበልጥ እየሠረጉ ገቡ፡፡ ሥርገቱም በፈቃዳችንና በተፅዕኖም እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት እንረዳለን፡፡ በፈቃዳችን የሆነው እኛ በሰላምም ሆነ በጦርነት መልክ በሄድንባቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ ከነበረው የክርስቲያን ወይም የሙስሊም ሕዝብ ጋር ስንዋሃድ ሲሆን በተፅዕኖ የሆነው እነዚሁ ኃይሎች የኛን ግዛቶች በሚወርሩ ጊዜ በሚያሳድሩት ተፅዕኖ ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ያን ክስተት አሁን የኋሊት ዞረን ስናየው ጉዳዩ የሁለትዮሽ እንጂ በብቸኝነት አንደኛው ሃይማኖት በሌላኛው ላይ የበላይነትን የሚጭንበት ሁኔታ ስላልነበረ አንዱ ከአንዱ ጎልቶ የወጣበትና የኦሮሞን ሃይማኖታዊ ማንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይበት ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡ በዚህ ረገድ አሁን እንኳን ብናይ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ውስጥ ያለው  የሁለቱ ሃይማኖቶች የተከታይ ብዛት ተካካይ እንጂ ያን ያህል አፍን ሞልቶ ሊያናግር የሚያስችል የቁጥር መበላለጥ የላቸውም፡፡ (የመጨረሻው የ2000 ዓ.ም የሕዝብ ቆጠራ እንደሚያሳየው 48 በመቶ የሚሆነው ኦሮሞ የ(ማንኛውም ዘርፍ) ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሲሆን 47 በመቶው ደግሞ ሙስሊም ነው፡፡ እንደሚባለው ከሆነ ግን የእስልምና ሃይማት ተከታዩ ቁጥር በፍጥነት እያደገና በአንጻሩም የክርስትና ሃይማኖት እየጫጫ በመሄድ ላይ ያለ በመሆኑ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኦሮሞዎች ዘንድ የሙስሊም ማኅበረሰብ ቁጥር ከክርስቲያኑ ሊበልጥ እንደሚችል ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል፡፡
 ልቦለድ ቁጥር ሦስት፡-
 “ሀበሾች ኦሮሞዎችን ለማንቋሸሽ አሉታዊ ትርጉም ባዘለ ቃል ‹ጋላ› እያሉ ይጠሯቸዋል፡፡”
 ሃቅ ቁጥር ሦስት፡-
 ይህን እብለትና ቅጥፈት የተሞላበትን የፈጠራ አባባል የሚጠቀሙበት ከፍ ሲል የተጠቀሱት መገንጠልን የሚያራምዱ የኦሮሞ ኤሊቶችና አጫፋሪዎቻቸው ናቸው፡፡ ይህን የሚያደርጉት በአባባሉ እውነትነት አምነው ሣይሆን በኦሮሞው ውስጥ የመረረ ስሜት ለመፍጠርና ሕዝቡ ሴማዊ ሀበሾችን(አማሮችን፣ ትግሬዎችንና ጉራጌዎችን) ፈጽሞ እንዲጠላ ለማድረግ ነው፡፡ ይህን በማድረጋቸው ቅራኔውን ያከረሩና በአቋራጭ የመገንጠል ዓላማቸውን ያሣኩ ይመስላቸዋል፡፡ የዚህ ቃል ጥንተ አመጣጥና ትርጉሙ ግን እንደዚህ ነው፡- ይህ አንቋሻሽ የሚመስል ‹ጋላ› የሚባል ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው በዐረቦችና በሙስሊም ሶማሌዎች ሲሆን ኦሮሞዎችን ‹ጋል› በማለት መጥራታቸው በቃሉ ትርጉም መሠረት ኦሮሞዎች ‹ሃይማኖት የሌላቸው›ና ከነሱ የተለዩ ‹ባዕዳን› መሆናቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ሙስሊሞች በዚህ ቃል ኦሮሞዎችን መጥራት የፈለጉት ኦሮሞዎች የነበራቸው ባህላዊ ሃይማኖት/እምነት ከተለመደው የእስልምና ወይም የክርስትና ሃይማኖቶች የሚያፈነግጥ ሆኖ ስላገኙትና ያንንም በግዑዝ ነገሮች እንደማምለክ ወይም ከነአካቴው እንደሃይማኖት የለሽነት ስለቆጠሩት ነበር ተብሎ ይገመታል፡፡ እየቆዬ ግን ይህ አሉታዊ ፍቺ እንዲይዝ ጫና የተደረገበት ‹ጋላ› የሚል ቃል የኦሮሞን ማኅበረሰብ አባላት በቡድንም ይሁን በተናጠል ለመጥራት ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ይጠቀሙበት ጀመር፡፡
 ልቦለድ ቁጥር አራት፡-
 “(በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ) ኦሮሞዎች በአፄ ምኒልክ ቅኝ አገዛዝ ሥር ወደቁ፡፡”
 ሃቅ ቁጥር አራት፡-
 የኦሮሞ ተገንጣይ ቡድኖች ከሚያናፍሷቸውና አንዳንድ የውጭ ጋዜጠኞችም በጭፍን ተቀብለው በተደጋጋሚ ከሚያራግቡላቸው የፈጠራ ወሬዎች መካከል አንደኛው አንድ ኢትዮጵያዊ ዘውግ (አማራ) ሌላውን ኢትዮጵያዊ ዘውግ (ኦሮሞን)በቅኝ ግዛት ሥር አስገብቷል የሚለው አስቂኝ ድራማ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ብዙውን ጊዜ “ሀበሾች ኦሮሞዎችን በቅኝ ግዛት ያዙ” ወዘተ. እየተባለ እንደመፈክር ይስተጋባል፡፡ ይህ የቅኝ ግዛት ነገር በኦነግና በመሰል የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲሁም በአሜሪካና በአውሮፓ ሀገራት በሚገኙ የኦሮሞን ብሔርተኝነት አቀንቃኞች ዘንድ እንደእውነት ተወስዶ ለትግል ማነሳሻነትና ማነቃቂያነት ሲባል በስፋት ይወሳል፤ በሕዝብ ውስጥም ውስጥ ውስጡን ይሰበካል፡፡ በተለዬ አገላለጽና የዕይታ አቅጣጫ ሊታይ በሚችል መልኩ ይህ አንዱ ሌላውን ለመቆጣጠር የመሻትና የመሞከርም ሁኔታ ጨርሶውን ሊካድ ባይችልም … እንደአጠቃላይ ግን የኦሮሞ ብሔር መቼም ቢሆን በሌላ (የኢትዮጵያ) ዘውግ ቅኝ ተገዝቶ አያውቅም፡፡ ይህ ዓይነቱ ወሬ ሰሚን ሣይቀር ግራ የሚያጋባ ተራ ወሬ እንጂ ቅንጣት እውነትነት የለውም፡፡  በመጀመሪያ ደረጃ ሌላው ቀርቶ አንድ የተባበረ የኦሮሞ ብሔር፣ ተለይቶ ከሚታወቅ አንድ ወጥ የኦሮሞ ግዛት ጋር በነዚያ ሩቅ ጊዜያት አልነበረም፡፡ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ የሌለባቸው የታሪክ መጻሕፍት ሁሉ የሚመሰክሩት አንድ እውነት አለ፡፡ ያም እውነት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ቋንቋቸው አንድ በሆነ ነገር ግን የተለያዩ የጎሣ/የነገድ ስብጥር ባላቸው ማኅበረሰቦች መካከል ለዘመናት ጦርነቶች መካሄዳቸው ነው፡፡ በልማዳዊ አነጋገር የ“ሀበሾች” ሥፍራዎች ናቸው በሚባሉ የሰሜን ኢትዮጵያ ብዙ ቦታዎች ሳይቀር ኦሮሞዎች በመስፋፋት ከትግሬዎች፣ ከአማራዎች፣ ከአፋሮችና ከሌሎችም የክልሉ ነዋሪዎች ጋር በመቀላቀላቸውና በመዋሃዳቸው ይህ በአንዳንድ የዋሃን “የሀበሾች ምድር” እየተባለ አላግባብ የሚጠራው የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ራሱ የአንዱ ወይም የሌላው ብሔር ወይም ዘውግ ብቸኛ መኖሪያ ሣይሆን የሁሉም እንደሆነ በታሪክ ምሁራን ዘንድ ይታመናል፡፡ እርግጥ ነው በ1700ዎቹ ገደማ ራያ ኦሮሞዎችና የጁ ኦሮሞዎች የተወሰኑ የትግሬና የአማራ ግዛቶችን ተቆጣጥረው በነበረበት ጊዜ ለተወሰኑ ዓመታት የኢትዮጵያን ኦፊሴል ቋንቋ ኦሮምኛ አድርገው እንደነበር ከታሪክ ማኅደር መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህም ማለት በኢትዮጵያ የተለያየ ቋንቋና ባህል ያላቸው ጎሣዎችና ነገዶች እየተፈራረቁ ሥልጣን ይናጠቁ እንደነበረና በታሪክ ግምዶሽ እየተቆራኙ እርስ በርስ እንደተዋሃዱ፣ በዚህ ሂደትም ይበልጥ ጉልበተኛ የነበረው ዘውግ ለአገዛዝ አመቺ ነው ብሎ የሚያስበውን ቋንቋም (ሆነ ባህል) በሌሎች ላይ ይጭን እንደነበር መረዳት አይቸግርም፡፡ የዚያን ዘመኑ የአንድ ቋንቋ የበላይነት ግን እንደዛሬው ዘመን አጨቃጫቂና ከመጠን በላይ በተለጠጡ የቅራኔና ቁርሾ መዘዞች የታጨቀ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም በንግድም ሆነ በሌላ ሥራ ከቦታ ቦታ ይዘዋወሩ የነበሩ ዜጎች ለሥራቸው ስኬት ሲሉ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የሌሎች ጎሣዎችን ቋንቋዎች ይናገሩ ስለነበርና ቋንቋን ማወቅም ከግል ጥቅም ጋር በቀጥታ ስለሚያያዝ በዚያን ዘመን ይስተዋል የነበረው ሥነ ልሣናዊ ችግር እንዳሁኑ በፖለቲካዊ አስተሳሰቦች የተንኮል ድርና ማግ የተሸመነ አልነበረምና ያን ያህል ጎልቶ የሚታይ ለታሪክ መዝገብ ፍጆታም የሚበቃ ቋንቋ ነክ ችግር አልነበረም፡፡ ይህ እንግዲህ ኦሮሞ የሠፈረበትን ግዛት የሚጠቁመን የኋላ ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩም የሚያሳየን ኦሮሞ ያልተዳረሰበት ኢትዮጵያዊ ሥፍራ እንደሌለና ነገር ግን በየሄደበት ባህልና ቋንቋ እየተዋጠ ከሁሉም ጋር እንደሰም ቀልጦ አንድ መሆኑን ነው፡፡ ወደኋለኛው የአፄ ምኒልክ ዘመን ስንመጣ እንግዲህ የሚስተዋል አንድ ሃቅ መኖሩን እንረዳለን፡፡ ይሄውም ብዙዎች የታሪክ ተመራማሪዎችና ጸሐፍት እንደሚከራከሩበትና አሳማኝም ነው ብለው በርካቶች እንደሚቀበሉት ጉዳዩ የአማራና የኦሮሞ ዝርያ ወይም የደም ትስስር ሣይሆን አማርኛን በዋናነት የሚናገር ማኅበረሰብ ኦሮምኛን በዋናነት የሚናገርን ማኅበረሰብ በጊዜ ሂደት ሊያሸንፍ የመቻሉ ታሪካዊ አጋጣሚ መከሰቱ ነው፡፡ ይህ ሲሆን አማርኛን በሚናገረው ማኅበረሰብ ውስጥ ኦሮሞ አለ፤ ኦሮምኛን በሚናገረው ማኅበረሰብ ውስጥም አማራ አለ ማለት ነውና ትግሉ ይበልጡን የኢኮኖሚና የሥልጣን እንጂ የዘርና የቋንቋ አለመሆኑን ልብ ይሏል፤ እርግጥ ነው ግጭቶች ሁሉ የሀሰትም ይሁን የእውነት አንዳች የሚነገርላቸው ምክንያት ስለሚያስፈልጋቸው በሁሉም ወገን የሚነገሩ ግን እውነት ውሸትነታቸው ሊጣራ የሚገቡ ሰበበ-ድርጊቶች መኖራቸው የሚካድ አይደለም፡፡  ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንግዲህ በነዚህ ዓይነቶቹ የኋላ ዳፋ ሊኖራቸው በሚችል ጠንቀኛ ንግግሮችና ሰብቆች ላይ ነው፤ ምክንያቱም ‹አንድ ወሬኛ ያባረረውን ሺ ጦረኛ አይመልሰውም› እንዲሉ ተጣሞ የተነዛን ወሬ ለማቃናት አስቸጋሪ ከመሆኑም በተጨማሪ ወሬው እየተበጠሰ እየተቀጠለ ይሄድና ያልተጠበቀ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራልና ነው፡፡ ይህ ከፍ ሲል የተገለጸው የግጭትና አንዱ ሌላውን እያሸነፈ የማስገበር ሁኔታ የሚያመለክተን አማራ ኦሮሞን ወይም ኦሮሞ አማራን የማሸነፍ ጉዳይ አለመሆኑንና ታሪካዊ አንድምታው ከዚህ የፊት ለፊት ሽፋን ረቀቅ ያለና የተለዬ መሆኑን ነው፡፡ በተቻኮለ ፍርደገምድልነት የተሳሳተ አመለካከት ከማዳበር በፊት እውነትን መረዳት ለሁሉም ይጠቅማል፡፡
ሰሜነኞቹ አማሮች ጎራ ለይተው እንደተጋጩና ለጉዳት እንደተዳረጉ ሁሉ ኦሮሞዎችም እንዲሁ ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ለዚህ አንዱ ግልጽ ማስረጃ የሚሆነን አፄ ምኒልክ በወጣትነታቸው ዘመን በአፄ ቴዎድሮስ ተይዘው ታስረው በነበረበት ወቅት በጎንደርና በሸዋ የአማሮች መኳንንትና መሣፍንት መካከል የታየው ፍጥጫ ነው፡፡ ወጣቱ ምኒልክ በተፈቱ ሰሞንም የኦሮሞ ነገዶች ኃይለኛ የርስ በርስ ውጊያ ላይ ነበሩ፡፡ የተቀናቃኞቻቸውን አከርካሪ በመምታት ያን ግጭት በአሸናፊነት ለመውጣት የፈለጉ የተወሰኑ የኦሮሞ ጦር ቡድኖች ከሸዋ አማሮች ንጉሥ አፄ ምኒልክ ጋር ኅብረት ፈጠሩ፡፡ ቱለማ ኦሮሞ፣ ሊሙና ሜጫ ኦሮሞ የሚባሉት የኦሮሞ ጦሮች ከሸዋው ንጉሥ ከአፄ ምኒልክ ጦር ጋር በመተባበር ሌሎችን የኦሮሞ ጦሮች በተለያዩ አስከፊ ዐወደ ዉጊያዎች በማሸነፍ ብትንትናቸውን አወጡት፡፡ ባጭሩ ኦሮሞዎች በኦሮሞነታቸው በአንድ ኦሮሞ ያልሆነ ባዕድ አካል በቅኝ ግዛት አልተያዙም፡፡ እርግጥ ነው የኦነግ መሥራች አባላት ይህን የ”ቅኝ ግዛት” ተረት ተረት ስላላመኑበት በተለይ በመጀመሪያ አካባቢ ይህን ያህል አፍ ሞልተው ሲናገሩት አልተስተዋለም፡፡ ይሁንና በ1960ዎቹ አካባቢ የኦነግ አመራሮች በግማሽ ኦሮሞ በሆኑት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ኦሮሞዎች እንዲያምጹባቸው ለማድረግ ስሜትን የሚማርክ አንዳች የመቀስቀሻ ዘዴ መቀየስ አስፈለጋቸው፡፡ ለዚያም ሲሉ ይህችን መናኛ የ‹ቅኝ ግዛት› ካርድ በማንሣት ‹ለኦሮሚያ ነጻነት› ሁሉም ኦሮሞ በትግሉ እንዲሣተፍና “ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት” ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ይቀሰቅሱበት ጀመሩ፡፡ በዚህ የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ድንገተኛ የአቋም ለውጥ ምክንያት ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጋር ለበርካታ ምዕተ ዓመታት በሁሉም ረገድ ተዋህደን እንዳልኖርንና በደምና በአጥንት እንዳልተሳሰርን ሁሉ እኛ ኦሮሞዎች “በማያውቁንና በማናውቃቸው አማሮች” አማካይነት እንደከብት በቅኝ ግዛት በረት ውስጥ የመገኘታችንን ምሥጢር ኦነግ ይፋ አደረገልን፡፡ ይህ ዓይነቱ የመጨረሻ ውራጅና ከተስፋ መቁረጥ የሚመነጭ የትግል ሥልት በሌሎች ሀገሮች ውስጥ በሚካሄዱ የነጻነት እንቅስቃሴዎችም ዘንድ ሥራ ላይ ሲውል ታይቷል፡፡ የኛን ሀገር ሁኔታ በሚመለከት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሚረዱት ገሃዱ እውነታ ግን በታሪክ ጥንቃቄ የተሞላበት ልዩ ሙያ ተዳውረው የተሸመኑት የሸዋ አማሮችና ኦሮሞዎች ለዘመናዊት ኢትዮጵያ መፈጠር ዋና መንስኤ መሆናቸው ነው፡፡ “ሸዋዎች እነማን ናቸው?” በሚለው በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፈ መጸሐፉ ላይ፣ የታሪክ ምሁሩና የሰው ዘር አመጣጥ ተመራማሪው ዶክተር ጌሪ ሳሎል ይህን የመሰለ ጠቅለል ያለ ድምዳሜ አስፍሯል፤ “ ዘር ቆጠራን በሚመለከት ሸዋ ውስጥ (ከዚያም በመላዋ ኢትዮጵያ) የፖለቲካ የበላይነትን የጨበጡትን ቡድኖች ብናይ ከአማራና ከኦሮሞ የተወለዱ ቅዩጣን ዜጎች ናቸው፡፡”
ወደማጠቃለያችን ስንመጣ እንግዲህ በዋናነት መገንዘብ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ከፍ ሲል የተጠቀሱት አራት መሠረታዊ ስህተቶች የኦሮሞን ታሪክና ኦሮሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት የሚጫወተውን ሚና በሚመለከት መዘገብ የሚፈልጉ በተለይ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችን በማሳሳትና እውነቱን እንዳይዘግቡ በማወናበድ እያደናቀፉ መሆናቸውን ነው፡፡ አልጀዚራን የመሳሰሉ ዕውቅ የመገናኛ ብዙኃን የኦሮሞንና የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ችግርና እንግልት መዘገባቸው እሰዬው የሚያሰኝ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ያለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ይወጡ ዘንድ ዘገባው ሚዛናዊ እንዲሆን ተጨማሪና ከፍተኛም ጥረት ማድረግ እደሚገባቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ አለበለዚያ የሚሠሩት የተዛነፈ ሥራ በተለይ ወጣቱን ክፍል ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይመራውና ለችግሮች መፍትሔ ከማግኘት ይልቅ ችግሮች እየተባባሱ እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡ እንደውነቱ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ እየመጡ በሚሄዱ የተለያዩ መንግሥታት አማካይነት ከፍተኛ የአስተዳደር በደልና ጭቆና የደረሰባቸውና የሚደርስባቸው ኦሮሞዎች ብቻ ሣይሆኑ ሁሉም ዜጎች ናቸው፡፡ ከዚህ አስከፊ የብረት አጥር ወጥተው ወደተሻለ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዘመን ሊሸጋገሩ የሚችሉት ደግሞ የጎሣና መሰል ልዩነቶቻቸውን ትተው ለጋራ መብቶቻቸው መከበር በአንድነት ሲቆሙና በአንድነት ሲታገሉ ብቻ ነው፡፡ በጋራ ሲሰለፉ ደግሞ የጋራ ጠላቶቻቸው በማር ለውሰው በመሃከላቸው በረጯቸው መርዘኛ አሉቧልታዎችና የሀሰት ወሬዎች መበርገግና በነጭ ውሸት የመሠሪዎች መሠረተቢስ ወሬ መረታት የለባቸውም - ‹ተደጋግሞ የተነገረ ውሸት እንደ እውነት ይቆጠራል› የሚባለውን ምሳሌያዊ አባባል በማስታወስ የሚነገረው ሁሉ እውነት እንዳልሆነ ማጤንና ሁሉም ትኩረቱን ከባርነት አገዛዝ ነጻ ወደሚያወጣው የጋራ መንገድ ማዞር ይኖርበታል፡፡ የውጭ የመገናኛ ብዙኃንም ያልተረጋገጠ የሀሰት ዘገባ በማቅረብ በሕዝብ መሀል ጥርጣሬንና መፈራራትን ከማንገሥ ተቆጥበው ትክክለኛነቱ በሁሉም ወገኖች ዘንድ የተመሠከረለትን ዘገባ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ከዚህ ቀደም ኅትመት ወይም አየር ላይ ባዋሏቸው መሰናዶዎቻቸው ላይ ስህተት ካለም ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከተው አካል ማስተካከያ መቀበልና ማስተላለፍ፣ ለቀደመ ስህተታቸውም ይቅርታን መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ከአሁን በኋላ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ከቀሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር ለዴሞክራሲ፣ ለልማትና ለፍትህ  የሚያደርገውን ትግል የሚያደናቅፉ ከፋፋይና መሠረተቢስ ዝግጅቶችን ከማቅረብ እንዲቆጠቡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡

-- ፈቃዱ ለሜሣ የናዝሬት ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ፕሮፌሰርና ጸሐፊ ናቸው፡፡

ለማንኛውም አስተያየትና ሂስ የኔ አድራሻ፡- yinegal3@gmail.com
Original title of this translation:- History 101: Fiction and Facts on Oromos of Ethiopia
የኢትዮሚዲያ ምንጭ፡  Salem News

የኔ ምንጭ፡- Ethiomedia.com - An African-American news and views website.
Copyright 2012 Ethiomedia.com. Email: editor@ethiomedia.com
staff reporter | August 11, 2013 at 1:41 pm | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-27f
Comment   See all comments

Wednesday, August 7, 2013

የተፈናጠረው 11ኛ ሰአት – የወያኔ የመጨረሻው የጥላቻ አጣብቂኝ



    የታሰሩትን መፍታት ለኢሕኣዴግ የፖለቲካ ኪሳራ ያስከትላል::

ለሊቱን በስብሰባ ተወጥሮ ያደረው ወያኔ መስማማት ተስኖታል:: አደርባዮች እና የድል አጥቢያ አርበኞች ጨንቋቸዋል::ከየተኛው ወገን እንደሚለጠፉ ግራ ገብቷቸዋል:: የደህንነት እና የህወሓት ወታደራዊው ክንፍ በተጠንቀቅ ላይ ነው:: ባለስልጣናቱ ከውጪው አለም እየተደረገባቸውን ጫና እና ግፊት በፍጹም አንቀበለም የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እርስ በእርስ ሲላተሙ አድረዋል::
ሃገራችን የጥበበኛ ህዝቦች እና የጥበበኛ መሪዎች ሃገር የምትሆንበትን ጊዜ የምንፈልግ እኛ ለውጥ ፈላጊ ልጆቿ ዛሬ ላይን ተቀምጠን ትላንትን የምንመኝ ለነገው ትውልድ የማናስብ በፍርሃት ድባብ ተውጠን ስደትን እና ገንዝእብን የምናሳድድ መሆናችን በመታወቁ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ስልጣኑንን እንዴት አስረዝሞ ሃገር ወዳድ የሆኑ ጠላት የሚላቸውን ኢትዮጵያውያንን ነቃቅሎ የሚያጠፋበት ስልት በቡድናዊ አምባገነንነት እየዶለተ እና በስልጣን ሽኩቻ እርስ በእርሱ እየተባላ ባለበት ወቅት እኛ አንድነት አጥተል በጋራ ዘመም በቀኝ አክራሪ እና ባፈጀ ባረጀ የፖለቲካ ግራውንድ እየተሽከረከርን ህዝብዊ መቆላለፍን ልንፈጥር አለመቻላችን ለአገዛዙ አመቺ አድርጎታል:: እስኪ የወያኔን ስጋት ያነቡ ዘንድ ጋብዘናል::
ከትላንት ሃምሌ 28 ሊነጋ የተበተነው የወያነው የውጥረት ስብሰባ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ነበረ ለሊቱን የተጓዘው::እንደቀድሞው እቅዳችን ትራንስፎርሜሽናችን ልማታችን ምናምናችን ዲሞክራሲያችን ሰላማችን የጼረ ህዝቦቻችን ...ምናምን የሚል አልነበረም ..በአተካሮ የተሞላ ውጥረት የነገሰበት አድርባዮች ፍራቻ ይነበብባቸው የነበረበት የነባር ታጋዮች ጩሐት ውይይቱት ደበላልቆት ያደረበት እንደነበር በስብሰባው ላይ የነበሩ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጭ ተናግረዋል::
የት ከርሞ ከየት እንደመጣ ወዴትስ ሄዶ እንደነበር በማይታወቀው የአምባገነን ቡድን አስተባባሪ በደብረጽዮን የተመራው ይህ አተካራዊ ስብሰባ የወያኔ አባላቱን ለከፍተኛ ፍጥጫ ከመዳረጉም አርፎ ዘለፋ እና ዛቻ እንዲሁም የቀድሞ ጉዳዮች ወቀሳ ያካተተ የነበረ ሲሆን በብኣዴን ነባር አባላት እና በጫካው ሕወሓት እንዲሁም በሕወሃት የከተማ ህዋስ እና በጫካው ሕወሓት መካከል ከፍተኛ የሆነ ጭቅጭቅ ተስተናግዷል:: ዋናው አትኩሮት የነበረው ይላሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ወቅታዊው የአንድነት ፓርቲ እንቅስቃሴ;የሙስሊሙ ጥያቄ; የምእራባውያን ጫና;እና የዲያስፖራው ድጋፍ በተመለከተ ነበር::
የስብሰባው ላይ አነጋጋሪ የነበረው የአንድነት ፓርቲ ጉዳይ በስፋት መንቀሳቀስ በዚሁ ከቀጠለ ካለው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ችግር አኳያ ህዝቡ ሆ! ብሎ ሊነሳ ስለሚችል ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ፓርቲውን በወከባ እና በጥቅም ማክሰም ወይንም ከፓርቲው ጋር መደራደር እስከሚሉ ጨከን ያሉ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል:: ከፓርቲዎች ጋር መደራደር የሚባል ነገር አይዋጥልኝም የሚሉት አለቃ ጸጋዬ በቁጣ እና በጩኽት ይህንን የመደራደር ሃሳብ ያቀረበችውን የሕወሓት የከተማ ህዋስ አባልን ያመጣንሽ እኮ እንድትጦሪን እንጂ ጠላት እንድትሆኚን አይደለም በማለት በቋንቋቸው አይሆኑ ዘለፋ ዘልፈዋታል::ቤቱ በዝምታ ድባብ እንዲዋጥ ያደረጉት የጫካው ሕወሓቶች የታገልነው ለድርድር አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል:: ሰማያዊ ፓርቲ ቢነሳም ብዙም አያሰጋንም በሚል ታልፏል::
ከኦህዴድ ሙክታር ብቻ የተካፈለበት ይህ ስብሰባ 16 የህወሃት ጄኔራሎች የተመከሩ ይመስል ጂንስ በጃኬት ለብሰው ነበር በስብሰባው ላይ የተገኙት :: በአሁን ሰአት የደህንነቱ እና የወታደሩ ክፍል በተጠንቀቅ ሊሆን ይገባዋል በሚል የሚያሳዝን አንደበት መናገር የጀመሩት አቶ በረከት አትኩረውት የነበረው በሙስሊሙ እና በዲያስፖራው ጉዳይ ነበር :: ሙስሊሙች ጥያቄያቸው ሰፍቶ አለምም ጆሮ ሰቷቸዋል እንሱን ዝም ማሰኘት አሊያም ለፖለቲካ ስልት መጠቀም አስፈላጊ ነው ቢሉም የታሰሩትን መፍታት ለኢህኣዴግ የፖለቲካ ኪሳራ ስለሆነ ያለንን ሃይል መጠቀም አለብን ብለዋል:የዲያስፖራው ጥላቻ ከ60% ወደ 90% አድጓል:: 10% ደሞ ንብረት አገር ቤት ያፈሩ ወይም ከፖለቲካ ነጻ ነን የሚሉ ግለሰቦች ሲሆኑ ይህ ደሞ 10% ደጋፊ ሳይሆን የምንላቸው ለንብረቶቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት የሚለማመጡ ብንል ይቀላል :: በዲያስፖራው ዘንድ ያለው ጉዳይ ብዙም ተስፋ ሰጪ ስላልሆነ ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል:: ይህ የራሳችን የፖሊሲ ውጤት ነው ብለው ደፍረው የሚናገሩ አባላት አልተገኙም::
የህወሃት አንጋፋ ታጋዮች የተሳተፉበት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ያልተጠሩበት ጥቂት ብኣዴኖች እና አንድ ኦህዴድ የፈጠጡበት ይህ ስብሰባ የምእራቡን ጫና በተመለከተ ሰፋ ያለ የዲፕሎማቲክ ስራ እና ዝርዝር ሪፖርት ይዞ የማስረዳት ስራ እንዲሰራ የሕወሓት የውጪ ጉዳይ አትኩሮት እንዲሰጥበት ያደረገ ሲሆን ለአንድ አገር የውጪ ፖሊሲ የአንድ ፓርቲ ሰዎችን እንዲሰሩ ማዘዝ በአንዳንድ ተሰብሳቢዎች ላይ አግራሞትን ፈጥሯል::ምንም አይነት ስምምነት ያልታየበት ይህ ስብሰባ በፍጥጫ በአተካሮ እና በጩኽት የተሞላ ቢሆንም አብዛኛዎቹ አንጋፋ ታጋዮች ማስታውሻቸው ላይ ሲቸከችኩ ተስተውለዋል::
ወደማይፈታ ችግር ራሱን እየወሰደ ያለው ቡድናዊው አምባገነን ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለ የሚያሳየው ይህ ጨለማ የሚደረግ ስብሰባ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሰዎች እየተመረጡ ደጋፊዎች እየታዩ እየተጠራሩ በጎጥ እና በመንደር በመሰባሰብ ሃገርን ወደማትወጣበት አዘቅት ቁልቁል እየከተቷት ነው:: በመጪው ቀናቶች የሚጠሩ ስብሰባዎች በእነዚሁ ወቅታዊ ጉዳዮን ላይ አተኩርው እንደሚወያዩ ይጠበቃል መልካም የለሊት ስብሰባ::  ምንልክ ሳልሳዊ
maleda times | August 7, 2013 at 1:35 pm | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-26r



Comment   See all comments

Monday, August 5, 2013

ETHIOPIAN REGIME KILLS 25 PEACEFUL PROTESTERS AND ARREST 1,500 CIVILIANS


ETHIOPIAN REGIME KILLS 25 PEACEFUL PROTESTERS AND ARREST 1,500 CIVILIANS
Ethiopian government forces open fire on unarmed demonstrators throughout the country, killing 25 and injuring dozens more, according to Ethiopian activists who took part in the demonstrations.
One witness says at least one child was among the the dead. He also stated government security forces arrested over 1,500 protesters on Friday.
For over a year, Ethiopian Muslims have been holding peaceful protests and mosque sit-ins over the regime's human rights abuses against their community and interference in their religion.for more news source http://ireport.cnn.com/docs/DOC-1015286
maleda times | August 4, 2013 at 11:56 am | Categories: Africa | URL: http://wp.me/p2gxmh-25X
Comment   See all comments

የአሲምባ ፍቅር” – መጽሃፍ ቅኝት (በክንፉ አሰፋ) ደራሲ፣ ካሕሳይ አብርሃ ብስራት


ብዛት 446 ገጾች
 ye-asimba-fikir
በተስፋዬ ወልደዮሃንስ አዲስ አበባ ታትሞ የተሰራጨ

* ከስር በስእሉ እንደሚታየው ኢሲምባ 3250 ሜትር ከፍታ ላይ በትግራይ ውስጥ ያለ ተራራ ነው አሲምባ በዚህ ከፍታው ሳቢያ ሌሊት ላይ በጉም ይሸፈናል። አሲምባ "ቀይ አንባ" ማለት ነው።

           እንደ መንደርደርያ
ይሀ መጽሃፍ በዋሽንግተን ዲሲ - ሳንኮፋ ቢሮ ውስጥ ሲመረቅ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝቼ ነበር። መገኘት ብቻ ሳይሆን በዝግጅቱ ላይ ግራ ያጋቡኝን ጥያቄዎች ለመጽሃፉ ደራሲ አቅርቤለት ነበር። የኔ ግርታ ምናልባትም የብዙዎቻችሁ ጥያቄ ሊሆን ስለሚችል እዚህ ላይ እንደገና ማንሳቱን መረጥኩ። የመጀመርያው ጥያቄ "ይህ ታሪክ 30 አመታት አለፈው። ታዲያ አንድ ትውልድ ካለፈ በኋላ አሁን ይፋ መሆኑ ለምን አስፈለገ?" የሚልና ሁለተኛው ደግሞ "ስለዚያ ትውልድ ሌሎች ከጻፏቸው መጽሃፍትና መጣጥፎች 'የአሲምባ ታሪክ' ን ለየት የሚያደርገውስ ምንድነው? ስለቀደመው ትውልድ አሉታዊ ይዘት ይኖረው ይሆን? ' የሚሉ ነበሩ።
ለጥያቄዎቼ ያገኘሁት መልስ ሳይሆን የመልስ ምት ነበር። በዚያች ትንሽ አዳራሽ ውስጥ የነበሩት የኢህአፓ ሰዎች ጥያቄውን በበጎ ሳይሆን በክፉ ስለተመለከቱት፤ ምላሻችውም የበጎ አልነበረም።  የመጽሃፉ ደራሲ አቶ ካሕሳይ አብርሃም በመልሳችው አንድ አረፍተ-ነገር በተናገሩ ቁጥር ይጨበጨብላቸው ነበር። እናም ቤቱን የሞሉት የዚያ ትውልድ ወገኖች ምላሽ የማብራራትና የማስረዳት ሳይሆን ይልቁንም ራስን የመከላከል (ዲፌንሲቭ) አይነት ነው የነበረው። ውይይቱ እየገፋ ሲሄድ ትውልድን እያንጻጸሩ አንዱን ትውልድ ብቻ የማወደስ አዝማሚያ ላይም ተደረሰ። በመጽሃፉ ምረቃ ዋና ተናጋሪ የነበሩት ፕ/ር ሃይሌ ገሪማ ግን ሂደቱን ስላልወደዱት በመሃል ጣልቃ መግባት ነበረባቸው። ተናጋሪዎቹን በመውቀስ ለቀረቡት ጥያቄዎች በስርዓቱ መለስ መስጠት እንዳለባቸውና የዚህ ጥያቄ ምላሽም በጣም አስፈላጊ ስለመሆኑ ምክር ሰጡ።
ከዚያ በኋላም የውይይቱ አጀንዳ አልተቀየረም። ርዕሱም ከዚህ መስመር ሳይወጣ ዝግጅቱ ተገባደደ። ሁሉም በዚያ ዘመን ስለነበረው ትውልድ ጽናት፣ ፍቅር እና መተሳሰብ እያንሳ 30 አመት ወደኋላ ተመልሶ ነጎደ። እኔ ግን ለጥያቄዎቼ ተገቢውን መልስ ሳላገኝ፤ ይልቁንም የራሴውኑ ትውልድ እስኪበቃው አስወቅሼ ከሳንኮፋ ቢሮ ወጣሁ። መውጫው በር ላይ ግን አንዲት ጠና ያሉ የቀድሞ ኢህአፓ ታጋይ የነበሩ ወይዘሮ ያዙኝ።
".. ሰቆቃውን ማስታወስ እንኳን አንፈልግም። በፊታችን ሲደፉ የነበሩ ወገኖች፣ ይደርስብን የነበረው ግፍና በደል.... የጓዶች አሰቃቂ እልቂት... ይህንን ሁሉ ስናስታውስ ያመናል። በዚህም የተነሳ በተቻለ መጠን ሁሉንም ለመርሳት ነው ይምንሻው...።" አሉኝ።
እኔም ለዚሁ ነበር የጠየቅኩት። ደራሲው ከመድረክ ላይ ይህንን ምላሽ ቢሰጠኝ ኖሮ ባልተከፋሁ ነበር። በርግጥ ታሪኩ ዘግይቶ ለመውጣቱ ምክንያቱ ይህ ከሆነ ሁሉም ሊረዳው ይችላል። የኛ ትውልድ ግን ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)  በጎ የሆነ አመለካከት የለውም።  ከዚህ ቀደም ስለ ኢሕአፓ ያነበብናቸውም ሆኑ የሰማናቸው ታሪኮች ሁሉ አሉታዊ ይዘት ያላቸው ናቸው። የክፍሉ ታደሰ "ያ ትውልድ" እና በልጂግ አሊ በቅርብ ያሳተመው "ቀለበቴን ስጧት" መጽሃፎች ትንሽ ለየት ይላሉ። በተለይ "ቀለበቴን ስጧት" የሚለውን መድብል አንብቤ እንደጨረስኩ ስላዛ ትውልድ ያለኝ አመለካከት የተቀየረ ይመስለኛል። ምንም እንኳን ድርጅታዊ ችግሮች ቢታዩበትም፣ ያ ትውልድ ለተነሳለት አላማ የከፈለው መስዋዕትነት እና ያሳይ የነበረው የአላማ ጽናት በእጅጉ የሚደነቅ መሆኑን ከመጽሃፉ ታሪኮች መገንዘብ ይቻላል።
***
          "የአሲምባ ፍቅር" መጽሃፍ ደግሞ እንደወረደ የተተረከ የዚያ ትውልድ የጦር ሜዳ ውሎ ላይ ያጠነጥናል።
 ከሰላሳ አመታት የስደት ኑሮ በኋላ ከሚኖርበት ዴንቨር ኮሎራዶ በመነሳት ይመር ንጉሴ የተባለን ገበሬ ለመጠየቅ ወደ ወልዲያ፣ ክዚያም ወደ አሲምባ ያመራል - ካሕሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል)። ካሕሳይ ስፍራው እስኪደርስ የነበረው ታሪክ ልብ እያንጠለጠለ ይሄድና በስፍራው ሲደርስ ያጋጠመውን አሳዛኝ ዜና ይተርካል። ካሕሳይ በ 1968 ከአሲምባ ወደ ወልዲያ ለወታደራዊ ተልዕኮ ሄዶ በሚሊሽያ ይመር ንጉሴ ነበር የተማረከው።
የመጽሃፉ ደራሲ ካሕሳይ አብርሃ በ1999 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ እሱን የሚመለከት ታሪክ በጋዜጣ ላይ መውጣቱን ያነብባል። በጋዜጣው የወጣው የእሱ እና የሦስት የትግል ጓደኞቹ ታሪክ በደራሲው ውስጥ ለዓመታት ታፍኖ የከረመውን ፥ ታሪኩን በመጽሃፍ የማውጣት ህልም ነፍስ  እንደዘራበት ይናገራል። ከአመታት ውጣ ውረድ በኋላም ህልሙ እውን ሆኖ መጽሃፉ ለንባብ በቃ።
 ታሪኩ ከ1968 ዓ.ም. እስከ 1970 ዓ.ም. ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት (ኢሕአሠ) የትግል ሂደት በስፋት ይቃኛል። በደራሲው የግል የትግል ውጣ-ውረድ ላይ የተሞረኮዘው ይህ ትረካ በመጀመሪያ በመቅረጸ-ድምጽ (ቴፕ) እንዲቀረጽ ተደርጎ ከዚያም የብዙዎች አስተያየት ከታከለበት በኋላ ወደ መጽሃፍ የተለወጠ ታሪክ ነው።
ካሕሳይ ኢሕአሠን በ15 አመቱ ሲቀላቀል በትምህርቱ ብዙም ያልግፋ የአርሶ አደር ልጅ ነበር። አሲምባ እንደደረሰ እውነተኛ ስሙን ረስቶ "አማኑኤል" የሚል መጠርያ ተሰጠው።  ብዙም ሳይቆይ ከጥቂት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና በኋላ ለወታደራዊ ግዳጅ ተላከ። አሲምባን ለቅቆ እስኪኮበልል ድረስም በበርካታ የፍልሚያ መስኮችም ተሰማርቶ እንደነበር በአሲምባ ፍቅር ይተርካል።
የመጽሃፉ ደራሲ በዚያ በለጋ እድሜው ወደ ትጥቅ ትግሉ እንዲገባ ያነሳሱት ምክንያቶች ላይ በጽሁፉ ብዙም ትኩረት አላደረገም። ከምክንያቶቹ ይልቅ በተግባራቱ ላይ በስፋት ሄዶባቸዋል። ይሁንና የብሄር መብት እና የመሬት ጥያቄ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ከመጽሃፉ መገንዘብ ይቻላል። ስለ ብሄር ጥያቄ ያነሳው ነጥብ "ዩኒቨርሲቲ ለማለፍ ከፈለጋችሁ አማርኛ በደንብ ማወቅ አለባችሁ። አማርኛ ካላለፋችሁ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት አትችሉም።"  (የአሲምባ ፍቅር ገጽ 33) የሚለውን የስምንተኛ ክፍል መምህሩን ማብራሪያ ይጠቅሳል። እናም ከሌሎች ትምህርቶች በተለየ አማርኛን ብዙ ግዜ ሰጥቶ ማጥናቱን ካሕሳይ አምርሮ ይተቻል።
ይህ ከብሄር ጥያቄ ጋር ለምን እንደተያያዘ ግራ ያጋባል። ዩኒቨርሲቲ ለመግባት አማርኛ ብቻ ሳይሆን እንግሊዝኛም መስፈርት ነበር። የሂሳብ ትምህርትም እንዲሁ። እነዚህ እንደመስፈርት መቅረባቸው ስህተት ነው የምንል ከሆነ፡ ሁሉንም መጥቀስ ይገባናል። ካሕሳይ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መስፈርት ስለመሆኑ ምንም የጠቀሰው ነገር የለም።  ለካሕሳይ ከእንግሊዝኛ ይልቅ  አማርኛ ነው የሚቀርበው። አማርኛን ጠንቅቆ ማውቁ ነው "የአሲምባ ፍቅር"ን በአማርኛ ለንባብ ያበቃልን። የአንድ ሃገር ህዝብ ለመግባባት አንድ የጋራ ቋንቋ መኖሩ ጉዳቱ ምኑ ላይ ነው?  የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ሆነ። ይህ ከብሄር ጭቆና ጋር ምን አገናኘው? አማርኛ ከአረብኛ ቀጥሎ በአለም ላይ ሁለተኛው የሴም ቋንቋ አይደላም እንዴ? ኢህአፓ በወቅቱ የብሄር ጥያቄን በዚህ አይን የሚያየው ከሆነ በጣም ያሳዝናል።
የመሬት ጥያቄን በተመለከተ ደግሞ ደራሲው በአባቱ ላይ ይደርስ የነበረው በደል እንዳስቆጨው በገጽ 31-32 ላይ አስፍሯል። ከመሬት ጋር በተያያዘ አባቱ ለዳኛ ጉቦ እየሰጡ እንደሚኖሩ ጽፏል (የአሲምባ ፍቅር ገጽ 32)።  እንዚህ ጉዳዮች እና ከዩኒቨርሲቲ በክረምቱ ወራት የሚመጡ ወጣቶች "መሬት ላራሹ" እያሉ ወደ ትግሉ እንዲገባ እንደገፋፉት ይናገራል። ፍትህን ለማምጣትም ቆርጦ ወደ አሲምባ ተራራ አመራ።
ፍትሕ ላጡ ወገኖቹ ተቆርቁሮና የህዝብ ብሶት ገፍቶት ወደ አሲምባ በረሃ የገባው ካህሳይ በገጽ 52 ላይ እንዲህ ይለናል።
"ኪንኪታ የሚባል ቦታ በሌሊት ገባን። ሊነጋጋ ሲል የደርግ ሰላይ መሆኑ የተነገረንን ሃይሉ ካህሳይ የሚባለውን ሰው ቤት ከበብነው። ... ሃይሉ ካህሳይ ሰንገዴ ከደረስን በኋላ ውሳኔ ተሰጥቶበት በሰራዊቱ የተገደለ የመጀመሪያው ሰው ሆነ።" (የአሲምባ ፍቅር ገጽ 52)
ይህ የመጀመሪያ እርምጃ ኢፍታዊነትን በኢፍታዊ መንገድ ለመታገል መነሳትን ያሳየናል።  ድርጊቱ ያ ትውልድ የተነሳለት መብትን የማስጠበቅ አላማ መስመሩን እንዲለቅ ማድረጉን ይጠቁማል። ወጣቱ ወደ አሲምባ ሲነጉድ ለነጻነት ትግል እንጂ ለግድያና ለዝርፊያ እንዳልነበር ከጅምሩ ተናግሯልና።
ካህሳይ ኪዚያም ቀጠለ። በገጽ 65-66 ላይ በመጀመሪያዎቹ ወራት በዳሎል ለዘረፋ በተሰማሩበት ወቅት በየነ አብረሃ የሚባል "ነጭ ለባሽ" መኖሪያ ቤት በመሄድ፣
"... ንብረቱን ዘረፍነው፤ ከነበሩት ከብቶች እና ከእህሉ ግማሹን ከፍለን ለሚስቱ በመተው እኩሌታውን ወሰድን።... አንዱን በሬ ለማረድ ፈለግንና ለመያዝ ሞከርን፤ በሬው ሃይለኛ ስለነበር በመሳሪያ ተመትቶ ወደቀና አርደን ስጋውን ይዘን ሄድን።" (የአሲምባ ፍቅር ገጽ 65)
ካህሳይ ግን ይህ ኢፍትሃዊ ውሳኔ ስሜቱን እንደነካው በመጽሃፉ አስፍሯል።
ከመጽሃፉ እንደምንረዳው የኢህአፓ ወታደራዊ ክንፍ ነው የተባለው ኢህአሠ የፖለቲካ አመራሩን ከየትኛው አንጃ እንደሚያገኝ ግልጽ አልነበረም።  ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ እና ጸጋዬ ደብተራው አሲምባ ግንቦት ወር 1968 ዓ.ም. ሲገናኙ የተወያዩበት አንደኛው አጀንዳ ይኸው ጉዳይ ነበር። በገጽ 100 ላይ እንደሰፈረው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳታደርጉ የሚል ትዕዛዝ የያዘ የጽሁፍ ማስረጃ  ጸጋዬ ደብተራው ከእጅ ቦርሳው አውጥቶ ለዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ አሳየው። "ዶ/ር ተስፋዬ ወረቀቱን ተቀብሎ ተመለከተና፡ ያሳየው መረጃ የፓርቲው ትዕዛዝ እንዳልሆን ለደብተራው ነገረው።" (የአሲምባ ፍቅር ገጽ 100) ኢህአፓ አመራሩም ሆነ አሰራሩ ምስጢራዊ በመሆኑ፡ ማን ምን እንደሚሰራ፡ መመርያና ትዕዛዞች ከየት እንደሚመጡ በግልጽ የሚታወቅ ነገር አልነበረም።
በገጽ 107 ላይ ደግሞ የጆርጅ ኦርዌልን "አኒማል ፋርም" የሚያስታውሰን አንድ አስገራሚ ክስተት ሰፍሯል። የኢህአሠ ሰራዊት ከአሲምባ ወጥቶ ወደ ወሎና ጎንደር እንደርታ ሲጓዝ የጸጋዬ ደብተራው ሽጉጥ ጠፍቶ በከተማው ሁሉ ተፈልጎ ሳይገኝ ቀረ። በሰራዊቱ ደንብ ጸጋዬ መቀጣት ነበረበት። ሌሎቻችን ስናጠፋ እና እቃ ስንጥል እንደምንቀጣው ጸጋዬም መቀጣት አለበት እያለ ሰራዊቱ ማጉረምረም ጀመረ። ደራሲውም ከአርጎምጓሚዎቹ አንዱ እንደነበር አምኗል። ጸጋዬ ደብተራው ካህሳይን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤
"አንዳንድ ጊዜ ሃቅ መናገር ያስወነጅላል። ... ስታስበው ማነው ቀጪ፤ ማነው ተቀጪ? አንዳንድ ጊዜ አይቶ እንዳላየ ማለፍ አለብህ። ... ሲል ጸጋዬ ደብተራው ካህሳይን መክሮ ሸኘው... (የአሲምባ ፍቅር ገጽ 107)።  ጆርጅ ኦርዌል "እንሣት ሁሉ እኩል ናቸው። አንዳንድ እንስሳ ግን ከሌሎቹ እንስሳት የበለጠ እኩል ናቸው።" ይለናል።
ከዚያ ባሻገር በኢሕአፓ አመራር አባላት መካከል የተፈጠረው የአካሄድ ልዩነት፥  ያልተማሩ አባላትን የመናቅ እና የማግለል ሂደት፣  የትጥቅ ትግሉ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ  እንዳሳደረ ደራሲው ፈራ ተባ እያለ አስፍሯል። የአካሄድ ልዩነት የሚያሳዩ አባላት በ"አንጃ"ነት  የተፈረጁትን መገደል፣ ማሰር እና ሽሽት፣  የአመራር ብቃት መጉደል፥ ሰራዊቱን እያስመታው መጥቶ፣ በመጨረሻ አሲምባ ከኢሕአሠ ምሽግነቱ ለማክተሙ ምክንያት ሆኗል።
ታሪኩ በጥቅል ሲታይ ከሞት ፍርድ አስመልጦ ለዛሬ መኖሩ ያበቃው የወሎው ገበሬ ይመር ንጉሤና  በትግል ወቅት ስላገኛት የመጀመርያ የፍቅር ጓደኛኛው በታጋይ ድላይ ዙርያ ያጠነጥናል።
በአሲምባ ለመጀመሪያ ጊዜ በድላይ ፍቅር ቢለከፍም በፍቅሩ ምክንያት ከአላማው ላለመውጣት ሲታገል እንደነበር ትረካው ጉልህ አድርጎ ያሳየናል። ካህሳይ ፍቅርን ያጣጣመው በድላይ ነው። ከሷ ጋር በበረሃ የማይረሳ ትውስታዎችምም አሉት።  ካህሳይ ከድላይ ይልቅ ለአሲምባ ተራራ ያለው ፍቅር ግን ይበረታል።
ካህሳይ በትምህርቱ ብዙም ያልገፋ ወጣት ቢሆንም የዚያን ወቅት ውስብሰብ ክስተቶች የማስታወስ ችሎታው ይሚደነቅ ነው። በሦስት ዓመት የትግል ጊዜያት በኢሕአሠ ውስጥ ያሳለፋቸውን ውጣ ውረዶች በስፋት ይተረካል።   የከተማውን፣ የቀበሌውን፣ የመንደሮችን ስሞች፣ ከዚህ አልፎም የቀየዎችንና ተራሮች፣ ወንዞችና  የኮረብታዎችን ስሞች ሁሉ በመጽሃፉ ቁልጭ አድርጎ ስሏቸዋል። የታጋይ ጓዶቹን እርከን፣  እውነተኛ ስሞች፣  ቅጽልና ምስጢራዊ ስሞችም ሁሉ ከሰላሳ አመታት በኋላ አልረሳቸውም። ማን መች እንደተሰዋ፣ የት እና እንዴት እንደተሰዋ ሁሉ ያስታውሳል።
ደራሲው ከአሜሪካ የስደት  ቆይታቸው በኋላ አሲምባ ተብሎ የሚጠራውን ይህንን  "ቀይ አንባ" ተራራ ጐብኝቷል። ወደ አሲምባ የሄደበትም ምክንያት ከዛሬ ሰላሳ አመት በፊት የማረከውንና ከሞት ያተረፈውን የገበሬ ሚሊሽያ ለማመስገን ነበር። በዚህ ጉብኝቱ ታዲያ የአሲምባ አካባቢ መልማቱን መንገድ መግባቱን፣ ውኃ መገደቡን፣ ትምህርት ቤት መሠራቱን ይመሰክራል። እሱ ራሱ ከ 30 ዓመታት በፊት ታግሎለት ስለነበረው የመብትና የፍትህ ጥያቄ መሟላት ላይ ግን ምንም አላለም።
መጽሃፉ በዚያ ዘመን በትግሉ ውስጥ ለነበረ፡  በትዝታ ማዕበል ሰላሳ አመት ወደኋላ ይወስደዋል። ለአዲሱ ትውልድ ደግሞ ስለዚያ ውስብስብና አስቸጋሪ የትግል ዘመን ውጣ ውረድ ያስቃኘዋል።  ይህንን በይዘቱ ለየት ያለ መጽሃፍ ገዝቶ ማንበቡ ስላለፈው ትውልድ በርካታ ግንዛቤዎች ይሰጠናል። (ስዕል - የአሲምባ ተራራ)
maleda times | August 4, 2013 at 11:44 am | Categories: AMHARIC NEWS | URL: http://wp.me/p2gxmh-25S
Comment   See all comments