BY MINILIK SALSAWI
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተከፈተው በር ሰተት ብለው መግባት አለባቸው:: በወያኔ ውስጥ የተደረገውን የስልጣን ሽግሽግ ተከትሎ አዳዲስ ለውጦች እየታዩ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የበላይነት ጎልቶ ለመውጣት እያቆበቆበ መሆኑን ከ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ ከአከባቢው የህወሃት አክራሪዎች መወገድ እና የአቶ ደብረጺሆን የግለኝነት አትኩሮት ለአቶ ሃይለማርያም እድሉን ገርበብ አድርጎ የከፈተላቸው ሲሆን የአቶ ደብረጺሆን ግለኝነት በሙስና ስም ሊደፈቅ እንደሚችል ያከባቢው ገማቾች ሲናገሩ ወታደራዊው አካል ራሱን ለማዳን ሲል በተጠንቀቅ ከሃይለማሪያም አዲስ ካበበው ቡድን ጋር እንደሚሰለፍ አንዳንድ ፍንጮች ታይተዋል:: አቶ ሃይለማርያም በሙሉ መንፈስ ባይሆኑም ድፍረት እንዳገኙ ከደቡብ ጉባዬ በሁዋላ እየታየ ሲሆን የደቡብ ባለስልጣናት አንድነት ወያኔን አስደንግጦታል::
የሕወሓት የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ባለስልጣናት በአቶ ሃይለማርያም ዙሪያ ጥያቄ በማንሳት ላይ ቢሆኑን በባህር ዳር በተደረገው ጉባዬ ላይ ያላቸውን የበላይነት እንዲያሳዩ ከፓርቲያቸው ግፊት እንደተደረገባቸው ምንጮች ጠቁመዋል::የደቡብ ባለስልጣናት አብዛኛዎቹ በግል አቶ ሃይለማርያምን በደቡቡ ጉባዬ ወቅን አግኝተው ያናገሯቸው ሲሆን በአንድነት ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እና ከሕወሓት የበላይነት እንዲላቀቁ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው መክረዋል::ለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚረዳቸው ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር አስታከው ተወያይተውል::
በህወሓት ውስጥ ያለው ፍትጊያ በአባይ ወልዱ የበላይነት ያበቃ ነው ብለን መደምደም እንደማንችል እና መሃል ሰፋሪ ሆነው ወዳሸናፊው ለማዘንበል የግለኝነት ሚና እየተጫወቱ ያሉት ደብረጺሆን ደቡቦችን አመቻችቶ መያዝ አስፈላጊ እንደሆን ስለተረዱት በሃይለማርያም ድፍረት ጀርባ ሆነው ጨዋታውን ማጋጋል ተይይዘውታል::
ምንጮቹ በአከባቢያቸው ያለውን ሁኔታ በማየት እንዳሉት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃይለቃል ጭምር የሚደፋፈራቸው የደህንነት አማካሪው አለቃ ጸጋይ ከፓርቲው መነሳቱን ተከትሎ በደብረጺሆን ተዘዋዋሪ ቁጥጥር ስር መሆኑን ከጠ/ሚ ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ እንደት ከስልጣን እንደሚባረር ታቅዶለታል::
በስበሃት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋይ የነበሩት እና በአሁን ሰአት በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በማሰባሰብ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ እና ከሕወሓት ሰው ጠፍቶ ነው ወይ ከደቡብ ለትግሉ አስታውጾ ያላበረከቱ ሰዎች የሚመሩን ነገ ስጋት ሆኖብናል የሚሉ ታጋዮች ይህን ፕሮፓጋንዳ ይዘው በአቶ ስበሃት በኩል መሰለፋቸው በዚህ ሰሞን እንደገና ተረጋግቷል የተባለውን የወያኔ ክፍፍል እንደ አዲስ አግሎታል::

የሃይለማርያም ስልጣን መያዝ ያልጣማቸው አክራሪ ሕወሓቶች ከባህር ዳር መልስ አዲስ አበባ ውስጥ በስበሃት ነጋ ሰብሳቢነት አርከበ እቁባይ ;ብርሃነ ገብረክርስቶስ ;አዲሳለም ባሌማ;አባዲ ዘሙ ;አለቃ ጸጋይ በርሄ; ቅዱሳን ነጋ; ሃይለኪሮስ እና ሌሎችም ተሰባሰበው በህወሃት ውስጥ ስለለው ሁኔታ እና ራሳችን በፈጠርናቸው ደቡቦች ልንዋጥ ነው የሚል እደምታ ያለው ውይይት አካሂደው ነበር:;
በአንድ ወገን ሆነው በአባይ ወልዱ መሪነት ብኣዴንን አስከትለው የስብሃትን ቡድን እየተዋጉ የሚገኙት አዜብ መስፍን እና ሌሎች..ሳሞራ የኑስን እንደመከታ አድርገው ቢተሙም ሳሞራ ሁኔታዎችን ከመከታተል ዉች ተሳትፎው የተልፈሰፈሰ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል::
የደቡብ ባለስልጣናት ወይም በስበሃት አጠራር የከተማ ጮሌዎች ወደ ከፍተኛ የስልጣን እርከን መምጣታቸው እያንገበገባቸው ሲሆን መለስ ዜናዊ ላልሰለጠኑ አናሳ ብሄሮች ሸጠን በማለት በሟቹ ላይ ከንፈር ነክሰው እየሞገቱ ሲሆን ይህም አልበቃ ብሎ ከድርጅታችንን መመሪያ እና ደንብ ዉጭ በተለያየ ቦታ የመለስን ምስል ማየት ሰለቸን በሚል ምስሉ እንዲነሳ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል ምናልባት ሁኔታዎችን ያረግብ ይሆናል በሚል አቶ አዲሱ ምስሉ እንዲነሳ ቢናገሩም አቶ በረከት ጠላት እና ወዳጅን አጥርቶ ለመለየት በሚል እንዲቆይ አድርገዋል..
የስበሃት ቡድን ዉስጥ ውስጡን በትግራይ ለሚገኙ የሕወሓት የበታች አመራሮች እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ ለሚገኙ የህወሓት መኮንኖች በሚያሰራጩት ፕሮፓጋንዳ በበረሃ ወንድም እና እህት ታጋዮችን ሰውተን ደማችንን አፍሠን የልጅነት ወዛችንን ጨርሰን ለዚህ የደረስነው ለደቡብ ሰዎች እና ለከተማ ጮሌዎች ስልጣን ለመስጠት አይደለም አብረውን የታገሉ ኦሆዴዶች እንኳን ያላገኙትን ስልጣን ነው ያገኙት በማለት እና ለነገ የፖለቲካ ኪሳራ ያመጡብናል የሚያዘነብሉት ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ነው ለኛ አደጋ ስለሆኑ ከአሁኑ ልናሶግዳቸው ይገባል በማለታቸው የወያኔ የውስጥ ቀውስ ግሎ ይገኛል::

በአሁን ሰኣት የደህንነት መዋቅሩን እና የጦር ሰራዊቱ ባለስልጣናት አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት እየሰሩ የሚገኙት ደብረጺሆን አቶ ሃይለማርያም ያላቸውን ሃይል ተጠቅመው የወሳኝነት ሚና እንዲጫወቱ እያደፋፈሯቸው ሲሆን ከጎናቸው እንደሚሆኑ እና ምንም እንደማይመጣ እየመከሯቸው ሲሆን ለሁለት አመት ነው ያስቀመጥንህ የሚለውን የአለቃ ጸጋይ ዛቻ ከአሁን በኋላ ሰሚ የሌለው ጩሀት እንደሆነ መናገራቸውን ምንጮቹ አስቀምጠዋል::
የደቡብ ባለስልጣናት ማሰብ/ድፍረት መጀመር; የህወሃት ክፍፍል መጋል; የኦህዲድ አህያዊ ሞኝነት; የብኣዴን በዝምታ ነገሮችን መከታተል; የኢሕኣዴግ ባልተጠበቀ መልኩ ቀውስ ውስጥ መግባት እና ሌሎች ተደማምረው የወያኔን ውድቀት የሚያመላክቱ ሲሆን በሃገሪቷ ላይ የፖለቲካ ለውጥ እንዲኖር ለማየት የሚጓጓውን ህዝብ ስል ነቀል ለውጥ እንዲያደርግ መስራት ደሞ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ነው::

Comment | See |